💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.59K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.17K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
ምርጫዬ ሷሊህ ነው
〰〰〰〰〰〰〰
ሳይኖርም ልዩነት በመካከላችን
በፍቅር ተሞልቶ የሱናው ቤታችን
ሷሊህ ሷሊህ ልጆች ሲሰጠን ጌታችን
ሱናን ስንከተል እስከ ልጆቻችን
በቁርአን በሀድስ ታንፃ ቀልባችን
ስንሰራ እኖራለን ለዛኛው ቤታችን‼️

https://t.me/https_Asselfya
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ዘጠኝ وَأَنَّ ٱلْمَسَٰجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدًۭا እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ ➧በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ይህ አንቀጽ አምልኮ ለአላህ ብቻና ብቻ እንደሚገባ ከሚያመለክቱ ዋና ዋና አንቀጾች ውስጥ አንዱ ነው።አንቀጹ ላይ መስጅድ ለተባለው ከተሰጡት ትርጉምች ውስጥ በጥቂቱ ➳ሰባቱ…
➧መንዙማ
➬➬➬➬➬

እውነታው፡አደጋዎቹና መዘዞቹ

➧ክፍል አስር

➤ከዚህ ሐዲሥ እንደምንረዳው አህለል ኪታቦች ተውራት እና ኢንጂል
የወረደላቸው “የመጸሀፍቱ ባለቤቶች” ተብለው ቢጠሩም የተውራት እና የኢንጂል ዋና መልክት የሆነውን ተውሒድ በሺርክ እና በኩፍር ስለ ለወጡት አላህ መልክተኛውን (صلى الله عليه وسلم (ልኮ ወደ ሁሉ ነብዩ መንገድ እንዲመለሱ ጥሪ እንዲደረግላቸው አዘዘ።

➧ለዚያም ነው ነብዩ (ص
➲በዚህ ሀዲስ መሰረት ከምንም ነገር
በፊት እምነትን የማስተካከል ነገር ይቀደማል። ወደ አላህ መንገድ እንጣራለን የሚሉ ሁላ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ለሙኣዝ የሰጡትን ትእዛዝ፣ ሙአዝ በተግባር ያሳዩትን መንገድ ተቀብሎ ወደ ተውሒድ ጥሪ ከምንም በፊት ሊያደርግ ይገባዋል።


➳እምነቱ ያልተስተካከለ ሰው የሰራውን ያህል ቢሰራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት
የለውም። ለዚህም ማስረጃው ኢማሙ ሙስሊም የዘገቡት ታሪክ ነው። የሆኑ ሰዎች ከበስራ (ኢራቅ) አካባቢ ለሀጅ መጡ። ሶሐባው ዐብደላህ ኢብን ዑመርን (ረድየላሁ ዐንሁማ) አገኙ። ከዚያም በአካባቢያቸው ቀደርን (የአላህን ውሳኔ) የሚያስተባብሉ ሰዎች እንዳሉ ነገሯቸው።

➧በዚህን ጊዜ ኢብኑ ዑመር “ንገሯቸው እኔም ከነሱ አይደለሁም፣ እነሱም ከእኔ አይሉም። በቀደር እስከሚምኑ ድረስ በአላህ መንገድ ላይ የኡሁድ ተራራን የሚያክል ወርቅ ቢሰጡ አላህ አይቀበላቸውም” በማለት መለሱላቸው።

➲ይህ ታሪክ የሚያስረዳን እምነት ሳይስተካከል የተሰራ ስራ የኡሁድ ተራራን የሚያክል ወርቅ በአላህ መንገድ ላይ ቢለግሱ እንኳን ተቀባይነት እንደሌለው ነው። ለዚህም ነው ከምንም በፊት እምነትን፣ አቂዳን፣ ተውሒድን ማስተካከል ግድ የሆነበት
ምክንያት። መልካምን ነገር ሌላ መልካም ነገር ይበልጠዋል።

➳የመልካም ነገሮች ሁሉ ቁንጮ
ተውሒድ እምነትን ማስተካከል ስለሆነ የመጀመሪያው ጥሪ የተደረገው በዚህ ጉዳይ ላይ ነው። ከዚያም ነብዩ (صلى الله عليه وسلم” (ይሄን እሺ ካሉህ” በማለት ወደ ሁለተኛው መልካም ትእዛዝ
ጠቆሙ። መልካም ስራዎች ሁሉ የሚገነቡት ተውሒድ የሚባለው ታላቁ መሰረት ሲስተካከል ነው::


➧ለዚያም ነው “የመጀመሪያ የምትጠራቸው ከአላህ በስተቀር (እውነተኛ) አምላክ እንደሌለ እና እኔም የአላህ መልክተኛ መሆኔን እንዲመሰክሩ” በሌላ ዘገባ “አላህን በብቸኝነት በአምልኮ እስኪነጥሉት ድረስ” የሚል ነብያዊ ተእዛዝ ለሙአዝ የተላለፈው። እሱም እንደታዘዘው የፈጸመው።

✍ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል◉◉◉◉

📚መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል{ሀፊዘሁሏህ} የተወሰደ

📖አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል።

➤ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
▪️የአርበኢን ሀዲስ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖➖

➰ክፍል ②➰
〰〰〰〰

➡️ ሀዲስ ቁጥር ሁለት

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

የተሀረከ የኪታቡን pdf ለማግኘት
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/4484
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/4484
عن عبدالله بن مسعود رضي الله عنه:

قال رسول اللهﷺ :

أوتِرُوا يا أهلَ القرآنِ، إنَّ اللهَ وِتْرٌ يُحبُّ الوِتْرَ
-
📚الألباني صحيح الجامع ٢٥٣٨
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እውቀት ብርሃን ነው

የዲን እውቀት አላህ በመረጣቸው ባሮቹ ልብ ውስጥ የሚያፈሰው ብርሃን ነው። ከዚህ ብርሃን ቀልቡን ያራቀ በጨለማዎች ውስጥ ይንከራተታል።

ዲናችንን ተግተን እንማር
https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
اللهمَّ بعلْمِك الغيبِ، وقدْرتِك على الخلقِ أحْيِني ما علمتَ الحياةَ خيرًا لي، وتوفَّني إذا علِمْتَ الوفاةَ خيرًا لي.
وَقَالَ -صلى الله وسلم-: « أَقْرَبُ مَا يَكُوْنُ الرَّبُّ مِنَ الْعَبْدِ فِيْ جَوْفِ اللَّيْلِ اْلآخِرِ فَإِنِ اسْتَطَعْتَ أَنْ تَكُوْنَ مِمَّنْ يَذْكُرُ اللهَ فِيْ تِلْكَ السَّاعَةِ فَكُنْ »

ነቢዩ (ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-

▪️ ‹‹አላህ ለባሪያው ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ከመጨረሻው የሌሊቱ ክፍል ላይ ነው፡፡ በዚያ ወቅት አላህን ከሚያወሱት ለመሆን ከቻልክ ሁን፡‼️’

وَقَالَ -صلى الله وسلم-: « أَقْرَبُ مَا يَكُوْنُ الْعَبْدُ مِنْ رَبِّهِ وَهُوَ سَاجِدٌ فَأَكْثِرُوا الدُّعَاءَ »

↪️የአላህ መልዕክተኛ (ሰለሏሁአለይሂ ወሰለን) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሰውየው ለአላህ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ነው፡፡ (ሱጁድ ላይ) ዱዓ አብዙ፡፡›› ’
الصلاة على النبي ﷺ بصوت جميل يريح النفس ويسعد القلب || #هيثم_الدخين
هيثم الدخين - Haithm Aldokhin
✅የጁሙዓ ቀን ሱናዎች
〰〰〰〰〰〰〰〰
①) ገላን መታጠብ
②) ሲዋክ መጠቀም
③) ጥሩ ልብስ መልበስ
④) ሱረቱል ከህፍን መቅራት
⑤) ሽቶ መቀባት (ለወንዶች)
⑥) ሑጥባ በጥሞና ማዳመጥ
⑦) በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ
⑧) በነብዩ ﷺ ላይ ሶላትና ሰለዋት ማብዛት
⑨) ዱአ ተቀባይነት ያለበትን ሰአት ስላለ መጠባበቅ
ኹጥባ_በሙስሊም ህይዎት ላይ የተዉሂድ ቦታ
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም
✅ቆየት ካሉ የጁሙዓ ኹጥባ መካከል ርዕስ👇
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🇸🇦 በሙስሊም ህይዎት ዉስጥ የተዉሂድ ቦታ!!

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም አላህ ባለበት ይጠብቀዉ!!

➲የሱ ኹጥባ እና ትምህርቶች ከታች ባለዉ ሊንክ ያገኙታል ይቀላቀሉ!👇

t.me/abu_reyyis_arreyyis/3192
t.me/abu_reyyis_arreyyis/3192
↪️የሙእሚኖች መሪ የሆነው ዑመር ኢብኒ ኸጣብ እንዲህ አለ፦
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
📚 “የሆነ ቀን ከአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀምጠን እያለ፡ በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው፥ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰ፥ የመንገደኛ ምልክት የማይታይበት፥ ከኛ ውስጥም ማንም የማያውቀው ሰውዬ ብቅ አለና እነብዩ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀመጠ። ጉልበቱን ከጉልበታቸው ጋር አገጣጠመ፥ መዳፉንም ታፋው ላይ አስቀመጠ። ከዛም አንተ ሙሓመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ አላቸው።

↪️ የአላህ
መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ኢስላም ማለት ፦ በእውነት የሚመለክ ጌታ አንድ አላህ ብቻ ነው ብሎ እና ሙሓመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣ ሶላትን በወቅቱና ቀጣይነት ባለው መልኩ መስገድ፣ ዘካን ማውጣት፣ ረመዳንን መጾም፣ የአላህ ቤትን ከቻልን መጎብኘት።” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ዑመርም እንዲህ አለ “በሱ ተገረምን! እሳቸውን ይጠይቃል መልሶ እውነት ተናገርክ ይላቸዋል!” ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢማን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ[ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢማን ማለት ፦ በአላህ ማመን፣ በመላኢኮች ማመን፣ በመጻህፍት ማመን፣ በመልእክተኞች ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን፣ በአላህ ውሳኔ ከፋም በጀም ማመን” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢሕሳን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢሕሳን ማለት አላህን እንደምታየው አድርገህ ልታመልከው ነው፥ አንተ ባታየውም እሱ ያየሃል እና።” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ሰአቷን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ የሚያውቅ አይደለም” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ምልክቶቿን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ባርያ ጌታዋን ልትወልድ ነው፣ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ፥ እርቃናቸውን የነበሩ፥ ድሆች የነበሩ የፍየል ጠባቂዎች ህንጻ ለመስራት ሲሽቀዳደሙ ልታይ ነው።” ከዛ ቡሃላ ሰውየው ሄደና ብዙ ቆየን። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “አንተ ዑመር ሆይ!ጠያቂው ማን እንደሆነ ታውቃለህን?” ዑመርም “አላህና መልእክተኛው ያወቁ ናቸው።” በማለት መለሰ። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ የመጣው እኮ ጂብሪል ነው፥ ሃይማኖታቹህን ሊያስተምራቹህ መጣቹህ።

(ሙስሊም ዘግበውታል)

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
➧መንዙማ ➬➬➬➬➬ እውነታው፡አደጋዎቹና መዘዞቹ ➧ክፍል አስር ➤ከዚህ ሐዲሥ እንደምንረዳው አህለል ኪታቦች ተውራት እና ኢንጂል የወረደላቸው “የመጸሀፍቱ ባለቤቶች” ተብለው ቢጠሩም የተውራት እና የኢንጂል ዋና መልክት የሆነውን ተውሒድ በሺርክ እና በኩፍር ስለ ለወጡት አላህ መልክተኛውን (صلى الله عليه وسلم (ልኮ ወደ ሁሉ ነብዩ መንገድ እንዲመለሱ ጥሪ እንዲደረግላቸው አዘዘ። …
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ➀➀

➣ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ስልጣናቸው እና ደረጃቸው ምን ደረስ ነው?
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ባልደረባዎቻቸውን “እኔ ባርያ ነኝ። ስለዚህ የአላህ ባርያ እና መልክተኛው በሉ” ብለዋል። ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (የአላህ ባርያ እና መልክተኛ
መሆናቸውን አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡



سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡ ሱረቱል ኢስራዕ 1

➧መልክተኛው ስለመሆናቸውም እንዲህ ይላል፡

مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ ۖ
“ሙሐመድ የአላህ መልክተኛ ነው።” [አልፈትሕ፡ 29]

◆የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم (የሩቅን አያውቁም። አላህ እንዲህ ይላል፡

قُل لَّا أَقُولُ لَكُمْ عِندِي خَزَائِنُ اللَّهِ وَلَا أَعْلَمُ الْغَيْبَ وَلَا أَقُولُ لَكُمْ إِنِّي مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰ إِلَيَّ ۚ

“ለእናንተ የአላህግምጃቤቶችእኔ ዘንድናቸውአልልም። ሩቅንም አላውቅም። ለእናንተም እኔ መልአክነኝ አልልም።ወደእኔ የሚወርድልኝን እንጅሌላን አልከተልም” በላቸው።” [አል-አንኣም50]

የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم (ከሰዎች ልቦና ውስጥ መቀናትን (ሂዳያን) ማስረፅ አይችሉም። አላህ እንዲህ ይላል፡-

إِنَّكَ لَا تَهْدِي مَنْ أَحْبَبْتَ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ يَهْدِي مَن يَشَاءُ ۚ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ

አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን ዐዋቂ ነው፡፡አል ቀሶስ 56

የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم (እራሳቸውን ከጉዳት መጠበቅ አይችሉም። አላህ እንዲህ ይላል፡

وَإِن يَمْسَسْكَ اللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُ إِلَّا هُوَ ۖ وَإِن يَمْسَسْكَ بِخَيْرٍ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

አላህም በጉዳት ቢነካህ ለእርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም፡፡ በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡አልአንአም 17

➧ሰው ናቸው፡- አንዳንድ አላዋቂዎች እንደሚሉት ብርሃን ወይንም ከብርሀን የተፈጠሩ አይደሉም። ከአባታቸው ዐብደላህ እና ከእናታቸው አሚና የተወለዱ ሰው ናቸው።አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ አልተወለደም።

➲ይታመማሉ፡- ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ብዙ ጊዜ ታመው የነበሩባቸው ክስተቶች ነበሩ።ሞት አፋፍ ላይ ሆነውም ከባድ ትኩሳት በሽታ አጋጥሟቸው ነበር። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን ግን የታመመን ሁሉ የሚያድነው እሱ ብቻ ነው።

➲ይረሳሉ፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (እንዲህ ይላሉ “እናንተ እንደምትረሱት እኔም እረሳለሁ። ስረሳ አስታወሱኝ።” አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ ግን ምንንም ነገር አይረሳም።

➳ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉✍

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
ፕሮፍይላቹ ላይ በሚፃፉ ፅሁፎች

❶ ሀዘንን ምትገልፁ

➩ ሀዘንን ማብዛት በሸሪአ አልታዘዘም።

ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ እንዲህ ይላሉ:

የአላህ እንድናዝን አላዘዘንም መልእክተኛውም ቢሆን እንድናዝን አላዘዙንም። እንዲያውም አላህ ቁርአን ላይ በተለያዩ ቦታዎች ከማዘን ከልክሎናል በዲን ጉዳይ የተንጠለጠለ ቢሆን እንኳን

❷ በግዜ ምታማርሩና ዘመንን ምትሰድቡ

➩ በሀዲስ ላይ እንደመጣው ዘመንን ከመስደብ ተከልክሏል። በዘመን ላይ ሚከናወኑ ነገራቶች ሁሉ አላህ ነው ሚያከናውናቸው እና ማንን ነው ምትሳደቡት?

❸ በህይወታችሁ መማረራችሁን ምትገልፁ

➩ በመልካሙም በመጥፎውም በሁሉም የአላህ ውሳኔ ማመን ግዴታ ነው።

➩በቀደር ማማረር ደግሞ አይፈቀድም

❹ በተሰጣችሁ ነገር ማነስ የምትማረሩ

➩ ለተሰጣችሁ አመስግናችሁ በነበረ በተጨመረላችሁ ነበረ። ከስጦታም ደግሞ እስልምና በቂያችሁ ነበር

❺ ስለደረሰባችሁ በደል የምታወሩ

➩ ስሞታውን ለአላህ ብታቀርቡ በተቀበላችሁ ነበር። የተበዳይ ዱአ ተቀባይነት አላት። ሰዎች ግን ከንፈር ከመምጠጥ አያልፉም

❻ መጥፎ እድል እንዳላችሁ ምታወሩ

➩አላህ በጠረጠራችሁት ቦታ እንደሆነ በሀዲስ መነገሩን አስታውሱ።

❼ ተስፍ መቁረጣችሁን የምትገልፁ

➩በአላህ ላይ ተስፍ መቁረጥ ከከባባድ ወንጀሎች እንደሚመደብ እወቁ

❽ በሰዎች ላይ ምትቀልዱ

➩በቁርአን ላይ ከፊላቹ በከፊሉ አያሹፋ መባሉን አስታውሱ

❾ በዲን ጉዳይ ምትቀልዱ

➩ይህ ተግባር ኩፍር ላይ እንደሚያደርስ እወቁ

❿ ስለማይመለከትህ ጉዳይ ምትለጥፍ

➩የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ማለታቸውን አስታውስ

"ከአንድ ሰው እስልምና ማማር ማይመለከተውን ነገር መተው ነው"

ታዲያ እስልምናችሁ እንዲያምር አትፈልጉም?

❶❶ ብቸኝነታቹን ምትገልፁ

➩ ሙስሊሙ ወንድማቹ መሆኑን አትዘንጉ

❶❷ ጭንቃችሁን ምታወሩ

➩ ይህን ለመለጠፍ በወሰደባቹ ሰአት ዚክር ወይ ዱአ አርጋችሁ ቢሆን ጭንቁ ተወግዶላችሁ ነበር

❶❸ ረዳት አጣን የምትሉ

➩ የአላህ እርዳታ ይሻላችሇል። ስሞታውን ለአላህ ብታቀርቡ በሰማቹ ነበረ።

❶❹ ጥሩ ተስፍን የምታወሩ

➩➩ በስራችሁ ቀጥሎ➩➩
ሙሐደራ 019 ግንዛቤያችንን በተገቢው መልኩ እናስተካክል!!!
🎙 በወንድም አቡ ዒምራን
ሙሐደራ 019
➩➪➩➪➩➧

↪️ ርዕስ፦ ➘
#ግንዛቤያችንን_በተገቢው
#መልኩ_እናስተካክል!!!

✅ አግባብ ባልሆነ መልኩ የያዝናቸውን እና የተገነዘብናቸውን መርሆዎች ትክክለኛ ወደሆነው ሸሪዓዊ ግንዛቤ መመለስና ማስተካከል ይጠበቅብናል።

🎙 በወንድም አቡ ዒምራን
[ሙሐመድ መኮንን]
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
▪️💦ጠያቂ፦ አንድን ሰው ለአላህ ብሎ የወደደ ሰው "ለአላህ ብየ እወድሃለሁ" ብሎ ማሳወቅ አለበትን?
🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜
▪️💦ሸይኹል_አልባኒ፦ አዎ፡፡ ግን ለአላህ ብሎ መውደድ ዋጋው ከባድ በመሆኑ የሚከፍለው ጥቂት ነው፡፡ ለአላህ ብሎ የመውደድ ዋጋ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? እስኪ ማነው የሚያውቅ መልሱን የሚሰጠን?

▪️💦አንዱ_አድማጭ፦ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ [ሰባት አይነት ሰዎች አላህ ከሱ ጥላ ውጪ ጥላ በሌለበት (በቂያማ) ቀን ከጥላው ስር ያስጠልላቸዋል፡፡] ከነዚህም ውስጥ [ለአላህ ብለው ተዋደው በዚያም ላይ ተገናኝተው በዚያው ላይ የተለያዩ ናቸው፡፡]

▪️💦ሸይኹል_አልባኒ፦ እሱ በራሱ ትክክለኛ ንግግር ነው፡፡ ግን የጥያቄው መልስ አይደለም፡፡ አንተ የጠቀስከው ነገር ሙሉ ለሙሉ ሳይሆን ቀረብ ባለ መልኩ ለአላህ ብሎ መውደድ ምን እንደሆነ የሚገልፅ ነው፡፡ የኔ ጥያቄ ግን "ሁለት ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሰዎች አንዱ ለሌላው ሊከፍለው የሚገባው ዋጋ ምንድን ነው?" የሚል ነው፡፡ እንጂ የአኺራ ሽልማቱን (አጅሩን) ማለቴ አይደለም፡፡ ስለዚህ ማለት የፈለግኩት ሁለት ሰዎች እውነት መዋደዳቸው ለአላህ እንደሆነ በተግባር የሚያመላክተው ምንድን ነው የሚል ነው፡፡

▪️💦 ሁለት ሰዎች ሊዋደዱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ውዴታቸው እውነተኛ ያልሆነ እንዲሁ ቅርፃዊ ሊሆን ይችላል፡፡ እውነተኛ እንደሆነ የሚያመላክተው ምንድነው?

▪️💦አንዱ_አድማጭ፦ ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ መውደዱ፡፡

▪️💦ሸይኹል_አልባኒ፦ ይሄ የመውደድ ነፀብራቅ ነው ወይም ከመውደድ ነፀብራቆች አንዱ ነው፡፡

▪️💦አንዱ_አድማጭ፦ የላቀው ጌታችን እንዲህ ብሏል፡ {"አላህን የምትወዱ ከሆናችሁ መልእክተኛውን ተከተሉ፡፡ አላህ ይወዳችኋልና" በላቸው፡፡}

▪️💦ሸይኹል_አልባኒ፦ ይሄ ትክክለኛ መልስ ነው- ግን ለዚህ ሳይሆን ለሌላ ጥያቄ!

▪️💦አንዱ_አድማጭ፦ ምናልባት መልሱ በዚህ ሶሒሕ ሐዲስ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡ [ሶስት ነገሮች በውስጡ ያሉበት የኢማን ጥፍጥና አግኝቷል...] ከነዚህ ውስጥ [ለአላህ ብለው የተዋደዱ ናቸው፡፡]

▪️💦ሸይኹል_አልባኒ፦ ይሄ ለአላህ ብሎ መውደድ የሚያስከትለው ውጤት ነው- በልቡ የሚያገኘው ጥፍጥና!

▪️💦አንዱ_አድማጭ፦ የላቀው ጌታችን እንዲህ ብሏል፡ {በዘመን እምላለሁ! በእርግጥ ሰው ሁሉ በክስረት ውስጥ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት፤ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡}

▪️💦ሸይኹል_አልባኒ፦ በጣም ጥሩ ብለሃል! ይህ ነው ትክክለኛው መልስ!! ይህም ሲብራራ እኔ አንተን እውነት ለአላህ ብየ የምወድህ ከሆነ በምክር ልከተልህ ይገባል፡፡ አንተም እንደዚያው፡፡ ለዚህም ነው "ለአላህ ብለን እንዋደዳለን" በሚሉ ሰዎች ዘንድ ይሄ አንዱ ሌላውን በምክር መከተል በጣም ውስን የሆነው፡፡ ምናልባት መዋደዳቸው ከፊል እውነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ግን ሙሉእ አይደለም፡፡ ለምን ቢባል አንዳቸው የሌላውን ስሜት ይጠብቃልና፡፡ "እውነቱን ስነግረው ቢቆጣስ፣ ቢሸሽስ፣... ወዘተ" እያለ ሐቅን ሳያስተላልፍ ይቀራል፡፡

▪️💦 ስለዚህ ለአላህ ብሎ መውደድ ዋጋው አንዳችን ለሌላው በምክር ኢኽላስ ሊኖረው ነው- እውነተኛ መካሪ ሊሆን፡፡ ሁሌም በመልካም ሊያዘው ከመጥፎም ሊከለክለው ይገባል፡፡ ወዳጅ ለሚወደው ከጥላው የበለጠ በምክር የሚከተለው ሊሆን ይገባል ማለት ነው፡፡ ሶሐቦች ተገናኝተው ሲለያዩ አንዱ ለሌላው ይችን ምእራፍ ይቀሩ እንደነበር የሚያመላክተው ሶሒሕ ማስረጃ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡

(አልሓዊ ሚን ፈተወል አልባኒ፡ 165-166)
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
➲ይችን አያ የሚያስተነትን አዕምሮ ያለው ሰው እንደት አላህን ያመፃል?


كَيْفَ تَكْفُرُونَ بِاللَّهِ وَكُنتُمْ أَمْوَاتًا فَأَحْيَاكُمْ ۖ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

ሙታን የነበራችሁ ስትኾኑ ሕያው ያደረጋችሁ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ሲኾን ከዚያም ወደርሱ የምትመለሱ ስትኾኑ በአላህ እንዴት ትክዳለችሁ!

➛አላህ ባማረውና ውብ በሆነው ቃሉ ልባችንን ያርጥብልን! የእኛ ነገር ያሳዝናል
↩️عن Ř­ŮŘ°ŮŽŮŠŮ’فٮةُ ﺭﺿ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ سَمِعْتُ النَّبِيَّ  يَقُولُ : [ لَا يَدْخُلُ الْجَنَّةَ Ů‚ŮŽŘŞŮ‘ŮŽŘ§ŘŞŮŒ]
(رواه البخاري وغيره)

▪️ሁዘይፋ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁኝ (ወሬ አመላላሽ ጀነትን አይገባም)

(ቡኻሪና ሌሎችም ዘግበውታል)


↩️ﻗﺎﻝ ﺭﺟﻞ ﻟﻮﻫﺐ ﺑﻦ ﻣﻨﺒﻪ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ: ﺇﻥ ﻓﻼﻧﺎ ﺷﺘﻤﻚ .. ﻗﺎﻝ:ﺃﻣﺎ ﻭﺟﺪ ﺍﻟﺸﻴﻄﺎﻥ ﺭﺳﻮﻻ ﻏﻴﺮﻙ ]

▪️አንድ ሰው ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ ዘንድ መጣና፦
እከሌ ሰድቦሀል አለው… ሸይጧን ካንተ ውጭ ሌላ የሚልከው መልእክተኛ አጣእንዴ አለው።)

↩️[ﺟﺎﺀ ﺭﺟﻞ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺸﺎﻓﻌﻲ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ: ﻓﻘﺎﻝ ﻟﻪ ﻓﻼﻥ ﻳﺬﻛﺮﻙ ﺑﺴﻮﺀ .. ﻓﺄﺟﺎﺑﻪ: ﺇﺫﺍ ﺻﺪﻗﺖ ﻓﺄﻧﺖ ﻧﻤﺎﻡ ، ﻭﺇﺫﺍ ﻛﺬﺑﺖ ﻓﺄﻧﺖﻓﺎﺳﻖ . ﻓﺨﺠﻞ ﻭﺍﻧﺼﺮﻑ ]

▪️አንድ ሰው ኢማም አሻፊኢ ዘንድ መጣና እከሌ በመጥፎ ያነሳሀል አላቸው…እውነትህን ከሆነ አንተ ወሬ አመላላሽነህ ዋሽተህ ከሆነ ፋሲቅ ነህ አሉት። ሰውየውም አፍሮ ሄደ።
https://t.me/https_Asselfya
▪️ሱፍያን አስሰውርይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አለ።

✅ ውስጥህን (ቀልብህን) አስተካክል አላህ ውጭህ ያስተካክለዋል። አደራህ ንግግር አታብዛ። ንግግር መቀነስ ቀልብ እንዲረጥብ ያደርጋል።
📚 حلية الأولياء (٨٢/٧)
💦የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ።

◾️ከዚክሮች ሁሉ በላጩ 👉 لا إله إلا الله ነው
◾️ከዱአዎች ሁሉ በላጩ 👉 الحمد لله ነው

📚(ቲርሚዚ ዘግቦታል)
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌۭ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍۢ ۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرٌۢ بِمَا تَعْمَلُونَ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡
================================