💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
🛍ጥሩ እናት ለልጇ እንዲህ ብላ መከረች!!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

〰ልጄ ሆይ〰
【عندما يغضب زوجك أغلقي أذنيك وعندما تغضبين أقفلي فمك..وستكون الحياة جميلة】
ባልሽ በተቆጣ ጊዜ ጆሮሽን ያዢ። አንቺ በተቆጣሽ ጊዜ አፍሽን ዝጊ። ይህ ካደረግሽ የትዳር ህይወትሽ ያማረና የሰመረ ይሆናል።

=
https://t.me/https_Asselfya
▪️ ሁሌም እውነተኛ ሁን !!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
📩አዛኙ ውዱ ነብያችን እንዲህ በማለት ይመክሩናል

▪️አደራ እውነተኛ በመሆን ላይ
▪️እውነት ወደ መልካም ተግባር ይመራል
▪️መልካም ተግባር ደሞ ወደ ጀነት ይመራል

=
https://t.me/https_Asselfya
"  እኔ እወድሻለሁ"
==========

እህቴ ጠንክሪ  በተውሂድሽ ብቻ።

በጨመረ ቁጥር የጥላት ጥላቻ፣

ወዳጆችሽ ይብዙ ጠላትሽ ይኮሽሽ፣

አይዞሽ እህቴ ሁሌም ከጎንሽ ነኝ፣

አብሬ አልጠላሽም ሙስሊም እህት ነኝ፣

ጉዞሽን ቀጥይ ከሰለፎች ጋራ፣

ጆሮሽ እንዳይሰማ ያወራ ቢያወራ፣

እህቴ በርችልኝ ከተውሂድሽ ጋራ፣

ሀያሽን  ጠብቂ ከአቂዳሽ ጋራ፣

እወድሻለሁኝ ኑሪልኝ በደህና፣

መልካምሽን እንጂ ክፉሽን አልስማ፣


🍃🍃🌺🍃🍃

https://t.me/https_Asselfya
☑️ ብልህ ሙዕሚን የዚህችን ዱኒያ ማሸንገያ አታሸነግለውም ሁሌም ለመጨረሻው ቀን(ለአኼራው ) ለፊ ነው!

ሁሌም ለአኼራው ሚሆነውን ስንቅ ለማዘጋጀት አመቺ ሚሆኑ እናም ወደ አላህ ይበልጥ ሚያቃርቡ ጊዜያቶችን እድል አያስመልጥም!

እኛም ከትክክለኛ ሙዕሚኖች ዘንድ እንድንመደብ ይህን ትልቅ እድል ጠፊ በሆነችው ዱኒያ ማስመለጥ የለብንም!


      {بَلْ تُؤْثِرُونَ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا※وَٱلْـَٔاخِرَةُ خَيْرٌۭ وَأَبْقَىٰٓ}

{ይልቁንም የዱኒያን ሕይወት ትመርጣላችሁ※
የመጨረሻይቱ አኺራ (ሕይወት) በላጭ እና ሁል ጊዜ ዘውታሪም ናት}

አላህ ጊዜያቸውን በአግባቡ ከሚጠቀሙት ያድርገን!

=
https://t.me/https_Asselfya
ኢስላምን መገንዘብ
NABAWI TUBE
ኡስታዝ ሳዳት ከማል

ኢስላምን መገንዘብ

በበድረል  ኩብራ  መስጂድ
የቀረበ  ሙሐደራ

t.me/NABAWITUBE
☑️ እናታችን አኢሻ (رضي الله عنها) እንዳስተላለፈችው የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል።

«እናንተ ሰዎች ሆይ! (ከመልካም) ስራ የምትችሉትን ያክል ብቻ ያዙ። እናንተ እስካልተሰላቻችሁ አላህ አይሰለችም። አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስራ ትንሽ እንኳ ብትሆን ዘውታሪነት ያለውን ነው።»

[ 📖 صحيح البخاري (٥٨٦١) ]
=

t.me/https_Asselfya
በቁርአን መሀፈዝ ላይ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች  መካከል  ዋነኛው ነገር
           
➘➘➘
🔍ኢኸላስ ሌላ አላማ በጭራሽ ሊኖር
      አይገባም
🔍ሲተሀፈዝ አያውን መደጋገም
🔍ሁሌም ቢሆን ከሙራጀአ(የሀፈዝነውን
    ከማጥናት) አለመዘናጋት
🔍በትክክል መተሀፈዙ ማረጋገጥ ከመሀፈዙ
     የበለጠ አሳሳቢና ትኩረት የሚሻ ነው።
🔍ሙራጀአ(የሀፈዙትን መጠበቅ) ከሂፍዙ
     የበለጠ አሳሳቢ መሆኑን መገንዘብ
🔍ሂፍዝ ማለት ሙራጀአው መሆኑ በደምብ
     ማመን።

ከቁርአን ጋር ያለን ግንኙነት አፍ ከፈታንበት አንስቶ እስከ ቀብር ድረስ ሊሆን ይገባል::


https://t.me/https_Asselfya
ጀግናዬ፦ኢማሙ አሕመድ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
•
"አላህ የምትወደውን ነገር እንዲያዘወትርልህ ከፈለግክ አንተ አላህ በሚወደው ነገር ላይ ዘውትር"
•
【አል–ቢዳያ ወኒሃያ (10/330)】
=
📍ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦

ጃሂሎችን ከማስተማር የቦዘኑት አሊሞች ወዮላቸው አሊሞችንም የማይቀበሉ ጃሂሎች ወዮላቸው።

ምንጭ፦📚[{مجموع الفتاوي{ 281/2]

✍️
Audio
🔴👉 አላህን በእውቀት ላይ ሆናችሁ ታመልኩት ዘንዳ ዲናችሁ ተማሩ

📍 قال الشيخ/ ابن عثيمين رحمه الله:

إخواني: تفقهوا في دين الله تعالى لتعبدوا الله على بصيرة، فإنه لا يستوي الذين يعلمون والذين لا يعلمون، ومن يُرِد الله به خيرا يفقّهه في الدين.

📚 مجالس شهر رمضان صـ ١٢٢
Audio
➷والذين آمنوا أشد حباً لله
☑️ ሙእሚኖች ለአላህ ያላቸው ውዴታ የበረታ ነው።

=
https://t.me/https_Asselfya
☑️ በአላህ ከማመን በኋላ የደስታ
ምንጮች------
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

‏قال الشيخ
مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله:

▪️ሼኸ ሙቅቢል ቢን ሀዲ አልዋድእይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።

"أحسن ما يستريح به العبد في هذا الزمان بعد الإيمان بالله، طلب العلم: والزوجة الصالحة"》

አንድ ሰው በዚህ ዘመን ላይ በአላህ ከማመን በኋላ እረፍትና ደስታ የሚያገኘው
▪️ኢልምን በመፈለግና
▪️በመልካም ሚስት ነው።

- الإمام الألمعي(٢٥٣)
=
✍️
t.me/https_Asselfya
የኢስላማዊ እውቀት ትሩፋት
~
የሸሪዐ እውቀት ከቁሳዊ ንብረት የላቀ ውድ ሃብት ነው። በዒልም የመሀይምነትን ድቅድቅ ፅልመት ትገፍበታለህ፣ ራስህን ታንፅበታለህ፣ ጥመትን ትዋጋበታለህ። እንደ ዒልም የሚያረካ ምን አለ? ለዚህም ነውኮ ኢማሙ አሕመድ - ረሒመሁላህ - "ዒልምን ምንም የሚስተካከለው ነገር የለም" ማለታቸው። [መሳኢሉ ኢብኒ ሃኒእ፡ 1932]
ባይሆን ዒልም ማለት ደረቅ የመረጃ ክምችት አይደለም። ይልቁንም እውቀት ማለት ተቅዋ ያወረሰ ነው፣ አላህን መፍራትን ያላበሰ። የላቀው አላህ ምን እንደሚል አታይም?
{هَلۡ یَسۡتَوِی ٱلَّذِینَ یَعۡلَمُونَ وَٱلَّذِینَ لَا یَعۡلَمُونَۗ إِنَّمَا یَتَذَكَّرُ أُو۟لُوا۟ ٱلۡأَلۡبَـٰبِ}
"እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን? የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው።" [ዙመር፡ 9]

አኺል ከሪም ኡኽቲል ከሪማህ! የፈለገ ኑሮ ባይደላ፣ የፈለገ ቢዝነስ ቢያጨናንቅ ከዒልም ማእድ መራቅ አይገባም። ከዒልም መራቅ ከብዙ ኸይር መራቅ ነው። የዒልም ጉባኤ ላይ መታደም አይነተ ብዙ ኸይር ላይ መታደም ነው። ታላቁ ሶሐቢይ አቡ ደርዳእ - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላሉ፦
‏"ما من رجل يغدو إلى المسجد بخير يتعلمه أو يعلمه إلا كتب الله له ŘŁŘŹŘą المجاهد، ولا ينقلب إلا غانما".
"አንድም ሰው ኸይርን ሊማር ወይም ሊያስተምር ወደ መስጂድ አይሄድም አላህ የሙጃሂድን አጅር የፃፈለት ቢሆን እንጂ። አትራፊ ሆኖ እንጂ አይመለስም።" [አዙህድ፣ ኢማሙ አሕመድ፡ ቁ.756]

ይህንን የዒልም ዋጋ የተረዱት ሰለፎች የዒልም ማእዶችን ያጨናንቁ ነበር። ሐቢብ አልዓቢድ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"በስራ ከተማ ስገባ ሱቆች ተዘጋግተዋል።
'የሆነ የማላውቀው ዒድ አላችሁንዴ?' አልኩኝ።
'አይደለም። ሐሰኑል በስሪይ መስጂድ ውስጥ ሰዎችን እየመከረ ስለሆነ ነው' አሉኝ።" [አልመዋዒዝ ወልመጃሊስ፡ 181]

ስለዚህ:
አደራ ደርሶች ላይ!
አደራ የደዕዋ ድግሶች ላይ!
አደራ የተቀዱ ትምህርቶችን ማዳመጥ ላይ!
አደራ ጠቃሚ ንባብ ላይ!
በዚህ ዘመን ብዙ ሰው ጊዜውን በዋል ፈሰስ እያሳለፈው ነው። ይሄ ብክነት ነው፡፡ ዑመር ብኑል ኸጧብ - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላሉ፦
إني أكره الرجل أراه يمشي سبهللا
"እኔ አንድ ሰው ተንበሀሎ (ባክኖ) ሳየው እጠላለሁ።" [አልኣዳቡ ሸርዒያህ፡ 3/588]
ለዱንያም፣ ለአኺራም ሳይሆኑ እንዲሁ ባክኖ መቅረት። የዛሬ ብዙሃን ወጣቶች ተጨባጭ እውነታ!

#ከደጋጎቹ_ቀዬ
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 24/2015)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
☑️ ደካማው ጠንካራ..
〰️〰️〰️〰️〰️
በመሰረቱ የሰው ልጅ ልቡም አካሉም ደካማ ነው።
ነገር ግን በመልካም ስራውና ጌታው ላይ ባለው ተወኩል ልክ ጥንካሬን ይታደላል።
አላህ ያላገዘውና ያላጸናው በሙሉ ተሸናፊ ነው።

"አላህን -ህግጋቱን- ጠብቅ እርሱ አንተን ይጠብቅሃል፤ በድሎት ጊዜ ከአላህ ጋር ተዋወቅ በችግር ጊዜ ያውቅሃል-ይረዳሃል-"

ነቢዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም።

=

http://t.me/https_Asselfya