💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.68K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
ለሱና ደዕዋ የእውነት መቆርቆር ያላችሁ ወገኖች!
~
ደዕዋው በጩኸት፣ በግርግር፣ በፍጥጫ፣ በንትርክ እንዲታወቅ አናድርግ። አላህን እንፍራ። እንዲህ አይነት አካሄድ ደዕዋው ላይ ከባድ ጠባሳ ነው የሚጥለው።
* እርጋታ፣ ስክነት ይኑረን። በትንሽ በትልቁ ከመጯጯህ እንውጣ።
* ለደዕዋው መልካም ስም እንጨነቅ። መልካም ስም ዋጋው ከምናስበው በላይ ዋጋው ትልቅ ነው። ለራሳችን ክብር ስንል ያለፈ ያገደመው ላይ የምንጮህ ከሆነ ደዕዋውን እንጎዳለን።
* ወገናችንን ከስር ጀምሮ በስርአት በዒልም መኮትኮት ላይ ቅድሚያ ሰጥተን ተግተን እንስራ።
* ክፉ አመላችንን እንግራ። ጀብደኝነት፣ ከዚያም ከዚህም ጋር መላተም ይጎዳናል እንጂ አይጠቅመንም።
* በየ አካባቢያችን በተቻለን አቅም ማህበራዊ ተሳትፎ ቢኖረን መልካም ነው። የተቸገረን መርዳትና ማስተባበር፣ የታመመን መጠየቅ፣ ማሳከም፣ መሻይኾችን ማክበር፣ ማገዝ፣ ወዘተ. ተግባር ከንግግር በላይ ይጣራል።

የቴሌግራም ቻናል፡-
=
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
👈‏كانت فاطمةُ رضيَ اللهُ عنهَا إذا كانَ يومُ الجمعة، أرسلَت غلامًا لها ينظرُ لها الشّمس، فإذا أخبرَها أنها تدلّت للغُروب، أقبلَت علىٰ الدُّعَاء إلىٰ أن تغِيب.

📕 [ فتح الباري كتاب الجمعة (۱۹۲۲) ]


🔖ፋጢማ አላህ መልካም ስራዋ ይውደድላትና የጅሙአ ቀን ከአሱር በኋላ አንድ ልጅ ታስቀምጥና ፀሀይ እንዲመለከትላት ታዘዋለች። ይህ ሰው ፀሀይ ልትገባ እየተቃረበች መሆኑን ሲነግራት፦ ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጋ በመተው ፀሀይዋ እስክትጠልቅ ድረስ ወደ ዱአ ትዞር ነበር

~
t.me/https_Asselfya
🔖በቁርኣን ማንባት የአላህ መልካም ባሮች ምልክት ነው፡፡ አላህ ሲገልፃቸው  “የአልረሕማን አንቀጾች በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ ሰጋጆችና አልቃሾች ኾነው ይወድቃሉ፡፡” ይላቸዋል፡፡

(መርየም ፡58)

t.me/https_Asselfya
በስደት ላይ የምትኖሩ እህቶቼ እራሳችሁን ውደዱ፤ #ለማን ብላችሁ ነው እንዲህ የምትሆኑት!? ሰዉነታችሁን መጠበቂያ የሚሆን ቫዝሊን፣ ሎሽን የመሳሰሉትን ገዝታችሁ ተቀቡ። ስራ ስትጨርሱ እራሳችሁን ጠብቁ። ሐቂቃ እንድህ ተበሳቁላ፣ ራሷን አጥታ፤ ሰርታ ነው ብር የምትልክልን ብለው ማንም አያዝንላችሁም። እህቶቼ ለራሳችሁ እራሳችሁ ናችሁ ያላችሁት

t.me/https_Asselfya
👍13
ዶዒፍ!
~
اللَّهمَّ بارِكْ لَنا في رجبٍ وشعبانَ وبلِّغنا رمضانَ
"አላህ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ባርክልን። ረመዷንን ደግሞ አድርሰን።"
-
ነወዊ፣ ኢብኑ ሐጀር፣ አልባኒ፣ . . . ዶዒፍ (ለመረጃ ብቁ ያልሆነ) እንደሆነ ገልፀዋል።
=
የተከበሩ ወራቶች!

ከአቢ በክራህ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ:  ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ الزَّمانَ قَدِ اسْتَدارَ كَهَيْئَتِهِ يَومَ خَلَقَ اللَّهُ السَّمَواتِ والأرْضَ، السَّنَةُ اثْنا عَشَرَ شَهْرًا، مِنْها أرْبَعَةٌ حُرُمٌ، ثَلاثٌ مُتَوالِياتٌ: ذُو القَعْدَةِ، وذُو الحِجَّةِ، والمُحَرَّمُ، ورَجَبُ، مُضَرَ الذي بيْنَ جُمادى، وشَعْبانَ.﴾

“አላህ ሰማይና ምድርን በፈጠረ ግዜ አመትን አስራ ሁለት ወር አድርጎቸዋል። ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት)  የ”ረጀብ” ወር ነው።”

📚 ቡኻሪ  ሙስሊም  ዘግበውታል

     t.me/https_Asselfya
👍4
«ከሰው ሁሉ ጠንካራ መሆን ያሰኘው ሰው በአላህ ላይ ብቻ ይመካ»።

ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ)

ምንጭ፦📚 ዛዱል መዓድ (2/364)
=
👍8
ከልማድ የወጣ ነገር
አጫጭር ምክሮች
ከልምድ የወጣ አለባበስን መራቅ

🎙 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
وأنّهُ لاَ مُستراح للرُّوحِ ولا لذّةٌ للقلبِ إلاّ بالعيشِ فِي رِحاب القُرآن!.
👍1
الأيام ثلاثة...


قالَ ابنُ الجَوزِي -رَحِمَهُ الله تَعَالَى : -

«يا هَذا، الأيَّامُ ثلاثةٌ:

~أمسٍ قَد مضَىٰ بِمَا فِيه،

~وغَدٍ لعلَّكَ لا تُدرِكُه،

~وإنَّما هُوَ يومُكَ هَذا، فاجتَهِدْ فِيه،

ولِلَّـهِ درُّ مَن تنبَّهَ لِنَفسِه، وتزوَّدَ لِرَسمِه، واستدرَكَ ما مضَىٰ مِن أمسِهِ قبلَ طولِ حَبسِه».


📘 التبصِرَةُ: (١٥٨/١)
🔖 ከአኺራው ጀነት በፊት በዱንያው ጀነት ውስጥ እራስህን ማግኘት ከፈለግክ የጥዋት እና የማታ ዚክር ላይ ተጠናከር።

~
👍12
የሹዐይብ ጥሪ!
~
((وَيَا قَوْمِ أَوْفُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ * بَقِيَّتُ اللَّهِ خَيْرٌ لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ ۚ وَمَا أَنَا عَلَيْكُمْ بِحَفِيظٍ)
«ሕዝቦቼም ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ፡፡ ሰዎችንም ምንም ነገራቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ፡፡ አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ ምእመናን እንደሆናችሁ (አላህ በሰጣችሁ ውደዱ)፡፡ እኔም (መካሪ እንጅ) በናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም፡፡» [ሁድ: 85–86]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
👍6
ደጋጎቹን ደጋግ ያደረግክ ጌታችን ሆይ ከደጋግ ባሮችህ እስክንሆን ድረስ አግዘን።

~
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
👍6
🔖ሁሌም እጃችሁን ወደጌታቹህ ከፍ ስታደርጉ በመልካም ዱአቹህ እህት ወንድሞቻችሁን አትርሱ!

ሙዕሚን ከራሡ አልፎ የሌሎች ጭንቀት የሌሎች ማጣት ያሣሥበዋል! አትርሱ እናንተ ለሌሎች ስትቆሙ አላህ ለእናንተ ይቆማል

المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»
👍11
Forwarded from ስለ ቀልባችን
▫️ውድ እህቴ ይህ የምትጠይቂው ጥያቄ የብዙ እህቶቻችን የልብ ትርታ፣ የብዙ ቤተሰቦች ጭንቀት ነው።

✔️እህቴ... ምክሬን የምጀምረው «የሴት ልጅ እድሜ እንደ ጤዛ ነው» በሚለው ሀቅ ነው። ጤዛ ተኝቶ ሲነቁ ይጠፋል፤ የሴት ልጅም ወጣትነትና ውበት እንደዚሁ ነው። እድሜ መቆሚያ የለውም፤ ጊዜው ደግሞ ፈታኝ ነው። እናትሽ የሚጨቀጭቁሽ ይህ «ጤዛነትሽ» እያሳሰባቸው፣ ነገ እድሜሽ ገፍቶ ብቻሽን እንዳትቀሪ ካላቸው የናትነት ፍቅርና ስስት የመነጨ ነው።

🎯ወደ ዋናው ነጥብ ስመጣ፤ «ሁለተኛ መሆንን መፍራትና እንደ ነውር መቁጠር»
ውድ እህቴ! ዛሬ ላይ ብዙ ሴቶች «ከሌሎች እህቶች ምን ይጎድለኛል?»፣ «እንዴት ተደራቢ እሆናለሁ?» በሚል ስሜትና በፊልም በተለከፈ አስተሳሰብ ምክንያት ወርቃማ እድሎችን እያበላሹ፣ በመጨረሻም ወይ ፈላጊ በማጣት ወይም የማይሆን ሰው አግብቶ በመጦር ይቆጫሉ።

💭ልንገርሽ ስሚኝ! በድናችን ሁለተኛ ሚስት ማለት ግማሽ ሚስት ወይም ትርፍ ሚስት ማለት አይደለም። ሁለተኛ ሚስት ማለት ልክ እንደ መጀመሪያዋ ሚስት ሙሉ መብት ያላት፣ ክብር ያላት፣ የቤት እመቤት ናት። ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ወይም አራተኛ መሆን ነውርም፣ ውርደትም፣ መቀነስም አይደለም።
እስቲ ቆም ብለሽ አስቢ፤
እናቶቻችን (የነብዩ ﷺ ሚስቶች)፣ ምርጥ የሆኑት ሶሀብያቶች አብዛኞቹ እኮ ሁለተኛ፣ ሶስተኛና አራተኛ ሆነው ነው የኖሩት። ታዲያ ለእነሱ ያልሆነው ውርደት ለአንቺ እንዴት ውርደት ይሆናል?ይህ ዲን የሰጠሽ መብት እንጂ ባህሉ የሰጠሽ ስም አይደለም።

🎀እህቴ ሆይ! ላንቺ የሚጠቅምሽ ብቸኛ ሚስት ሆኖ ከማይረባና ዲን ከሌለው፣ አላህን ከማይፈራ ሰው ጋር መኖር ወይስ አላህን ከሚፈራ፣ ዲን ካለው፣ ከሚያከብርሽና ከሚንከባከብሽ ሰው ጋር ሁለተኛ ሆኖ በክብር መኖር? ምርጫው ግልፅ ነው። ስንትና ስንት ብቸኛ ነኝ ብለው ያገቡ እህቶች ዛሬ በትዳራቸው ሲሰቃዩ እናያለን። በአንጻሩ ደግሞ ስንትና ስንት በሁለተኛነት የገቡ እህቶች፣ ባሎቻቸው አላህን የሚፈሩ በመሆናቸው ምክንያት የልብ ሰላም አግኝተው፣ ዲናቸውን ጠብቀው ይኖራሉ።
አሁን ላይ እድሜሽ በሃያዎች መጨረሻ ላይ ነው። ነገ ወደ ሰላሳዎቹ ስትገቢ ምርጫዎችሽ እየጠበቡ መምጣታቸው አይቀርም። የመጣው ሰው አላህን የሚፈራ፣ ስነ-ምግባሩ ያማረ፣ ሊያስተዳድርሽ አቅም ያለው ከሆነ፤ መስፈርቱን ካሟላ 2ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛም ቢሆን እሺ ብለሽ ማግባት የብልህ ሴት ውሳኔ ነው።

🌟ስለዚህ መፍተሔ ብየ የምመክርሽ፦
✅️የእናትሽን ምክር ስሚ።እናትሽ "አግቢ" የምትለው ካየችው የህይወት ተሞክሮ ነው። የምትሰሪው ስራ፣ የምታገኘው ደሞዝ፣ የለበስሽው ዘመናዊ ልብስ የባልን ቦታ አይተካም፣ የልጅን ጣም አይሰጥም።

✅️መስፈርትሽን ቀለል አድርጊ።እንዲህ ካልሆነ፣ ካልተማረ፣ ካልከበረ...የሚሉ መስፈርቶችሽን ወደ ጎን ትተሽ፤ ዲን አለው ወይ? አላህን ይፈራል ወይ? ጥሩ ስነ-ምግባር አለው ወይ? የሚለውን ብቻ አጥብቀሽ ያዢ።

✅️ሁለተኛ መሆንን አትጥይ። ሸይጣን የሚያስፈራራሽን ሀሳብ ትተሽ፤ አላህ የፈቀደውን ሀላል አትግፊ። ጥሩ ወንድ ከመጣ አግብቶ የፈታ ነው፣ ወይም ሚስት አለው ብለሽ አትመልሺ። ጨዋና ዲን ያለው ባል በዘመናችን ውድ ነው። ካገኘሽው አትልቀቂው።

✅️ዱዓ አድርጊ። ያ አላህ! ለአንተ ብዬ፣ ዲኔን ለመጠበቅ ብዬ የመጣውን ሀላል ተቀብያለሁና አንተ ደግሞ ህይወቴን አሳምርልኝ፣ ባሌን መልካም አድርግልኝ፣ትዳሬን የተባረከ አድርግልኝ ብለሽ ለምኚው።

💡ውድ እህቴ! ትዳር የኢማን ግማሽ ነው። ግማሽ ኢማንሽን ለመሙላት፣ እራስሽን ከፊትና ለመጠበቅ፣ እናትሽንም ለማስደሰት ስትይ፤ ከመጣው አማራጭ ውስጥ መርጠሽ፣ ቁጥር ሳትቆጥሪ በሀላል ተሳሰሪ። አላህ መልካም፣ ሩህሩህና አላህን ፈሪ የሆነ ባል ይስጥሽ። መጨረሻሽን ያሳምረው።
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍11
አንዳንዴ ግን በጣም ከሚገርመኝ ውሸት መካከል ያላንተ መኖር አልችልም ያለ አንቺ መኖር አልችልም
ሚለው ቃል ነው እኛ ህይወታቸው ውስጥ ከመኖራችን በፊት እኮ ኖረዋል እኛ ስንኖር ኖረዋል ከኛም ሲለዩ ይኖራሉ
ውሀ አየር ወይ ደሞ ምግብ አደለንም ሰው ነን እንመጣለን እንሄዳለን ምንአልባት ብዙ መላመድ ይኖራል ግን ደሞ ማይካድ ሀቅ አለ የእኛ ምንላቸው ቤተሰቦቻችን እንኳን በህይወት ሳይኖሩ ህይወታችን ቀጥሏል
👍16
🔖ሷሊሆችን ሷሊህ ያስባላቸዉ ወንጀል አለመስራታቸዉ ሳይሆን፦ወንጀል ሰርተዉ ተዉበት ማድረጋቸዉ ፦ወደ አላህ መመለሳቸዉ ነዉ።

~
t.me/https_Asselfya
👍17