💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
እህቶቻችን ወደ ዲን ሲቀርቡ፣ ኒቃብ ሲለብሱ፣ ቁርኣት ላይ ሲያተኩሩ አቅማቸውን የሚፈታተኑ ብዙ ፈተናዎችን ያስተናግዳሉ። ይበልጥ የሚያመው ደግሞ ከውጪው በበለጠ በቅርብ ሰው የሚመጣው ፈተና ነው። ከዚህም ይበልጥ የሚያመው ወደ ዲን ከቀረበው፣ ሰበብ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ከሚጣልበት ወንድም የሚታየው ነገር ይበልጥ ሞራልን የሚያቀዘቅዝ፣ ስሜትን የሚጎዳ መሆኑ ነው። ቀጥሎ የማሰፍረው ከአንዲት እህት የደረሰኝ መልእክት ነው። መቼም የሁላችንም ልብ አንድ አይደለም። ምናልባት ቆም ብለን እናስብ ዘንድ በአላህ ፈቃድ የሆነ ያክል እገዛ ይኖረው ይሆናል።
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎
አንዳንዴ ነገሩ ይከብዳል...
ብዙ እህቶች የሚወድቁበት የሆነ ብዙ ከባድ ፈተና አለ። በጣም ጠንካራ የሆኑት እንጂ የማይቋቋሙት። ደግሞ ሴቶች ደካማ እንደሆኑ ታውቃለህ። የታላቁ ጌታ በፍፁም ከኔ ራህመት ተስፋ አትቁረጡ የሚል የተስፋ ቃል ባልነበረ ብዙ እህቶች ተስፋ በቆረጡ ነበር....

አሏህ ካዘነላቸው የሱና ወንድሞች ዉጪ ነገሩ እንዲህ ሆኗል ከዲን ይልቅ መልክ እድሜ ላይ በርትተዋል። መስፈርቶቹ ከአንድ ሰው ነው የሚላኩት ተብሎ እስኪጠረጠር ድረስ እንድ አይነት በመልክ ወላ በእድሜ ቀይ ቆንጆ እድሜዋ ከዚህ በታች ብዙ ኪታብ የቀራች የተማረች...ብዙ ብዙ ደግሞ እሱ ጋር ኖሮ ቢሆን እሺ።

ሁሉም ሴቶች ቀይ ናቸውን??
እሺ አንድ ሴት ቢያንስ መልኩንና ቂርዓቱን ብታሟላ እንዴት የተማረችና እድሜዋ ከዚህ በታች እንዴት ሊሆን ይችላል??
Maybe ሊኖር ይችላል ግን እጅግ ጥቂት ነው።

የምር እስኪ አንድ ወንድ ሱኒይ ሲሆን ወደ ሱና ሲጠጋ ፂሙን ይለቃል ልብሱን ከፍ ያደርጋል እና ሌሎችንም ነገሮች ይፈፅማል። የታዘዘውን ይሄን በማድረጉ ወሀቢይ ሊባል ይችላል እና ሌላም ፈተና ሊደርስበት ይችላል። ግን ሀቂቃ እንደ ሴቷ አይፈተንም። ሴቷ ኒቃብ ስትለብስ ሙተበሪጅ ሆና ዝም ያሏት ቤተሰቦቿ ሙተሀጂብ የሆነች ቀን ከገዛ ቤተሰቦቿ ፊትናው ይጀምራል። ከዛን ስራዋን ታጣለች። ሌላ ስራ ለማግኝትም ትቸገራለች። እቤት በገባች በወጣች ቁጥር አዛ ትደረጋለች። "እኔ ያስተማርኩሽ ለዚ አይደለም፣ እንደሷ አመድ አፋሽ ሆነሽ እንዳትቀሪ" እየተባለ ምሳሌ ይሰጥባታል። ሀታ በገዛ ቤቷ ባዳ የሆነች ያክል እስኪሰማት ድረስ። ታውቀዋለህ ግን ይሄ ስሜት ምን ያክል እንደሚያም?!! እኔ ግን በጭራሽ አመድ አፋሽ አልሆንኩም። እንዲያውም የጌታዬን እዝነትና ዉዴታን ነው ያፈስኩት። ከዚያም ደርስ ትከለከላለች። ግን የሚገርመው ደርስ ልትሄድ ልትቀራ "የትራንስፖርት አልሰጥም" ያለ ቤተሰብ ለዱንያዊ ትምህርት በሺዎች አውጥቶ ያስተምራል!!

ትራንስፖርት አጥታ በእግርም ቢሆን እየሄድኩ ቂርዓቴን እቀራለሁ ብላ በህመም ምክንያት ያቆመች እህት እንዳለችስ...??

ከዚህ ሁሉ መውጫ ዲኗንም ለመማር ያላት አማራጭ ኒካህ ማሰር እንደሆነ ታስባለች። በቤተሰቦቿ ቤት እንዳትቀራ ተከልክላለችና። ግን ለኒካህ የሚመጡ ወደ ሱና ተጠግተዋል የሚባሉ ወንዶች ይሄ ነው መስፈርታቸው አላህ ካዘነለት ውጪ። ቢያንስ ዲንን አስቀድመው ቢሆን፣ ዲን የላትም ብሎ ቢሆን የሚተዋት በጣም ደስ ይል ነበር።
እስኪ እናንተ የሱና ወንድሞች ካላዘናችሁልን ማን ያዝንልናል? ኢኽዋኑ!? አህባሹ!? በጭራሽ እነሱማ ሂጃባችንንም አቂዳችንንም ሊያጠፉ ነው ሚፈልጉት።

አልገጠመህምን አልሰማህምን ሱኒይ ሆና ኢኽዋኒ አገባች ሲባል?! አንድ የሱና እህት ከዚህ ሁሉ በቃ አስተካክለዋለሁ ብላ ኢኽዋን አግብታ በዛው የቀረች የተገለበጠች። ግን አንዳንዷ ደግሞ የሱና ጀግና እንጂ አይሆንም ብላ ትንሽ እድሜዋ ከፍ ካለ......የሱና ወንድ የሚባሉት ደግም የሚፈልጉት በእድሜ ትንሿን ነው። ሁሉንም እየወቀስኩ አይደለም። ደግሞ የፈለጉትን መሰፈርት ማውጣት መብታቸው ነው።
ማንም የፈለገውን መስፈርት ማድረግ መብቱ ነው ግን...???

አላህ ለነሱ ያለውን ሪዝቅ ማንም አይወስደውም ሶብር ማድረግ ነው አላህ የተሻለውን ምርጡን ያመጣል ግን ያው ሴቶች ደካማ አይደለን
አንዳንዴ ያቅታል። ህመማችን እንዲገባችሁ ነው ይህን የምለው።

ምን እንደምፈራ ግን ታውቃለህ? በፊት ኒቃብ ስለብስ ኡሚ አሪፍ ስራ ነው ያለሽ (የመንግስት ስራ ነበር የምሰራው) "ይሄን ስራ አትተይው። ሌላው ቢቀር ቢያንስ ኒካህ እስከምታስሪ ቆይ። እንዲህ ኒቃብ ከለበሽ ባል አታገኚም። ማን ያይሻል?" ብላኝ ነበር። እኔ ግን ለነፍሴ: "በጭራሽ አላህን በመታዘዝሽ ሪዝቅሽ ቢሰፋ እንጂ አይጠብም። እንዲያውም አላህን መታዘዝ ሪዝቅ ለመምጣት ሰበብ ነው" እያልኩ አበረታት ነበር የመንግስቱን ስራም ተውኩት፣ በኒቃብ መስራት አይቻልምና።
አሁን ግን ድሮም ነግሬሽ ነበር
እኔ ያልኩሽን ብትሰሚ ኖሮ ... መባሉ ያስፈራኛል።
እሷን ደስ ይበላት ብዬ የምወደውን ቂርዓት ትቼ እሷ ደስ የሚያሰኛትን ነገር እየሰራሁ ነው አላህ ነገሮቼን እስከሚያስተካክልልኝ ድረስ።

ኒቃብ ስለለበስኩ ኡሚ ለወራቶች ነው ያኮረፈችኝ። አብረን አንድ ቤት ውስጥ ሆነን ትናፍቀኝ ነበር። ሀቂቃ በጣም የሚያሳምም ነው ስሜቱ። ግን መፀናኛዬ ጌታዬ ነበር። እሱ ቅርብ የሆነ ሁሉን ነገር እያየልኝ እየሰማ ስለሆነ ደስ ይለኝ ነበር። ወሏሂ በጣም የሚያስከፋ ነገር ገጥሞኝ እኔ ግን ጌታዬን እያሰብኩ እስቅ ነበር። ሶብር በማድረጌ ከእሱ የማገኝውን አጅር እያሰብኩ እፅናና ነበር። አልሀምዱሊላህ በፊትም አሁንም በቃላትም በንግግርም ልገልፀው የማልችለው ሰላምና መረጋጋት ደስታ በውስጤ አለ።

ሌሎችም ኒቃባቸውን ቤተሰብ የሚያቃጥልባቸው በጣም ከባድ ፊትና የሚገጥማቸው ብዙ እህቶች አሉ። ከኔም የባሰ ብዙ አለና አብዝቼ ጌታዬን አመሰግነዋል ሁሌም። ኒቃቤ ለኔ ክብሬ ውበቴ ነው ከአጉል እይታ የሚከላከለኝ በጌታዬ ፍቃድ መጠበቂያዬም ጭምር። አላህ ከፊትና ይጠብቀንና የሞትኩ ቀን ቢሆን እንጂ አይወልቅም ኢንሻ አላህ። ዱንያ ላይ ያለውን ነገር ሁሉ እንስጥሽ ቢሉኝ እንኳን ወላሂ ሱመ ወላሂ እኔ በኒቃቤ አልደራደርም። ከፍ ያለው አላህ ለሁላችንም እስቲቃማውን ይስጠን።
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እህቶቻችን ወደ ዲን ሲቀርቡ፣ ኒቃብ ሲለብሱ፣ ቁርኣት ላይ ሲያተኩሩ አቅማቸውን የሚፈታተኑ ብዙ ፈተናዎችን ያስተናግዳሉ። ይበልጥ የሚያመው ደግሞ ከውጪው በበለጠ በቅርብ ሰው የሚመጣው ፈተና ነው። ከዚህም ይበልጥ የሚያመው ወደ ዲን ከቀረበው፣ ሰበብ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ከሚጣልበት ወንድም የሚታየው ነገር ይበልጥ ሞራልን የሚያቀዘቅዝ፣ ስሜትን የሚጎዳ መሆኑ ነው። ቀጥሎ የማሰፍረው ከአንዲት እህት የደረሰኝ መልእክት…
!!!
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እህቶቻችን ወደ ዲን ሲቀርቡ፣ ኒቃብ ሲለብሱ፣ ቁርኣት ላይ ሲያተኩሩ አቅማቸውን የሚፈታተኑ ብዙ ፈተናዎችን ያስተናግዳሉ። ይበልጥ የሚያመው ደግሞ ከውጪው በበለጠ በቅርብ ሰው የሚመጣው ፈተና ነው። ከዚህም ይበልጥ የሚያመው ወደ ዲን ከቀረበው፣ ሰበብ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ከሚጣልበት ወንድም የሚታየው ነገር ይበልጥ ሞራልን የሚያቀዘቅዝ፣ ስሜትን የሚጎዳ መሆኑ ነው። ቀጥሎ የማሰፍረው ከአንዲት እህት የደረሰኝ መልእክት…
➧ምንም ለማለት ቃላቶች አጠሩኝ!!!

ሀቂቀትን ሀገራችን ላይ ያለው ተጨባጭ ይሄ ነው! የቤተሰብ ግፊት በጣም ከባድ ነው ከቤተሰብ እገዛ ኑሮ ከውጭ መገፋት ይሻላል ብያለሁ!!

ውድ የሱና እህቶቸ አውቃለሁ ፈተናው በጣም ብዙ ነው ግን አላህ ጥንካሬውን እንድሰጠን የሁል ጊዜም ዱአየ ነው! ቤተሰቦች የሱና ተከታይ ካልሆኑ ሙሉ ቤተሰቦቻችን አጠገባችን ሁነው ብቻችንን ማንም እንደሌለን የሚሰማውስ ነገር ያአላህ አዛኙ ጌታችን የሱን ባሪያዎች መቸም አይረሳቸውም ጌታችን ከእኛ ጋር ነው ሁል ጊዜም አልሃምዱሊላህ!

ከችግር በኃላ ድሎት አለ የአላህን ራህመት በትዕግስት እንጠብቃለን!!
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➭የመልካም ሚስት ስብዕና ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧የባሏን ውለታ የማትክድ ▰▱▰▱▰▱▰▱ ➝የአላህ መልዕክተኛصَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم ሆይ"በጎ የዋሉልንን መካድ ምን ማለት ነው? አልኳቸው እርሳቸውም እንድህ አሉ፦ 🔃"لعلَّ إحداكنَّ تطول أيْمَتها من أبويها ،ثم يرزقها اللّٰه زوجََا ويرزقها منه ولدًا فتغضبُ الغضبة…
➩የመልካም ሚስት ስብዕና
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➧ባሏን የምታከብርና ሐቁን የምትጠብቅ
➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪

➧በተለይ ደግሞ ባልየው የመልካም ስብዕና ባለቤት፣ አላህን ፈሪ፣ በዲኑ ፅናት ያለው፣ አምልኮውን በአግባቡ የሚያከናውንና የአላህን ትዕዛዝ የሚጠብቅ ከሆነ ሐቁ የዛኑ ያክል እጥፍ ድርብ ይሆናል። ኢማሙ ቲርሚዚይ እና ኢብኑ ማጃህ ከሙአዝ ቢን ጀበል እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم እንድህ ብለዋል ፦

🔃قال رَسُوْل صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم :، "لَا تُؤْذِي امْرَأَةٌ زَوْجُهَا فِي الدُّنْيَا إلَّا قَالَتْ زَوْجَتُهُ مِنَ الْحُورِ العِينِ ; لَا تُؤْذِيهِ قَاتَلَكِ اللّٰهُ.، فَإِنَّمَا هُوَعِنْدَكِ دَخِيلٌ يُوشِكُ أَنْ يُفَارِقَكِ إِلَيْنَا"

➪"ዱኒያ ላይ አንድት ሴት ባሏን የምታስቸግር ከሆነ ፤በተቃራኒው ጀነት ያለችው ሚስቱ (አልሑሪል ዒይን) አታስቸግሪው! አላህ ይርገምሺና! እርሱ እኮ ልክ አንቺ ዘንድ እንዳለ እንግዳ ነው፤ አንቺን ተለይቶ ወደኛ መምጣቱ አይቀርም። "ትላለች።

➮የዕውቀት ባለቤቶች (ዑለማዎች) ይህን ሀድስ አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፦ ይህ ሀድስ ባሎቻቸውን ለሚያስቸግሩ ሴቶች ከባድ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው!

➩በልጆቿ መሀል ፍትሀዊ የሆነች
➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻

➧ከመልካም ሚስት መገለጫ ባህሪያት መካከል አላህ የልጅ ፀጋን ከለገሳትና ክብርንም ካጎናፀፋት በመካከላቸው ፍትሃዊ ትሆናለች።

የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ፦

🔃قال عَلَيْهِ الْصَّلَاةُ وَالسَّلَامُ " اعْدِلُوا بَيْنَ أَوْلَادِكُمْ ،اعْدِلُوا بَيْنَ أَوْلَادِكُمْ

በልጆቻችሁ መካከል ፍትሀዊ ሁኑ! በልጆቻችሁ መካከል ፍትሀዊ ሁኑ
!
ይህ ሀድስ በሱነን አቢ ዳውድ የተዘገበ ሲሆን። በዚህ አይነት መልዕክት ያላቸው ብዛት ያላቸው ሐድሶች ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተወርተዋል።

➲ቤቷ ውስጥ የምትረጋጋ!
➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊

➧ከመልካም ሚስት መገለጫ ባህሪያት መካከል ቤቷ ውስጥ ረግታ የምትቀመጥና ወጣ ገባ ያማታበዛ መሆኗ ነው! ከቤት ከወጣችም ለጉዳይ ካልሆነ በቀር አትወጣም። እንድሁም ከቤቷ ተገላልጣና ተራቁታ አትወጣም! ዓይኗንም (በሸሪአ የተከለከለ ነገር ከመመልከት) ትጠብቃለች! ሰበር ታደርጋለች ብልቷንም (ከሀራም) ትጠብቃለች።

➧ይህንን በተመለከተ የተወሰኑ የቁረአንና ሀድስ አስረጂዎች ከፊት አሳልፈናል ከእነዚህም መካከል ኢማሙ አጠበራኒ "አል አውሰጥ"በተሰኜ ኪታባቸው ሳሊም ቢን አብዲላህ ቢን ኡመር ከአባታቸው እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ፦

🔃المَرْأَةُ عورةٌ خرجتِ استشرفها الشَّيطان ، وإِنَّها لاتكونُ أقرْبَ إلى اللّٰهِ منها فِي قَعْرِبيتها.

ሴት ልጅ " ዐውራህ" ናት ከቤት ከወጣች ሸይጣን
ያሱባታል (የአላማው መምቻ) ያደርጋታል፤ ወደ አላህ የበለጠ ቅርብ የምትሆነው ቤቷ (ጓዳዋ)ውስጥ ስትሆን ነው ።
◉
◉
◉
◉✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል

➧የመልካም ሚስት ስብዕና ከሚለው ከአብዱረዛቅ ቢን ዐብዱልሙሕሲን አልበድር ኪታብ የተወሰደች!

✍የፋሩቅ እናት

📚አንብብ! ከማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል

➩ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Forwarded from Ibnu Muhammedzeyn
መቼስ ሰው እንደፍዬል ቅጠል በልቶ !!
የአላህን ቤት እንድህ አቆሽሹ !!
ዱቤ እየደበደቡ ተደልቀው !!
በጭብጫቦና ጪሆት !!
ኢማን መጨመሩ የማይጠረጠር ጉዳይ ነው?!


​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn
☞ብዙ እህቶች በጠራራ ፀሐይ ባላቸዉን እየተነጠቁ ነው፡፡ ትዳራቸው እየፈረሰ ነው፡፡የዚህ ምክኒያቱም የ እህቶች ደዩስ መሆን ነው።አወ ዝም የተባለ ወንድ በጥፋቱ እየገፋ ይሄዳል፡፡ ምንም አያውቅም፣ ምንም አያደርግም፣ ጓደኞቹ ጋ ነው፣ ለሥራ ጉዳይ ወጥቶ ነው፣ ሲመሽበት አድሮ ነው፣ … ተብሎ የእምነት በሩ በሰፊው የተከፈተለት ባል ነገ ብዙ ጣጣ ሊያመጣ ይችላል፡፡ በቻት እና በሰላምታ ዝም የተባለ ከዚያ አልፎ እውጭ ያድራል፡፡

☞በባሏ የማትቀና ሴት ደዩስ ናት፡፡ አዎ የማትቀና፣ ዙርያዋ ምን እየተካሄደ እንዳለ የማታነፍንፍ፣ በግልፅ በቤቷና ትዳሯ አካባቢ የሚታዩ ነገሮችን ምንድነው? ምን እየተካሄደ ነው? …ማለት ግድ ነው የኔ እህት ። ከጭቅጭቅና ከንትርክ በፀዳ መልኩ ሳይበዛ ማነው? ማናት? ማለት ጥሩ ነው፡፡ አንድም ከመጥፎ መንገድ ይመልሰዋል፣ ከክፉ ጎዳናም ያስቀረዋል፡፡

☞ቅናት በልክ ሲሆን ጤና ነው፡፡ ሲበዛ ግን እብደትና በሽታ ነው፡፡ በቅናት ዉስጥም የእዝነት፣ የስስት፣ የቅንነት፣ የተቆርቋሪነትና የመውደድ ስሜት መንፀባረቅ አለበት፡፡
ለትዳር ተቆርቋሪነት መልካም ነው፡፡እናማ ሳይበዛ በባልሽ ላይ ቅናት ይኑርሽ‼
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
☞ብዙ እህቶች በጠራራ ፀሐይ ባላቸዉን እየተነጠቁ ነው፡፡ ትዳራቸው እየፈረሰ ነው፡፡የዚህ ምክኒያቱም የ እህቶች ደዩስ መሆን ነው።አወ ዝም የተባለ ወንድ በጥፋቱ እየገፋ ይሄዳል፡፡ ምንም አያውቅም፣ ምንም አያደርግም፣ ጓደኞቹ ጋ ነው፣ ለሥራ ጉዳይ ወጥቶ ነው፣ ሲመሽበት አድሮ ነው፣ … ተብሎ የእምነት በሩ በሰፊው የተከፈተለት ባል ነገ ብዙ ጣጣ ሊያመጣ ይችላል፡፡ በቻት እና በሰላምታ ዝም የተባለ ከዚያ አልፎ…
በደንብ አንብቡት እ!?ሴቶችዬ በልኩ ቅኑ በቃ ባላችሁ ዝም ብላችሁ እንደፈለገ አትበሉ ጠበቅ አድርጋችሁ ያዙ!!!
☞ሴቶች ሆይ! ቤተሰቦቻችሁን አማክሩ‼
<==============>

⇛እስልምና ጋብቻ ይፋ እንዲሆን ያዛል፡፡ የቤተሰብ ትዉዉቅንም ያበረታታል፡፡ ከሁለቱም ወገን በኩል ወኪል ይኖር ዘንድ መስፈርት ያደርጋል፡፡ የባል ወኪል/ዋስ የሆነ ሰው ባል ድንገት ቢጠፋ ፈልጎ ያቀርባል፡፡ የሚታወቅ የባል ቤተሰብ፤ ባል በሌለበት ሁኔታ ሚስት ብትቸገር ሚስትን ያረጋጋል፣ ያግዛል፣ ልጆችን ይንከባከባል፡፡

⇛የሚስት ወኪል ደግሞ ለምትዳረው ልጅ ጠበቃ ነው፡፡ እንዳትስት፣ እንዳትሳሳት፣ እንዳትታለል፣ የተሻለዉን ነገር እንድትመርጥ ያግዛታል፡፡ የሚጠቅም የሚጎዳትን ይጠቁማታል፡፡

⇛ሴት ልጅን ለማይታወቅ ሰው መዳር ጣጣው ብዙ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ደሞ ይባስ ብሎ… በሶሻል ሚድያ ላይ ብቻ ስለተዋወቁ ዘለው ወደ ትዳር የሚገቡ እህቶች በርክተዋል። አባቷንም ሆነ እናቷን የምትነግራቸውና የምታማክራቸው እሷና እሱ ከጨረሱ ብኃላ ነው።ሀቂቃ በጣም ያሳዝናል! የማን ነው ልጁ? ለ ወላጆቹ ምን አይነት ክብር አለው? ማሕበረሰቡስ ለሱ ምን አይነት አመለካከት አለው? የሚባሉትን ማጣራት ቀርቷል። ከስሙ መጨረሻ ላይ አስ_ሰለፊይ፣ አል-አሰሪይ…ስላለ ብቻ ሰለፍይ ነው ማለት አይደለምኮ እህቴ! አልያም ደሞ ቻናል ከፍቶ አርብኛ ስለ ፃፈ፣ወይም ቃለ ረሱሉሏህ ስላለ ብቻም ኡስታዝ ነው ማለት አይደለም! እስኪ ተረጋጊ በረቢ!

☞ካሁን በፊት ተናግሪያለሁ!…በትዳር ጉዳይ ቤተሰብ የሚላችሁን ሥሙ፡፡ እነርሱ ትልቅ የሕይወት ልምድ ዉስጥ ያለፉ በመሆናቸው ነገሮችን በትክክል ይረዳሉ፡፡ ሁኔታዎች በሚገባ ያስተዉላሉ፣ ጉዳዮችን በጥልቀት አርቀው ያያሉ፤ በትክክል ይገነዘባሉ፡፡ የሚጠቅማችሁን እንጂ የሚጎዳችሁን አያደርጉም፡፡ ወላጆቻችንን የምንወድ፣ ክብራቸው የሚያስጨንቀን ከሆነ የነሱ ትዕዛዝና ምርጫ ከ ሸሪዓ የወጣ እስካልሆነ ድረስ ትዕዛዛቸዉን እናክብር፤ አስተያየታቸዉን እንቀበል።
√ አላህ ለሁላችንም የተሻለውን ይምረጥልን!
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
Audio
☑️ አዲስ የቂርአት ፕሮግራም!!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

♦️የኪታቡ ርዕስ
➫➫➫➫➫

🌐«የነብዩ ልደት (መውሊድ) በተመለከተ።»

↪️ (ክፍል  ➆)


♦️የመጨረሻ ክፍል

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

➷የኪታቡ PDF ለማግኘት⤵️
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/8307
4_5922523514773965996.pdf
1.2 MB
☑️ አዲስ የቂርአት ማስታወቂያ

⚡️የኪታቡ ስም፦ ሹሩጡ ላኢላሀ ኢለላህ ወነዋቂዱል ኢስላም
⚡️የኪታቡ አዘጋጅ፦ ሸኽ መሀመድ ቢን ሰኢድ ረስላን

በአላህ ፍቃድ ነገ ሀሙስ ከዝሁር ሶላት በኋላ በሳኡዲ ሰአት አቆጣጠር ልክ 2:00 ላይ ይጀመራል። ኪታቡን በማዘጋጀት ጠብቁን።

♦️የኪታቡ pdf ለማግኘት👇👇
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/8403
ፈኑ-ተጅዊድ - فن التجويد .apk
142.4 MB
🆕 📲 አዲስ አፕሊኬሽን ተለቀቀ

❝ ፈኑ ተጅዊድ | فن التجويد❞

🎙 በኡስታዝ: አቡ ዓብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

📲 መተግበሪያው የያዘው:-

➛የኪታቡ ሙሉ ደርስ በድምፅ
➛የኪታቡ መትን በ pdf እና
➛ ምርጥ ማስታወሻ መያዣ


🏷 በምርጥ ጥራት

https://t.me/almuhajir_app
ለስደት እህቶች በሙሉ


እጂግ ጥብቅ ማሳሰቢያ ‼️
---------------------------------

መቸም ሁሌም እናገራለሁ አትሰሙም ከእንቅልፋችሁ የምትባንኑት ስትዘረፉ፣ስትገፈፉ፣ ስትጠለፉ፣ስትሸነፉ ብሎም ድርጊቱ ሲደርስባችሁ ነው ይህ ደግሞ የሞኞች መገለጫ ነው።

ሙስሊም ሁሌም ብልጥ ነው ''በስደት ያላችሁ በተለህ እህቶች ግን የዋህነታችሁ ወደ ሞኝነት እያመራ ከመሆንም አልፎ ወደ ብዙ አስከፊና አፀያፊ  ነገር እየተሸጋገረ እንደሆነ እያየን እየሰማን ነው።

.......እህቶችን ከማስጠንቀቄና ሲነግሯቸውም ባለመስማታቸው ተስፋ ቆርጨ በቃ አልናገርም እስከማለት ደርሸ ነበር.....ግና ሙስሊሞች መሆናቸው ብቻ አላስችልህ እያለኝ የእምነት እህቶቼ በመሆናቸው ብቻ ሲደፈሩ ሲጠቁና በጠላት ሲሞኙ እየሰማሁ እንደት ልቻለው ''የእምነቴ ጉዳይ ባይሰማኝ ኖሮ ''ወላሒ''ፈፅሞ ብዕር አላነሳም ነበር...ግን ውስጤ አይችልምና እምቢ አለኝ።

ምክንያቱም በስደት ያሉ 'በተለይ እህቶች''የሚዘርፋቸውን እንጂ የሚመክራቸውን አይሰሙም ይህን በተደጋጋሚ ተመልክቻለሁ አረጋግጫለሁም።

ብዙወቹ በሚባል ደረጃ ስትመክራቸው የቀናህባቸው ወይም ከነርሱ ጥቅም የፈለካቸው ይመስላቸዋል ምክርህ ትዝ የሚላቸው ሲዘረፉ ወይም በደል ሲደርስባቸው ብቻ ነው።

በፊት ነበር እንጂ ሲመከሩ መስማት
ከሆነ በኋላ ምን ይሰራል ማማት

ይህን ስል ምክር የሚሰሙ የሉም ማለት አይደለም አሉ ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው ብዙወቹ የዋሆች ከመሆናቸው የተነሳ የሚዘርፋቸውን እና የሚጠቅማቸውን የመለየት አቅም የላቸውም።

ከዚህ አንፃር ለብዙ ጊዜ ብዙ መረጃ ቢደርሰኝም ላይሰሙኝ በሚል መናገር አቁሜ ነበር ግን ሲበዛ ደግሞ አላስችል ብሎኝ ብዕር አነሳሁ።

በስደት ያላችሁ እህቶች እባካችሁ ''ከሌቦች''ተጠበቁ ኸረ ንቁ ከሀገር የተሰደዳችሁት ለምን እንደሆነ እወቁ እባካችሁ⁉️

  👉#ጉዳዩይህነው‼️

ነገሩ በጣም በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ እየተፈፀመባችሁ ቢሆንም ሁላችሁንም እስኪያዳርስ ድረስ በሚመስል መልኩ አንዳችሁ ለአንዳችሁ እንኳን መረጃ አትለዋወጡም አንዱ ላይ በደረሰው ነገር ሌሎቻችሁ አትማሩም ምን ሆናችሁ ነው ግን በጤናናችሁ ነው⁉️

ነው ወይስ የሚያስነኳችሁ ነገር አለ⁉️
ይህ ነገር ግን እኔን ብቻ ነው የሚገርመኝ⁉️

ብዙወቹ እኮ ከሙስሊም መካሪያቸው ይልቅ የጠላት መዝባሪያቸውን ንግግር ያምናሉ ለምን⁉️
ሚስጥሩ ምንድን ነው⁉️

ለማንኛውም ጠላቶቻችን ስውር በሆነ መልኩ ተደራጂተው በተለያዩ ዘደወች ''ሙስሊም ሴቶችን''እምነታቸውን እስከማስቀየርና ይህ ካልተሳካ ደግሞ የተለያዩ ማታለያ ዘደወችን በመጠቀም ገንዘባቸውን መዝረፍ ይህ ካልሆነ የሙስሊም ሴቶችን ክብር ዝቅ የሚያደርግ ዘግናኝ ነገር መፈፀምና በማህበረሰቡ ውስጥ ሙስሊም ሴቶች በተለይ ኒቃቢስቶች ክብር እንዲያጡ በሰው አዕምሮ ላይ ቀመጥፎ እንድቀረፁ የሚያደርጉ ''የተደራጁ የሌላ እምነት ተከታዮች ''ተመሳስለው ተሰግስገው ብዙወችን ገንዘባቸውን ዘርፈዋል ብዙወችን አስጨንቀዋል አሁንም ይህን ተግባር እየፈፀሙት ይገኛሉ።

ይህ ድርጊት የሚፈፀመው በብዛት
➊በዱባይ በሚገኙ ሙስሊም እህቶች ላይ ሲሆን
❷ደግሞ በሳዑድ አረቢያ በሚገኙ እህቶች ላይ ነው ድርጊቱ ሙስሊሞች ላይ ያተኮረ ተልዕኮ ቢኖረውም ''#በኒቃቢስቶች'' ላይ ይበረታል።

👉ከማታለያ ዘዳቸው ውስጥ አንዱ
(➊)ፓስፖርት ላሰራላችሁ በኢትዮጲያ #3400 ላኩልኝ በሚል ማታለያ ያሳምንና ገንዘቡን ከላኩለት በኋላ ፓስፖርቱስ⁉️ የሚል ጥያቄ ሲመጣ  #ፎቷችሁን ላኩልኝና ገንዘባችሁን ልመልስላችሁ ይላቸዋል።

ከዚያ ምን ችግር አለው ብለው ፎቶ ከላኩለት ገንዘባቸውን ሊመልስም ላይመልስም ይችላል።
የዚህ ሰው አላማው ገንዘብ አይደለም የሙስሊሞችን ክብር ለማዋረድ ከተለያዩ አካላት ተልዕኮ ተቀብሎ ማስፈፀም እንጂ የተቀበላቸውን ፎቶወችም ለላኩት አካላቶች በመላክ በተለያዩ ሙስሊሞችን በማይመጥኑ#መጥፎ_ቪዲወወች ላይ በማቀናበር የሙስሊም ሴቶችን ክብር ዝቅ የማድረግ የተሰጠውን ተልዕኮ ይጠቀምበታል።

(❷ኛው) ማጭበርበሪያ ደግሞ፦

ሙስሊም መስለው ከተቀራረቧችሁ በኋላ የተለያዩ ሹብሀወችን በመርጨት ኢስላምን እንድትጠራጠሩ ማድረግና ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በንግድ ሰበብ ገንዘብ ተቀብሎ ከተቻለ እምነታችሁን ማስቀየር ካልተቻለ ገንዘባችሁን መቀማትና ስነልቦናችሁን መጉዳት ነው።

በዚህ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ተታለው የተሸወዱ እህቶች አሉ (መቸም አትማሩም)ግን ምናልባት ብትነቁ ጥቆማ  ይሆን ዘንድ ከፈቀዱልኝ ዝርዝሩን እመለስበታለሁ።

ሙስሊም እህቶች እባካችሁ ንቁ‼️
በአሏህ ይሁንባችሁ ንቁ‼️
ክብራችሁን ገንዘባችሁን እምነታችሁን ጠብቁ‼️

ሸር በማድረግ ለሌሎች አድርሱላቸው

....✍️በኑረዲን አል አረቢ

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
የተገለጠችዋ እህት እንድህ ትላለች ትክክል ነው
ልብሴ ሸሪአዊ አይደለም ነገር ግን ቀልቤ የጠራና ንፁህ ነው።የአላህ መልእክተኛ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ደግሞ እንድህ እያሉሽ ነው


አዋጅ ስሙ በሰውነት ውስጥ ቁራጭ ስጋ አለች፡
እሷ ከተስተካከለች ሰውነት ሁሉ ይስተካከላል፡፡ እሷ ከተበላሸች ሰውነት ሁሉ ይበላሻል፡፡
እሷም "ቀልብ" ነች፡፡


  ስለዚህ እህቴ የመገለጥሽ ምክንያት የቀልሽ አለመስተካከል ነው ። ምክንያቱም ቀልብ ስትስተካከል ሰውነትም ይስተካከላል ያ ማለት ልብስሽ ወይም አለባበስሽ ሸሪአዊ ና የተስተካከለ ይሆናል።
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
            https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➡አንዳንዴ ዳግም የማታዝን እስኪመስልክ ድረስ ደስ ይልካል!! አጃኢብ.....እኛም ክፉ ቀን እደማያገኘን እስኪመስለን እንፈነጥዛለን!!

➲ጊዜ ያልፍና ደግሞ የማይነጋ የሚመስል ጨለማ ውስጥ እራስክን ታገኘዋለክ!?


 âž˛"ሱብሀነክ ሙغዪር አል አኽዋል"
"የሁኔታዎች ለዋዋጭ ጌታ  ጥራት ይገባው!!"

➲በዚ ጊዜ ግን እኛ አቅል ሊኖረን ይገባል ስናጣም ስናገኝም ስንደሰትም ይሁን ስንከፋ አልሀምዱሊላህ ማለት  አሏህን ከማመስገን አለመዘናጋት!!


➲እሱ ያሻው ይሆናል ከጭንቀት በኋላ ደስታ እዳለና ለሶብረኞች አሏህ ምንዳ እደሚከፍለን የነገረንን እናስታውስ!!

👉so latahzenu  ኢነሏሀ ማአነ ከችግር ጋር ምቾት አለ!!

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
🖋ፈገግታ_ከኡለሞች_ጋር

አንድ ሰው ኢማሙ_ሸዕቢይ ጋር መጣና እንዲህ ብሎ  ጠየቃቸው፡_

☑️የሆነችን ልጅ ካገባኋት በኋላ እንደምታነክስ ገባኝ፣ ታዲያ መፍታት እችላለሁን❓

✅ኢማሙ ሸዕቢይም፦ ያገባሃት ግልቢያ ለትወዳደርባት ከሆነ ፍታት አሉት‼️