💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.68K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
(وَلَا یَغۡتَب بَّعۡضُكُم بَعۡضًاۚ أَیُحِبُّ أَحَدُكُمۡ أَن یَأۡكُلَ لَحۡمَ أَخِیهِ مَیۡتࣰا فَكَرِهۡتُمُوهُۚ)

ከፊላችሁ ከፊሉን አይማ።አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞቶ ሆኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱንም እንደጠላችሁት ሃሜቱንም ጥሉት ብሏል የላቀው አላህ።
የሞተ ሆኖ ሰጋውን መብላትን እርም እንዳደረገባችሁ በህይወት እያለ እሱን ማማትንም እርም አድርጎባቹሃል።ሞቶ ስጋውን መብላት እንደጠላችሁት በህይወት እያለ የሱን መታማትንም ጥሉ።(ተፈሲሩ ጠበሪይ)

ሰውን የሚያማ ሰውን አላህ በሰዎች የሚጠላ እንዲሆን በማድረግ እንደሚፈትነው አመላካች ነውም ይላሉ።ምክነያቱም ሃሜት ተናጋሪ ሃሳቡ የሚያማውን ሰው ሰዎች እንዲጠሉት በማሰብ ስለሆነ ሀሳቡ ተመልሶ በራሱ ላይ ተፈፃሚ ሆኖ ያገኘዋል።

#ማስታወሻ
🔖ሼኸ ሷሊህ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

አንድ ሙስሊም ከሌሊት ሶላት ቁጥሩ ቢያንስም እንኳን ሁሌም የሚዘወትርበት የሆነ የተወሰነ ድርሻ ሊኖረው ይገባል

📚الملخص الفقهي(صـ ٩٣)
=
         t.me/https_Asselfya
👍9
«ከምላስህ ይልቅ ተግባር ማንነትን ይገልፃል!!

«እውነተኛ ባልሆነ ማንነታችን ሠዎች ዘንድ መልካም መስሎ ለመታየት ከመጣር ይልቅ እውነተኛ ማንነትን አውቆ ለለውጥ መንቀሳቀስ ምንም ጊዜው ቢረዝም ውጤቱ ግን ታላቅ ነው!!!
🔖ኢማም አላማህ አል-ሰአዲይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ፡-

አላህ ለሙእሚን ባርያ ከለገሰው ታላቅ ፀጋ መካከል አንዱ ምርጥ አማኝ ጓደኞችን መስጠቱ ነው።ከአንድ ሰው ቅጣቶች መካከል በክፉ ጓደኞች መፈተኑ ነው። የምርጥ አማኝ  ጓደኝነት ሰውዬውን ወደ ከፍተኛ ደረጃዎች ወደ ጀነት ለማድረስ ምክንያት ሲሆን የመጥፎ ሰው ጓደኝነት ደግሞ ጥሩ ሰዎችን ወደ አዘቅት ወደ እሳት ለማውረድ ምክንያት ነውና።የምርጥ ሰዎች ጓደኝነት ትልቅ ስነምግባር ላይ እና ጠቃሚ እውቀት ላይ ያደርስሃል። የክፉ ሰዎች ጓደኝነት ደግሞ እነዚህን ሁሉ ያሳጣሃልና።

📚[شرح جوامع الأخبار) للسعدي(189)] .

t.me/https_Asselfya
Forwarded from ስለ ቀልባችን
~ከ ወንጀል ዉጤቶች መካከል አንዱ«ስኬትን ማጣት ነው» ይላሉ ኢብኑ አል-ቀይም ረሒመሁላህ፡፡

ወንጀል ባንተ እና በጌታ መካከል እክል ነው፤ ጋሬጣ ነው፣ ግርዶ ነው፡፡ለምነህ ለዱዓህ ምላሽ አታገኝም፣ ሠርተህ ከድህነት አትወጣም፣ አስበህ አይሳካልህም፣ ተወዳድረህ ትሸነፋለህ፣ ለሥራና ለትህምርት ተፈትነህ ትወድቃለህ፣ ምኞትህ አይሰምርልህም፣ ያቀድከው አይሆንልህም፡፡ ምክንያቱም ነገሮች መንስኤና ዉጤት አላቸውና፡፡

የወንጀል ባለቤት ከሆንክ እቆጥባለሁ ብትልም አይሆንልህም፣ ወንጀል ብል ነው፡፡ ኃጢኣት ተምች ነው፤ ኃጢኣት ቫይረስ ነው በልቶ ይጨርስሃል፤ አተንም ፀጋህንም ይበላል፡፡ የኃጢኣት ዉጤቱ በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ አየርን ይለውጣል፣ ቤትን ያበላሻል፣ ትዳርን ያደፍርሳል።

ወንጀልህ ሲበዛ ፊትህ ይጠቁራል፣ ኑርህ ይጠፋል፣ ሞገስህ ይገፈፋል፡፡እናም ለአንዳንንድ ነገሮች ጓጉተህ፣ አንዳንድ ነገሮችን ሞክረህ …. አልሳካ  ያለህ እንደሆነ መለስ ብለህ ራስህን ፈትሽ፡፡ ከስኬትህ ያገደ ጋሬጣ ሊኖር ይችላልና ያንን አስወግድ፡፡ ከራስህ ጀምር። ከማሳበብህ በፊት ሁኔታህን መርምር።

አላህ ይርዳን!
👍1
‏قال الإمام #ابن_القيم - رحمه الله - :

اليقين أفضل مواهب الربِّ لعبدِه؛ ولا تثبت قدم الرِّضا إلَّا على درجة اليقين.

[ مفتاح دار السّعادة (ص١٥٥) ]
🔖ኢማን ያልቃል ያለን ግንዛቤ በየጊዜዉ እየሟሸሸ ሊሄድ ይችላል። ከግዜ ርዝመት ጋር የልብ ድርቀት ሊገጥም ይችላል። ኢማናችን ልክ እንደ ልብስ ሊያልቅ ይችላል ።

عن عبد الله بن عمرو  قال: قال رسول الله ﷺ: إن الإيمان ليخلق في جوف أحدكم كما يخلق الثوب، فاسألوا الله أن يجدد الإيمان في قلوبكم

📚 [رواه الطبراني في المعجم الكبير: ،وصححه الألبانيفي صحيح الجامع:

~የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል። 

~በአንዳችሁ ቀልብ ዉስጥ ኢማን ያልቃል።
ልክ ልብስ እንደሚያልቀዉ ኢማን ያልቃል ።አላህ ኢማናችሁን እንዳዲስላችሁ ለምኑት ።

~በየግዜዉ  ዲናችንን ማደስ አንድ ጊዜ ተረድቻለሁ ብለን አለመዘናጋት ለማስፋት መታገል አለብን።

🔖ሼኽ ኢስላም አሕመድ ኢብኑ ተይሚያ ሰዎች ሲያወዲሷቸዉ እንዲህ ይላሉ፦
~በአላህ ይሁንብኝ አሁን ድረስ እስላሜን በየጊዜዉ አድሳለሁ በሁሉም ወቅት ገናየተሟላን የሆነ እስላምን ሰልሜለሁ ማለት አልችልም
من أقوال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله : (وأنا أحلل كل مسلم . وأنا أحب الخير للمسلمين بل لجميع الناس . والله إني إلى الآن أجدد إسلامي كل وقت وماأسلمت بعد إسلاماً جيدا 

~ድናቸዉን ለመጠበቅ ግንዛቤቸዉን ለማስፋት ወደ አላህ ያላቸዉን ቅርበት ለመጨመር ። የበለጥ እታገላለሁ እያሉ ነዉ
~
t.me/https_Asselfya
👍1
نسائمُ القرآن عليلةٌ، تزيحُ الهموم وتسكنُ النّفس وتريح الرّوح.
🔖ለምን እንደለበሽዉ ቢገባቸዉ ኖሮ፤ ሒጃብሽ^ን ከራስሽ ላይ እንድታወልቂ ባዘዙበት አፋቸዉ ያለ ሒጃብ መግባት ክልክል መሆኑን በየ-ተቋሙ እየፃፉ ይለጥፉ ነበር።

t.me/https_Asselfya
👍5
‏قال الإمام #ابن_رجب - رحمه الله - :

فلا سعادة للعبد ولا فلاح بِدون ذِكْر الله
والصَّلاة؛ فلذلك حرَّم عليه الاشتغال بِكُلِّ
ما صدَّ عن ذلك.


[ مجموع الرسائل (٢٧٦/١) ]
አንድ ሰው ጌታዬ ሆይ " እኔ  ጥሪህን ልቀበል፣ መልስ ልሰጥ፣ በትእዛዝህ ስር ልሆን፣ ከከለከልከኝ ነገር ራሴን ላርቅ አንግቻለሁ" ካለ በውሎው ላይ ቃሉን ማክበር አለበት።ንግግሩና ስራው መመሳሰል አለበት። ከዚህ በተቃራኒ ከሆነ ስራው ንግግሩን ዋሽቷል።ስራውን አበላሽቷል። ለዚህ ሰው ሊመለስለት ዘንድ ተሰፋ አይደረግም።

ልክ  ሃራም በሆነ ገንዘብ ሀጅ እንዳደረገ ሰው ነው። ሃጅ ሄዶ "ለበይክ(አቤት) አላሁማ ለበይክ" ብሎ ቢል "ምንም አቤት የለህም" እንደሚባልለት

رسائل ابن رجب (102 / 1)
በርህን ዘግተህ ከፈጣሪህ ጋር ስትጣላ

በርህን ቆልፈሃል። መጋረጃህን ጣል አድርገሃል። ማንም እንደማያይህ አረጋግጠህ ስልክህን ከፈትክ። ከሰዎች አይን ተሸሸግህ፤ ነገር ግን ከዓለማቱ ጌታ እይታ የት ልትሸሸግ ነው?አንተ ያኔ ብቻህን ሆነህ ወንጀል ላይ ስትወድቅ፣ አላህ እኮ ያይሃል!ሰዎችን ፈርተህ፣ የአላህን ክብር ግን አቃለልክ? ሰዎች እንዳያዩህ ጥንቃቄ አደረግህ፤ ነገር ግን "አላህ ያየኛል" የሚለው እውነት ልብህን አልረበሸውም?

ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ አንድ አስፈሪ ጊዜ ነግረውናል፡-
የቂያማ ቀን ተራራ የሚያክሉ መልካም ስራዎችን የያዙ ሰዎች ይመጣሉ። ነገር ግን አላህ ስራቸውን እንደ ብናኝ ይበትንባቸዋል። ለምን?
«እነሱ በሰዎች ፊት አላህን የሚፈሩ ሆነው ይታያሉ፤ ነገር ግን ብቻቸውን ሲሆኑ የአላህን ድንበር ይጥሳሉ!» ይሉናል ነብያችን።

ወንድሜ ሆይ!
ዛሬ በጨለማና በድብቅ የምትሰራው ወንጀል፣ ነገ በለሊት ጨለማ ቀብር ውስጥ ብቻህን ስትሆን አብሮህ የሚቀበረው እሱ ነው።
☞ያ የተመለከትከው ሀራም ምስል፣
☞ያ የተፃፃፍከው ቆሻሻ መልእክት፣
☞ያ የሰማኸው ወንጀል...
ነገ በአላህ ፊት ቀርበህ፣ ምላስህ ታሽጎ እጅና እግርህ ሲመሰክሩብህ ምን ልትመልስ ነው?

ሞት ቀጠሮ የለውም። ልክ ያን የድብቅ ወንጀል እየፈፀምክ እያለ ነፍስህ ብትወጣስ? በዚያው አስቀያሚ ሁኔታ ጌታህን መገናኘት ትችላለህን?ዛሬ ማንም አላየኝም ብለህ አትታለል። የድብቅ ወንጀል የውስጥ ማንነትህን ይቦረቡራል፣ ከአላህ ጋር ያጣላሃል፣ መጨረሻህንም ያበላሻል።አሁኑኑ ተመለስ! በሩ ሳይዘጋ፣ ነፍስህ ሳትወጣ ተመለስ። አላህ ያያል... አላህ ያውቃል!

t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
"እንደው እርስ በርስ አትቀባበሩም ብዬ ባልፈራ ኖሮ የቀብርን ቅጣት እንዲያሰማችሁ አላህን እጠይቀው ነበር።"
«لولا أن لا تدافنوا لدعوتُ اللهَ عزَّ وجلَّ أن يُسمِعَكم  من عذابِ القبرِ  ما أسمعني»
رواه مسلم.
ረሱል صلي الله عليه وسلم

ብልጥ ሰወ ለዚህ አስፍሪ ቦታ ራሱን ያዘጋጃል።

#ማስታወሻ
ከሰዎች ጋር አውንታዊ መስተጋብር እንዲኖርህ ምክር አታብዛስህተታቸውን ዘውትር አታንሳ።

~
~ሀዋላ የምትፈልጉ በተሰቦቼ አናግሩን

በታማኝነት እንልካለን።

@Umu_Abdella_t
ወደ ትዳር የምትገቡ ጥንዶች የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ ከማድረግ አትዘናጉ። በተለይ ዐረብ አገር ያላችሁ ወገኖች ቸልተኝነት ከባድ ዋጋ እንዳይስከፍላችሁ ጥንቃቄ አድርጉ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
«በጥበቡ አንድን በር ይዘጋና፤በእዝነቱ ሺህ በርን ይከፍትልሃል!!

የኛ ጌታ
👍13