💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
👉ልብ በይ ውዷ❗️

ወደ አላህ በተጠጋሽ ቁጥር ፈተናዎች
ይበረቱብሻል ነገር ግን በአቋምሽ ፅኚ
በሂጃብሽ በዲንሽ አትደራደሪ

➧አንቺ ሂጃብ ስለለበሽ ስለተሸፈንሽ እርቃኔን አልሄድም ስላልሽ ብቻ ብዙ ስሞች ሊወጡልሽ ይችላል ብዙ ትችቶች ሊደርሱብሽ ይችላል !

ግን ግን ሶብር አድርጊ አላህ እንዲህ ይላል
إنما يوفى الصابرون أجرهم بغير حساب
ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው
ይላል በላቸው [ አል-ዙመር - 10 ]

✍️አላህ ጠንካሮች ያድርገን!!


ሌሎች ተጨማሪ ትምህርቶች ለመከታተል
ወደ ቤታችን ይቀላቀሉ የሱና ቤት አይጠብም!
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
 https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
✍️የምሺቷ ዉብ መልዕክት ለዉዷ እህቴ

ውድ እህቴ ፈገግታ ከፊትሽ ላይ ፈፅሞ አይለይ ምክንያቱም ፈገግታ ውበት ነው:: ፈገግታ ካለሽ ሁሉ እሚያምር ይሆንልሻል በአላህ ፍቃድ!! ሰው ፊት ስትቀርቢ ፈፅሞ ፊትሽን አታኮሳትሪ!! ለምሳሌ እንደ  ሃላፊ ሆነሽ ሌላን ሰው እያሰራሽ ከሆነ በጥሩ ፊት እዘዣቸው ፈገግታን ተላብሰሽ!
! እነሱም ደስ እያላቸው ነው እሚሰሩት ግና ፊትሽ እሚጋረፍ ከሆነ በጣም ተበሳጭተው ስራው እስኪያልቅና ያንቺን ፊት ላለማየት ቶሎ ካንቺ እሚሄዱበትን ሰአት ይጠብቃሉ::በስራ ቤታ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም አጋጣሚ ለሰው ልጅ ፈገግታን አትንፈጊው ደግሞ እያስመሰልሽ ሳይሆን ከልብሽ:: ይሁን በዚህን ሰአት አላህም ይወድሻል ለሰዎች ጥሩ ፊት በማሳየትሽ ምክንያት ያም ሲሆን ሰውም ይወድሻል ሁሌ ካንቺ መለየትን አይፈልጉም በመጣች እንጂ በሄደች አይሉሽም ሁሉንም በፈገግታ እለፊው::

👉አላህ ተግባሩ ይግጠመን!!
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
إِنَّ هَذَا لَهُوَ الْقَصَصُ الْحَقّ

🎙 القارئ ؛
#عبدالله_خياط رحمه الله

👉ደግ እደሩ!
Audio
☑️ አዲስ የቂርአት ፕሮግራም!!


♦️የኪታቡ ርዕስ
➫➫➫➫➫➫

🌐«የነብዩ ልደት (መውሊድ) በተመለከተ።»

↪️ (ክፍል  ➄)


🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

የኪታቡ PDF ለማግኘት⤵️
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/8307
👉 ስትመክር ተመካሪው ምክሬን ሊቀበለኝ ይገባል ከሚል መነሻ አይሁን።

👉ስትሰጥ መመስገንና መወደስን አስበህ አትስጥ።

👉ስታሸ'ማግል ግድ መታረቅ አለባችሁ ከሚል ቅድመ ሁኔታ ሊሆን አይገባም።


ከላይ የተጠቀሱትን ስታደርግ ሃሳብህ መሆን ያለበት መልካምን መፈጸም፣ሀላፍትናን መወጣት እንድሁም ሌሎችን ለመጥቀም በማሰብ ብቻና ብቻ ይሁን።

✍️ከኢብኑ_ሀዝም_ምክሮች

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
"የተኩላዎችን ተንኮል ራቂ፣

በላይሽ ላይ ያለውን ሁሉንም (የተንኮል መዳረሻ) በሮችን ዝጊ፣

ቤትሽን ያዥ (ያለ ሃጃ አትውጭ)ኪታብን(ቁርአንን) ቅሪ!!


(በሁለመናሽ ሃያእሽ) ከዳመና በላይ ብረሪ።"


💐የኔዋ/እንቁ በርቺ በሂጃብሽ💐

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
🔊 አድስ የኪታብ ቂርአት


▪️ክፍል  (⓸)

➧ማህበረሰብን በማስተካከልና በማነፅ ላይ የሴቶች የጎላ ሚና በተመለከተ የሚዳስስ!!

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ


https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

➲የኪታቡን pdf ለማግኘት👇
➧t.me/https_Asselefya1/6385
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የመልካም ሚስት ስብዕና ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➧በወጪ ጉዳይ ላይ ባሏን የማታስጨንቅ ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ ↔️ይህ ስራዋ ግን ምንኛ የዚህን ዘመን ባለ ረጅም ጫማ ታኮ (ሂል) ጫማ እንደሚመሳሰል አስተውላችኃል!? ይህን (ረጅም ታኮ (ሂል) ጫማ ማድረግን)አስመልክቶ የኡለማዎች ቋሚ የፈተዋ ኮሚቴ የሰጠውን ብይን ቃል በቃል እንመልከት:- ◀️ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى…
የመልካም ሚስት ስብዕና
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

የባሏን ውለታ የማትክድ
▰▱▰▱▰▱▰▱

➝የአላህ መልዕክተኛصَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم ሆይ"በጎ የዋሉልንን መካድ ምን ማለት ነው? አልኳቸው እርሳቸውም እንድህ አሉ፦

🔃"لعلَّ إحداكنَّ تطول أيْمَتها من أبويها ،ثم يرزقها اللّٰه زوجََا ويرزقها منه ولدًا فتغضبُ الغضبة ،فتكفر فتقول : ما رأيت منك خيرًا قط"
ከእናንተ መካከል አንዳችሁ ትዳር ይዘገይባትና ከዚያም ባልን ይሰጣታል ከእርሱም ልጅን ይቸራታል። አንደ ስትቆጣ ግን ውለታውን ሁሉ ትረሳና ከአንተ ላይ ፈፅሞ አንድም ቀን መልካምን ነገር አይቼ አላውቅም ትላለች

🔃"تطول أيمتها أبويها"
➘የሚለው ትዳር ይዘገይባታል ማለት ነው።

በሌላ ሀድስ ደግሞ ነሳኢይ "አስሱነን አልኩብራ" በተሰኘው ሀድስ ጥንቅራቸው ከአብዱላህ ኢብኑ ኡመር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛصَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم እንድህ ብለዋል

🔃"لا يَنظوُ اللَّهُ إلى امرأةٍ لا تَشكرُ لزوجِها وَهيَ لا تَستَغني عنهُ"

"ከእርሱ የማትብቃቃ(የምያስፈልጋትን ሁሉ የሚያደርግላት) ሆና ሳለ ባሏን የማታመሰግን ሴት አላህ ወደ እርሷ (በእውነት)አይመለከትም

ባሏን የምታከብርና ሐቁን የምትጠብቅ
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➧ከመልካም ሚስት ስብዕናዎች መካከል አንዱ ባሏን የምታከብር፣ መብቱን የምትጠብቅ ክብርና ልኩን የምታውቅ መሆኗ ነው።

👉በዚህ ርዕስ ላይ ብዙ ሀድሶች የመጡ ሲሆን ከእርሱም መካከል ጠበራኒ " አል ሙዕጀም አል ከቢር"በተሰኘው ድርሳናቸው ላይ ያሰፈሩት ይገኘበታል።

ከአብዲላህ ኢብኑ አባስ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛصَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم እንድህ ብለዋል ፦

🔃عن ابن عباس رَضِيَ اللّٰهُ عَنْهُما أنّ رسول اللّٰه صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم قال:" لا آمر أحدًا أن يسجد لأحدٍ ، ولو أمرتُ أحدًا أن يسجدَ لأحدٍ لأمرتُ المرأة أن تسجدَ لزوجها"
አንድም ሰው ለሌላ ሰው (ማንም ለማንም) እንዲሰግድ አላዝም ፤ አንድ ሰው ለሌላ ሰው እንድሰግድ ባዝ ኖሮ ሴት ልጅ ለባሏ እንድትሰግድ አዛት ነበር

እንደዚሁም ጠበራኒ በ "አልሙዕጀም አል ከቢር"ከየዚድ ኢብኑ አርቀም እንዳስተላለፉት።

🔃أنّ معاذًا قال يا رَسُول اللّٰه أرأيت أهل الكتاب يسجدون لأساقفتهم وبطارقتهم أفلا نسجد لك؟

ሙዓዝ እንድህ አለ፦ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አህለል ኪታቦች (አይሁድና ነሷራ) ለጳጳሶቻቸውና ለመሪዎቻቸው ሲሰግዱ አላዩምን እኛስ ለምን ለእርሶ አንሰግድም?

ነብዩ صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم እንድህ አሉ፦

🔃قال "لَوْ كُنْتُ آمِرًا أَحَدًا أنْ يَسْجُدَ لِغَيْرِ اللَّه لأَمَرْتُ الْمَرْأَةَ أَنْ تَسجُدَ لِزَوْجِهَا ،وَلاتُؤَدِّي الْمَرْأَةُ حَقَّ زَوْجِهَا حَتَّى لَوْ سَأَلَهَا نَفْسَهَا عَلَى قَتَبٍ لَمْتَمْنَعْهُ"

"አንድ ሰው ለሌላ ሰው እንድሰግድ ባዝ ኖሮ አንድት ሴት ለባሏ እንድትሰግድ አዝ ነበር፤ አንድ ሴት ባሏ ለፍቅር ጨዋታ ፈልጓት የግመል ጀርባ ላይ ሆና እንኳ ሲጠራት እሺ ብላው ብትመጣ የባሏን ሀቅ አታሟላም



✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል

የመልካም ሚስት ስብዕና ከሚለው ከአብዱረዛቅ ቢን ዐብዱልሙሕሲን አልበድር ኪታብ የተወሰደች!

የፋሩቅ እናት

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

ከመጀመሪያው ክፍል ጀምሮ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
https://t.me/https_Asselefya1/4982
https://t.me/https_Asselefya1/4982

➧ው ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
በጣም የምትወዳቸው እንደ እራስህ የምትሳሳላቸው ሰዎች በሆነ አጋጣሚ አንተ የእነሱን እገዛ በምትፈልግበት ጊዜ እንዳልሆነ ነገር ጥለውህ ይሄዳሉ!!

ባጋጣሚ ደግሞ ከዚህ በፊት ከነመፈጠራቸው የማታውቃቸው ሰዎች በድርገት ህይወትህ ውስጥ ይገቡና ያለህበትን ችግር ችግራቸው ደስታህ ደስታቸው ሆኖ ስታይ ግርም ይልሃል!! ያንን ውለታ ለመመለስ ብታስብ እራሱ የምትችል አይመስልህም በቃላት እንኳን ጀዛከላህ ኸይር ለማለት ቃላቶችም ያጥራሉ ሀቂቀተን የምናደርገው ነው ጥፍት ይሚለን!!

ብቻ ከባድ ነው መወለድ ቋንቋ ነው የሚለው አባባል አሁን አሁን ነው እየገባኝ የመጣው። ለሰወች መልካም እንሁን መሆን ባንችል አንጉዳቸው! ሁል ጊዜም ለሰዎች ጥሩን ስራ ስንሰራ ደስታው ልዩ ነው! የሚያውቅ ያውቀዋል። ጥቅምን ፈልገን ሳይሆን ከአላህ ምንዳን ፈልገን በኢኽላስ እንስራው! የዱኒያ ጥቅም እዚሁ ቀሪ ነው።

ከእህታችሁ..........
አንብብ!! ማንበብ👇👇📚📕📖
➱➱➱➱➱➱➱➱

➧ምላሥን ይገራል!
➧እውቀትን ያሠፋል!
➧ጥበብን ያሥተምራል!
➧ከሥራ ፈቶች ይነጥላል!
➧ከሀሣብ ያሣርፋል!

➧ሥኬትን ይጠቁማል!
➧ድክመትን ያሣያል!
➧ክብርን ይጠብቃል!
➧ሰውን ሙሉ ያረጋልማንበብ!
➧ጊዜን በከንቱ እንዳንገድል ይጠቅማል!
➧ሥህተትን እንደ መሥታወት ያሣያል!
➧መካሪ በጠፋ ጊዜም ይገስፃል!


ካላነበብክ በዕውቀትህ አትጨምርም። ለነገም ብትደርሥ ከዛሬ አትሻልም ! ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን! ትጠቀማለህ።
➘➷➘➷➘➷➘➷➘➷➘➷➘➷➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
04 - شرح أصول السنة
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም
➡️ አዲስ ተከታታይ ትምህርት
  ➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛

📚 أصول السنة للإمام أحمد

☑️ ክፍል 04


➧የኪታብ pdf👇
t.me/https_Asselefya1/7396

🎙በተከበሩ ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም ሀፊዘሁሏህ ተዓላ!!!

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
@SheikhMuhammedZainAdam
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ ላኢላህ ኢለላህ መጨፈር
~
የተውሒድን ቃል (ላኢላህ ኢለላህ) ለጭፈራ ማዋል በጣም አስነዋሪ ተግባር ነው። ኢብኑል ጀውዚይ (597 ሂ.)፡-
የሱፍያ ክፍሎችን ተግባር አንስተው ሲያወግዙ እንዲህ ይላሉ:–
“በየምግቡ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ሲጠግቡ ጊዜ ይደንሳሉ፡፡ … ከመዐቶቻቸው ሁሉ የከፋው መዐት ግን ይህንን (ጭፈራ) መቃረቢያ (ዒባዳ) አድርገው መሞገታቸው ነው፡፡ ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው ከኢስላም እንደሚወጣ በርግጥም የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጥሯል፡፡” [ሶይዱል ኻጢር፡ 168]
በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ለመውሊድ የሚጨፍሩ ሱፊዮች ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
አርቴፊሻል ጓደኛ

አንዳንድ አርቴፊሻል ጓደኛ እንደተቆርቋሪ ያስወራህና ዞር ብሎ ያመሀል።እንዳታወራ ብለህ የነገርከውን እንደ ሚስጥር ያማከርከውን ያወራል። ንቃ! ጓደኛና ጉደኛን ለይ! ብልህ ፣በሳል፣አስተዋይ፣ነቄ ሁን!ሙእሚን ሁሌም ንቁ ነው ።አጉል ብልጥ ነን ባዮች እንዳያታልሉህ።

@AbuHafsaYimam
👑ኒቃቤ_ነው_ለኔ 👑

ኒቃቤነው ለኔ ጌጥና ማማሬ፣
የሴትነት ወጌ ሀያእ እና ክብሬ፣
የሱሀባን መንገድ በፀና ተግብሬ፣
ሙስሊም ሴት ንፁህነች ቆሻሻ አይነካትም፣
ጅላጅል ሰካራሙም ሞኙም አይደፍራትም፣
ባደባባይ ወታ ክብሯን አትጥልም፣
በዘመን አመጣሽ በፋሺን አልኖርም፣
ኒቃቤ ነው ክብሬ ሂጃቤን አልጥልም፣
ባልማር ይቅርብኝ ከኢስላም አልዞርም፣
አካሌን ገልጬ ስልጣኔ አልሻም፣

ዘመንያልበከላት ሷሊህሴትለመሆን፣
ሂወቴን ላሳልፋት በሱና ብራሀን፣
የዱኒያ ብልጭልጭ ፋሽኑ ሳይስበን፣
ዱኒያን ተረድተናት ለአኼራ ሰርተን፣
ከሸይጧን ጉትጎታ ባሏህ ተጠብቀን፣
ሂጃብን ጠብቀን በኒቃብ ተውበን፣
የዲንን ጥፍጥና በኒቃብ አጣጥመን፣
የድንን ጥፍጥና በሱና አጣጥመን፣
አሏህ ካወሳቸው ሳሊህ ሴት እንሁን፣
ከሙንከር ማራቂያ ኒቃቤነው ለኔ፣
በፋሺን መጃጃል አይስበኝምኔ፣


➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
የምንፈራው ሞት ድንገት መምጣቱ ስለማይቀር እንዘጋጅ!!

ሁላችንም ሞትን እንፈራለን። ወደሞት ከሚያደርሱን ማንኛቸውም ነገሮች በቻልነው አቅም በመጠንቀቅ ከሞት እንሸሻለን። ግን የተጠነቀቅነውን ያክል ብንጠነቀቅ የቻልነውን ያክልም ከሞት ብንሸሽ አንድ ቀን የምንፈራው ሞት በእኛ ላይ መምጣቱ ምንም ጥርጥር የለውም። አላህ እንድህ ይላል:-

{ قُلْ إِنَّ الْمَوْتَ الَّذِي تَفِرُّونَ مِنْهُ فَإِنَّهُ مُلَاقِيكُمْ ۖ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَالِمِ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ }

«ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኛችሁ ነው (ያገኛችሗል) ።
ከዚያም ሩቁን እና ቅርቡን ዐዋቂ ወደ ኾነው ጌታ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው፡፡ [ጁሙዐ (8)]

አንድ ነገር ልብ እንበል:- መሞታችን ምንም ቅሮት ከሌላው አንድ ቀን እችን ዱኒያ መሰናበታችን ጥርጥር ከሌለው ለሞት ከወዲሁ እንዘጋጅ አንዘናጋ!!
ሞት አማክሮ አይመጣም ድንገት ነው የሚከሰተው ስለዚህ መፀፀት በማይጠቅምበት ጊዜ ከመፀፀት በስተፊት በተሰጠን የዱኒያ ጊዜ ለአኼራችን እንዘጋጅ
የተሰጠን እድል ከማለፉ በስተፊት ከሞት በሗላ ላለው ሒወታችን እንስራ!!

ኢብኑ ሙሐመድዘይን
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn