💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.65K subscribers
1.29K photos
494 videos
125 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
{ የእስልምናችን ታላቅነት } !!
Abu Useymin
➡️አድስ ~ሙሓደራ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️

🔊የእስልምናችን ታላቅነት !!

🕌 በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን በዳሞት ጋሌ ወረዳ በሻሻ ጋሌ ቀበሌ በቢላል መስጊድ የተደረገ!!

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➧https://t.me/abuUseyminabdurehman/8912
➧ለአል ኢህሳን ጀግና እህቶቻችን ማስታወሻ ትሁንልኝ

➲ጀግና ነሽ ብርቅየ


❖ሰለፍይ ጀግና በሱና ያጌጥሽው
በሱሀቦች ፋና ኒቃብ የለበስሽው
ተውሂድን በመማር ጊዜ የፈጀሽው
የመንሀጅ እህቴ ኢስላምን ያወቅሽው


በአል ኢህሳን መርከዝ የተገናኘነው
ከእንቁ ኡሰስታዞች በደርስ የተጣድነው
በመንሀጀ ሰለፍን የተረዳዳነው
ድንገት ስንለያይ ቀዘፈኝ እንባየ
እጅጉን ተሰማኝ መጣ ትዝታየ
እንባ ስታፈሽ እህትሽ ስትሄድ
ባጃጅ ስትሳፈር ስትገባ መንገድ
ስተትዘያየሩ በኒቃብ አምራችሁ
በጣም ገራሚ ነው ያስቀናል ፍቅራችሁ

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷

ታሪክ አይረሳውም የሰራሽው ስራ
በተውሂድ ጠንክሪ ምርትሽ ፍሬ ያፍራ
በቀጣይ ትውልዱ ደጋግሞ ይወራ
አንች ውዷ እህቴ መንሀጅ ያገናኘን
እንደ እድል ሆነና ሀገር ያለያየን
አላህ በእዝነቱ በዱኒያ ሰብስቦን
በእንቁ ኡስታዞች ለመማር ወፍቆን
በአል ኢህሳን መርከዝ ወስኖ አሰባስቦን
ደግሞ በውሳኔው ድንገት ያለያን
እንባ እየተራጨን እየተሸኛኘን
መለያየታችን እጅጉን ቢያመኝም
ውሳኔው የአላህ ነው ምንም አናረግም


እኔ ግን እህቴ ብዙ ተምሬ አለሁ
የሴቶች አለቃ መሆንሽ  ተረዳሁ
ቆራጥና አስተዋይ አርቆ አሳቢ ነሽ
ለድንሽ አሳቢ  እንቁ ጀግና የሆንሽ
የተውሂድ ዘበኛ የሱና ነበልባል
ሽርክን አራጋፊ የቢድአ እስክንፋል
መሆንሽ ግልፅ ነው ስራሽ ይናገራል
ለአህባሽ ለሱፍይ የእግር እሳታቸው
ለኢኽዋን ቡቃያ በእውቀት ገራፊያቸው
ሀዳድይ ሀጁሪን አንገት አስደፊያቸው
ለሙብተዲእ ሁሉ የእራስ ምታታቸው
አንች ነሽ እህቴ እኔ አይቸሻለሁ
ከምነግርሽ በላይ ብዙ ሰምቻለሁ
በአላህ ውሳኔ ዛሬ ብንለያይ
ኢንሻኡ ረቡና ብዙ አመት ሳንቆይ
እንገናኛለን በተውሃድ ዳእዋ ላይ
አንች ብቻ በርቺ በጅልባብ በኒቃብ
በአቂዳሽ ኑረሽ በሱናሽ በመዋብ
የነቢን ትእዛዝ ተግብረሽ በአግባብ
በሶብር ላይ ቆይ  እስኪሻ ጌታየ
እስከምንገናኝ አይናችን እያየ
የሁለት ሀገር ውብ ብርቅየ



✍ገጣሚ ወንድማችን አቡ ሹራ አህመድ
አልብኪይ

➷ለአል ኢህሳን መርከዝ ሴት ተማሪወች ማስተዋሻ የተነበበች
እህቶቸ በርቱልኝ አልሀምዱሊላህ የአላህ ውሳኔ ሆኖ ብንለያይም
እንደነገርኳችሁ ትእግስት አድርጉ
፡

➷የእኔ ውዶች በሰላም ግቡልኝ➷
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
➲የጧት ዚክር
➱➱➱➱➱➱

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

➲የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
👍1
( يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا مَا لَكُمْ إِذَا قِيلَ لَكُمُ انْفِرُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ اثَّاقَلْتُمْ إِلَى الْأَرْضِ ۚ ..)
👍2
🔹ከጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ – አላህ ይውደድለትና–ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም " «ከሰዎች በላጩ ሰውን የሚጠቅም ነው» ብለዋል።

📝 ጦበራኒ ዘግበውታል… ሐዲሱን አልባኒ ሐሠን ብለውታል።

👉«አላህ ባርያውን በመርዳት ላይ ነው ባርያው ወንድሙን በመርዳት ላይ እስካለ ድረስ»
↪️የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች

👉ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-


➧ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]

➧ ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]

➧ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]

➧ ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።

➧ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]

2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።


3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-


👉አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
👉አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
👉የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
👉እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!

የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)


የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
#ዘመን_መለወጫ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ዘመን መለወጫ የለንም ወዳጄ፡
ኮተት አልፈልግም ዘወር በል ከደጄ፡
ሙሉ ፅድት ያለ ሐቅ ነው መንሀጄ፡
ከሉቃስ ዩሀንስ ከማርቆስ ክርስቶስ፡
ከሰውች ወደሰው ከቄርቆስ ቆሮንጦስ፡
ኸረ ለቀቅ አርገኝ አያልቅም ያንተ ጦስ?
ወደ ሰው መጠጋት ሙስሊሞች አንወድም፡
ከአንድ አምላክ በስተቀር ለማንም አንሰግድም፡
ለማርቆስ ለሉቃስ አናጎበድድም፡
ምንክንያቱም ሙታን ምንም አይፈይድም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ስለዚህ ራቂኝ ማነሽ እንቁጣጣሽ፡
ወደኛ አትጠጊ ዞር በይ እስከ ሻንጣሽ፡
እኛ እናውቅሻለን ከየት እንደመጣሽ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በእስልምናችን የለም እንቁ ጣጣሽ፡
ዘመን መለወጫ የሽርክ ብጥስጣሽ፡
የድግምት የመተት ክፋት መተግበሪያ፡
የክፋት የሴራ ተንኮል መቀመሪያ፡
እውነታ የሌለሽ የኩፋር መመሪያ፡
እውነትን ሰርዘሽ ውሸት ማስተማሪያ፡
ሐቅን ባጢል ብለሽ ጥመት ማበጠሪያ፡
ውስጥሽ ውጭሽ ቦድ ግድግዳሽም ጣሪያ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ኢብሊስ የገነባሽ የጭፍሮቹ መተት፡
አማኞች አያውቁም እንድህ አይነት ኮተት፡
ሐቁ መመሪያችን ካላፀደቀልን፡
ውዱ ነብያችን ካልመሰከረልን።
በነሉቃስ ቀመር ተጓዥ አይደለንም፡
ዘመን መለወጫ ፈፅሞ የለንም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የአመፅ የበደል የወንጀሎች ቅርጫ፡
የሸይጣን የአጋንንት የጥመት መፈንጫ፡
የመጥፎነት ማዕረግ የሙሽሪኮች ዋንጫ፡
ሽርክን ክህደትን በጥብጦ መጠጫ፡
ሙስሊሞች የለንም ዘመን መለወጫ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
[ ኑረዲን አል አረቢ 01/26/1443
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
👍2
▫️قال رسول الله ﷺ :

"أڪثروا الصلاة عليَّ يوم الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ ، فمَن صلَّى عليَّ صلاةً صلى اللهُ عليهِ عشرًا".

📚 [صحيح الجامع - رقم: (1209)]

《اللَّهُمَّ صَلِّ علَى مُحَمَّدٍ وعلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كما صَلَّيْتَ علَى إبْرَاهِيمَ، وعلَى آلِ إبْرَاهِيمَ، إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ علَى مُحَمَّدٍ وعلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كما بَارَكْتَ علَى إبْرَاهِيمَ، وعلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.》

📌 لا تنسوا الصلاة والسلام على رسول الله -صلى الله عليه وسلم- يوم الجمعة وليلتها.
➧ልጅ መውለድን አብዙ ሲሳያችሁ ይበዛል

💭ሙሀመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:-

➲"በጌታው ላይ መጥፎ ጥርጣሬን በማሳደር ልጆችን አታብዙ፤ ሲሳያችሁ ይጠባል ያለ ሰው በእርግጥም ግልጽ የሆነ ጥመትን ተጣሟል።

➲በአርሹ ጌታ እምላለሁ በዚህ ንግግራቸው ዋሽተዋል። ይልቁንም ልጅ ሲያበዙ አሏህ ሲሳያቸውን ያበዛላቸዋል።


➲ምክንያቱም በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ሪዝቋ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ወጪ ታደርግላቸው ዘንድ የልጆችህን ሲሳይ የሚከፍትልህ አሏህ ነው።


➲አብዛኛው ሰው ግን በጌታው ላይ መጥፎ ጥርጣሬ ያሳድራል፤ ፊት ለፊቱ ባለው በሚታየው ቁሳዊ ነገር ላይ ብቻ ይደገፋል፤ የወደፊቱንም አያይም፣ የጌታውንም ችሎታ አይመለከትም። ልጆች ቢበዙም ሲሳይን የሚለግሰው እሱ 7 ነው።ልጆችን አብዛ ሲሳይህ ይሰፋል።ትክክለኛው ይህ ነው ።"

📚ሸርህ ሪያዱሷሊሂን [1/91]


https://t.me/https_Asselefya1
ያ አላህ

በንግግሬም በተግባሬም  እዉነተኛ የሠለፊ ሴት አድርገኝ።

አንተ ከከለከልካቸዉ ነገሮች በሙሉ አርቀኝ ።
👍6
እስከ መቼ?
~
ነጋ ጠባ ስለ ብሄርህ የምታወራ፣ ጧት ማታ "ኦሮሞ፣ ኦሮሞ"፣ "አማራ፣ አማራ"፣ "ትግሬ፣ ትግሬ"፣ "አፋር፣ አፋር"፣ "ስልጤ፣ ስልጤ"፣ "ጉራጌ፣ ጉራጌ"፣ ... የምትዘምር፣ የምታለቅስ፣ ... ከሆነ መመዘኛህ ሁሉ ዘር ነው የሚሆነው። ዘር ተከትለህ ትወዳለህ። ዘር ለይተህ ትጠላለህ።
እወቅ! ያንተ ብሄር ከሌላው የሚለየው ቅንጣት ታክል ደረጃ የለውም። ደግሞም በለቅሶውም፣ በሰርጉም፣ በሀዘኑም፣ በፌሽታውም፣ በቤትም፣ በመስጂድም፣ በቡናውም፣ በጫቱም ላይ ሁሌ ስለብሄር ስታኝክ ልታፍር ይገባሃል። በብሄር አጀንዳ በተጠመድን ቁጥር በሌሎች ላይ ጥላቻ እየጨመርን ነው የምንሄደው። አንድ ሰው ዘረኝነት ልቡን ከተቆጣጠረው ሰውነቱን ያጣል። በመንጋ እንደሚጓዝ አውሬ ያለ ምክንያት ያልመሰለውን ሁሉ ይናከሳል። "ቆይ እኛ ቤት ትመጣለህ!" እንደሚል ህፃን ከደጃፉ ያገኘውን ሁሉ ያጠቃል። ደግሞም ሁሌ ሌላውን ብሄር እያብጠለጠልን ከሌላው አክብሮትን ልንጠብቅ አይገባም። Respect is a two-way street!
ወንድሜ ሆይ! ሰው ሁን። ጭንቅላትህን ካልተጠቀምክበት ላንገትህ ሸክም ሆኖ ቢንገታገት ምን ይሰራል?! ሰው ሰርቶ ሲለወጥ "ከኛ የሰበሰበው ገንዘብ ነው" አይነት ቅናት የወለደው ብሶት አታንቋር። ከቻልክ እንደሰው ሰርተህ ተለወጥ። ካልሆነልህን እራስህን በቅናት አታቃጥል። "ምቀኛ ከራሱ ማግኘት ይልቅ የሌላው ማጣት ነው የሚያሳስበው" ይባላል።
ዘረኝነት ተደጋግፈን እንዳንኖር የተጋረጠ እጅግ አደገኛ በሽታ ነው። በዚህ ዘመን በየቦታው ለሚደርሰው ግጭትና እልቂት ቀዳሚው ምክንያት ዘረኝነት ነው። ሌላው ቀርቶ በየመስጂዱ ሳይቀር እየገባ ሰዎችን ልብ ለልብ እያራራቀ ነው። ችግሩ በዚህ መጠን እንዲያውም ከተገለፀውም በከፋ ደረጃ ቢሆንም የዲን አስተማሪዎች ግን አብዛኞቹ ደራርበው ተኝተዋል። ከፈሎቹማ ጭራሽ የችግሩ አካል ናቸው። ጥቂቶች ደፍረው የሚናገሩ ከኖሩም አንዳንዶቻችን "እኛን ለመንካት ነው" ብለን ደርሰን የምናኮርፍ፣ ልባችን በጥላቻ የሚጓሽ ሆነናል። ይሄ በጣም የሚያሳፍር ነው።
ብቻ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም። ጥንብ በሆነው ዘረኝነት የተነሳ ከማንወጣበት አዘቅት ውስጥ እየገባን ዝም ብሎ ማየት አያዋጣንም። ስለዚህ በቃ ልንል ይገባል። እስካሁን የደረሰብን ጉዳት ለመማር ከበቂ በላይ ነው። ነገ የነ ርዋንዳ አይነት እልቂት እንዳይገጥመን ጥርሳችንን ነክሰን ችግሩን ልንጋፈጠው ይገባል። ባግባቡ መወቃቀስ ባለመቻላችን ይሄው በድንቁርናው የሚኮፈስ፣ ድንዛዜውን "በክብር" ሰቅሎ የሚያሳይ ገራሚ ትውልድ መጥቶልናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
🏠ሴት ልጅ ስራዋም ሆነ የትኞቹም
የዕለት ተዕለት ተግባራቶችዋ የግድ ከቤት መውጣትዋን የሚሹ ተግባራት ሲቀሩ ቤቷ ውስጥ የመሆኑ ግዴታነት🏠

 
💎ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና


➧አንዳንድ ሙስሊም ዳዒ  የሆኑ ሰዎች ሳይቀር ሴቶች ቤት መቀመጥ የለባቸውም ከቤት ወጥተው በገበያ ስፍራ፣በየሱቁና በማምረቻ ቦታዎች መስራት ሲገባቸው ቤት በመቀመጣቸው የተነሳ በሴቶች መሸፈን የነበረባቸው የስራ ዘርፎች ተራቁተዋል(ባዶ ቀርተዋል) ይላሉ ተብለው ተጠይቀው ሲመልሱ

➧ይህን የሚሉ ግለሰቦች በእርግጥ ትክክለኛውን በሴት  እንጂ በወንዶች በፍፁም ሊሸፈን የማይችለውን ወሳኙን የተተኪን ትውልድ ቀረፃ የህበረተሰብ ግንባታንና የሰው ሀብት ልማትን ለማራቆት(ባዶ) ለማድረግ የሚታገሉ ግለሰቦች ናቸው።

➧ሴቶች(እናቶች) በሁሉም ዘርፍ ብቃት ያለው ትውልድ የሚቀርፁ የመጀመርያ የእውቀት ዩኒቨርሲቲ መሆናቸው ማንም የማይክደው ሀቅ ነው።

➧ታድያ ሴቶች(እናቶች) ለስራ በሚል ሰበብ ከቤት ውጭ መዋል ሲጀምሩ ህፃናት በቤት ሰራተኞች እጅ ማደጋቸው አማራጭ የሌለው የመጨረሻ እድል ይሆናል።

➻በመሆኑም እኛ ሙስሊሞች የወለድናቸው ልጆች ባህሪያቸው ግን የሌላ ህብረተሰብ ባህሪ ይሆናል ማለት ነው።

➧በግዜ  ሂደት ደግሞ አጠቃላይ ህዝበ ሙስሊሙ በስም ሙስሊም በባህሪና በተግባር የኢስላም ተቃራኒና የከሀዲያንን(የካፊሮችን) ባህሪ አራማጅ ይሆናል ማለት ነው።

📚ምንጭ ፍታዋ ኑሩን አለደርብ 371


➮የተሌግራም ቻናላችን ጆይን በማለት ይቀላቀሉ
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/abuUseyminabdurehman
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❖ قال #ابن_القيم  رحمه الله :

" فإن العلم طعام القلب وشرابه ودواؤه ، وحياته موقوفة على ذلك ، فإذا فَقد القلب العلم فهو موت ، ولو كان لا يشعر بموته
  📚مفتاح داع السعادة ٤٠٥/ŮĄ

➡️ኢማም ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንለት) እንዲህ ይላል

☑️ኢልም (እውቀት) ማለት፦
🔹የቀልብ ምግብ
🔹የቀልብ መጠጥ
🔹የቀልብ መድሀኒት
🔹የቀልብ ህይወት ሲሆን
🔹በአጠቃላይ ቀልብ በእውቀት ላይ የቆመች ናት
።
☑️ነገር ግን ቀልብ እውቀትን ካጣች
የሞተ ይሆናል
።https://t.me/https_Asselfya
ለመጨረሻ ግዜ ስለ ወሎ ጀግኖች
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/nuredinal_arebi/14636
https://t.me/nuredinal_arebi/14636
Audio
🔹 تلاوة من سورة الزخرف
🔹 القارئ: #سيد_كمال
•••━══❁✿❁══━•••