💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.49K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
መታወቅን መውደድ‼

ቢሽር ኢብኑል ሃሪስ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል:–

"መታወቅን የሚወድ ሰው አላህን አለፈራም /አይፈራም/"

ወንድም እህቶቼ አንድን መልካም ስራ ስን ሰራ የ አላህን ፊት ፈልገን ሊሆን ይገባል።


አላህ የሱን ፊት ፈልገው መልካም ከሚሰሩት ያድርገን ።

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
t.me/abuUseyminabdurehman
➲አደራ ለዱአት
➭➭➭➭➭➭➭➭

➧ሀይማኖትህን የምታስተምረው ወንድሜ ሆይ፣ የምታስተምሪው እህቴ ሆይ! የገባችሁበት መንገድ ምንኛ ያማረ መንገድ ነው?!! ጌታችን (ወደ አላህ ከሚጣራ፣ መልካምንም ከሚሰራ፣ እንድሁም "እኔ ሙስሊም ነኝ" ካለ ሰው ይብለጥ ንግግሩ የማረው ማን ነው? )ይላል ፉሲለት 33

➭አላህ እሱ ካወደሳቸው መልካም ተጣሪዎች እንዲያደርገን እማፀናለሁ!

👉ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ኡስታዛችን ኢብኑ ሙነወር ተውሂድ የሁለት ሀገር ስኬት ቁልፍ በሚለው ኪታቡ ውስጥ ለዱዓቶች ከሰጠው ምክሮች ቀንጨብ አድርጌ በተከታታይ እንድፃፍላችሁ የምትፈልጉ 👍👈የዚችን ምልክት ታሳዩኛላችሁ!

የማትፈልጉ ደግሞ👎👈 የዚችን ምልክት ታሳዩኛላችሁ!


ኢንሻአላህ ፈላጊው ብዙ ከሆነ ይፃፋል

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
⇛አንዳንዴ…ጥርስህ ሳቅ አይለየውም ውስጥህ ግን ፈገግታ አያውቅም።መሳቅ ስለ ቻልክ መደሰት የምትችል የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ።አንዳንዴ«የማይከፋ ሰው»ተደርገህ በሰው ዘንድ ትሳላለህ። አንተም በሳቅህ ሁሉንም ለመከላከል ትሞክራለህ። ያኔ«ታድለህ ሁሌም ደስተኛ ነህ!»ይሉሀል ሳቅህ እምባህ መሆኑ ሳይገባቸው…።

⇛ አንዳንዴ ደስታ የሚመስል ሀዘን ከሀዘን ይከፋል። በሳቅ ለማጥፋት የሚሞክሩት ሀዘን እንደ ሞት ያስጨንቃል። ከደረሰብን ሀዘን በላይ ከሀዘናችን ጋር መሟገታችን ነው ይበልጥ የሚያሰቃየን። አንዳንዴ……


t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
➭ያኢላሂ! አንተ የመረጥክልኝን ነገር ወድጀ የምቀበል አድርገኝ!! እኔ ከወደድኩት ያንተ ምርጫ በላጭ ነውና!
سورة الفیل
Abu Useymin
☑️የምሺቱ ዉብ ቲላዋ

➧ሱረቱል ፊል በቀስታ አቀራር!

🎙በአብዱረህማንአቡ ዑሰይሚን

👉ደግ እደሩ!!

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/abuUseyminabdurehman
قال تعالى:
  ‌‌‏﴿وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ﴾.
(البقرة_45)

✍🏻قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله: ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‏من فوا،د الآية :

* ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌أنه إذا طالت أحزانك فعليك بالصبر والصلاة.
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‏ومنها : أن الأعمال الصالحة شاقة على غير الخاشعين، ولا سيما الصلاة .
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌أن تحقيق العبادة لله سبحانه وتعالى بالخشوع له مما يسهل العبادة على العبد. فكل من كان لله أخشع كان لله أطوع .

📚 تفسير القرآن الكريم  (ŮĄ / ŮĄŮŚŮĽ)
Audio
↪️ አዲስ ሙሀደራ
➖➖➖➖➖➖

♦️የሙሀደራው ርዕስ
➫➫➫➫➫➫➫➫

🌐«ሴት ልጅ በባሏ ቤት ውስጥ ያለባት ግዴታና ተጠያቂነት በሰፊው ተዳሶበታል።»

📍ሴቶች አዳምጣችሁ ወደ ተግባር ቀይሩት።

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Audio
🔊 አድስ የኪታብ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖➖

▪️ክፍል  (⓵⓹)

➧ማህበረሰብን በማስተካከልና በማነፅ ላይ የሴቶች የጎላ ሚና በተመለከተ የሚዳስስ!!

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ


https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

➲የኪታቡን pdf ለማግኘት👇
➧t.me/https_Asselefya1/6385
ጀማዓቱ ተብሊግ { 01 }
𝕬𝖇𝖚 𝖀𝖘𝖊𝖞𝖒𝖎𝖓
አደራ! ቁርኣን እንቅራ
~
በርግጠኝነት እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ ከሚርመሰመሱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁርኣን ያልቀሩ ብዙ ወገኖች ይኖራሉ። ወላሂ ሊቆጨን ይገባል። በዚህ አማራጮች በበዙበት ዘመን እንዴት ድንቁርናን አሚን ብለን ተቀብለን በጨለማ ውስጥ እንኖራለን? የትም ብንሆን ካለንበት ቦታ ሆነን መማር እንደሚቻል የሚታወቅ ነው። አላህ ባገራልን መንገድ እንማር። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን የተማረና ያስተማረው ነው" ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 5027]
ስለዚህ ያልተማርን ጊዜ ሰጥተን እንማር። የተማርን መልክቱን እንማር፣ ባወቅነው እንስራ። በየቀኑ ከጊዜያችን ውስጥ ለቁርኣን ድርሻ ይኑረን። በምንችላት መጠን ለመሐፈዝ እንሞክር። የእድሜ መግፋት ቁርኣን ከመማር አያግድም። በርካታ ሶሐቦች በጎልማሳነት ዘመናቸው ነው ቁርኣን የቀሩት። ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አል0ባድ "አንድ ሰው ከሃምሳ አመቱ በኋላ ቁርኣን ሊሐፍዝ ይችላል ወይ?" ተብለው ተጠይቀው ነበር። ምላሻቸው እንዲህ የሚል ነበር፦
"አዎ! እኔ ራሱ ከሃምሳ በኋላ ቁርኣን ከሐፈዙት ውስጥ ነኝ። ሶሐቦች - ረዲየላሁ ዐንሁ - ትልልቅ ሰዎች ሆነው ነው ኢስላም ያገኛቸው። ከመሆኑም ጋር ቁርኣንን ሐፍዘዋል።"
ስለዚህ በየትኛውም ምክንያት በልጅነቱ ቁርኣን ያልቀራ ሁሉ እራሱን አያዳክም። "በአላህ ፈቃድ እችላለሁ" ብሎ ይነሳ። ኢንሻአላህ ይችላል። አለማወቅን ታቅፈን ፈፅሞ ምቾት ሊሰማን አይገባም። ሰው እንዴት ቁርኣን ሳይቀራ እድሜውን ይፈጃል?!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
ማረኝ የኔ ጌታ…! በ ኡስታዝ መ/ድ ሲራጁ
ድምፅ፦ወንድም አቡ ሱፍያን
🖼ማረኝ ጌታየ ሆይ!!

📮ምርጥ ግጥም…

📜በ ኡስታዝ፦ሙሓመድሲራጅ አቡ ዒምራን
t.me/Muhammedsirage

🎙ድምፅ፦ወንድም አቡ ሡፍያን
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
ነጃሳው የበዛበት የቲክ ቶክ ግቢ ውስጥ የረባ ያልረባውን የምትሰሙና የምትመለከቱ ወንድሞችና እህቶች አሏህን ፍሩ ! ሁሉም ነገር አልፎ የቀብርን አፈር መንተራስ ይመጣል ፣ ይሄ ሁሉ አክትሞለት አሏህ ፊት መቆም ይከሰታል !

✍️አሏህ ነገራችንን ሁሉ ተመልካች ነው !

እዚህ መንደር እውነተኛን ደስታ ማግኘት የሚታሰብ አይደለም ። የረከሱ እርኩሳንን መመልከትና መከታተል ከአማኞች ክብር ጋር የማይሄድ ምግባር ነው ።  ነፍስን የሚያረክስ ጎጂ ልማድ ነው !

እናንተ አማኞች ሆይ ፣ የተከበራችሁ ናችሁና የረከሰውን ለሚገባው ተውት !

ወደ እምነታችን ፣ ወደ ክብራችን እንመለስ !

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/Muhammedsirage
➲ዳዒያው ሆይ! ለተውሂድ ተገቢውን ቦታ ስጥ!!
➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊

➧ክፍል አንድ

➧ጥረትህ ፍሬ ሊያፈራ ዘንድ ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ ስጥ። "የዳዕዋ አላማው ባሪያዎችን ውደተፈጠሩበት ጉዳይ ማድረስ ነው፣ ጌታችሁን ተጋሪ ሳታደርጉለት በብቸኚነት ማምለክ።" (አልፈታዋ 2/6)

➩የነብዩ صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم ትምህርት አታዛንፍ። ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ ስጥ! ነብዩ ትምህርታቸውን የጀመሩት በተውሂድ ነው። {ላ ኢላሀ ኢለላህ በሉ ትድናላችሁ} በማለት። (ሙኽተሶሩ ሲራህ፡ 142) ያጠናቀቁትም በተውሂድ ነው። {የአላህ እርግማን በአይሁድና በነሳራዎች ላይ ይሁን! የነብዮቻቸውን መቃብር የአምልኮት ቦታዎች አድርገው ይዟቸው!} እያሉ በማስጠንቀቅ። (ቡኻሪ 435 [ሙስሊም 1215)

በዚህ መሀል ያለፈ ሂይወታቸውም አብዛሃኛው ለተውሂድ የዋለ ነው የተላኩት ለዚሁ ነውና። ሶሐባው አምር ብኑ ዐበሳህ ረድየላህ አንሁ "በምንድን ነው የላከህ?" ብለው ሲጠይቋቸው {አላህን ብቸኛ በማድረግና በሱ ላይ ምንንም ባለማጋራት፣ ጣኦታትን በመስበርና ዝምድናን በመቀጠል} ብለዋል። [ሙስሊም፡ 832] (አህመድ 27019)

➲ቀደምት ነብያትም [ከሱ ሌላ አምላክ የላችሁም)" እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለህዝቦቻቸው አስተምረዋል። በተውሂድ እየተናዘዙም ተልእኳቸውን ቋጭተዋል። ያዕቆም ዐለይሂ ሰላም ከሞት አፋፍ ላይ ሆነው ከእኔ በኃላ ማንን ነው የምታመልኩት? በማለት ልጆቻቸውን ሲጠይቁ እነዚያ ክቡራን የክቡር ልጆች የነብይ ፍሬዎች ያንተም የአባቶችህም የኢብራሂም፣ የኢስማኢል፣ የኢስሐቅም አምላክ የሆነውን አንድ አምላክ ነው የምናመልከው። ለእሱም እጅ ሰጥተናል ሲሉ መልሰዋል። [በቀርራህ፡ 133]

➭የዘመናችን ታላቅ አሊም ሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ይላሉ፦ "ልክ እንዲሁ ከዱዐትና የለውጥ አራማጆች ከሆኑ የመልእክተኞች ተከታዮች የመጀመሪያ የሚያተኩሩበት ነገር ተውሂድ ነው። ምክንያቱም ተውሂድ ላይ የማይፀና አስተምህሮት ሁሉ አላማዋቹን የማያሳካ፣ ውጤት የማይኖረው እንዲሁ ወዳቂ ነውና። እያንዳንዱ ተውሂድን ዝቅ የሚያደርግና ትኩረት የማይሰጥ አስተምህሮት ሁሉ ያለጥርጥር በውጤቱ ከሳሪ የሆነ ስብከት ነው። ይሄ የሚታይና የሚታወቅ ነው። [ዳሩሱን ሚነል ቁርኣኒል ከሪም]

➩ውንድሜ ሆይ! የአላህ ነብይ ኑሕ ዐሊይሂ ሰላም ዘጠኝ መቶ ሃምሳ አመት ተውሂድ ሲያስተምሩ አልሰለቹም። አንተ ስንት አመት አስተምረህ ነው የተውሂድ ርእስ የሰለቸህ? ለመሆኑ ምን ብታይ ነው ውስጥህ ለተውሂድ የደፈረሰው? ከማንም በፊት ለራስህ እዘን። " ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ። ያለበለዚያ ድንጋይ ነህ ተብለህ ትወረወራለህ" ይላል በሂሉ። አደራህን ካልተወጣህ አላህ የራሱን ሰው ይተካል። ይልቅ ነገ የውመል ቂያማ በእሳት ልጓም እንዳትለጎም ፍራ። በዙሪያህ ላሉት እውነቱን ካላወጣህ ነገ አላህ ፊት ሞጋቾችህ ይሆናል። መርማሪው ውስጥ አዋቂው፣ ሁሉን መዝጋቢው ጠቢቡና ሃይል ጌታ መሆኑን አትዘንጋ።
◉
◉
◉
◉✍️ኢንሻአላህ

➲ተውሂድ የሁለት ሀገር ስኬት ቁልፍ ከሚለው ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሃፊዘሁላህ ኪታብ የተወሰደ

🖊የፋሩቅ እናት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1