💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.49K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ጥሩ ጓደኛ ከራስህ የበለጠ ላንተ መልካም ነው!

ከዛች በጎንህ ካለችው ነፍስህ ምክንያቱም 
ነፍስ በመጥፎ አዛዥ ናትና!!

ጥሩ ጓደኛ ደግሞ በጥሩ እንጅ አያዝህም
አሏህ ሆይ ጥሩዎችን  ጓደኞችን ወፍቀን!!


t.me/abuUseyminabdurehman
👉አሏህ ሆይ! አፈጣጠራችንን እንዳሳመርከው ባህሪያችንንም አሳምርልን መልካሞች አድርገን!!
"اللهم اجعل حبك والسعي في رضاك أحب إلينا من الدنيا وما فيها ".
➰ሴቶች ሶስት አይነት ናቸው ይላል ዑመር ቢን ኸጧብ رضي الله عنه

✍️1አንደኛዋ- ገራገር፣ ምቹ፣ ቁጥብና ጥብቅ የሆነች ሙስሊም ሴት ነኝ። አፍቃሪም፣ ተፈቃሪም፣ ማህጸነ ለምለም የሆነች ሴት።
ባሏ ሲቸገር ከጎኑ የምትቆም፣ አብሽር ያልፋል እያለች የምታጠናክር፣ ይገባሃል፣ የእጂህን ነው ያገኘኸው፣ ደግ ሆነሃል፣ ኧረ ሲያንስህ ነው በማለት በመከራው ላይ ሌላን መከራ የማትደራርብ አይነት ሴት። የዚች አይነት ሴት በጣም ጥቂት ናቸውና ማግኘቱም ከባድ ነው።


✍️2ኛዋ አይነት ሴት:
ቁጥብና ጥብቅ ሙስሊም ሴት ነች። ባይሆን ግን ልጅ ከመውለድ ያለፈ ምንም ሚና የላትም። (ይችም ለክፉ አትሰጥም።)


✍️3ኛዋ ሴት፦
አመለ ክፉ መከራና ቅማል የሆነች ሴት ነች። ከራስ ላይ የማትወርድ፣ በአንገት ላይ የተጠመጠመች ማነቆ፣ በእጅ ላይ የገባች የመከራ ካቴና፣ ራቂ ቢሏት የማትርቅ፣ አብረሽ ኑሪ ብለው ቢተዋት ሰላም የማትሰጥ፣ አላህ ፈተናን ለፈለገበት ባሪያው የሚሰጣት፣ አላህ ካልሆነ በስተቀር የማያስወግዳት አይነት የፈተና ሸክም የሆነች ሴት።

{ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይባ}


https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ያአሏህ
            አብዛልኝ ጓደኛን


አብዛልኝ እህቶቼን አንተያረህማን
በመልካም የሚያዙ ምርጥ እህቶችን
ስተቴን አራሚ በመልካም አበርታች
የሱናዋን ቆንጆ እዉቀት የቀሰመች
ለሀቅ ዘብ ቋሚ ቢደአን አንኮትኳች
አብዛ ጓደኞቼን ኢልምን አስተማሪ
ለተዉሂድ የቆሙ የሱናተማሪ

በምታዉቀዉ ነገር የምታበራታኝ
ምርጢቱን ጓደኛ ጌታየ አብዛልኝ
እህቴ አደራሽን በርቺ በድንሽ
ከጥመቶች ርቀሽ እህቴ ልይሽ
ሀቅን ተግብሪልኝ ዉደ አይዞሽ
በርትተሽ ተማሪ ከጎንሽ አለሁሽ
በማዉቀዉ ነገራት እኔአለሁልሽ
የምትለኝ እህት ያረቢ አደራ
በሱና ደምቄ ልኑር ከሷጋራ

ባወቀችዉ ነገር የማትሽኮረመም
አላዉቅም እያለች የማትል ሁልጊዜም
ምንም የማትደብቅ እዉቀቷን አካፋይ
ባወቀችዉ አስተማሪ የሆነች አብሽርባይ
ጌታየ ያብዛልኝ ስተቴን አራሚ

ሀቅን የማትደብቅ ለእዉነት ከራሚ
ዉድ ጓደኞችን አብዛልኝ ያረህማን
በሱና እንድፀና ሰበብ የምትሆን
ሰለፍያ እንስቶች አብዛ ጓደኞቼን


🖋እህታችን ነኢማ  ኡሙ ዑሰይሚን



በኢብኑ ተይሚያ ሴቶች ለሴቶች ነሲሓ ላይ የቀረበች!!

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
ሀገሬ ስገባ ?!
➖➖➖➖


➷ሀገሬ ስገባ ኒቃብ እለብሳለሁ
➷ሀገሬ ስገባ ቂርአት እቀራለሁ
➷ሀገሬ ስገባ ጠንካራ እሆናለሁ


➲ከዛ ወከዛ የስደተኞች  ምኞት ነገር ግን አሁን ብዙ እየተመቸን  በተለይ ለድን ለመማር ሁሉም ምቹ ሆኖ አንጠቀምም መሸ ዝጋ  ነጋ ክፈት ሆኗል ስራችን አላህ ይዘንልንና!!

➧ግን ይሄ ነገር አብረዉን ሲሉ የነበሩ  ሀገር ገብተዉ ተገበሩት ወይ  እንዳሉትስ ተመቻቸዉ ወይ ነዉ ጥያቄዉ??ነገር ግን  ምንም እንዳላደረጉ እንደዉም እንደማይመች የምንሰማዉ!!

➰ታድያ አንቺ ዉዷ እህቴ ሀገሬ ስገባ እያልሺ አሁን ብዙ  መስራት  መጠቀም እየቻልሺ ምነዉ እንቅልፍ አበዛሺ  ምነዉ ተዘናጋሺ  ነፃ ኢንተርኔቱ  በማይጠቅምሺ ነገር ላይ ትዘሊያለሺ!!ለምን ዲንሺ አትማሪም  አትቀሪም?እኮ ምነካሺ? አሁንም አልመሸም ተነሺ ታጠቅ ብለሺ  ተማሪ ጠንክሪ!!

✍️ጀግና እና ምርጥ ሴት ማለት!!!!

➰ጀግና ሴት ማለት ለነገ ልጆቿ የምታወርሰዉን ሸሪዓዊ እዉቀት በመሸመት ቀን ሌት የምትለፋ፤ስለ ዲኗ እንጂ ስለ ዱኒያ የማትጨነቅ፤ቤተሰቦቿን ኢልምን ተምራ የምታስተምር፤ባሏን ወደ መስጂድ የምትገፋፋ፤ኢልመ ዲንን እንዲማርና የተማረዉን ላልተማሩ እንዲያስተምር የምትገፋፋ፤የቤተሰቡ ልእልት የሆነች የዱኒያ ሂወቷን በዲን ላይ ያሳለፈች ሱመያ ናት፡፡

▪️ታላቁ አሊም ሼይኽ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፦

➲እያንንዷ ሴት ያለ ዕውቀት ሷሊህ የሚባለው ደረጃ ላይ መድረስ እንደማትችል ልታውቅ ይገባል፣ ዕውቀት ስል ሸሪዓዊ ዕውቀትን ለማለት ፈልጌ ነው።

📝ደውሩ አልመረኣህ  7

✍️
አላህ  መልካሙን ሁሉ ያግራልን
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
✍️በባልሺ ላይ አላህን ፍሪ!!

➬የእሱ ጭንቀት እና ማበሳጫ መንስኤ አትሁኝ ያ ኡኽታ ሀቁን አሟይለት በአንች ላይ ያለው የባልሽ ሀቅ ከባድ ነውና ጌታሽን በማያምፅ መልኩ ባዘዘሽ ሁሉ ታዘዥው ባልሽ ላንች ጀነትሽ ነውና ‼️

➬በትዳርሽ ላይ ማንም እንዲገባ ቦታ አትክፈችላቸው ጥንቁቅ እንስት ሁኝ‼️

➬ በማንኛውም ነገር ሶብርተኛ እጅ ቁጡ አትሁኝ ምንም ቢከፋሽ ለጌታሽ እንጅ ለሰዎች አታማክሪ የቤትሽ ጉዳይ እዛው እቤትሽ ይቅር ምንም ቢሆን ከቤት ውጭ እንዲወጣ ሰበብ አትሁኝ የቤትሽን ሚስጥር የባልሽን ሚስጥር አጥብቀሽ ያዥ ለቤተሰቦችሽ ሆነ ለምትወጃቸው ጓደኞችሽም ቢሆን ምንም ትንፍሽ እንዳትይ::

🍃ነብዩ صلى الله عليه وسلم. እንዲህ ብለዋል፦🍃

ሴት ልጅ የኢማን ጣፋጭነትን አታገኝም የባሏን መብት እስክታሟላ ድረስ።


➬ምንጭ
📚 ((صحـــيح التـــرغيـــب ~ 1939))

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
#ከመጥፎ ባህሪያት በአላህ እንጠበቃለን!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنّ Ř´ŘąŮ‘ŮŽ Ř§Ů„ناسِ Ů…نزل؊ً ŘšŮ†ŘŻ Ř§Ů„Ů„Ů‡Ů يومَ القيامةِ من تركه الناسُ اتِّقاءَ فُحشِه﴾

“ከሰዎች መጥፎ ሆኖ በትንሳዔ ዕለት አላህ ዘንድ የሚመጣው፤ áŠ¨áˆ˜áŒĽáŽ ባህሪው ለመጠንቀቅ ሲሉ ሰዎች የተዉት ሰው ነው።”

📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 2095

ጆይን፦ https://t.me/BuhariMuslimAmharic
ለትዳር ወንድ ልጂ እድሜዉ ወሳኝ ነዉ።

ለምን? ተከተሉኝ👇

ምን መሠላችሁ ሴት ትንሺ ብትሆንም ቤት ይዛ መምራት ትችላለች ወንድ ግን የመምራት ችሎታዉ ጠባብ ነዉ!


ሴቶች ብዙ ፀባዮች አሉብን ብዙ ጉድለቶች አሉብን እና ያን ፀባይ እና ጉድለት የሚሸፍን የሚችል መሆን አለበት ወንዱ!
ለዚህ ደግሞ እድሜ ወሳኝ ነዉ እድሜዉ ከፍ ካለ አእምሮዉ በሰል ስለሚል የመቻል አቅሙ ይኖረዋል።
ልጂ ከሆነ ግን አይችልም የሆነ ነገር ስታናድደዉ ስታጠፍ ምናባቷ ወዳ ፈትቼ ሌላ አገባለሁ የሚል አእምሮዉ ስላልበሰለ የልጂነት እድሜ ስላልጨረሰ ማለት ነዉ።

ለምን መሠላችሁ በዚህ ኢንተርኔት እየተጋቡ ፍች የበዛ የወንዶቹ እድሜ አለመብሰሉ ነዉ።ስልክ ካላነሳች ወይ ደሞ በሆነ ነገር ተናዳ ከተናገረችዉ ወይ ሀይድ ላይ ስትሆን ስትበሳጭበት ገና ስላልበሰለ አእምሮዉ ይችማ በስልክ እንድህ የሆነች ስንገናኝማ ትደፍኛለች ብሎ ወደ ፍች ይሮጣል። እድሜ ተለቅ ያለ ቢሆን ግን ታግሶ ያሳልፍታል እስክትበርድ።

የዛሬ ጥናት ይሄ ይመስላል እ¡¡

✍️

https://t.me/https_Asselefya1
Ar-Rahman
Ali Alhuthaifi
♦️سورة الرحمن

🎙 الشيخ الحذيفي حفظه الله.


☑️ ቁርአንን በትክክል መቅራት የፈለገ ይህንን ሸይኽ በትኩረት በተከታታይ ያድምጥ። አንዳንድ የዘመኑ ወጣት ቃሪኦች የተለያየ የሙዚቃ መሳሪያ ተጠቅመው በስቱድዮ ድምፃቸውን አሳምረው ስለቀሩ በነሱ አትሸወዱ። ድምፃቸው በጣም የሚያምር ነገር ግን መዃሪጀል ኹሩፍና ሌሎችም የተጅዊድ ህጎች በወጉ የማያውቁ እንዲሁም በግልፅ ሱናን የሚቃረኑ አሉ። እነዚህ ቃሪኦች ሺ ጊዜ ብታዳምጡ ምንም ለውጥ አታመጡም። ለማንኛውም በድምፅ ቅላፄ ብቻ አትሸወዱ።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Ali Alhuthaifi – Ar-Rahman
ኤ ወላህ እኚህ ሸይኽ በጣም ጎበዝ ናቸዉ አላህ ይጠብቃቸዉ ብዙ ብታደምጧቸዉ የአቀራር ስልት ያስተምሯችሁል ተጂዊዱ ይጠብቃሉ ረጋ ያሉም ናቸዉ።

Check out "قرأن كامل علي الحذيفي بدون نت"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.andromo.dev540689.app524446


ከፕሉስቶር ታገኛላችሁ አዉርዱ👆👆👆