💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.59K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.17K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
ሙሓደራ 111 ኢኽላሥ እውነታው ደርጃው ጥቅምቹና እሱን የማግኛ መንገዶች በኡስታዝ አቡ ሙስሊም المحاضرة…
በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር ሀሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁሏህ)
🔶 ኢኽላሥ: እውነታው ፣ ደርጃው ፣ ጥቅምቹና እሱን የማግኛ መንገዶች

ክፍል (2)
🔹 فوائد الإخلاص

🔹 የኢኽላሥ ጥቅምቹ።

♦️በሚል የተደረገ ሙሐደራ📚

📚By Usetaz Abu Muslim📚

#ተ_ቀ_ላ_ቀ_ሉ
https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
أذكار الصباح بصوت وصوره يريح القلب رائعه (مكتوبه) azkar al sabah
Learn Us
🍃""""""አዝካሩ ሰባህ """"""🍃

🥀""""""دعاء الصباح""""""""🥀

አዝካሩ ሰባህ (የጠዋት ዚክር)

ሌሊቱ ሲነጋ ሲገፈፍ ጨለማው
ፀሀይዋ ስቶጣ ቀኑን ልታደምቀው!!

አልኩ الحمدلله ሲገለጡ አይኖቸ
ዛሬም እድል ሰጠኝ አላደርኩም ሙቸ!!

ሱጁደ ላይ ሆኘ ላመስግን ጌታየን
ቀኑ እድያምርልኝ ነገም እድያደርሰን!!

╭─••─═••••••═─
﴿فَاصْبِرْ عَلَى مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ غُرُوبِهَا وَمِنْ آنَاءِ اللَّيْلِ فَسَبِّحْ وَأَطْرَافَ النَّهَارِ لَعَلَّكَ تَرْضَى﴾.
_ከአቡሁረይራ በተዘገበ ሀዲስ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፤_
_🍀 عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ : ”...احْرِصْ عَلَى مَا يَنْفَعُكَ وَاسْتَعِنْ بِاللهِ وَلَا تَعْجَزْ، وَإِنْ أَصَابَكَ شَرٌّ فَلَا تَقُلْ لَوْ أَنِّي فَعَلْتُ كَذَا وَكَذَا قُلْ قَدَّرَ اللهُ وَمَا شَاءَ اللهُ فَعَلَ، فَإِنَّ لَوْ تَفْتَحُ عَمَلَ الشَّيْطَانِ“ رَوَاهُ مُسْلِم_
*🍀 «በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ አትሰላች፤ መጥፎ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ፤ ‘ይህን ነገር እንዲህ ወይም እንዲያ ባደርገው ኖሮ…’ አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ፤ አላህ የፈለገውን ይሰራል’ በል። ‘እንዲህ ቢሆን ኖሮ’ የሚለው ንግግር ለሰይጣን ስራ በር ይከፍታል» ሙስሊም ዘግበዉታል*
┈┉┅━
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ዘጠኝ وَأَنَّ ٱلْمَسَٰجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدًۭا እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ ➧በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ይህ አንቀጽ አምልኮ ለአላህ ብቻና ብቻ እንደሚገባ ከሚያመለክቱ ዋና ዋና አንቀጾች ውስጥ አንዱ ነው።አንቀጹ ላይ መስጅድ ለተባለው ከተሰጡት ትርጉምች ውስጥ በጥቂቱ ➳ሰባቱ…
መንዙማ
➬➬➬➬➬

እውነታው፡አደጋዎቹና መዘዞቹ

➧ክፍል አስር

➤ከዚህ ሐዲሥ እንደምንረዳው አህለል ኪታቦች ተውራት እና ኢንጂል
የወረደላቸው “የመጸሀፍቱ ባለቤቶች” ተብለው ቢጠሩም የተውራት እና የኢንጂል ዋና መልክት የሆነውን ተውሒድ በሺርክ እና በኩፍር ስለ ለወጡት አላህ መልክተኛውን (صلى الله عليه وسلم (ልኮ ወደ ሁሉ ነብዩ መንገድ እንዲመለሱ ጥሪ እንዲደረግላቸው አዘዘ።

➧ለዚያም ነው ነብዩ (ص
➲በዚህ ሀዲስ መሰረት ከምንም ነገር
በፊት እምነትን የማስተካከል ነገር ይቀደማል። ወደ አላህ መንገድ እንጣራለን የሚሉ ሁላ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ለሙኣዝ የሰጡትን ትእዛዝ፣ ሙአዝ በተግባር ያሳዩትን መንገድ ተቀብሎ ወደ ተውሒድ ጥሪ ከምንም በፊት ሊያደርግ ይገባዋል።


እምነቱ ያልተስተካከለ ሰው የሰራውን ያህል ቢሰራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት
የለውም። ለዚህም ማስረጃው ኢማሙ ሙስሊም የዘገቡት ታሪክ ነው። የሆኑ ሰዎች ከበስራ (ኢራቅ) አካባቢ ለሀጅ መጡ። ሶሐባው ዐብደላህ ኢብን ዑመርን (ረድየላሁ ዐንሁማ) አገኙ። ከዚያም በአካባቢያቸው ቀደርን (የአላህን ውሳኔ) የሚያስተባብሉ ሰዎች እንዳሉ ነገሯቸው።

በዚህን ጊዜ ኢብኑ ዑመር “ንገሯቸው እኔም ከነሱ አይደለሁም፣ እነሱም ከእኔ አይሉም። በቀደር እስከሚምኑ ድረስ በአላህ መንገድ ላይ የኡሁድ ተራራን የሚያክል ወርቅ ቢሰጡ አላህ አይቀበላቸውም” በማለት መለሱላቸው

➲ይህ ታሪክ የሚያስረዳን እምነት ሳይስተካከል የተሰራ ስራ የኡሁድ ተራራን የሚያክል ወርቅ በአላህ መንገድ ላይ ቢለግሱ እንኳን ተቀባይነት እንደሌለው ነው። ለዚህም ነው ከምንም በፊት እምነትን፣ አቂዳን፣ ተውሒድን ማስተካከል ግድ የሆነበት
ምክንያት። መልካምን ነገር ሌላ መልካም ነገር ይበልጠዋል።

የመልካም ነገሮች ሁሉ ቁንጮ
ተውሒድ እምነትን ማስተካከል ስለሆነ የመጀመሪያው ጥሪ የተደረገው በዚህ ጉዳይ ላይ ነው። ከዚያም ነብዩ (صلى الله عليه وسلم” (ይሄን እሺ ካሉህ” በማለት ወደ ሁለተኛው መልካም ትእዛዝ
ጠቆሙ። መልካም ስራዎች ሁሉ የሚገነቡት ተውሒድ የሚባለው ታላቁ መሰረት ሲስተካከል ነው::


➧ለዚያም ነው “የመጀመሪያ የምትጠራቸው ከአላህ በስተቀር (እውነተኛ) አምላክ እንደሌለ እና እኔም የአላህ መልክተኛ መሆኔን እንዲመሰክሩ” በሌላ ዘገባ “አላህን በብቸኝነት በአምልኮ እስኪነጥሉት ድረስ” የሚል ነብያዊ ተእዛዝ ለሙአዝ የተላለፈው። እሱም እንደታዘዘው የፈጸመው።

ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል◉◉◉◉

📚መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል{ሀፊዘሁሏህ} የተወሰደ

📖አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➤ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
▪️የአርበኢን ሀዲስ ቂርአት


ክፍል ②


➡️ ሀዲስ ቁጥር ሁለት

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

የተሀረከ የኪታቡን pdf ለማግኘት
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/4484
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/4484
عن عبدالله بن مسعود رضي الله عنه:

قال رسول اللهﷺ :

أوتِرُوا يا أهلَ القرآنِ، إنَّ اللهَ وِتْرٌ يُحبُّ الوِتْرَ
-
📚الألباني صحيح الجامع ٢٥٣٨
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እውቀት ብርሃን ነው

የዲን እውቀት አላህ በመረጣቸው ባሮቹ ልብ ውስጥ የሚያፈሰው ብርሃን ነው። ከዚህ ብርሃን ቀልቡን ያራቀ በጨለማዎች ውስጥ ይንከራተታል።

ዲናችንን ተግተን እንማር
https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
اللهمَّ بعلْمِك الغيبِ، وقدْرتِك على الخلقِ أحْيِني ما علمتَ الحياةَ خيرًا لي، وتوفَّني إذا علِمْتَ الوفاةَ خيرًا لي.
وَقَالَ -صلى الله وسلم-: « أَقْرَبُ مَا يَكُوْنُ الرَّبُّ مِنَ الْعَبْدِ فِيْ جَوْفِ اللَّيْلِ اْلآخِرِ فَإِنِ اسْتَطَعْتَ أَنْ تَكُوْنَ مِمَّنْ يَذْكُرُ اللهَ فِيْ تِلْكَ السَّاعَةِ فَكُنْ »

ነቢዩ (ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-

▪️ ‹‹አላህ ለባሪያው ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ከመጨረሻው የሌሊቱ ክፍል ላይ ነው፡፡ በዚያ ወቅት አላህን ከሚያወሱት ለመሆን ከቻልክ ሁን፡‼️

وَقَالَ -صلى الله وسلم-: « أَقْرَبُ مَا يَكُوْنُ الْعَبْدُ مِنْ رَبِّهِ وَهُوَ سَاجِدٌ فَأَكْثِرُوا الدُّعَاءَ »

↪️የአላህ መልዕክተኛ (ሰለሏሁአለይሂ ወሰለን) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሰውየው ለአላህ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ነው፡፡ (ሱጁድ ላይ) ዱዓ አብዙ፡፡›› ’
الصلاة على النبي ﷺ بصوت جميل يريح النفس ويسعد القلب || #هيثم_الدخين
هيثم الدخين - Haithm Aldokhin
የጁሙዓ ቀን ሱናዎች

①) ገላን መታጠብ
②) ሲዋክ መጠቀም
③) ጥሩ ልብስ መልበስ
④) ሱረቱል ከህፍን መቅራት
⑤) ሽቶ መቀባት (ለወንዶች)
⑥) ሑጥባ በጥሞና ማዳመጥ
⑦) በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ
⑧) በነብዩ ﷺ ላይ ሶላትና ሰለዋት ማብዛት
⑨) ዱአ ተቀባይነት ያለበትን ሰአት ስላለ መጠባበቅ
ኹጥባ_በሙስሊም ህይዎት ላይ የተዉሂድ ቦታ
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም
ቆየት ካሉ የጁሙዓ ኹጥባ መካከል ርዕስ👇

🇸🇦 በሙስሊም ህይዎት ዉስጥ የተዉሂድ ቦታ!!

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም አላህ ባለበት ይጠብቀዉ!!

➲የሱ ኹጥባ እና ትምህርቶች ከታች ባለዉ ሊንክ ያገኙታል ይቀላቀሉ!👇

t.me/abu_reyyis_arreyyis/3192
t.me/abu_reyyis_arreyyis/3192
↪️የሙእሚኖች መሪ የሆነው ዑመር ኢብኒ ኸጣብ እንዲህ አለ፦

📚 “የሆነ ቀን ከአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀምጠን እያለ፡ በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው፥ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰ፥ የመንገደኛ ምልክት የማይታይበት፥ ከኛ ውስጥም ማንም የማያውቀው ሰውዬ ብቅ አለና እነብዩ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀመጠ። ጉልበቱን ከጉልበታቸው ጋር አገጣጠመ፥ መዳፉንም ታፋው ላይ አስቀመጠ። ከዛም አንተ ሙሓመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ አላቸው።

↪️ የአላህ
መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ኢስላም ማለት ፦ በእውነት የሚመለክ ጌታ አንድ አላህ ብቻ ነው ብሎ እና ሙሓመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣ ሶላትን በወቅቱና ቀጣይነት ባለው መልኩ መስገድ፣ ዘካን ማውጣት፣ ረመዳንን መጾም፣ የአላህ ቤትን ከቻልን መጎብኘት።” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ዑመርም እንዲህ አለ “በሱ ተገረምን! እሳቸውን ይጠይቃል መልሶ እውነት ተናገርክ ይላቸዋል!” ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢማን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ[ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢማን ማለት ፦ በአላህ ማመን፣ በመላኢኮች ማመን፣ በመጻህፍት ማመን፣ በመልእክተኞች ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን፣ በአላህ ውሳኔ ከፋም በጀም ማመን” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢሕሳን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢሕሳን ማለት አላህን እንደምታየው አድርገህ ልታመልከው ነው፥ አንተ ባታየውም እሱ ያየሃል እና።” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ሰአቷን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ የሚያውቅ አይደለም” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ምልክቶቿን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ባርያ ጌታዋን ልትወልድ ነው፣ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ፥ እርቃናቸውን የነበሩ፥ ድሆች የነበሩ የፍየል ጠባቂዎች ህንጻ ለመስራት ሲሽቀዳደሙ ልታይ ነው።” ከዛ ቡሃላ ሰውየው ሄደና ብዙ ቆየን። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “አንተ ዑመር ሆይ!ጠያቂው ማን እንደሆነ ታውቃለህን?” ዑመርም “አላህና መልእክተኛው ያወቁ ናቸው።” በማለት መለሰ። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ የመጣው እኮ ጂብሪል ነው፥ ሃይማኖታቹህን ሊያስተምራቹህ መጣቹህ።

(ሙስሊም ዘግበውታል)

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya