💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.65K subscribers
1.29K photos
494 videos
125 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
Audio
☑️ አላህን ፈርቶ ማልቀስ
〰〰〰〰〰〰〰〰

👉አዲስ ምክር


⭕️👉አንዳንዱ በፊልም በሙዚቃና በድራማ እናቱን እንዳጣ ግልገል ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ ታየዋለህ። ነገር ግን ቁርአን ሲቀራ፣ ስለ ጀሀነምና ስቃዩ ሲወሳ ልቡ አይደነግጥም። የልቡ መድረቅ አያስለቅሰውም። የቀብር ጥበትና ጨለማ አያስፈራውም። በጀሀነም ላይ የተዘረጋው ድልድይ (ሲራጥ) ላይ ማለፍ እንኳን ሊያስለቅሰው ምንም አይመስለውም።

⭕️👉የሰው ልጅ ፊልም እና ድራማ ሀራም፣ ውሸት፣ ጊዜ ገዳይና ከአሄራ አዘናጊ መሆናቸውን እያወቀ ያለቅሳል። ነገር ግን ጀሃነም እውነት መሆኑን እያወቀ አያለቅስም።

⭕️👉አላህን ፈርቶ ማልቀስ የሷሊሆችና የደጋጎች መገለጫ እንዲሁም የልብ እዝነትና የኢማን ከፍታ የሚያሳይ ሲሆን በተቃራኒው በፊልምና በድራማ ማልቀስ ግን የፋሲቆች መገለጫ እና የልብ መድረቅ የኢማን ማነስ ምልክት ነው።

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

©ኢብኑ ተይሚያ የተዉሒድየሱና ቻናል
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
👍1
Audio
▪️ تلاوة من سورة النحل
▪️ القارئ: #ياسر_الدوسري
•••━══❁✿❁══━•••
▪️إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُوا۟ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسْتَقَٰمُوا۟ تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا۟ وَلَا تَحْزَنُوا۟ وَأَبْشِرُوا۟ بِٱلْجَنَّةِ ٱلَّتِى كُنتُمْ تُوعَدُونَ
☑️እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡

📚ሱረቱል ፉሲለት 30}
➡️እስቲግፋር እና ተውባህ
     ➯➯➯➯➯➯➯➯➯

➡️የአላህ መልእክተኛ  ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም እንዲህ ብለዋል። እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ በፀፀት ተመለሱ፡፡ እኔ በየቀኑ ከመቶ ጊዜ ያላነሰ ተውበት አደርጋለሁ፡፡

📚{ሙስሊም ዘግቦታል።}

➡️የአላህ መልእክተኛ  ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም እንዲህ ብለዋል። ‹‹አላህ ለባሪያው ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ከመጨረሻው የሌሊቱ ክፍል ላይ ነው፡፡ በዚያ ወቅት አላህን ከሚያወሱት ለመሆን ከቻልክ ሁን።
📚{ሙስሊም ዘግቦታል ።}

➡️የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም  እንዲህ ብለዋል። በቀን መቶ ጊዜ አላህን ምህረት የመለመን ፍላጎት ልቦናዬ ውስጥ ያድራል፡፡
📚{ሙስሊም ዘግቦታል።}

➡️የአላህ መልዕክተኛ  ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም እንዲህ ብለዋል።
አንድ ባሪያ አላህ ዘንድ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ነው፡፡ ሱጁድ ላይ ዱዓ አብዙ፡፡

📚{ሙስሊምዘግቦታል።}

➡️የአላህ መልእክተኛ ሰላሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል።
አላህ ጥራት ይገባው እንዲሁም ምሰጋና ለርሱ ነው። ሱብሃነ አላሂ ወቢሀምዲሂ (سبحان الله وبحمده) የሚለውን ዚክር በቀን መቶ ግዜ ያለ ሰው ወንጀሉ እንደ ባህር አረፋ የበዛ እንኳ ቢሆን ይራገፍለታል።

📚{ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበውታል።}

✅በሶስት ነገራቶች ላይ የኢማንን ጥፍጥናን ካገኛችሁ ፈልጉት።አልበለዚያ በሩ ዝግ ነው።
➘በሶላት ፣በዚክር፣ በቁረአን።

📚ሃሰኑል በስሪ رحمه الله።}

♦️አላህ  ሆይ!  አንተን በማውሳት፣ በማመሰገን እና በሚገባ አንተን በማምለክ ላይ እርዳን።
Forwarded from ŮŮ‚يع؊ ؼلى الله
➲እውቀት ፈላጊዋ እህቴ!
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

ቢስሚላሂ ብየ ልጀምር ፅሁፌን
በረካ ፈልጌ ከዚያም ለማመስገን
ለትልቁ ጌታ ለአርሹ ባለቤት
በሙሉ ጌታየ ጉድለት ለሌለበት
አንቺ ውድ እህቴ ኢልም ፈላጊዋ
የጀነቷ ጓደ አንቺ ከርታታዋ።


ወደድኩሺ ወደድኩሺ በጣምም ወደድኩሺ
ኢልም ፈላጊዋ ለእኔ ልዩኮ ነሺ
እውቀት ለማገኘት ቤተሰብ ርቀሺ
አቂዳን ለመማር ከሀገርሺ ወተሺ
ይገርመኝ ነበረ በጣሙን ባልወድሺ
ትንሹን ልገርሺ ትንሹን ላስታውስሺ
ከእሙ ሀብለና ከደካማዋ እህትሺ።


በኢልም ላይ ሆነሺ ፈተናሺ ቢበዛም
ቢርብሺ ቢጠማም ብርዱ ቢበረታም
ኢንሻአላህ ታገሺ ያልፋል እህት አለም
አንችኮ ታላቅ ነሺ አላህ የመረጠሺ
ቁረአንና ሱናን ያደረግሺ መመሪያሺ


➷አረ አንቺ ልዩ ነሺ
እህት አለም አይተሻቸዋል ግን
በየ መጠጥ ቤቶች የሚጃጃሉትን
በቁርአን በሀድስ የሚያላግጡትን
ኒቃብን ረግጠው እርቃን የወጡትን
አጅነብይ ወንድ ጋር የሚማግጡትን
።

➷አስቢ እንጂ ውዴ
ታዳ ከእነዚህ ጋር በምን ተገናኝተሺ
ሰላም መረጋጋት ኢማንን አድሎሺ
አላህ በትዕዛዙ ከመጥፎ ጠብቆሺ
ምስጋና አቅርቢ እንጂ ለታላቁ ጌታሺ
የሴቶች አለቃ የምርጥ ምርጥ ነሺ

➷አህባሺ ቢውተረተር ክብርሺን ለማጉደል
ኢልም እንዳታገኚ ኢኽዋን ቢታገል
ከእነሱ ፈተና እራስሺን አግለሺ
ኢልምን ለመፈለግ መንገድሺን ጀመርሺ
በሰለፍያ ላይ መጓዝን ከፈለግሺ
አልጋ በአልጋ አይሆንም ይበዛል ፈተናሺ
እይ እስኪ ቀደምቶች እንደት እንደለፉ
በስቆቃ እንግልት ሂወትን ያለፉ
ሰዎችን ለማቅናት በጣሙን ቢለፉ
ታሰሩ ተመቱ በጣም ተገላቱ

ህይወትንም አጡ በእየ እስር ቤቱ።

ለድናቸው ሲሉ ይሄን ካሳለፉ
ታድያ ለምንድን ነው ያንቺ መርበትበቱ

👉እህቴ ልገርሺ

ዛሬ በኢልም ላይ ትንሹን ካልታገልሺ
መሆንሺ አይቀርም ውዳቂና እርካሺ
ስለዚህ ታገሺ የዛሬን ፈተና
ጀሊሉ እንድሰጥሺ በአኼራ ላይ ጀና
መታገሉ አይከፋም ዛሬ በዱኒያ
ለቤተሰቦችሺ እንድትሆኚ መመሪያ
አላህ ይወፍቅሺ ኢልም በኢልም ላይ
የበላይ ያድርግሺ ነገም በጀነት ላይ።


✍ከእሙ ሃብለና ከአል ኢህሳን ተማሪ
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/AlihsanCharityAssociation
https://t.me/AlihsanCharityAssociation
👍3
Audio
☑️ ከሴቶች ጋር የሀራም ግኑኝነት (መፃፃፍ፣ መላላክ፣ መነጋገር…) በራቅክ ቁጥር ወደ አላህ እየቀረብክ ትሄዳለህ።

☑️ ከሴቶች ጋር የሀራም ግኑኝነት ባበዛህ ቁጥር ከአላህ፣ ከትክክለኛና ከሙሉ ኢማን እየራቅክ ትሄዳለህ።

▪️ሴቶችም ከወንዶች በተመሳሳይ መልኩ ነው።

🎙الشيخ مزمل فقيري "حفظه الله"

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

በተጨማሪ
የሀራም ግኑኝነት በበዛ ቁጥር፦
♦️ኢማንህ ይተናል
♦️ተቅዋህ ይቀንሳል
♦️ልብህ ይደክማል
♦️ወኔህ ይጠፋል
♦️ነሻጣህ ይከስማል
♦️ጀግንነትህ ይቀንሳል
♦️ወንድነትህ ይከዳሀል

♦️የዝሙት መንገድ ይቀልሀል
♦️የኢባዳ ጥፍጥና ይወገዳል
ሌላም ሌላም……

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
👍1
📲 ተንቀሳቃሽ ስልክ እና አደቦቹ
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
📱خُطْبَةُ الْجُمُعَةِ
📱የጁሙዓ ኹጥባ

📲 الهاتف النقال وآدابه
📲 ተንቀሳቃሽ ስልክ እና አደቦቹ

🕌 ደሴ አል-አዝሐር መስጂድ

📅محرم/28/ 1444

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
      ↓↓↓
t.me/abu_reyyis_arreyyis/6281
t.me/abu_reyyis_arreyyis/6281
👍1
{ የእስልምናችን ታላቅነት } !!
Abu Useymin
➡️አድስ ~ሙሓደራ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️

🔊የእስልምናችን ታላቅነት !!

🕌 በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን በዳሞት ጋሌ ወረዳ በሻሻ ጋሌ ቀበሌ በቢላል መስጊድ የተደረገ!!

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➧https://t.me/abuUseyminabdurehman/8912
➧ለአል ኢህሳን ጀግና እህቶቻችን ማስታወሻ ትሁንልኝ

➲ጀግና ነሽ ብርቅየ


❖ሰለፍይ ጀግና በሱና ያጌጥሽው
በሱሀቦች ፋና ኒቃብ የለበስሽው
ተውሂድን በመማር ጊዜ የፈጀሽው
የመንሀጅ እህቴ ኢስላምን ያወቅሽው


በአል ኢህሳን መርከዝ የተገናኘነው
ከእንቁ ኡሰስታዞች በደርስ የተጣድነው
በመንሀጀ ሰለፍን የተረዳዳነው
ድንገት ስንለያይ ቀዘፈኝ እንባየ
እጅጉን ተሰማኝ መጣ ትዝታየ
እንባ ስታፈሽ እህትሽ ስትሄድ
ባጃጅ ስትሳፈር ስትገባ መንገድ
ስተትዘያየሩ በኒቃብ አምራችሁ
በጣም ገራሚ ነው ያስቀናል ፍቅራችሁ

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷

ታሪክ አይረሳውም የሰራሽው ስራ
በተውሂድ ጠንክሪ ምርትሽ ፍሬ ያፍራ
በቀጣይ ትውልዱ ደጋግሞ ይወራ
አንች ውዷ እህቴ መንሀጅ ያገናኘን
እንደ እድል ሆነና ሀገር ያለያየን
አላህ በእዝነቱ በዱኒያ ሰብስቦን
በእንቁ ኡስታዞች ለመማር ወፍቆን
በአል ኢህሳን መርከዝ ወስኖ አሰባስቦን
ደግሞ በውሳኔው ድንገት ያለያን
እንባ እየተራጨን እየተሸኛኘን
መለያየታችን እጅጉን ቢያመኝም
ውሳኔው የአላህ ነው ምንም አናረግም


እኔ ግን እህቴ ብዙ ተምሬ አለሁ
የሴቶች አለቃ መሆንሽ  ተረዳሁ
ቆራጥና አስተዋይ አርቆ አሳቢ ነሽ
ለድንሽ አሳቢ  እንቁ ጀግና የሆንሽ
የተውሂድ ዘበኛ የሱና ነበልባል
ሽርክን አራጋፊ የቢድአ እስክንፋል
መሆንሽ ግልፅ ነው ስራሽ ይናገራል
ለአህባሽ ለሱፍይ የእግር እሳታቸው
ለኢኽዋን ቡቃያ በእውቀት ገራፊያቸው
ሀዳድይ ሀጁሪን አንገት አስደፊያቸው
ለሙብተዲእ ሁሉ የእራስ ምታታቸው
አንች ነሽ እህቴ እኔ አይቸሻለሁ
ከምነግርሽ በላይ ብዙ ሰምቻለሁ
በአላህ ውሳኔ ዛሬ ብንለያይ
ኢንሻኡ ረቡና ብዙ አመት ሳንቆይ
እንገናኛለን በተውሃድ ዳእዋ ላይ
አንች ብቻ በርቺ በጅልባብ በኒቃብ
በአቂዳሽ ኑረሽ በሱናሽ በመዋብ
የነቢን ትእዛዝ ተግብረሽ በአግባብ
በሶብር ላይ ቆይ  እስኪሻ ጌታየ
እስከምንገናኝ አይናችን እያየ
የሁለት ሀገር ውብ ብርቅየ



✍ገጣሚ ወንድማችን አቡ ሹራ አህመድ
አልብኪይ

➷ለአል ኢህሳን መርከዝ ሴት ተማሪወች ማስተዋሻ የተነበበች
እህቶቸ በርቱልኝ አልሀምዱሊላህ የአላህ ውሳኔ ሆኖ ብንለያይም
እንደነገርኳችሁ ትእግስት አድርጉ
፡

➷የእኔ ውዶች በሰላም ግቡልኝ➷
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
➲የጧት ዚክር
➱➱➱➱➱➱

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

➲የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
👍1
( يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا مَا لَكُمْ إِذَا قِيلَ لَكُمُ انْفِرُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ اثَّاقَلْتُمْ إِلَى الْأَرْضِ ۚ ..)
👍2
🔹ከጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ – አላህ ይውደድለትና–ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም " «ከሰዎች በላጩ ሰውን የሚጠቅም ነው» ብለዋል።

📝 ጦበራኒ ዘግበውታል… ሐዲሱን አልባኒ ሐሠን ብለውታል።

👉«አላህ ባርያውን በመርዳት ላይ ነው ባርያው ወንድሙን በመርዳት ላይ እስካለ ድረስ»
↪️የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች

👉ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-


➧ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]

➧ ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]

➧ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]

➧ ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።

➧ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]

2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።


3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-


👉አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
👉አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
👉የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
👉እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!

የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)


የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor