💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
≺≺ኢብኑ ተይምያ የሱናው አንበሳ≻የእውቀት ማእድ የዋትሳፕ ግሩፕ

«ኮድ ➀   ⇓⇓
https://chat.whatsapp.com/Gq46QQFVlQKG4Jv77eAwOC

«ኮድ  ➁  ⇓⇓
https://chat.whatsapp.com/H1N5Ugqz9O6GwIBtCOnxZ4

«ኮድ ➂  ⇓⇓
https://chat.whatsapp.com/JZsJJcYkgSnLpFNhqinRCY

=
بـــــســـــم الله الرحـــــمــــن الرحــــيــــم
اما بعد
(ፍቅር) او ልብን በሌላ አካል ላይ ማንጠልጠልን በተመለከተ ስላለው ጉዳት ነው የማወራው,,
←كما قال ابن قيم رحمه الله
انه ( من تعلق قلبه بغير الله عذب به )
ኢብን ቀይም→ከአላህ ውጪ ባለ ነገር ላይ ልቡን የሚያንጠለጥል አካል በርሱው በወደደው ነገር ይሰቃያል እንዳሉት።
ፍቅር ከድን መራቃችን እና የመሳሰሉት ጉዳቶች ከመኖራቸውም ጋ
ዱንያውይ ህይወታችንንም ጭምር በአግባቡ እንዳንመራ ዝብርቅርቅ እና ድንዝዝ የሚያደርግ ህመም ነው»
ፍቅር ራስን ይቀማል፣ በምታፈቅሩት ሰው አለም ውስጥ ራሳችሁን በራሳትሁ የምታስሩበት ስጅን ነው
ከሁሉም ነገሮች ጋ ያለንን ግንኙነት ይበጠብጣል፣ የውስጥ ረፍት እና ሀሴት የሚባልን ነገር ከህይወታችን ያርቃል...
የተፈጠርንበትን አላማ አስረስቶ የስሜታችን ተከታይ እንድንሆንም ያደርጋል
የነፍስን ፍላጎት መከተል ደግሞ ከርሱ መንገድ ያስወጣል
ልክ ጌታየ፦ ከአላህ መንገድ ያስወጣካል እና ዝንባሌክን/ ሀዋክን እንዳትከተል እንዳለው
( وَلَا تَتَّبِعِ الْهَوَىٰ فَيُضِلَّكَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ )

نعم انه طريق الضياع / وانه طريق المميت / وطريق ضلال
ሁለቱንም ሀገር ያበላሻል፣ የአላህን መንገድ ይጋርዳል
ዒልምን ከመፈለግ ያቅባክ፣ አኽላቅን ያበላሻል
ሀያዕን፣ አደብን ያራቁታል..
ብዙ ወጣቶችን ከተስተካከሉ በኋላ መንገድን አስቷቸዋል
አእላፍ ተምሳሌት ሊሆኑ የሚችሉ ጨዋ እና ቁጥብ ሴቶችንም ጭምር ሃያዕቸውን፣ ስርዓታቸውን አሳጥቷል
ስንት እና ስንት ሰዎች ከድናቸው ርቀዋሉ!
ስንቶችስ ብዙ ለፉተው የሀፈዙትን፣ የተማሩትን ረስረዋሉ!
ወረቢ ኢማንን ይገድላል፣ የልብን ብርሃን ያጨልማል፣ ኢማን ሢሞት ልብ ሢጨልም ደግሞ ሰው መንገድን ይስታል።
انه فتن العظيم  / وانه مرض خطير يا إخواني
ሹፉ (አላህ ይዘንላችሁና) ይሄ ተዓሉቅ አው ፍቅር የሚባለው ስሜት የሚወለደው አስሉ ሸርዕየን የሚፈቀድ ባይሆንም በእህትና በወንድምነትም በሉት..
በጓደኝነትም በሉት..
በተማሪ ባስተማሪነትም በሉት..
በአብሮ አደግነትም በሉት ብቻ ሁለቱም ጎን ከማይፈቀድለት አካል ጋ ህገወጥ የሆነን ቅርርብ ሢፈጥር በጊዜ ሂደት ውስጥ የሚመጣ ጦስ ነው።
ለዚህም ሢባል ያለ ሀጃ፣ ያለ ገደብ፣ ያለ አግባብ፣ ወንዶችም ከሴትጋ ሴቶችም ከወንድጋ አትቀራረቡ፣ አትቀላቀሉ።
ፈተናንም በራሳችሁ ላይ አትመኑ
اما قال النبي ﷺ : ما تركت بعدي فتنة هي أضر على الرجال من النساء،!
ከኔ በኋላ በወንዶች ላይ እንደ ሴቶች ጎጅ አው ከባድ የሆነ ፈተናን አልተውኩም ብለዋሉ።
እንዲሁም፦
فاتقوا الدنيا واتقوا النساءَ، فإن أولَ فتنةِ بني إسرائيلَ كانت في النساءِ
ሴቶችን እና ዱንያን ተጠንቀቁ የበኑ ኢስራዔል የመጀመሪያ ፈተና ሴቶች ነበሩ በማለት አስጠንቅቀዋል።
እኛ ሴቶችም፦ ለሃጃ እንኳ ስናወራ ድምጻችንን እንዳናለሰልስ፣فلا تخضعن بالقول
በማለት እንዳንቅለሰለት ታዘናል።
ሸሪዓው ባስቀመጠው መልኩም እንድንሸፋፈን፣ እንደ ጃሂልያ ሴቶች እንዳንራቆትም ተከልክለናል።  

ምክንያቱም የፊተን መዳረሻወችን እንድንዘጋ እና በታዘዝንበት መልኩ እንድንኖር ሲባል።
ولكن لمن كان له قلب..

                                     👑..sêlwã🫧
👍7

« هُمُ الْجُلَسَاءُ لَا يَشْقَى بِهِمْ جَلِيسُهُمْ »

💦
አላዋቂ ሴት ማለት ይቺ ናት
~ ~
【من أحمق النساء امرأة اضطرت زوجها إلى أن يسيء إليها بعدما كان يعاملها بالحسنى】

~ሞኝ ወይም ቂል ሴት ማለት ባሏ በመልካም እየተኗኗራትና መልካም እየሰራላት ሳለ በንግግሯ ወይም በተግባሯ በሷ ላይ መጥፎ እንዲሆንና መጥፎ እንዲሰራባት ያስገደደችው ሴት ናት።

~
t.me/https_Asselfya
👍22
🔖አላህን ስናመልክ ልባችንን ወደሱ ሰተን (ከጅለን) ናፈርተን ነዉ መሆን ያለበት ካልሆነ ኢባዳ አይባልም።
🌼وَٱذْكُر رَّبَّكَ فِى نَفْسِكَ تَضَرُّعًۭا وَخِيفَةًۭ وَدُونَ ٱلْجَهْرِ مِنَ ٱلْقَوْلِ بِٱلْغُدُوِّ وَٱلْـَٔاصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْغَٰفِلِينَ

~ጌታህን በምስጢር ተዋድቀህ (ልብህን ጠጋ አድርገህ) ጌታህንም ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል# በጧትም በማታም አውሳው፡፡ አላህን ከማዉሳት ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡

📚ሱረቱል አእራፍ(205)

=
t.me/https_Asselfya
👍5
🎁 ihsan jobs
ኢህሳን
ይህ ቻናል ለሙስሊሙ ማህበረሰብ
ይጠቅም ዘንድ ታስቦ የተከፈተ የስራ ማስታወቂያ
የምንለቅበት አዲስ ቻናል ነው 💎

በቻናሉ ነፃ ማስታወቂያ እንለቃለን
ከናንተ የሚጠበቀው የትኛውም
ማስታወቂያ በውስጥ መሥመር
ለኛ ማሳወቅ ብቻ ነው ➡️

እኛም በነፃ ከሸሪዓ የማይጋጩ ስራዎች
አጣርተን በቻናሉ እንለቃለን
⭐️ @twhidfirst1
🌟 @Tolehaaaaaa
🌟 @AbuNuhibnufedlu

https://t.me/ihsan_jobs
https://t.me/ihsan_jobs
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2
ለሞት መዘጋጀት
~
"ከሙስሊም የሚጠበቀው እድሜው በጨመረ ቁጥር ይበልጥ ወደ አላህ የቀረበ ሊሆን፣ ይበልጥ ለአላህ የሚያደርገው ዒባዳ የጨመረ ሊሆን ነው። ከአላህ ጋር መገናኛው እየቀረበ እንደሆነ ሊያስብ ይገባል። መቼስ ማንም ሰው ቢሆን ሞት መቼ እጅ እንደሚያደርገው አያውቅም። ሙሉ ጤነኛ ሆኖ አንግቶ፣ የሞት ሃሳብ አንድ ከመቶ ያክል እንኳ አእምሮው ላይ ውል ሳይልበት ከዚያ ግን ከሞት ጋር ያመሸ ስንት ሰው አለ?! እና ሙስሊም የሆነ ሰው ዝግጁ ሊሆንና የተቅዋ ስንቅ ሊሰንቅ ይገባል።"

ሸይኽ  አልኸሥላን
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
👍7
🔖ነጃህ ፈላህ ለመወጣት ከፈለክ #በእነዚህ ስበቦችን መንገዶችን አጥበቀህ ያዝ !
~
🌼يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ =እናንተ እመኑ በተባላችሁበት  ያመናችሁ ሰዎች ሆይ

➀ٱصْبِرُوا۟=ታገሱ

➁ وَصَابِرُوا۟ = ተበራቱ ተረዳዱ.

⓷وَرَابِطُوا۟=በጦር ሜዳላይ ተሠለፉም

⓷ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
=ትድኑም ፈላህ  ትወጡ ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡

👉የሶብር አይነቶች
    ~
➀)በአላህ ትዕዛዝ ላይ ሶብር ማድረግ
➁) አላህ ከከለከላቸው ክልከላዎች ላይ
ላለመውደቅ ሶብር ማድረግ
⓷)አላህ በወሰናቸው ውሳኔዎች ላይ ሶብር ማድረግ


       =
t.me/https_Asselfya
👍14
🔖ጓደኞችህን ለይ !!
~
ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበትከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም።

~እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀልአልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ እራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ።

~ ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ።
"ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከ

✍️ ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች»ከሚለው ድንቅ የ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነዎር ፁሁፍ የተወሰደ…።

~

t.me/https_Asselfya
👍6
~ አንዳንዴ!!

በቅርብ ሆነህ ዋጋ ቢስ ከምትሆን በርቀት ሆነህ መከበር ትልቅ ረፍት ነው።

~
👍29
~አብዘሓኛዉ የአደም ልጅ ስህተቱ በምላሱ ነዉ።

~
👍16
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
🔖ጓደኞችህን ለይ !! ~ ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። ~እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ እራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። …
🔖ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀምአንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሐብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል።

~እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥየፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮች ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው።"ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።"
"አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ እራስህ እያለፍክ ነው።"

~
t.me/https_Asselfya
👍7
~ዋና አላማ ግብ ፦መብላትመጠጣት፦ማግባት አደለም ።ዋናዉ አላማ ግብ የአላህ ሱብሀነሁ ተአላ መልካም ባሪያ መሆን ነዉ።
🌼 وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

~
t.me/https_Asselfya
👍10
1. የምንቀራውን ኪታብ ቃላት ልቅም አድርጎ መያዝ። ከኪታቡ ውስጥ የማናውቀው ቃል ላይኖር።

2. የኪታቡ መልእክት ላይ ትኩረት ማድረግ። መልእክቱን በትክክል መረዳት። ቃላት ለቀማ #ብቻ እንዳይሆን።

3. ማስረጃ ሲጠቀስ ከርእሱ ጋር ያላቸውን ተዛምዶ መለየት። مَحَلَّ الشَّاهِد እና وَجْهُ الاِستِدلال

4. ከደርስ በፊት እና ከደርስ በኋላ ሙራጀዓ ማድረግ። ከጓደኛ ጋር ወይም ለብቻ ሁኖ።

ባጭሩ = የተማርነውን ኪታብ ለሌሎች ማስተላለፍ በሚያስችል አቅም መያዝ ያሰፈልጋል።
~
ከኢብኑ ሙነወር ደርሶች ላይ የተወሰደ።
👍17
አንድ ሷሊህ ሰው ጥሩ ጓደኛ እንዴት ነው ማገኘው ተብለው ተጠየቁ? እሱም አንተ ሷለሕ ሁን ጥሩ ጓደኞች አንተን ጓደኛ ለማድረግ ይጋፉብሃል ብሎ መለሰለት!!

.
አንዳንዴ እራሳችንን ንፁህ እያደረግን ሌሎችን በመውቀስ ዛሬ ጓደኛ የለም፡እያልን ሌላን የምንተቸው ነገር ተመልሶ የሚወጋን እራሳችንን ነዉ።

t.me/https_Asselfya
👍25
ብልጥ ሴት ካለች አላማ ያላት፣
በጅልባብ ፈክታ ኢማን የሞላት፣
ስነ-ምግባሯን የወደድክላት፣
ወደኀላ አትበል አፈፍ አድርጋት፤
ታማኟ አፍቃሪ ባሏም ሁንላት፡፡

@abu fewzan
👍27
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔖ገሳጭ የምሽት ጣፋጭ ቁርአን!
~ ~
🌼وَمَا ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَآ إِلَّا لَعِبٌۭ وَلَهْوٌۭ ۖ وَلَلدَّارُ ٱلْـَٔاخِرَةُ خَيْرٌۭ لِّلَّذِينَ يَتَّقُونَ ۗ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

~የዱኒያ  ሕይወት ጨዋታና ላግጣ ድብር ማስወገጃ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ #የመጨረሻይቱ ሀገር (ጀነት) ለእነዚያ አላህን ለሚፈሩት ለሚጠነቀቁት በጣም በላጭ ናት፡፡ #አቅል አይኖራችሁምን?አቅል ሊኖራችሁ ይገባል።
~
t.me/https_Asselfya
👍13
~ ከሁሉም በላይ ለራሴ ችግር የሆንኩት እኔው ራሴ ነኝ፡፡ ትልቁ ትግሌ ከራሴ ጋር ነው፤ ትልቁ ወሬዬም ከኔው ጋር ነው፡፡ አሳምሬ መገንባት የምፈልገው ትልቁ ህንፃ እኔነቴን ነው፤  ራሴን ካስተካከልኩ ሌላዉን ማስተካከል ቀላል ነው፡፡ መጀመርያ እኔ:ሌላው ጉዳይ ቀጥሎ ነው፡፡

ዛሬን ጠፋሁ ወይም አጠፋሁ ብዬ ተደፍቼና ተከፍቼ አልኖርም፡፡ ኃጢአት ብሠራ ከወደቅኩበት ለመነሳት እፍጨረጨራለሁ፤ ዕድሜ ዕድል ነው፡፡ አላህ ካቆየኝ እስከ ዕለተ ሞቴ በርካታ ዕድሎች እንዳለኝ አውቃለሁ፡፡ ማለዳ በመጣ ቁጥር ተስፋዬም ፈገግታዬም ይመለሳል፡፡ በጥፋቴም ከምንም በላይ የአላህን እዝነት እያሰብኩ ከተጓዥ ወንድሞቼ ጋር ወደ አኺራ ወንዝ እፈሳለሁ፡፡

ደስተኛ ነኝ፡፡ ጠዋት ከቤት ይዤ የምወጣዉም ሆነ ስተኛ ተሸክሜ የምተኛው ሀሳብ የለኝም፡፡ ስወጣ አራግፌ ጭንቅላቴን ወጣለሁ፣ ስገባ ሀሳቤን እደጅ አስቀምጬ ገባለሁ፣ ስተኛም ከትራሴ አርቄው እጋደማለሁ፣ ሐዘን በቤቴም በዉስጤም ሥፍራ ያገኝ ዘንድ አልፈቅድለትም፡፡ ሙሉ ቀን ከዋለብኝ ድክመቱ የኔ ነው፡፡ እሱ እንደ ድንገተኛ እንግዳ ሁሉ መጥቶ የሚሄድ ነገር ነው፡፡ በሰው ቤት ከሦስት ቀን በላይ የማደር ሐቅ የለዉም፡፡

ሶሻል ሚዲያ ላይ የምጣደው ለማንበብ ነው፡፡ ለራሴም ለተከታዮችም ደስ የሚል መልዕክት ለመምረጥ ነው፡፡ በመረጥኳቸው ነገሮችም የደከማቸዉን አበረታለሁ፣ ያዘኑትን አጽናናለሁ፣ ከከፋቸው ጋር እስቃለሁ እጫወታለሁ፡፡

ዓላማዬ የኢማን ህመምተኞችን መርዳት ነው፤ ዋናው እና ትልቁ በሽተኛም እኔው ነኝ፡፡

ከሰው ጋር ጨዋታ ይዤ ለተወሰነ ጊዜ እዘናጋ ይሆናል፡፡ ተዘናግቼ እንደማልቀር ግን ዉስጤ ይነግረኛል፡፡ አንድ ቀን ሳጠፋ ብዉል ኪሳራዬን በሌላኛው ቀን ለማካካስ እታገላለሁ፡፡

ሕይወት ትሂድ ትቀጥል፤ ተነጫንጨን አናስቆማትም፡፡ ተደስተንም አናቆያትም፡፡ ዱንያ ዛሬ ይሁን ነገ ጠፊ ናት፡፡የቀደሙን ሁሉ ምርጦች ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ በመሞታቸው ትልቅ ትምህርት ሠጥተዉናል፡፡ እነርሱ በርግጥ ታድለዋል።

ጌታዬ ሆይ ካንተ ጋር ወሬ እንዳለኝ አውቃለሁ፤ የኔን ነገር አደራ፡፡
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan
👍2
ስኬታማ መሆን ከፈለግህ ለህይወትህ 100% ሃላፊነት ውሰድ። ማንንም አትውቀስ። ስለጉዞህ አብሰልስል። ስለመድረሻህ ወጥን። እወቅ! አንተ ስለምትኖረው ህይወት ሃላፊነት መውሰድ ያለበት አንድ ሰው ብቻ ነው። ያም ሰው አንተ ነህ! በቃ ማንም ሰው መጥቶ እስኪያባብልህ አትጠብቅ። ወድቀህ ከሆነ ተነስ። ቁመህ ከሆነ ገስግስ!።

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman
👍4