💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
~ምርጥ ጓደኛ!
➀.ከፈገግታህ ጀርባ ያለዉን ሀዘን ያዉቃል !
➁.ከቁጣህ ጀርባ ያለዉን ፍቅር ይረዳል !
⓷.ከዝምታህ ጀርባ ያለዉን ምክንያት ካላወቀ ይጠይቀሃል።

~
t.me/https_Asselfya
كتاب_الصيام_من_العمدة_في_الأحكام_PDF.pdf
468.8 KB
ኪታቡ ሲያም - ከዑምደቱል አሕካም የተወሰደ

በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ እየቀረበ ያለ
~መልካም አንደበት ሕይወት ናት..
ከሁሉም ጋር ወዳጅ ታደርጋለች።

~
بركة الوقت 0×0

اللهم بارك لنا في أوقاتنا.

.
~የደስታ ሚስጥር

በጤንነት፣በእውቀትና፣በኑሮ ከአንተ በታች የሆኑ ሰዎችን በማየት አላህን ዘውትር በሰጠህ ችሮታ
ማመስገን።


~
t.me/https_Asselfya
''ለማስተማር እውቀትን ብቻ ማወቅ በቂ አይደለም, ማስተማርንም መማር ያስፈልጋል''።

~
t.me/https_Asselfya
እናትህ ደስ እንዲላት አውራት። ከአፍህ የሚወጣው ሁሉ ጠብታ ማር ይመስላታል ።

አባትህ ደስ እንዲለው አዳምጠው፤ ስታዳምጠው ኩራት ይሰማዋል።

ይላሉ ጠቢባን።

t.me/https_Asselfya
ስሞታ አታብዙ
~
እናንተ የአሏህ ባሮች ሆይ የቱን የካል ብትገፉ ብትበደሉ እንኳን ስሞታን አታብዙ።የሐሳባችሁ ተካፋይ"ሚስጥረኛ"አድርጋችሁ ከያዛችሁት አካል ውጭ ላለ የሆዳችሁን እያወጣችሁ አትስጡ ባዷችሁን ትቀራላችሁ እንጅ መፍትሄ አታገኙም።እከሌ ገንዘቤን በልቶኝ እከሌ አጭበርብሮኝ፣እከሌ ዋሽቶኝ፣እከሌ እንዲህ ብሎኝ ሲያበቃ ከድቶኝና…ወዘተ ለማንኛውም ሰው እየዞራችሁ ጉዴን ስማ አትበሉ።ጉሮፖችንና የኮመንት ቦታዎችን ሁሉ ስሞታ ተቀባይ አታድርጓቸው።አደብ አይደለም።ገንዘባችሁንም ሆነ ክብራችሁን የምታስመልሱበት መንገድ ካለ በመስመሩ ሂዱ ቢረዝምም ትደርሳላችሁ አላህም ያግዛችሁ።በተለይ እህቶችዬ እንዲህ አይነት ነገር ጉልቶ ይታይባችኋልና እርግፍ አድርጋችሁ ተውት።በዛም በዚህ ቢወተውቱት እራስን ማሳመም፣ጊዜን ማባከን አለፍ ሲልም ወንጀል ማምጣት ካልሆነ እንጂ ምን ይጠቅማል?

አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
~ኢላሂ መሽቶ የሚነጋዉ ባንተ ነዉ፣ ተኝተን የምንነሳዉም ባንተ ነዉ፣ ወጥተን የምንገባዉም በእዝነትህ ነዉ፣ ሰርተን የምናገኘዉም ሰለፈቀድክልን ነዉ፣ አልሓምዱሊላህ....

~ኢላሂ ለተጨነቀው ሁሉ ፈረጃን ፣ ላዘነው ሁሉ መፅናናትን ፣ ለዱአዎች ሁሉ ተቀባይነትን ፣ ለታመመው ሁሉ መሻርን ለግሰው ፣ ያአሏህ ከእዝነትህ አታርቀን ፣ ወንጀላችንን ሁሉ ማረን በሀቅ ላይ አፅናን መጨረሻችንን አሳምርልን ኣሚን ያረብ ።

==
t.me/https_Asselfya
~በነገራችን ላይ…የግድ አስፈላጊ ለሆነ ነገር ካልሆነ በስተቀር መታየት ከሌለብህ ሰው ጋር አትታይ፣ መገኘት በሌለብህ ቦታም ላይ አትገኝ፡፡ ሐላል ቢሆንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ መተዉዉ ከማድረጉ የሚሻለውን ነገር ትተዋለህ።

•አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ባልሆነ ቦታ ላይ እየታየህ እኔ ራሴን አውቃለሁና ሰው የፈለገውን ቢል ምን አገባኝ የሚለው አባባል ላያስኬድ ይችላል፡፡ሰውንም ራስንም መጠበቅ መልካም ነው፡፡ የራስህን ሥም ጠብቅ፤ሰዎችንም ከሀሜት ጠብቅ፡፡ አንዳንድ ዑለሞች«ያልሆነ ቦታ ተይቶ የታማ ሰው ዕዳውን እሱ ራሱ ይቻል!»ይላሉ።

አንዳንዴ የሚፈቀዱ ቢሆንም እንኳን ለሰው ብለህ የምትተዋቸው፣ለማኅበረሰቡ ጥቅም ብለህ የማታደርጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ።ሆኖምግን ጥንትም ይሁን ዛሬ አላህን የማይፈሩ ሰዎች ብዙ አሉ፡፡ያለ ማስረጃም እርግጠኛ ሆነው የሚያወሩና የሚያስወሩ አሉ፡፡

ሰዎች እውነታውን ውስጣቸው እያወቀ በቅድስት መርየም ላይ አስወርተዋል፣ንፅህት ዓኢሻንም በ ዝሙት ወንጅለዋልና ካወሩ ለምን አወሩ አይባልም፡፡አላህ የወሬ አርዕስት ከመሆን ይጠብቀን፡፡ ያዩትን ሁሉ ከሚያወሩትም አያድርገን።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
~በነገራችን ላይ…የግድ አስፈላጊ ለሆነ ነገር ካልሆነ በስተቀር መታየት ከሌለብህ ሰው ጋር አትታይ፣ መገኘት በሌለብህ ቦታም ላይ አትገኝ፡፡ ሐላል ቢሆንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ መተዉዉ ከማድረጉ የሚሻለውን ነገር ትተዋለህ። •አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ባልሆነ ቦታ ላይ እየታየህ እኔ ራሴን አውቃለሁና ሰው የፈለገውን ቢል ምን አገባኝ የሚለው አባባል ላያስኬድ ይችላል፡፡ሰውንም ራስንም መጠበቅ መልካም ነው፡፡…
ሀቂቃ አብዛሀኛዉ ሠዉ የተለከፈበት በሽታ ነዉ።
እንዲህ እየተባለ ነዉ ከዚህ ተግባር ተቆጠብ ሲባሉ እኔ ንጹህ ከሆንኩ ሠዉ ያውራ ወንጀሌን ያብሱልኛል የሚሉት ነገር.....!

~ሀቂቃ ለወንድም ፦ለእህት ያለመጨነቅ ነዉ።
ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ሚስታቸዉ ጋ ለሊት በሚሄዱ ጌዜ ሁለት ሰዎች አገኟቸዉ ፈጠን ብለዉ እነዚያ ሠዎች ሊያልፉ ሲሉ የአላህ መልእክተኛ ሚስቴ ነች ብለዉ ነዉ ያሏቸዉ። ሰዎች ጥርጣሬ እንዳያድርባቸዉ። የአላህ መልእክተኛ እንድህ ነበሩ ..እኛ ደሞ ካልተፈቀደልን ሰዉጋ እየታየን እኔ የለሁበት ይሙኝ ሰዉ ያለዉን ይበል አይባልም።ለእህትና ለወንድሞቻችን ልናስብላቸዉ ይገባል። እኛም በተቻለን ሠዎችን ከሚያስጠረጥር ቦታ ልንርቅ ይገባል።

t.me/https_Asselfya
~ኢላሂ አንተን በማስታወስ አግዘኝ!!

تذهب الحياة ..
وتبقى الباقِيات الصّالحات :


‏سبحان اللّہ .. الحمد للّہ ..  لا إلّہ إلا اللّہ .. اللّہُ أڪبع ..لاحول ولا قوة إلا بالله

‏تملأ قبرك نوراً وترافقك إلى يوم القيامة
فاجعل دائماً لسانك رطباً بذكر الله
. t.me/https_Asselfya