💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.71K subscribers
1.28K photos
494 videos
123 files
5.14K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
Audio
🟢🎧🎤አዲስ ሙሀደራ

በሸይኽ ኢማም ሰይድ  (حفظه الله)


🕌🟢☑️ በደሴ ከተማ አረብ ገንዳ መስጅድ የተደረገ

⚙💬💬 ርዕስ:–ዒልምን በመፈለግ ላይ መጠንከር(መትጋት)

https://t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
👍1
ይናፍቃል መካ !
ያለሁበት ኑሮ ጠፍሮ ባያስረኝ
በቀልቤማ መካ ቀጠሮ ነበረኝ !
ናፈቀኝ መዲና ናፈቀኝ ዓረፋ'
ነፍሴ ከነፈብኝ ወደ ሙዝደሊፋ
ልቤ ተሰደተ አደረብኝ ሚና
ና እያለ እየጠራኝ የሐጅ ጎዳና

ሙሐመድሲራጅ ሙ ኑር

https://t.me/Muhammedsirage
👍9
~የተከበሩት አስርቱ የዙል-ሒጃ ቀናቶቹ ሊገቡ 3 ወይም 4 ቀን ብቻ ቀርቷቸዋል።አላህ ቀናትን ሲያበላልጣቸው ያለምክንያት አይደለም፤ በነኚ ቀናት ዉስጥ የተሠሩ ሥራዎች ይህን ያህል ደረጃና ትሩፋት አላቸው ሲል ቦነስ እየሠጠን ነው፤ ብልህ ሰው ቀናትን አላህ የሠጣቸዉን ደረጃ ተገንዝቦ ይጠቀምባቸዋል፡፡ አላህም እሱ የሠጠንን ዕድል ስንጠቀም ይወዳል፡፡ አሥሩ ቀናት ሲባልም ቀላል ነገር እንዳይመስለን፡፡ በተቻለን መጠን በዋናነት ፆምን ጀምሮ ተክቢራን፣ ሶደቃን፣ ዚያራን … እና የመሣሠሉትን መልካም ሥራዎች ለማብዛት ከወድሁ እንዘጋጁ!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
👍4
~ዉድ የአላህ ባሪያዎች ፦ሐጅና ኡምራ ለማድረግ ወደ ተቀደሠችዉ መካ ያደረሳችሁን ጌታ አላህን የሚገባዉን ምስጋና አምስግኑት የቦታዉንም ክብር ጠብቁ ..!

🌻ذَٰلِكَ وَمَن يُعَظِّمْ شَعَٰٓئِرَ ٱللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقْوَى ٱلْقُلُوبِ

~የዲን ምልክቶችን ማክበር ልብ ዉስጥ የአላህ ፍራቻ  የመኖር ምልክት ነዉ። (አል-ሐጅ 32)

~ ኢባዳ መፈጸሚያ ስፍራዎች የዲን ምልክት ናቸዉ።በተከበረ ቦታና በተከበረ ጋዜ ዉስጥ መሆንህን አትርሳ።

        ~
       t.me/https_Asselfya
🔖የሃራም ፍቅር ያው ሃራም ነው!
~
ለወደፊ እንጋባለን ብትሉም፣
ፈጅር ላይ ብትቀሳቀሱም፣
ቂርዓት ላይ ብትደጋገፉም፣
ዳውዓ ብትላላኩም፣
ሒጃብ ቢገዣልሽም(ብትገዛላትም)፣
ስገጂ፣ ፁም፣ ሶደቃ ስጥ እየተባባላችሁ ብትመካከሩም ሃራምነቱን አይቀይረውም ራሳችንን አንሸውድ። ራሳችንን ችለን ከአላህ ጋር መጠንከር እንችላለን ከሸይጧንጋር ጥገኛ አንሁን፣ ከሃራም መንገድ እንራቅ።

~
t.me/https_Asselfya
👍12
Sheikh MohamedZain
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን
🔖ልጁ ጭፈራ ሲሄድ፣ ሴት ጋር ሲሄድ፣ ሲቅም ምንም አይመስለውም የሰለጠነለት ይመስለዋል!!

‛ዐቂዳ ለካ እንደዚህ ነወይ? ተጃጅየ ኖሪያለሁ መቶበት አለብኝ’ ብሎ ትክክለኛ ዐቂዳ ሲይዝ ሱና ሲታይበት ዱኒያ ትቆማለች አትቀመጥም!!

=
t.me/SheikhMuhammedZainAdam
•ትዳር መልካም ነገር ነው፡፡ መልካም ነገሮችን ሁሉ ስንጀምር ጥሩና ደግ ሀሳብ አስበን እንጀምር፡፡ጥሩ ካላሰብን እና ካላመሰገንን የመሻገር ጉልበቱን አናገኝም፡፡ ከመስመሩም እንወጣለን፤ ከብዙ በረከቱም እናጣለን፡፡

ወደ ትዳር ስንገባ መሠረቱ ሀሳብ ነዉና ሀሳባችን ይስተካክል፡፡ በጥርጣሬና በግማሽ ልብ የሚገቡበት ቤት ከቶዉኑ ቤት ሆኖ ሊቆም አይችልም፡፡ ዕድሜም፣ ደስታም፣ በረከትም አይኖረዉም፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ጋብቻ ታላቅ እና የተከበረ ተቋም መሆኑን አንርሳ፡፡ ታላቁን የትዳር ዓላማ ዘንግቶ ኑሮን ገና ሳይጀምሩ ንብረቱን አስቆጥሩኝ፣ ምን ምን እንዳለው አሳዩኝ፣ በስሜ አዙሩልኝ፣ ይሄን ይሄን መዝግቡልኝ … ብሎ መጨቃጨቅ ገና ከወዲሁ የጥርጣሬን በር መክፈት፣ አለመተማመንን ማስፋት፣ የአይጥና የድመት የመጠባበቅ ኑሮ ለመኖር ምክንያት ነው፡፡

የትዳርን ቁሳዊ ጥቅሙ ላይ ብቻ ማተኮር ለዘላቂነቱ እክል ነው፡፡ ራስን ብቻ ማሰብ፤ የለየለት ራስ ወዳድነትም ነው፡፡ ለጋራ ሕይወት ያለመጨነቅ ምልክትም ነው፡፡ የትዳርን ትልቅ ዋጋ ማርከስ፣ መንፈሱንም መረበሽ፣ ዓላማዉንም ማበላሸት ነው፡፡

ትዳር አላህን በመፍራት ከሐራም ለመሰተር ብለን የምንገባበት ማዕከል እንጂ ዱንያዊ ጥቅም ልናፍስበት፣ ብዙ የገንዘብ ትርፍ ልናጋብስበት የምንመሠርተው ሼር አይደለም፡፡ ተደጋግፎ ለመኖር ብሎ ዲናዊ ቤተሰብ መመሥረትን እንጂ ቪላና ህንፃ ለመገንባት ዓላማ ተይዞ የሚገቡበት አክሲዮን አይደለም፡፡ በልቼው ልውጣ፣ ንብረቱን ልካፈል … ተብሎ ኒያ ተደርጎ፣ታስቦና ታቅዶ የተገባበት ቤት ከቶዉኑ መቼም ቢሆን ቤት ሊሆን እንደማይችል ካሁኑ መታወቅ አለበት፡፡ መሠረቱ የሆነው አስኳል ነገር ንያው ተበላሽቷልና፡፡

ብዙ ትዳሮች መንገድ ላይ የሚቀሩት የንያቸው መሠረቱ ስላላማረ ነው፡፡ቆንጆ አገባ ለመባል፣ ሀብታም አገባች ለመባል፣ ኡስታዝ ጋር ተጣመረች ለመባል፣ ታዋቂ ሰው ያዘች ለመባል፣ የታዋቂ ሰው ልጅ አገባ ለመባል … የሚገቡበት ትዳር ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡
ከሐራም ለመሰተር፣ ኢስላማዊ ትውልድ ለመገንባት፣ ራስንና ሌላዉንም ለመጥቀም ብለው በመልካም እሳቤ የሚገቡበት ትዳር ደግሞ ዘላቂነቱ ከፍ ያለ ነው፡፡

በጊዜያዊ ጥቅም ኒያ የገቡበበት ማንኛዉም ነገር ከጥቅሙ ጋር እንደሚከስም ልብ እንበል፡፡ ጥቅም ሲጠፋ፣ ገንዘብ ሲያልቅ፣ ዉበት ሲረግፍ፣ ጉልበት ሲደክም ትዳሩም አብሮ ይወድቃል፡፡  
   
ኒያዎች ከሥራ ይቆጠራሉና፤ ሁሉም የሰው ልጅ የሮጠለትን ነገር ማግኘቱ ግድ ነዉና ነገሮች የተበላሹ እንደሆነ ምን ሆነው ነው የተበለሻሹት ብለን ከመነጫነጫችን በፊት ከአሁኑ መጀመሪያ ላይ ኒያችንን እናሳምር፡፡ ነገር ተበላሸ ማለት ኒያ ላይ ችግር አለ ማለት ነው፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
👍3
የሱና ቻናል  በአጭር ግዜ ተደራሽ
እንዲሆንላቹ የምትፈልጉ
በውስጥ መሥመር ሊንክ ላኩልኝ
+ 2k member 👇
ተቋርጦ የነበረው እንደ አዲስ ጀምሪያለሁ

@twhidfirst1
@twhidfirst1
💦አቡሁረይራ رضي الله عنه እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።

✅ ሰኞና ሀሙስ ስራዎች ወደ አላህ ይቀርባሉ። እኔ ደሞ ስራዬ ፃመኛ ሆኜ (ወደ አላህ) እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ።

📚(ኢማም አህመድ ዘግቦታል)
👍8
✅ ከሁሉም በፊት...!
        ~    ~
~ሙስሊሞች ሆይ !ለኢባዳ ወደ መካና መድና ከመጓዛችሁ በፊት ጠንቅቃችሁ ልታዉቁት የሚገባ ነገር ቢኖር የሚከተለዉ እዉነታ ነዉ ፥#ማንኛዉም መልካም ስራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኘዉ
# ሁለት መስፈርቶችን ሲያሟላ ነዉ እነርሱም..

⓵ኛ፡መልካም ስራን በሙሉ ከይዩልኝ ከይስሙልኝ በማጥራት ለአላህ ብቻ ብሎ በኢኸላስ መፈፀም

⓶ኛ፡የምንሠራዉ ስራ ነብያችን ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም በሠሩት መልኩ እንድሆን መጣር ይጠበቅብናል። የነዚህን የሁለት መስፈርቶች ማስረጃዉ ፦
فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا
ÂŤ ከጌታው ጋር -በሰላም  መገናኘት የፈለገ ሰዉ   ፦መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም ማንንም ምንንም አያጋራ (አል ከህፍ፡110)

#አንድ ስራ (ሷሊህ )መልካም ይባል ዘንድ ለአላህ ተብሎና በነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሱና መሠረት መተግበር ይኖረበታል።

~የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም በሐድሳቸዉ አንድህ ብለዋል።

إنما الأعمال بالنيات وإِنما لكل امريء مانوى....
📚رواه البخاري ومسلم
ስራ ተቀባይነት የሚያገኘዉና ደረጃዉም #የሚበላለጠዉ በኒያ -ስራዉን እንድንሠራ ባነሳሳን ፍላጓት -መሠረት ነዉ የሠዉ ልጅም በስራዉ የሚያገኘዉ ልቡ ዉስጥ ባለዉ እቅድና ሀሳብ መሠረት ነዉ።

          ~
         t.me/https_Asselfya
👍6
🔖ሷሊህ ባል የአባት ምትክ ነው።
     ~ ~
- قال عامر بن الظرب - رحمه الله:

«الزَّوج الصَّالح أبٌ بعد أب».

📚طبائع النساء(٢٧)                     
~«መልካም ባል ከአባት በኋላ ሌላ አባት ነው።»

🍃🕯 ˓٭˛ ،🌸
            t.me/https_Asselfya
👍12
ዱንያ መጣቀሚያ ናት ከምርጥ መጣቀሚያወቿ አንዱ ፀጥ ባለ ቦታ ከኪታብህ ጋር ቁጭ ማለት ነው።
👍21
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
✅ ከሁሉም በፊት...!         ~    ~ ~ሙስሊሞች ሆይ !ለኢባዳ ወደ መካና መድና ከመጓዛችሁ በፊት ጠንቅቃችሁ ልታዉቁት የሚገባ ነገር ቢኖር የሚከተለዉ እዉነታ ነዉ ፥#ማንኛዉም መልካም ሾል አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኘዉ # ሁለት መስፈርቶችን ሲያሟላ ነዉ እነርሱም.. ⓵ኛ፡መልካም ስራን በሙሉ ከይዩልኝ ከይስሙልኝ በማጥራት ለአላህ ብቻ ብሎ በኢኸላስ መፈፀም ⓶ኛ፡የምንሠራዉ ሾል ነብያችን ስለሏሁ…
🔖ስነ-ምግባርን ማሳመር...!
        ~
~የሐጅ ወይም የኡምራ ስነ-ስረአት ላይ በተለያዩ የኢባዳ ስፍራዎች ላይ ከምታገኟቸዉ የተለያየ ባህሪይና ባህል ካላቸዉ ሰዎች ጋር ፀባይን ማሣመርና መታገስ እንዲሁም በተቻለህ ያክል እነርሱን ለመርዳት መሞከር #አላህ ዘንድ ትልቅ ምንዳ ከሚሠጡ ተግባሮች አንዱ መሆኑን አትዘንጋ። ጌታችን አላህ በተከበረዉ ቃሉ እንዲህ ብሏል፦
🌻وَٱخْفِضْ جَنَاحَكَ لِلْمُؤْمِنِينَ
ክንፍህን ለምእመናን ዝቅ አድርግ -ለአማኞች ተናነስ(አልሒጅር88)

~በጥቅሉ ስነምግባር ማሳመር ኢስላም ላይ ትልቅ ቦታ አለዉ#ወደ አላህ ከሚያቀርቡ ቀላል ነገር ግን ትልቅ አጅር ከሚያሳጡ ነገሮች መሀል አንዱ ነዉ።

የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ከእናንተ ዉስጥ ጥሩ ከሚባሉት ፀባያቸዉ መልካም የሆኑ ሠዎች ናቸዉ።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል

   ~
       t.me/https_Asselfya
የዙል ሒጃ ስምንቱን ቀናት መፆም
~
ነብያችን ﷺ የዙልሒጃን አስር ቀናት አስመልክቶ እንዲህ ብለዋል፦

مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهِنَّ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنْ هَذِهِ الأَيَّامِ الْعَشْرِ . فَقَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ ، وَلا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ؟ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : وَلا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ، إِلا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ

''በውስጣቸው መልካም ስራ ከሚፈፀምባቸው ቀናት ውስጥ ከነዚህ አስር ቀናት በላይ አላህ ዘንድ የተወደደ የለም።" "በአላህ መንገድ መታገልም ቢሆን?" ብለው ሲጠይቋቸው የአላህ መልእክተኛ ﷺ "በአላህ መንገድ መታገልም ቢሆን! በነፍሱም፣ በገንዘቡም ወጥቶ ከዚህ ውስጥ ምንም ያልተመለሰ ሰው ሲቀር" ብለው መለሱ። [አልቡኻሪይ፡ 969]

በዚህ መሰረት በነዚህ የተከበሩ ቀናት የተለያዩ ዒባዳዎችን መፈፀም በጣም ትልቅ ዋጋ ያለው ነው። ፆም ወደ አላህ መቃረቢያ ከሆኑ ዒባዳዎች ውስጥ አንዱ መሆኑ ግልፅ ነው። ከመሆኑም ጋር በያመቱ "የዙል ሒጃን አስር ቀናት መፆም ይቻላል ወይ?" የሚል ጥያቄ ሲነሳ ያጋጥማል። የግርታው መነሻ እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ "በነዚህ አስር ቀናት ውስጥ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ፈፅሞ ፆመው አላየሁም" ማለቷ ነው። [ሙስሊም፡ 1179]

ይሄ ግን ግርታ ሊፈጥር የሚገባው አይደለም። እንደሚታወቀው የነብዩ ﷺ ሱና በሶስት መንገድ ይተላለፋል።
1- በቃላቸው
2- በተግባራቸው እና
3- ሌሎች ሲፈፅሙ አይተው የሚሰጡት ይሁንታ (ኢቅራር)።

የዙል ሒጃን ስምንት ቀናት መፆም ከነዚህ ውስጥ በቃላቸው የተላለፈው ሐዲሥ ውስጥ ይካተታል። ሐዲሡ አስተማማኝ፣ መልእክቱም ፆምን አካታች ነው። ከዚህ በኋላ የዓኢሻ ነብዩን ﷺ ሲፆሙ አለማየት የሳቸውን ጥቅል የቃል መልእክት ለመገደብ መነሻ መሆን የለበትም። ለዓኢሻ አለማየት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ደግሞ የሚገድብ መረጃ እስከሌለ ድረስ በጥቅል ቃላዊ መረጃ የተገኘው በቂ ነው።
ስለዚህ ሌሎች መረጃዎች ደካማዎች (ዶዒፎች) ቢሆኑ እንኳ መግቢያ ላይ የተጠቀሰው ሐዲሥ በቂ ማስረጃ ነው።

ይሄ እንግዲህ ስምንቱን ቀናት በተመለከተ ነው።
* ዘጠነኛው ቀን የሁለት አመት ወንጀል እንደሚያሳብስ አስተማማኝ መረጃ መጥቶበታል። [ሙስሊም፡ 1162] ስለዚህ ብዥታ የሚነሳበት አይደለም።
* አስረኛው ቀን በአል ስለሆነ አይፆምም።

ወሏሁ አዕለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
👍7
Forwarded from DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ] (Muhammed Ibnu Fedlu [Abu Nuh])
ነገ ረቡዕ የዙልሂጃ 1ኛው ቀን ነው።

ሱዑዲ ጨረቃ ስለታየች አላህ ካለ ነገ 1ኛው የዙልሂጃ ቀን ይሆናል።
👍8
الله أكبر الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله
الله أكبر الله أكبر الله أكبر ولله الحمد
👍9