💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.65K subscribers
1.29K photos
494 videos
125 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
የባልሽን ውዴታ እንዴት ማግኘት እንደምትችይ እወቂ:: ብልጥ እንዲሁ ፈጣን ሁኚ:: የባልሽን ውዴታ ከምታገኚበት መንገድ አንዱ የእርሱን መልካም ተግዳሮቶች ለእርሱ መንገርሽ ነው::
ሰዎች እነርሱ ዘንድ ባለው መልካም ነገር ሲወደሱ ደስ ይላቸዋልና ባልሽ ላንቺ ያለው ውዴታ እንዲጨምር አንቺ እርሱ ላይ ያለውን መልካም ነገር ጥቀሺለት::

ሁሌ የባላቸውን መልካም ተግዳሮት ደብቀው ጉለቱንና ስህተቱን ከሚዘረዝሩ ሚስቶች እንዳትሆኚ:: መልካም እና እውነተኛ ጓደኛ እንኳ የጓደኛውን እንከን እና ጉለት ትቶ መልካምነቱን ያወሳል!። ላንቺ ደግሞ ባልሽ ከጓደኛም በላይ ነው።ታዲያ ቢያንስ እንኳ እውነተኛ ጓደኛ መሆን እንኳ እንዴት ያቅትሻል?!

✍️በእነዚህ  ነገሮች ላይ ጥረት አድርጊ:- .

➲ባልሽ የሚለይበት እና መልካም የሚባሉትን ባህሪዎቹን አጥኚ::
➲ባለው መልካም ባህሪ እና ባለው መልካም አቋም አወድሺው::
➲የእርሱን መሰል ባል በማገኘትሽ ደስተኛ እንደሆንሽ ግለጪለት::
➲ውዳሴሽ እና ንግግርሽ እውነት ይሁን!


➘ኮፒ ነዉ! ከዚሁ ሰፈርተነካክቶ የተወሰዴ!

➘ ➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/abuUseyminabdurehman
አላህን ማወቅ
➫➫➫➫➫➫➫

አላህ ስለመኖሩ ማስረጃዎች
       ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

🔃وَهُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ النُّجُومَ لِتَهْتَدُوا بِهَا فِي ظُلُمَاتِ الْبَرِّ وَالْبَحْرِ ۗ قَدْ فَصَّلْنَا الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

እርሱም ያ ከዋክብትን በየብስና በባሕር ጨለማዎች ውስጥ በእርሷ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ ያደረገ ነው፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘረዘርን፡፡ (አል አንዓም 97)

🔃هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ ۚ مَا خَلَقَ اللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِالْحَقِّ ۚ يُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ (በከንቱ) አልፈጠረውም፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡[ዩኑስ 5]

🔃إِنَّمَا مَثَلُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا كَمَاءٍ أَنزَلْنَاهُ مِنَ السَّمَاءِ فَاخْتَلَطَ بِهِ نَبَاتُ الْأَرْضِ مِمَّا يَأْكُلُ النَّاسُ وَالْأَنْعَامُ حَتَّىٰ إِذَا أَخَذَتِ الْأَرْضُ زُخْرُفَهَا وَازَّيَّنَتْ وَظَنَّ أَهْلُهَا أَنَّهُمْ قَادِرُونَ عَلَيْهَا أَتَاهَا أَمْرُنَا لَيْلًا أَوْ نَهَارًا فَجَعَلْنَاهَا حَصِيدًا كَأَن لَّمْ تَغْنَ بِالْأَمْسِ ۚ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

የቅርቢቱ ሕይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ፣ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት (እንደ ፋፋ) ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋም በርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መኾናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትእዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው፡፡ እንደዚሁም ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡ {ዩኑስ 24}

🔃قُلِ انظُرُوا مَاذَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَا تُغْنِي الْآيَاتُ وَالنُّذُرُ عَن قَوْمٍ لَّا يُؤْمِنُونَ

«በሰማያትና በምድር ያለውን (ተዓምር) ተመልከቱ» በላቸው፡፡ ተዓምራቶችና አስፈራሪዎችም ለማያምኑ ሕዝቦች አይጠቅሙም፡፡ (ዩኑስ101)

🔃وَيُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

ለእናንተም አላህ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡(አል ኑር 18)

🔃وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ مُّحِيطًا

በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ከባቢ ነው፡፡ (አል ኒሳዕ 126)

🔃وَكَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ وَلَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

እንደዚሁም (እንዲያስቡ) እንዲመለሱም አንቀጾችን እናብራራለን፡፡
(አል አዕራፍ 174)

አጠቃላይ መልዕክት
➻➻➻➻➻➻➻➻

እዚህ ምዕራፍ ላይ የመፅሃፉ አዘጋጅ ለመጥቀስ የሞከሩትን አጠቃላይ መልዕክት በሚል የነብያትን ተልኮ እና አላማ ምን እንደሆነ ነው። አላህ ብቸኛው ፈጣሪ ሰውንም ሆነ ጋኔንን የፈጠራቸው እሱን በብቸኚነት እንዲያመልኩት ነውይህ አምልኮ ምን መምሰል እንዳለበት ደግሞ ከሰው ልጆች የሆኑ፣ ወንዶችን መልክተኛ እና ነብይ አድርጎ ለእያንዳንዱ ህዝብ ይልካል። እነዚህ መልዕክተኞች አስፈራሪና አብሳሪ ሆነው ነው የሚላኩት። የሚያስፈራሩት አላህን በብቸኚነት ሳያመልክ ለቀረ፣ መልዕክተኞቹን ላልታዘዘ እና ወንጀሎችን ተዳፍሮ ንስሃ ላልገባ የአላህ ቅጣት እንዳለበት ነውበአላህ አንድነት አምነው መልካሞችን ለሰሩ፣ መልክተኞቹን ለታዘዙ የአላህ ውደታ፣ ገነት እንዳላቸው ያበስራሉ። ሁሉም መልዕክተኞች የመልዕክታቸው አስኳል መሽከርከሪያው አንድና አንድ ብቻ ነው። እርሱም አምልኮን በጠቅላላ ለአንድ አላህ ብቻ አድርጉ፣ ከእርሱ ውጭ የሚመለኩትን በጠቅላላ ራቁ የሚል ነው።


✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል

አላህን ማወቅ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ!

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!

UMU FARUQ

➲ስለዚህ ፅሁፍ ያላችሁን አስተያየት ማስቀመጥ ትችላላችሁ! ፅሁፍ እየረዘመባችሁ ከሆነ እንድቀነስ ስህተትም ካለኝ እንዳስተካክል

ወደ አቡ ሂበቲላህ ቻናል ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
👍1
📢ታላቅ የምስራች ነገ ጁምአ ማታ የዳእዋ ፕሮግራም

የኢብኑ ተይሚያ መርከዝ አሻራ መጣያ ግሩፕ አባላቶች በሙሉ
 

➽በአይነቱ ለየት ያሉ የዳዕዋ ፕሮግራሞችና

📚የጥያቄና መልሶች እንዲሁም ለየት ያሉ ምክሮችን ያካተተ ለዩ የሆነ ልዩዩዩዩ የሆነ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ይጥብቅዎታል

🎙በአቡ አብዲላህ  ኢብኑ ኸይሩ ሐፊዘሁሏህ እንዲሁም ሌሎች የሱና ወንድሞቻችንም ይገኙበታል ኢንሻ አሏህ

ፕሮግራሙ የሚጀመርበት ስዓት

   ➴➴➴➴➴➴➴
   ➧በሳዑድ   9:00
     ➧በዱባይ   10:00
      ➧በኢትዮጲያ 3 :00

አይደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል አልሰማሁም አመለጠኝ አያዋጣም!!! በጊዜ ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉ ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ያድርጉ


አድራሻ➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/+GD8RJGEqP4xkOTg0
https://t.me/+GD8RJGEqP4xkOTg0
Audio
✍️በሐገራችን ላይ ተውሒድ እንዲስፋፋና ሽርክ እንዲወድም ባለው አቅም ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከተው ወንድማችን ሳዳት ከማል በእውነት ትልቅ ምስጋና የሚገባው ሰው ነው !!

➲በዚህም አላህ መልካም ምንዳውን ይከፍለው ዘንዳ እንለምነዋለን !!


🎙ለዛሬ ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ሙሃደራዎች ውስጥ አሚሬ አዞኛል የምትለዋ ስለምትመቸኝ እሷን ልጋብዛችሁ!


©ኢብኑ ተይሚያህ የሱናዉ አንበሳ የሱንዮችመድረክ!
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
@IbnuTeymyaYesunawAmbesa
Audio
«ቁርአን መሀፈዝ ያለው ጀረጃና እንዴት መሀፈዝ እንዳለብን ተዳሶበታል።»

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Audio
↪️ አዲስ ሙሀደራ


♦️የሙሀደራው ርዕስ
➫➫➫➫➫➫➫➫

📍በድብቅ የሚሰራ ወንጀል
📍የሚዲያ ፈተና በጥቅሉ
📍የስልክ አጠቃቀማን በተመለከተ

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
በከፍተኛ ስቃይ ላይ
ያለችውን እህት እናግዛት⁉️

ማናገር ከቻለች ስልኳ እነሆ
0935372242
#ሰአዳ_መኮነን__!!

ኦፕሬሽን ተደርጋ በከፍተኛ ስቃይ ላይ ትገኛለች እናም #እርህራሔው ያላችሁ እርዷት

በዚህ አካውንት ካደረሳችሁልኝ
አውጥቼ እሰጣታለሁ

👉1000309417554
ኑረዲን አል አረቢ

እባካችሁ ሙስሊሞች እንረዳዳ‼️
ማንን መርዳት እንዳለብንም እንወቅ

በተግባር መተዛዘንና መረዳዳት እንጂ
ስለ እናት
ስለ እህት
ሚዲያ ላይ መፃፍ ምን ዋጋ አለው⁉️
ምንም⁉️

ኢትዩጲያ ንግድ ባንክ
1000493844451
ሰአዳ መኮነን
ኹጥባ_የተዉሂድ ክልል
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
خُطْبَةُ الْجُمُعَةِ
የጁሙዓ ኹጥባ


حماية النبي حمى التوحيد!!

➧ነብዩ የተዉሂድንክልልመጠበቃቸዉ!!

🕌 ደሴ አል-አዝሐር መስጂድ

📅يوم الجمعة 25 من شهر ربيع الأول/1444)

🎙 أبو ريس محمد بن إمام آل إمام

      ↓↓↓
t.me/abu_reyyis_arreyyis/646
t.me/abu_reyyis_arreyyis/6467
✍️አድስ የሙሓደራ ዝግጂት ፕሮግራም


ዛሬ እሁድ ከምሺቱ 4:00ጀምሮ!

ተጋባዥ እንግዶች እና ርዕሶቻቸዉ
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

🎙ኡስታዝ አብዱልጀባር ሙ/ድ ኑር


➧ርዕስ፦መተናነስ አስፈላጊነቱ !!


🎙ኡስተዝ አቡ ዓብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ


➧ርዕስ ፦የሸይጧን ጉትጎታ!!

🔴ሙሓደራ የሚተላለፍበት ቴሌግራምአድራሻ👇
http://t.me/abuUseyminabdurehman
http://t.me/abuUseyminabdurehman
➧" ፍቅር "
➭➭➭➭➭

በመሰረቱ " ማፍቀር " ለጤነኛና ሰናይ ህሊና ባለቤቶች የተቸረ ታላቅና ውብ ፀጋ ነው ፡፡

በመብላት በመጠጣት እንዲሁም ሌሎች " መዝናኛ " ብለን የምንቆጥራቸውን ተግባራት ለአመታት በመፈፀማችን የማናገኘውን ደስታ የሰከንዶች እድሜ በሌለው የፍቅር ስሜት መሸመት እንችላለን ፡፡

ፍቅር ከአላህ ዘንድ የሆነ ታላቅ ተዐምርም ነው ፡፡ ይህንንም " ወዱዱ " ጌታችን በመጠቀው ቃሉ እንዲህ ሲል ገልፆታል።

وَمِنْ آَيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُمْ مِنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُمْ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآَيَاتٍ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ [ الروم : 21 ] ■

ለእናንተ ከነፍሶቻችሁ ሚስቶችን ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ ፥ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነት ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው፡፡ ■ [ ሱ - ሩም 21 ]

ፍቅር እጅግ በጣም የነፃ ውብ መሃረብ ( ጨርቅ ) ነው ፡፡ ይህን ነጭ ጨርቅ በአደፈ ( በቆሸሸ ) እጃችን ለመያዝ ከሞከርን የጨርቁን ውበትና ንፅህና እናጎድፈዋለን !

በተመሳሳይ ንፁህ ልብና ቅን ህሊናን ሳይዪዙ ወደ ፍቅር ዐለም ሰተት ማለት የተዋበውን ፍቅርን ልክ እንደ ነጩ ጨርቅ ማደክርየት ይሆናል ፡፡
ምክንያቱም ፍቅርን " በፍቅር " መያዝና ተንከባክበው ማቆየት የሚቻላቸው የንፁህ ልብና የብሩህ ህሊና ባለቤቶች ብቻ ናቸው ፡፡ ስለዚህም ወደዚህ ድንቅና ውብ አለም ( ወደ ፍቅር ) ከመግባታችን በፊት ልባችንና ህሊናችንን ልናፀዳ የግድ ይላል ፡፡

ሌላው ደግሞ ፍቅር ውድ ነውና ተልካሻና ርካሽ ቦታ ሊቀመጥ አይገባውም ፡፡ፍቅር በዘላቂነት እንዲቆይልን ብሎም ትክክለኛ ጣዕሙንና ጥፍጥናውን ይቸረን ዘንዳ " ያማረ ማስቀመጫ " ይፈልጋል ፡፡

ምን ማለት ነው

ፍቅርን ሳይበላሽ ማቆየት የሚችለውና ባማረና በጣፈጠ መልኩ ማቅረብ የሚችለው .... " ሀላል የሆነ ኒካህ "..... ብቻ ነው ! ከዚህ ውጪ በሆነ መልኩ የሚጠነሰስ የፍቅር እንቅስቃሴ ጣፋጭ መሳይ ነገር ግን እጅግ ጎምዛዛና ዘለቄታም የሌለው ስለሆነ ህሊና ላይ የማይሽር ጠባሳንም አሳርፎ ያልፋልና .... " እራቁት "...... !

ወንድሞችና እህቶች ጊዜያዊ ጣፋጭ መሳይ መራራ ገፈትን ..." በሀራም ፍቅር ".... መቀማመሱን ትታችሁ መሰላቸት የሌለበትንና ዘላቂነትን የተላበሰውን ...." ሀላሉን ፍቅር ጠብቁት ፤ ስታገኙትም አንቃችሁ ያዙት ".....
-
በተረፈ .....,

ፍቅር ጣፋጭ ነው = አጣጥሙት
ፍቅር ህይወት ነው = ኑሩት
ፍቅር መስወዐትነት ነው = ሙቱለት

ፍቅር............
ፍቅር............
ፍቅር............


በቃ ባካችሁ ፍቅር ፍቅር ነው = አፍቅሩት
___ካነበብኩት
➷➷➷➷➷➷➷
➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
👍2
Audio
AudioLab
የአሏህን ውዴታ ከሚያስገኙ ነገሮች ውስጥ አንዱ ….

ከኢርሻድ ደርስ የተቆረጠ


https://t.me/Muhammedsirage
سورۃ المرسلات
Abu Useymin
➭ተጋበዙ ቲላዋ

🎙 أبو عثيمين حفظه الله

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/tilawaAbu_Useymin