💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.73K subscribers
1.27K photos
494 videos
123 files
5.14K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
🔖በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ እዉቀትን መፈለግ ግዴታ ነዉ።

📝📝 ~https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam?livestream

📝📝
~https://t.me/IbnuMunewor?livestream

📝📝
~https://t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed?livestream

~
👍1
"تذكير بصيام الخميس غداً".

‏"مايزال عبدي يتقرب إلي
‏بالنوافل حتى أحبه".
ዚክር፦ የቀልብ ብርሀን፣ የልብ መድሀኒት፣ የአካል ብርታት፣ የምላስ ጌጥ ነው።

▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

~አላህ ሆይ
በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነናል፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡

(ቲርሚዝይ)
   ~
   
t.me/https_Asselfya
👍3
ከዑለማዎች ማእድ
~
ኢብኑ ሐዝም እንዲህ ይላሉ፡- “ሊቀበሉኝ ይገባል በሚል መስፈርት (ሰዎችን) አትምከር፡፡ ሊቀበሉኝ ይገባል በሚል መስፈርት አታሸማግል፡፡ ውለታን መስፈርት አድርገህ (አስበህ) ስጦታ አትስጥ፡፡ ይልቅ በጎ ለመስራት ስትል ይሁን፣ በምክር፣ በሽምግልና እና መልካም በመዋል ያለብህን አደራ በመወጣት መልክ፡፡” [ረሳኢሉ ኢብኒ ሐዝም፡ 1/361]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
👍2
Forwarded from Abu useymin (Mohammed Ali) (أم عبدالله بنت سعيد)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔖ይችን ጣፋጭ ምክር እስኪ አብረን እንስማት !!
~
👈الحب. الحقيقي

🎙للشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله تعالى
~
t.me/MohamedAliEdris
👍9
~የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል

👉የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል

=
👍3
014 Ibrahim إبراهيم
Abdullah Albuajan عبدالله البعيجان
🔖እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ መዲና ሐረም ውስጥ ያሰግድ ነበር

🎙አብዱላህ  አልቢዐይጃን ይባላል ቃሪኡ

📚ሱራ :- ኢብራሂም

t.me/Muhammedsirage
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
قُلْ هَـٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي ۖ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
«ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል፡፡
[ ሱረቱ ዩሱፍ 12፥108 ]

የማኅበራዊ ሚድያዎቻችን አካውንቶች :-

➨ ዩቲዩብ :- https://www.youtube.com/@daio_YT07
➤ ፌስቡክ :-
https://www.facebook.com/daioFB07
➤ ቲክቶክ :- https://www.tiktok.com/@daio07?_t=ZM-8vO1tFRaZ2E&_r=1
➤ ኢንስታግራም :- https://www.instagram.com/daio_in07?igsh=Yno5MWs5OGt2dWpl
➤ ቴሌግራም :- https://t.me/daio_TG07

#ዳዕወቱል_አንቢያ
#Dawatul_Anbiya
#የነቢያት_ጥሪ_በሁሉም_ቦታ_ጊዜ_እና_ሁኔታ
👍5
🔖ለአንተ እድገትም ይሁን ውድቀት ወሳኟ ለትዳር ትሆነኛለች ብለህ የመረጥካት ሴት ናት!!

=
         t.me/https_Asselfya
👍7
🏷ይሄን የምትመኝዉ ......
!
“በየትኛው ተውሒድ  ሸርጡን ባሟላሽው፣
በየትኛው ሶላት  ኹሽእ በሞላሽው፣
በየትኛው ፆምሽ  ከሀሜት ባራቅሽው፣
በየትኛው ዘካሽ  መቼ ባወጣሽው፣
በየትኛው ኢማን   በኢኽላስ ባጌጥሽው፣
በየትኛው ምላስ  በዚክር ባራስሽው፣
በየትኛው አይንሽ  ከሀራም ባዞርሽው፣
በየትኛው እግርሽ  ተሀጁድ በቆምሽው፣
በየትኛው ልብሽ  ተቅዋ ባጌጥሽው፣
በየትኛው ተውበት  የእውነት በገባሽው፣
በየትኛው ስንቅሽ   ሞትን ተመኘሽው??
ስራ ጨረስኩኝ አልሽ  ቀብርን ናፈቅሽው?

🏷ግን አስበሽዋል!?
እሺ ሞትሽ እንበል  አፈር ተጫነብሽ
ለነኪር ለሙንከር ምንድን ይሆን መልስሽ?
እሺ ሞትሽ እንበል ዱኒያን ተለየሽው፣
የቀብርን ህይዎት እንዴት አገኘሽው?

እውነት ነው ያደክማል  ዱንያ አስቀያሚ ናት፣
ስራችን አንሶ እንጅ  ማን ጣፍጣው ኖረባት?
አንድ ቀን ቢመችሽ  በማግስቱ ስቃይ፣
አንድ ቀን ብትስቂ  በነጋታው ዋይ ዋይ፣
ዱንያ  ሀለቷ ነው   ትቀያየራለች፣
ለሁሉም አንድ ቀን  ፊቷን ታዞራለች።
ስለዚህ እህቴ  ሀለቷን ገምግሚ፣
ተቀየረች ብለሽ  ብዙ አትገረሚ።
ለዚች ከንቱ አለም  ለዚች አጭበርባሪ፣
አትጨናነቂ  ፈታ ብለሽ ኑሪ፣
አኼራን አስታውሺ  ፈጣሪሽን ፍሪ፣
መልካም ስራን አብዢ  ሀራም አትቅረቢ፣
እያልሽ ዱዓ አርጊ  ያአላህ ያረቢ፣
=
https://t.me/Asselefya2
👍35👎1
✍️ቆንጆ ብትሆኚ.....

ቆንጆ ብትሆኚ ገዳይ በውበትሽ
ታምራለች እያሉ ሺ ወንድ ቢያደንቁሽ

እወቂ የኔ እህት ፀባይ ዲን ከሌለሽ
በኒቃብ በጅልባብ በደንብ ካልተሸፈንሽ
-ሲም የሌለው ቀፎ ቁመና ብቻ ነሽ!!!

~
    t.me/MohamedAliEdris
👍22
🔖ትልቁ ጂሃድ ማለት ከነፍስህ ጋር የምታደርገው ጂሀድ ነዉ።

➡️ነፍስህ ቁርአን መሀፈዝ በጣም ከባድ ነው አትችልም ስትልህ
እንዲህ ብለህ አበስራት

(وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِنْ مُدَّكِرٍ)
➡️ ቁርአንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው
ተገንዛቢም አለን?"
📚አል ቀመር 17

➡️ነፍስህ ባክህ ጊዜ የለህም ተወው ስትልህ
እንዲህ ብለህ አበስራት

(
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُلْهِكُمْ أَمْوَالُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ عَنْ ذِكْرِ اللَّهِ ۚ وَمَنْ يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ)
➡️ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁአላህን ከማስታወስ አያታሉዋችሁ፡፡
ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው ፡፡
📚አል ሙናፊቁን 9

▪️ነፍስህ ተኛ ብላ ስትጎተጉትህ
እንዲህ ብለህ አበስራት

( كَانُوا قَلِيلًا مِنَ اللَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ)
➡️ ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ ፡፡"
📚አዛሪያት 17


t.me/https_Asselfya
👍10
🔖የሰው ልጅ ልቡ በጌታው ውዴታና ፍራቻ ከተሞላ መልካም ስራ ይገራለታል
ሁለቱ ልቡ ላይ ከሌሉ ወይም ከቀነሱ ደግሞ መልካም ስራ ይከብደዋል

~
t.me/https_Asselfya
👍16
"ልጆች ላይ ያሉ እነዚህ አምስት ነገሮች ለ አዋቂዎች ቢኖር ወሊዮች በሆኑ ነበር:-
ስል
ሪዝቃቸው አይጨነቁም፣ ሲታመሙ ፈጣሪያቸው ላይ ስሞታ አያበዙምሲበሉ ተሰብስበው ነው፣ ሲፈሩ አይናቸው እምባ ያቁራል፣ በተጣሉ ሰአት ለመታረቅ ይቻኮላሉ።"

ሱዩጢይ رحمه الله

t.me/https_Asselfya
👍20
ትዳር ስትመሰርት ከባለቤትህ ጋር ጥሩ ህይወትን ለማሳለፍ፣ ከብቸኝነት ወጥተህ በተውሒድ የታነፀ ቤተሰብ ለማፍራት አስበህ ይሁን።
منقول
👍21
~የነፍስ እርካታ ያለው
አላህን ፈርቶ ወንጀልን
በመቀነስ ውስጥ ነው።

~
t.me/https_Asselfya
👍26
📌ሴቶች ሶስት አይነት ናቸው ይላሉ ዑመር ቢን ኸጧብ رضي الله عنه

"النساء ثلاثة:

⚪️امرأة هينة، لينة، عفيفة، مسلمة، ودود، ولود، تعين أهلها على الدهر، ولا تعين الدهر على أهلها، وقل ما تجدها.

🟤ثانية: امرأة عفيفة مسلمة، إنما هي وعاء للولد ليس عندها غير ذلك.

⚫️ثالثة: غُلٌّ قَمِلٌ جعلها الله في عنق من يشاء ولا ينزعها غيره.


👉አንደኛዋ- ገራገር፣ ምቹ፣ ቁጥብና ጥብቅ የሆነች ሙስሊም ሴት ነች። አፍቃሪም፣ ተፈቃሪም፣ ማህፀነ ለምለም የሆነችም ሴት ናት።
ባሏ ሲቸገር ከጎኑ የምትቆም፣ አብሽር ያልፋል እያለች የምታጠናክር፣ ይገባሃል፣ የእጅህን ነው ያገኘኸው፣ ደግ ሆነሃል፣ ኧረ ሲያንስህ ነው በማለት በመከራው ላይ ሌላን መከራ የማትደራርብ አይነት ሴት። የዚህች አይነት ሴት በጣም ጥቂት ናቸውና ማግኘቱም ከባድ ነው።

👉2ኛዋ አይነት ሴት:
ቁጥብና ጥብቅ ሙስሊም ሴት ነች። ባይሆን ግን ልጅ ከመውለድ ያለፈ ምንም ሚና የላትም። (ይህችም ለክፉ አትሰጥም።)

👉3ኛዋ ሴት
አመለ ክፉ መከራና ቅማል የሆነች ሴት ነች። ከራስ ላይ የማትወርድ፣ አንገት ላይ የተጠመጠመች ማነቆ፣ በእጅ ላይ የገባች የመከራ ካቴና፣ ራቂ ቢሏት የማትርቅ፣ አብረሽ ኑሪ ብለው ቢተዋት ሰላም የማትሰጥ፣ አላህ ፈተናን ለፈለገበት ባሪያው የሚሰጣት፣ አላህ ካልሆነ በስተቀር የማያስወግዳት አይነት የፈተና ሸክም የሆነች ሴት።

📚ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይባ/126

🏁ወንድሞቼ ከሶስተኛዋ የሰው መዥገር አላህ ይጠብቃችሁ👐🏻

منقول
~
👍13
አቦ ተሰተሪ


አባትሽም አሉ የኔ ልጅ ቁጥብ ናት

እናትሽም አሉ የኔ ልጅ ቁጥብ ናት
አንቺ የምትውይው ፍፁም ተቃራኒ እነሱ ከሚሉት:

ምን አለ ባሰክሪ ሰውም ባታሰክሪ
ከቤትሽ ተቀመጭ እዛው ተከበሪ

#ፎርዋርድ ቴክስት ልብሽ ተሰውሮ
በስክሪን  ሻት ኢሜጅ  ጋላሪሽ ታውሮ
እየተቅነዘነዝሽ  ታጠፊያለሽ ኑሮ

አረ ጉድ ዘንድሮ ቂያማ ደረሰ ወይ
ከሴት ልጅ ላይ ሀያዕ  እንድህ ይጠፋል ወይ

ስንቶች ተፋረሱ ስንቶቹ ተጋጩ  ከሞቀ ቤታቸው
እንዳቺ
#ወስላታ  ገብቶ እመሀላቸው

አረ ተሰተሪ አረ ተሰተሪ  እባክሽ ደመቁ
ባንቺ  የተነሳ ስንቶቹ ወደቁ


ያልተፃፈልሽን የማያገባሽን  ማንበብ ጀምረሻል
አንቺ ሰው ዘንድሮ ጤናሽን ነስቶሻል

እናማ የምልሽ ያንም ያንም አጋጠሽ አትይ 
በሚያምር  ሁኔታ አረፈሽ ቁጭ በይ

በ online  ሲሰጥ የምናውቀው ስሚኝ ትምርት ነው:-

ትዳርን ከፈለግሽ እሱ ከአላህ ነው::


የረያን ማሚ

t.me/https_Asselfya
👍23