💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.56K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
💦የተሸፈነ ነገር ዉስጥ እዉነተኛ ዉበትን ታገኛለህ አየሽ አንች እንቁ እንስት የመሸፈን ዋጋ ለዚህም ነው ላቅ ያለዉ ጌታችን እንድንሸፈን ያዘዘን

እሸትን በቀሎ በሸትነቱና ከማሳ ወደ ቤት ገብቶ ተገላልጦ ደርቆ ስታየዉ ለአይን እይታ የሚስበው እስኪ የትኛው ነው ????

ሱበሀነክ ያኢላሂ አልሀምዱሊላህ አላ ኒዕመተል ኢስላም

ወላሂ ነፃነትም በሉት ዘመናዊነትም ብቻ ባሻችሁ ሰይሙት በመሸፈን ዉስጥንጅ በየትኛውም መንገድ አይገኝም

▶️የሂጃቧን ንግስት የኒቃቧን ጀግና ፣
መቅናትስ በሷ ነው የጌታዋን ትዕዛዝ አክባሪ ናትና ፣

▶️አንተም አኺ አረህማን ወፍቆህ እሷን ካገባሀት ፣

ታድለሀልና ጌታህን አመስግን ማንም የማያያት የግልህ ካዝና ናት፣

🌸🌸ኒቃቢስቷ🌸🌸
〰〰〰〰〰〰〰
♻️ማስመሰል የሌለዉ ያልተበረዘዉ፣
እዉነተኛ ዉበት ያንቺ ብቻ ነው ።

የመሸፈንን ዋጋ የሚያዉቀዉ የተሸፈነ ብቻ ነው አላህ ይወፍቃችሁ ያረብ

የተሸፈናችሁም አላህ እስቲቃማውን ይስጣችሁ!!

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
✍ማስታወሻ
➖➖➖➖➖
✅በየቀኑ እና ለረጅም ሰዓት ሶሻል ሚዲያው ላይ ተጥዶ መዋልም ሆነ ማደር መልካም አይደለም።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹ዕድሜና ጊዜን ይፈጃል። ዕድሜ ማለቁ የማይቀር የሚቆጠር እስትንፋስ ነው። እስትንፋስህን በዉድ ዋጋ እንጂ አትሽጥ።

👌ራስህን ከትልቅ ቦታና ዉጤት ለማድረስ ብልህ ሁን። አንዳንዴም ከግርግሩ ሜዳ ገለል ብለህ ዉስጥህን የምታይበት ጊዜ ይኑርህ።

👉 ዛሬ ላይ ሥራ የሚያስፈቱ ነገሮችም ሰዎችም በዝተዋል። ዩ ቱዩቡና ሶሻል ሚዲያው፣ ዜናዉና የፖለቲካ ወሬው… ሰዎች ረጅም ጊዜ ሰጥተው ሰዓታቸውን የሚፈጁበት ነገር ሆኗል።

↪️በዚህ ዓይነቱ ጊዜ ነቃ በል። በመሃል የሚወስዱህ ነገሮች ቢኖሩ እንኳ "ዋናውን ሥራህን" አትጣል። ሰዎች በብዛት ስለተጠመዱበትና ስለሠሩት ብቻ አንድ ነገር ምርጥ ነው ማለት አይደለም ።

👌 ባይሆን ከብዙዎች ለየት በል። በዝምታ ሥራ። ለዱንያም ለአኺራም ብዙ ትርፍ ሊያስገኙልህ በሚችሉ ነገሮች ላይ አተኩር።

✅የሚዲያው ዓለም ባህር ነው። ሁሉ ነገሩ ይስባል። ሁሉ ነገሩ እዩኝ ይላል። ያዘናጋሃል፣ ጠልፎ ያስቀርሃል፣ ገብተህ መውጫው ይጠፋሃል።

↪️ ከዚህ አንፃር ጠንካራ እና ራሱን መቆጣጠር የሚችል ብርቱ ሁን። ከገባህም በቀላሉ መውጣት የምትችል ጎበዝ ሁን።

🔺በዚህም በዚያም ልብህ አይሰረቅ። የሚስቡና የሚያስፈልጉ ነገሮች ብዙ ቢሆኑም እጅግ በሚጠቅሙህ ነገሮች ላይ ብቻ አተኩር።

🔹 ያብለጨለጨ ሁሉ ወርቅ አይደለም። ደምቆ ርዕሱ የተፃፈ ዜና ሁሉ ፍሬ ላይኖረው ይችላል። እናም ጥቂት ብትዘናጋ እንኳ ቶሎ ብለህ ወደ ዋናው ጣቢያህ ተመለስ።

ዋናው ጣቢያችን የቁርአንና ሐዲሥ አስተምህሮ ነው❗️
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
◾️ተከታታይ የተንቢሀት ኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ ክፍል 5⃣5⃣ ↩️
〰〰〰〰〰〰

↪️የትዳር አስፈላጊነትና ጥቅም
↪️የጥሩ ትዳር መሰረቶች
↪️ከትዳር መሸሽና አደጋው


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
ትዳርና ተያያዥ ነጥቦች
💦አዲስ ሙሓደራ
〰〰〰〰〰
→ርዕስ↓

🌐 «ትዳርና ተያያዥ ነጥቦች»
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በዉስጡ የተዳሰሱ ርዕሶች

① በትዳር የሚገፋፉ ቁረረአናዊ አንቀፆች
② በትዳር የሚገፋፉ ነብያዊ ሓዲሶች
③ በትዳር የሚገፋፉ የቀደምት ንግግሮች
④ ሚስት ወይም ባል መምረጫ መሰረታዊ ነጥቦች

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
➱ኢማሙ ሻፊዒ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
💦አላህ ቀልቡን እዲከፍትለት ለቀልቡም ብርሀን እዲያደርግለት የፈለገ የማይመለከተውን ነገር ከማውራት ይቆጠብ፡፡

(አልመጅሙእ 41/1)
↪️የኢስላም ጠላቶች እና ጫጩቶቻቸው የሚፈልጉት ነገር
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
💦 የሴት ልጅን ክብር መንጠቅና ሀቋን መቀማት ነው:: ከሃዲዋች እና ሙናፊቆች እንዲሁም በልቦቻቸው ውስጥ ችግር ያለባቸው የኢሥላም ጠላቶች ኸረ እንደውም የሰው ልጅ ጠላቶች የሆኑት ሴት ልጅ በኢሥላም ውሥጥ ያገኘችው ክብር፥ ልቅና እና ጥብቅነት ቅናት አቃጥሏቸዋል።

💦 ምክንያቱም የኢሥላም ጠላቶች የሆኑት ከሃዲዎች ሙናፊቆች ሴት ልጅን የማውደሚያ መሣሪያ እንድትሆን እና ኢማነ ደካማዎችን እና ያፈነገጠ ፀባይ ባለት የሆኑትን የማጥመጃ ገመድ እንድትሆን ይፈልጋሉ።

↪️ ይህንንም የሚያደርጉት የራሣቸውን የተጠማ ሥሜት ካረኩ ቡሃላ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
👇👇👇👇👇
وَاللَّهُ يُرِيدُ أَن يَتُوبَ عَلَيْكُمْ وَيُرِيدُ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الشَّهَوَاتِ أَن تَمِيلُوا مَيْلًا عَظِيمًا

(ሱረቱ አል-ኒሳእ - 27)
አላህም በእናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል፡፡ እነዚያም ፍላጎታቸውን የሚከተሉት (ከውነት) ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ፡፡
💦ፈቂሁ ወጣት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መታ❕

↪️አንድ ወጣት አንዲትን ሙስሊም ሴት ለጋብቻ ማየት ፈለገ፣በተፈቀደው ሸሪዓዊ የመተያየት ሁኔታ ውስጥ እሷ ስለ አላህ አዘወጀለ ከፍጡራኑ ሁሉ የበላይ መሆን፣ ይህንን ወጣት እምነቱ ምን እነደሆነ ማወቅ ፈለገች።

↪️"አላህ የት ነው?" ብላ ጠየቀችው።
እሱም ፦
💦የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
"↪️ነፍሴ በእጁ በሆነች ጌታ (አላህ) አንድ ወንድ ሚስቱን ወደ አልጋ ጠርቷት እምቢ አትልም ፦ባልዋ ከሷ እስኪወድ ድረስ ከሰማያት በላይ ያለው (አላህ) ቢቆጣባት እንጂ ።"

📚【ኢማሙ ሙስሊም ዘግበውታል】
ብሎ መለሰላት።

(ለፈገግታ ያህል…)
ጆይን🌹

https://t.me/https_Asselfya
አማኝ ሴት ንቁ ናት(ማንቂያ ናት)
አንደኛዉና ዋነኛዉ አማኝ ሴትን ልዪ የሚያደርጋት ባህሪያቶች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
↪️በአላህ ያላት እምነት፤ የፀና እምነቷ በዚህ አለም የተከሰተዉ ቢከሰት መጥፎ አጋጣሚወች ቢፈጠሩ በአላህ ፍቃድ ነዉ የምትል የሆነች ናት::

💦የትክክለኛ ሙስሊም ሴት እምነቷ ወይም አቂዳዋ ንፁህ እና ግልፅ ሲሆን በድንቁርና እድፍ ፣ በተሳሳተ አመለካከት እና ጥንቆላ ያልተበከለ ወይም ያልተመረዘ የሆነ ነዉ:: እምነቷ ያአላህን እምነት መሠረት ያደረገ ፣ አንድነቱን ፣ ከሁሉ በላይ መሆኑን ፣ ዘላለማዊነቱን ፣ ሁሉን ማድረግ የሚችል መሆኑን ፣ ሙሉ አለምን ተቆጣጣሪ እና ሁሉም ነገር ወደርሱ ተመላሾች መሆናቸውን ታምናለች::
ዝሙት ፍቀዱልኝ
Sadat
◾️ዝሙት ፍቀዱልኝ
👆

💢በአቡ መርየም ሀፊዙሁላሁ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/menhajselefiya123
ጊዜ ማለት፡፡፡፡
♻️_➪ጊዜ ማለት ለሁላችን ልዩ ስጦታ ነው።ጊዜማለት፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
♻️_➪ጊዜ ወርቅ ሳይሆን! ጊዜ ሂወት ነው።_
♻️_➪ሂወትን በከንቱ ነገር ማሳለፍ እንደሻማ ማቅለጥ ነው።_
♻️ _➪ነገ አላህﷻፊት ስንቀርብ ከምንጠየቃቸው ጥያቄወች ውስጥ አንዱ ጊዜህን በምን አሣለፍከው ነው!?_
♻️_➪ጊዜ አችንን ለአሒራ በሚጠቅመን ነገር ቢሆን እንጂ በዋዛ ፈዛዛ አናቃጥልለዉ_
╚╩══• •✠•❀ ❀•✠ • •══╩╝
{{المحافظة على الأذكار}}

🔹قال ابن الصلاح رحمه الله:

"من حافظ على
➖ أذكار الصباح و المساء،
➖ و أذكار بعد الصلوات،
➖ و أذكار النوم،
〰> عُدَّ من الذاكرين الله كثيراً"

📚[الأذكار للنووي (١٠)]

💦አዝካሮችን(ውዳሴዎችን)መጠባበቅ

〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
↪️ ኢብኑ ሰልላሕ አላህ ይዘንለትና~

👉 የጠዋትና የማታ አዝካሮችን(ውዳሴዎችን)
👉 ከግዴታ ሰላቶች በኋላ ያሉትን ዚክሮችን
👉 የእንቅልፍ ዚክሮችን የተጠባበቀ ሰው አላህን በብዛት ከሚያወሱት ሰዎች ይመደባል። ይላል።

📚 አልአዝካር አንነወዊ (10)
〰〰〰〰〰〰〰〰
Audio
◾️ተከታታይ የተንቢሀት ኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ ክፍል 5⃣6⃣ ↩️
〰〰〰〰〰〰

↪️ትዳር የሀብት ምንጭ
↪️ትዳር በኢስላም መነፅር

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
#ለሰሚ_ምክር_ነው።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ።
ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ።
▬▬▬▬▬▬▬▬
ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ።
ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣
ስለዚህ መመሪያህን አንብብ ፣
ቁርዐን ሀዲስን ከርር፡
አዋቂዎችን ጠይቅ ፣
ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።
✍ኑረዲን
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በአንድ ነገር ላይ የአቋም ልዩነት ሲኖረን ወደ ምን እንመለሳለን ?

ወደ ትክክለኛው የሸሪአ መረጃ ተመልሰን እናያለን ፡፡ በጉዳዩም ላይ የመጨረሻና የበላይ የሚሆነው የአላህ (ﷻ) ቁርአንና የነብዩ ሙሀመድ (ﷺ) ሱና ብቻ ናቸው ፡፡

አላህ (ﷻ) እንዲህ ይለናል


يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡

ነብያቺን (ﷺ) ማሊክ በዘገቡት ሐዲስ ነብዩ እንዲህ አሉ " አጥብቃቺሁ ከያዛቺሆቸው የማትሳሳቱባቸውን ሁለት ነገሮች በመሀከላቺሁ ትቻለሁ ፡፡እሱም የአላህ ቁርአን እና የነብዩ ሱና ናቸው ፡፡" ብለዋል ፡፡

===========================
🖍 አብዱል ከሪም አል ሀናኒ
============================
https://t.me/https_Asselfya
ماهو اﻻيمان
ኢማን ማለት ምን ማለት ነው?

#መልስ
لغة - التصديق
#በቋንቋ ደረጃ ፦ ኢማን ማለት

እውነት ብሎ መመስክር
ማለት ነው

وشعؚا
#በሸሪአ ደረጃ ፦
١.اعتقاد بالقلب
٢. نطق باللسان.
٣.وعمل باالجوارح
٤. يزيد بالطاعة وينقص بالعصيان.
ኢማን ማለት
①በልብ ማመን
②በምላስ መናገር
➌ .በአካል መስራት
➍ እስልምና በሚያዘው ነገር በሚፈፅም ጊዜ ይጨምራል፡ ወንጀልን በሚፈፅምበት ጊዜ ይቀንሳል፡፡

وهو بضع وسبعون شعبة،
እሱም ሰባ ምናምን ቅርንጫፍ ነው፡፡

فأعلاها قول لا اله إلا الله،
ከነዚህ ውስጥ ቆንጮው "ላኢላሀ ኢልለላህ" የሚለው ቃል ነው፡፡

وأدناها إماطة الأذى عن الطريق، والحياء شعبة من الإيمان.
ዝቅተኛው ደግሞ ከመንገድ ላይ አስቸጋሪን ነገር ማስወገድ ነው፡፡ አይን አፋርነት ከኢማን ነው፡፡ ሙስሊም ዘግበውታል 35

وأركانه ستة
ምሰሶዎቹ ስድስት ናቸው፡፡

ان تؤمن بالله، وملائكته، وكتبه، ورسله، واليوم الآخر، وتؤمن بالقدر خيره وشره، رَوَاهُ مُسْلِمٌ [رقم:8]
➡️ እነሱም፦በአላህ፣ በመላእክቱ፣ በመፃሕፍቱ፣ በመልእክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀን እና መልካምም ይሁን መጥፎ በቀደር ልታምን ነው፡፡
هذه الأركان الستة قوله تعلى
ለነዚህ ስድስት መሰሶዎች ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦
⬇️
۞ لَّيْسَ ٱلْبِرَّ أَن تُوَلُّوا۟ وُجُوهَكُمْ قِبَلَ ٱلْمَشْرِقِ وَٱلْمَغْرِبِ وَلَٰكِنَّ ٱلْبِرَّ مَنْ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلْكِتَٰبِ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ وَءَاتَى ٱلْمَالَ عَلَىٰ حُبِّهِۦ ذَوِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينَ وَٱبْنَ ٱلسَّبِيلِ وَٱلسَّآئِلِينَ وَفِى ٱلرِّقَابِ وَأَقَامَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَى ٱلزَّكَوٰةَ وَٱلْمُوفُونَ بِعَهْدِهِمْ إِذَا عَٰهَدُوا۟ ۖ وَٱلصَّٰبِرِينَ فِى ٱلْبَأْسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَحِينَ ٱلْبَأْسِ ۗ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ صَدَقُوا۟ ۖ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُتَّقُونَ
✍መልካም ሥራ ፊቶቻችሁን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም፡፡ ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላእክትም፣ በመጻሕፍትም፣ በነቢያትም፣ ያመነ ሰው ገንዘብንም ከመውደዱ ጋር ለዝምድና ባለቤቶችና ለየቲሞች ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኞችም፣ ለለማኞችም፣ ለጫንቃዎችም (ማስለቀቅ) የሰጠ ሰውና ሶላትንም ደንቡን ጠብቆ የሰገደ፣ ዘካንም የሰጠ፣ ቃል ኪዳንም በገቡ ጊዜ በኪዳናቸው የሞሉ (ሰዎች ሥራ) ነው፡፡ በችግር በበሽታና በጦር ጊዜም ታጋሾችን (እናወድሳለን)፡፡ እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ ናቸው፡፡ እነዚያም ተጠንቃቂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
በቀራአ177
የቀደር ማስረጃው ደግሞ የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦
إِنَّا كُلَّ شَىْءٍ خَلَقْنَٰهُ بِقَدَرٍۢ
እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡

✍ቀመር49
ወሏሁ አለም✍
https://t.me/https_Asselfya
እህቴ ሆይ! ውብ ነሽ እኮ!

ሰው ስላደነቀሽ ሳይሆ አረህማን ባማረ ሁኔታ ስለፈጠረሽ ውብ ነሽ ....🥀
በሂጃብሽ ተዋቢ ጌታሽ እንዳዘዘሽ...🥀
ጨዋ ነትሽ ወሳኝ ነውና ሀያዕ ይኑርሽ....🥀
ውዷ እህቴ ለአላህ ብዬ ስወድሽ...አላህ ይውደድሽ....🥀

👇👇👇
https://t.me/menhajselefiya123
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
ماهو اﻻيمان ኢማን ማለት ምን ማለት ነው? #መልስ لغة - التصديق #በቋንቋ ደረጃ ፦ ኢማን ማለት እውነት ብሎ መመስክር ማለት ነው وشرعا #በሸሪአ ደረጃ ፦ ١.اعتقاد بالقلب ٢. نطق باللسان. ٣.وعمل باالجوارح ٤. يزيد بالطاعة وينقص بالعصيان. ኢማን ማለት ①በልብ ማመን ②በምላስ መናገር ➌ .በአካል…
📌♻️ #ኢማን ማለት ምን ማለት ነው? ♻️📌

📌🔺 ኢማን፦ ማለት የልብ እምነት፣ የምላስ ንግግር እና የአካላት ተግባርን የሚያጠቃልልና አቅፎ የያዘ ሲሆን መልካም በመስራት የሚጨምር እና መጥፎ በመስራት ደግሞ የሚቀንስ ነው፡፡

📌🔺የኢማን መሰረቶች ስድስት ናቸው እነሱም በአላህ ማመን፣ በመልእክተኞች ማመን፣ በመፃሕፍቶች ማመን፣ በመላኢካዎች ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና መልካምም ይሁን መጥፎ በአላህ ውሳኔ (በቀደር) ማመንን አቅፎ የያዘ ነው።

📌🔺ኢማን ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ ቁርጠኛ እና ምንም ጥርጣሬ ያልገባበት እምነት ማለት ሲሆን

📌🔺ሽሪአዊ ትርጉሙ ደግሞ በልብ የሚታመን፣ በምላስ የሚነገር፣ በስውነት አካሎቻችን ሚተገበር ፣ አላህን በመታዘዝ የሚጨምር እና አላህን በማመጽ የሚቀንስ ነው።

📌🔺 በዚህ መሰረት የሁሉ ሰው ኢማን እኩል እንዳልሆነና አንዱ ከአንዱ ሊበላለጥ እንደሚችል ማወቅ እንችላለን ማለት ነው። ይህም የሚሆነው ባለን ለአላህ ታዛዥነትና የመልእክተኛው ትእዛዛ በመተግበርና የሸይጧንን መንገድ በመተው ቀጥተኛው መንገድ በመያዛችን ልክ ይሆናል።

📌🔺 ኢማን ከመጨመሩ የተነሳ እንደ እሁድ ተራራ አክል ሊገዝፍ ይችላል፣ ከመቀነሱ የተነሳ ምንም እስከማይቀር ዜሮ ሊሆን ይችላል።

📌🔺ኢማን ከሰባ ሶስት እስከ ሰባ ዘጠኝ ቅርንጫፍ ያለው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ዋናውና ቁንጮው “ላኢላሀ ኢልለላህ (ተውሂድ)” ነው፡፡ ዝቅተኛው ደግሞ ከመንገድ ላይ አስቸጋሪን ነገር ማስወገድ ነው፡፡ አይን አፋርነት ከኢማን ቅርንጫፎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

https://t.me/https_Asselfya