💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.56K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
↪️ሴት ልጅ ለጌታዋ ከሰገደች ፣ በሀያዕ ካጌጠች ፣ ሂጃቧን ከለበሰችና በመልካም ስነ_ምግባር ከታነፀች ከሷ በላይ ቆንጆ የለም።
የቀልብን ሰላም ከሚያደፈርሱ ነገሮች ተጠንቀቁ!

አንድ ነገር ቀልብህን እረፍት እንደነሳው ከታወቀህ እርግፍ አድርገህ ተወው !!

[ ኢብን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ ]

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
ድግምት አደገኝነቱና መፍትሄዎቹ
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም
📍خطبة الجمعة
📍የጁሙዓ ኹጥባ
↓↓↓

🌐 ድግምት አደገኝነቱና መፍትሄዎቹ

🌐 السحر خطره وعلاجه

🕌 ደሴ አል-አዝሓር መስጂድ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Forwarded from Abdusomed MuhammedNur (Abdulsemed MNur Al-Jeberty)
Online ደርስ

https://t.me/AbdulsemedMohammed?voicechat=3d699ac537c151d5f3

ثلاثة الأصول - ٢

ስላሰቱል ኡሱል - 2
💢ከሁሉ በፊት ለእውቀት ቅድሚያ ስጥ


📌قال العلامة صالح الفوزان -حفظه الله -
☑️ ሸህ ሷሊህ አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ብለዋል።

【والعلمُ أَحقُّ ما تُصرفُ فيه الأوقات، ويتنافسُ في نيلهِ ذَوو العقولِ، فبه تحيى القلوبُ وتزكو الأعمال】
አውቀት፦ ከሁሉ በላይ ጊዜ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋናውና ተገቢው ነው።
እውቀት፦ የአቅል ባለቤቶች ለማግኘት ሊሽቀዳደሙላቸው ከሚገቡ ነገራቶች ውስጥ አንዱ ነው። ምክንያቱም፦
🔺ቀልብ ህያው የሚሆነውና
🔺ስራ የሚጠራው በእውቀት ነውና።
📚 [الملخص الفقهي]
Audio
↪️የቁረአን ቂረአት ክፍል አስራ ስምንት

👉የሱረቱል ፊል አቀራር

በኡስታዝ አቡ አብደሏህ

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
መንሃጅ ነክ ጥያቄዎች
Sunnah Light
ቆየት ካሉ ሙሐደራዎች‼️
--------------------------------
በ#ወረባቦ ለተነሱ መንሐጅ ነክ ጥያቄዎች የተሰጠ መልስ

🔹ብዙ ነገር ተዳሰውበታል

🎙በኡስታዛችን አቡ ጁወይሪያ #ኸድር_አሕመድ አል-ከሚሴ አላህ ይጠብቀው
📌📌📌ከግጥም ማዓድ📌📌📌

ከሀገር ሀገር እውቀትን በመፈለግ የሚከራተተው ደረሳና ዘመናዎነት ያጠቃው በጂንስ የተጣበቀው ወጣት ያደረጉት ቁም ነገር አዘል ጭውውት በግጥም መልክ።

ደረሳው ና ወጣቱ

📚አሰላሙአለይኩም፤ ወንድሜ እንደምነህ፣
ጠፋህ እሳ ምነው፤ መስጅድም አላይህ።

👉ሃይ ደረሴ እንዴት ነሽ፤ ሰላም ነሽ፣
ደግሞ አምሮብሻል ፤ በዚህ ሰዓት ወዴት ነሽ።

📚ምነው የኔ ወንድም?፤
በኢስላም ሰላምታ መልስልኝ እንጂ፣
የፈረንጁ እንደሆን፣
ላንተም ሆነ ለኔ ለማንም አይበጅ።

👉ኡፍ አንች ደግሞ ፤ ስታይል አታርፊም፣
በቃ ደስ ይበለሽ ዋአለይኩም ሰላም።

📚አዎ እንደዚህ ነው ፤ ተብሎ ሚመለሰው፣
ይሄንኛው እኮ ነው ፤ አስር አጅር ያለው።

👉በቃ ደስ እንዳለሽ ፤ አንቺን እንደተመቸሽ፣
ደረሳ ነሽና፤ እስታይል ሙድ አይገባሽ።

📚ምነው የኔ ወንድም? ሴት መሰልኩህ እንዴ፣
አንቺ አንቺ ምትለኝ፤ ሴት እመስላለሁ እንዴ?

👉አቦ ለምዶብኝ ነው፤ አንቺ የምልህ።
በቃ ካሁን በኋላ፤ አንተ ነው ምልህ።

📚ታዲያ ምነው ጠፋህ? መስጅድም አላይህ፣
መድረሳም አትመጣ፤ ምነው ምን ገጠመህ?

👉ኦማይጋድ! ኦማይጋድ! ደረሴ አየሃት?
አቤት ቁንጅና! አቤት ውበቷ፤
እንዴት ቀሽት ልጅ ናት።

📚ምነው የኔ ወንድም ፤ ምን ተመልክተህ ነው?
አኡዙ ቢላሂ፤ እይ ያልከኝ ይሄን ነው?

👉አወና ደረሴ፤ እስኪ እያት አታምርም?
ዉበት ቁንጅናዋ ፤ አፍዞ አያስቀርም?

📚አቦ ወግድልኝ ምን አይነት ወስዋስ ነው፣
አጅ ነቢ መመልከት፤ በኢስላም ሀራም ነው።

👉ቋይ ተፈኩር ማድረግ፤ ምን ችግር አለበት?
ዉበቷን እያዩ፤ ሱብሃነላህ ማለት።

📚ታዲያ ለተፈኩር፤ ስንት መንገድ እያለህ፣
አላህ በሐረመው፤ ምን ችክ ትላለህ።

👉ቆይ ምን ችግር አለው፤
እኔ እሷን ብመለከት፣
ቁንጅናዋን ባደንቅ፤
ምን ጥፋት አለበት?

📚እስኪ መልስልኝ፤ አንዴ ልጠይቅህ፣
ደስ ይለሃል እንዴ፤ እህትህን ቢያዩብህ?

👉ኧረ በፍፁም፤
በጭራሽ አልፈቅድም፣
ማንም ለከስካሳ እህቴን እንዲለክፋት፣
በፍፁም አልሻም።

📚አየህ የኔ ወንድም፤ እሷም ወንድም አላት፣
በፍፁም የማይፈቅድ ፤ አንተ እንድትለክፋት።

👉እኔ መች አወቅኩኝ፤ መች ተገነዘብኩኝ፣
ስሜቴን ብቻ እንጂ፤ ሌላ መች አየሁኝ።

📚ለሌላ አታድርግ ፤ ላንተ ማትወደውን፣
ሰው አይወድምና፤ አንተ ምትጠላውን።

👉በቃ እተዋለው፤ እንግዲህ፣
ሁለተኛ አላይም፤ በቃ ከእንግዲህ።

📚አዎ የኔ ወንድም፤ እንዲህ ነው ሚባለው፣
እንደዚህ እንዳንተ ምክር ሚሰማን ነው፤
አላህ የሚወደው።

👉በአላህ ደረሴ ፤ ከልብ አፉ በለኝ፣
በተናገርኩት ነገር፤ እንዳትቀየመኝ።

📚ኧረ እኔ ትቻለው፤ ብዩ አፈውቱሊላህ፣
ባይሆን አንተ ቶብት፤ በል አስተግፊሩላህ።

👉ጌታዩ አጥፍቻለው፤ ይቅር በለኝ እባክህ፣
ቶብቻለሁና፤ እያኝ በእዝነትህ።

📚አሁን ሰላት ደርሷል፤ ሀያ መስጅድ እንሂድ፣
ዉዱዕ እናድርግና ፤ በጀመዓ እንስገድ።


🔀ያን ገራገር የኢልም ፈላጊ ደረሳ አላህ ይዘንለት ለወጣቱ መመራት ሰበብ ነውና።

አንተ ውዱ ወንድሜ ሆይ የአይሁዳን ሱና ሳይሆን የነብዩን ሱና ተከተል አይንህን ስበር።

አንቺ ዉዱዋ እህቴ ሆይ እራስሽን በሒጃብ ና በኒቃብ አስከብሪ።

➡️ኢማሙ አሻፊኢ አላህይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦ አንዴ በመንገድ የተጓዝኩኝ ያለ የአንዲትን ልጅ አገረድ ባት በድንገት ተመለከትኩኝ ከዚያም የተማርኩትን መሀፈዝ ከበደኝ አቃተኝ ይህንንም ጉዳይ ወኪዓ ለሚባሉ ሸይኼ አማከርኳቸው እነሱም ወንጀልን ቀንስ ተው በማለት አመላከቱኝ ይላሉ።

🗝እንኛስ ስንቱን አላህ ያልፈቀደውን ነገር እንመለከታለን? ከሙሰልሰል ድራማ ጀምሮ አላህ በራህመቱ አይን ይመልከተን እንጂ።
አላህን ልንፈራ ይገባል።➡️

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ ሐሽር 18

{{ወንድማችሁ }}Abu bilal aslefiye
أخوكم أبو بلال السلفي

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
ርዕስ አላህን መፍራት

🎙 በወንድም ኑራድስ መርሳ
[ሓፊዞሁሏህ]

#የሸይኽ መሐመድ ሐያት ደረሳ ነው
አላህ እውቀትን ይጨምረለት

በትንሽ ደቂቃ ውስት በርካታ ቁንገሮችን አስጨብጦናል አላህን መፍራት

يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ وَالْأَرْحَامَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا

እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአዳም) የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን (ሔዋንን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ያንንም በርሱ የምትጠያየቁበትን አላህንና ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና፡፡

إِنَّمَا ذَٰلِكُمُ الشَّيْطَانُ يُخَوِّفُ أَوْلِيَاءَهُ فَلَا تَخَافُوهُمْ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

እንዲህ የሚላችሁ ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል፡፡ አትፍሩዋቸውም፡፡ ምእምናንም እንደኾናችሁ ፍሩኝ፡፡

🕌 መስጅዴ ሶፋ ላይ ሃራ ውላጋ

🕑ከመግሪብ ሶላት ቦኀላ

ዙል ቃኢዳ፣ ቀን/23/1442/ዓ/ሂጅራ
وَتَزَوَّدُوا۟ فَإِنَّ خَيْرَ ٱلزَّادِ ٱلتَّقْوَىٰ ۚ وَٱتَّقُونِ يَٰٓأُو۟لِى ٱلْأَلْبٰب ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው፡፡ የአእምሮዎችም ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ፡፡
በሙብተዲኦች ላይ ጥንካሬ
🎙በኡስታዝ አቡ ሀመዊያ
በሙበተዲኦች ላይ ጥንካሬ


የተዳሰሱት ነጥቦች ↙️↙️↙️
↪️ ማግራራት አደገኛ ፈተና ስለመሆኑ፤

➡️ በሙብተዲኦች ላይ ወጥ አቋም ይዞ በሱና መተሳሰር እንዳለብን፤

↪️ ስራን እንጂ ኒያን በአይን አናይም። በመሆኑም ጥፋተኛ ጥፋቱ እዳይጋለጥ ንያው ሌላ ነው ማለት ተቀባይነት የለውም

➡️ የኡላማዎችን ምክር ከልባችን መስማት እንዳለብን፤

↪️ አንዳንድ ሰዎች ሙኻሊፎች ላይ ረድ እንዳይደረግ እጅግ ውስብስብ የሆኑ ቁርአንና ሀዲስ ላይ የሌሉ አንድም ረድ አድራጊ የማያሟላቸውን ቅድመ-ሁኔታዎች ያስቀምጣሉ። ይህን የሚያደርጉት ሙብተዲዕ ላይ ረድ [ለጥፋቱ ማስተካከያ ምላሽ] እንዳይሰጥ በሩን ለመዝጋት ነው።

➡️ ከለዘብተኛ {መተሳሂል} ነገሮችን የሚያቃልል እና የሚያግራራ ከሆነ ግለሰብ ቀደምቶቻችን ሀዲስ አይዘግቡም ነበር። ይህ የሙተሳሂሎችን አደገኝነት ቁልጭ አደርጎ ያሳያል።

↪️ አንዱ ሰው በሆነ ሙብተዲዕ ላይ ረድ ካደረገ ሌላኛውም ቢያደርግ መጀመሪያ ላደረገው ድጋፍ (ማጠናከር) ነው። ልክ ሸይኽ ረቢዕ እንደሚሉት ማለት ነው።

🎙 በኡስታዝ ሸምሱ አቡ ሀመዊያ (ሀፊዘሁላህ)

በደንብ ይደመጥ ወሳኝ ሙሐደራ ነው። በብዕር እንመነዝረዋለን #ኢንሻአላህ

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
#ወንድ_ሆይ_ሴት_ልጅ_ካንተ_ምን_ትፈልጋለች

1//- ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት፡፡

2- //ሴት ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። (ባገኘከው አጋጣሚ) ፍቅርህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል።

3- //ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ። ደካማ ወንዶችን ደግሞ
ይንቃሉ አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር።

4- //ሴቶችን መልካም ንግግር፡ ውብ ገጽታ፡ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖሩህ ጥረት አድርግ።

5- //ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው። ቤቷ ስትሆን ዙፋኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት
ያህል ክብር ይሰማታል። በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባትን ነገር እንዳትፈጽም። ከንግስና
ዙፋኗ ላይ ልታወርዳትም አትሞክር። ይህን ካደረክ ንግስናዋን
እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ።

6-// ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም።
አንተን ከቤተሰቦቿ በላይ እንድትወድህ
ለማድረግ አትጣር። ይህን ማድረግ ፍጻሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል።

7- ///ሴት ከጎንህ (ጠማማ አጥንት) መፈጠሯን አትዘንጋ። ይህ
አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን እወቅ። ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለሁ እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ። ስብራቷ ፍቺ ነው። ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት። መካከለኛ ሰው ሁንላት።

8- ///ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች። (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ነገር
ግን እንዲህ አደረገች በማለት ብቻ እንዳትጠላት። ይህን ባህሪዋን ባትወድላት ሌሎች የሚስቡህ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ።

9- ///ሴት አካላዊ ድካምና ስነልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል። so ትእዛዝ አታብዛባት።

10-// ሴት አንተ ዘንድ ያለች (የፍቅር) ምርኮኛህ መሆኗን አትዘንጋ። ምርኮኛህን በጥሩ ሁኔታ ያዛት፡ እዘንላት፡ በድክመቷ
(የምትፈጽመውን ስህተት) እለፋት። ምርጥ የሂዎት አጋርህ
ትሆናለች።

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ تُوبُوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ تَوْبَةًۭ نَّصُوحًا
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ንጹሕ የኾነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፡፡
ከዚሁ ካገኘሁት ባይጠቅማችሁም አይጎዳችሁ"ለተጠቀመበት ትልቅ ትምህርት ነዉ።
አሏህ የፃፈልሽ ላያመልጥሽ መዝረክረክ
አታብዢ እህቴ በተለይ በዚህ ሚድያ"
:
:
⭕️ ጥንቁቅነቷ አስገረመው‼️
ከዛም ለሚስትነት እንደሚፈልጋት ነገራት

📱#እሷም_በበጎ_ጎኑ_በማየት_እንዲያወራት_በሩን #ከፈተችለት_ፈቀደችለት_ለረጂም_ጊዜ_አወሩ

🔻 ከቀን ቀን የጥንቁቅነቷ ገፆች መርገፍ ጀመሩ

ከዛም ተዋት! ✂️
⭕️ ምክንያቱም ጥንቁቅ ሴት እፈልጋለሁ #ስለሚልና እሷ ደግሞ ጥንቁቅነቷ ስለተወገደ ‼️

መልዕክቱ ላንቺ ነው ውዷ እህቴ
ንቂ! ........ አሁንም አረፈደም

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
ማጠቃለያ ምክር
Muhammedsirage M.NUR
አጠር ያለች ምክር‼️
=============
||
#ኢንተርኔት
#ማህበራዊ ድረገጾች እና ሌሎች ነገሮችም ተዳሰውበታል

💦 በማጠቃለያ ምክር

🎙#Ustaz Muhammedsirage M. NUR አሏህ ይጠብቀው

ጆይን በማለት ቤተሰብ ይሁኑ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
የተስቢህ፣ ተህሚድ እና ተክቢር ትሩፋት



قال صلى الله عليه وسلم : « من قال : سبحان الله وبحمده في يوم مائة مرة حطت خطاياه ولو كانت مثل زبد البحر »

↪️የአላህ መልዕክተኛ (ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-

سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ

💦‹‹በቀን መቶ ጊዜ (ለአላህ ምስጋናና ጥራት ይገባው፡፡) ያለ ሐጢአት የባህር አረፋ ያክል እንኳ ቢሆን ይታበስለታል፡፡››


وقال صلى الله عليه وسلم : « من قال لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ عشر مرار . كان كمن أعتق أربعة أنفس من ولد إسماعيل »

↪️የአላህ መልዕክተኛ (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-

لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ

🔻ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አጋር የለውም፡፡ ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢነቱ ለረርሱ ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው›› የሚለውም አሥር ጊዜ ያለ

🔹 ከኢስማኤል ልጆች አራት ያህሉን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፡፡ .

وقال صلى الله عليه وسلم : « كلمتان خفيفتان على اللسان , ثقيلتان في الميزان , حبيبتان إلى الرحمن : سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ سُبْحَانَ اللهِ الْعَظِيْمِ. »

">የአላህ መልዕክተኛ (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሁለት ንግግሮች አሉ፡፡ ምላስ ላይ ቀላሎች÷ ሚዛን ላይ ደግሞ ከባዶች ናቸው፡፡

↪️ከአላህ ዘንድም ተወዳጅነት አላቸው፡፡ (እነሱም)‹‹

سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ سُبْحَانَ اللهِ الْعَظِيْمِ

🔹‹ ለአላህ ጥራትና ምስጋና ይገባው፡፡ ለታላቁ አላህ ጥራት ይገባው››

وقال صلى الله عليه وسلم : « لأن أقول سُبْحَانَ اللهِ وَالْحَمْدُ لِلَّهِ وَلاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَاللهُ أَكْبَرُ , أحب إلي مما طلعت عليه الشمس »

የአላህ መልዕክተኛ (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡:

سُبْحَانَ اللهِ وَالْحَمْدُ لِلَّهِ وَلاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَاللهُ أَكْبَرُ

🔻‹አላህ ጥራት ይገባው፡፡ ምስጋናም ለአላህ ተገቢው ነው፡፡ ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አላህ ከሁሉም የላቀ ነው››

በማለት (አላህን ማወደስ) ፀሀይ ከምትወጣበት (ቦታና ሃብት) ሁሉ ይበልጥ ከኔ ዘንድ ተወዳጅ ነው፡፡.’
🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄
وَقَالَ -صلى الله وسلم-: ((أَيَعْجِزُ أَحَدُكُمْ أَنْ يَكْسِبَ كُلَّ يَوْمٍ أَلْفَ حَسَنَةٍ)) فَسَأَلَهُ سَائِلٌ مِنْ جُلَسَائِهِ، كَيْفَ يَكْسِبُ أَحَدُنَا أَلْفَ حَسَنَةٍ؟ قَالَ: ((يُسَبِّحُ مِائَةَ تَسْبِيْحَةٍ، فَيُكْتَبُ لَهُ أَلْفُ حَسَنَةٍ أَوْ يُحَطُّ عَنْهُ أَلْفُ خَطِيْئَةٍ))

መልዕክተኛው (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) ፡- ‹‹ከናንተ አናዳችሁ በየቀኑ አንድ ሺህ የመልካም ሥራ ምንዳ (ሐሰና) ማግኘት ይሳነዋልን?›› በማለት ጠየቁ፡፡

💦ከታዳሚዎች አንዱ ፡- ‹‹እንዴት በየቀኑ አንድ ሺህ ምንዳዎችን ማግኘት ይቻላል?›› በማለት ጠየቀ፡፡

💦‹‹መቶ ተሰቢሕ›› ያድርግ፡፡ አንድ ሺህ ምንዳ ይጻፍለታል፡፡ ወይንም አንድ ሺህ ሐጢአቶች ይታበሱለታል፡፡›› አሉ፡፡ ’

من قال : سبحان الله العظيم وبحمده غرست له نخلة في الجنة

سُبْحَانَ اللهِ العَظِيْم وَبِحَمْدِهِ

"🔹ለታላቁ አላህ ጥራትና ምስጋና ይገባው÷ያለ ጀንነት ውስጥ አንድ የተምር ዛፍ ይተከልለታል፡፡

وقال صلى الله عليه وسلم : « يا عبد الله بن قيس ألا أدلك على كنز من كنوز الجنة ؟ " فقلت : بلى يا رسول الله ، قال : " قل لا حول ولا قوة إلا بالله »

💦መልዕክተኛው (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) ፡፡ ዓብደላህ ኢብን ቀይስ ሆይ ከጀነት ድልቦች አንዱል ልጠቁመህን?>> አሉ። የ አላህ መልክተኛ ሆይ አዎ የጠቁሙኝ አላቸው

لاَ حَوْلَ وَلَا قُوَةَ إِلَا بِاللهِ
🔹ብልሐትም ኃይልም በአላህ ቢሆን እንጅ የለም
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
وقال صلى الله عليه وسلم : « أحب الكلام إلى الله أربع ، لا يضرك بأيهن بدأت : سبحان الله , الحمد لله , ولا إله إلا الله , والله أكبر»

↪️ነቢዩ (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ከአላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው። በየትኛውም ብትጀምር ልዩነት የለውም፡፡ .’

سُبْحَانَ الله , وَالحَمْدُ لله , وَلَا إِلَهَ إِلَا الله , وَاللهُ أَكْبَر

إِنَّ أَفْضَلَ الدُّعَاءِ الْحَمْدُ لِلَّهِ، وَأَفْضَلَ الذِّكْرِ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ

ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ

الْحَمْدُ لِلهِ
አልሐምዱ ሊላህ

ከዚክሮች ሁሉ በላጩ ደግሞ:

لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
سورۃ الفاتحۃ
<unknown>
በዳሩል ሀዲስ መድረሳ ለኮድ1 ተማሪዎች የሚሰጥ ተከታታይ ቅርአት ከተወሰነ የተጅዊድ ማብራሪያ ጋር

⤴️ #ክፍል_አንድ

🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya