💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
✅✅ ሀያእ የውበት መገለጫ ነው ✅

👉 የሴት ልጅ ውበቷ አይናፋርነቷ ነው
👉 ሀያእ ከመጥፎ ስራ ግርዶሽ ይሆናል
👉 ሀያእ ያላት ሴት ሁሌም በመልካም ባህርይ ላይ ናት ወደ መልካም ይገፋፋታል
👂👂👂👂👂
🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
《 هل الأفضل للمرأة أن تصلي في بيتها جماعة مع أهلها أم تصلي منفردة ؟ 》

▪️الشـيخ العلامـة
سليمـان بن سليـم الرحيلـﮯ
- حفظـہ اللّـہ تـعالـﮯ -

•┈┈••••○○❁🌷❁○○••••┈┈•

نسـأل اللــہ ان ينفــ؏ بهـذا المقـطـ؏ الجميـ؏ .
ሼህ ሱለይማን ኢብን ሰሊም አል-ራሄሊ እድህ ይላሉ ሴት ልጅ እቤትዋ ውስጥ ትስገድ ይህ የተወደደ ነው ከአይን አርቃ ትስገድ ጀመአ ይስገዱ የተወደደ ነው
Forwarded from đ‘ťđ‘Źđ‘žđ‘Żđ‘°đ‘Ťđ‘Ź 𝑴𝑬𝑫𝑰𝑨/ተውሂድ ሚዲያ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጀምዓተል ሓጃዊራ ሌት ከቀን ጮኸታቸው ጀምዒያ ማለት እና በታላላቅ ኡለማዎች ላይ መዋሸት ፣ የተቃረናቸውን ሁሉ ቢዲዓ ላይ ለመጣል ይህ ትልቁ መሳሪያቸው ነው!!!
Audio
✅ አድስ ሙሐደራ ✅

🔶 ስለ ሱፍዮች ጠማማነት እና ስለ አህባሾች አስከፊነት የተዳሰሰበት ሙሐደራ ነው‼️

🎙በሸይኽ አደም አዙበይር (ሀፊዘሁሏህ)
🎙ትርጉም፦ በወንድም አቡ ረይስ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ቢድዓ
ኢብኑ ሙነወር
ከኢብኑ ሙነወር ወሳኝ #ሙሐደራዎች

ክፍል ❻

ርዕስ  â†ˇâ‡Łâ†ś
ቢድዓ (በዲን ላይ ፈጠራ)

🎙 በኡስታዝ #ኢብኑ_ሙነወር ሀፊዘሁሏህ

➽ #ቢድዓ ማለት ምን ማለት ነው?
➲ በሀይማኖታችን ላይ #የቢድዓ አደገኝነት ምን ይመስላል?
➚ እና ሌሎችም #ጠቃሚ ትምህርቶችን #ከሙሐደራው ይከታተሉ!!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
የዶክተር ጀይላን ማንነት
ዶክተር ጀይላን ምን እየሰራ እንደሆነ
ሰለፍዮችን ሱፍይና አሽዓሪይ ለማድረግ
እንዴት እንደሚያሴር ለሰለፍዮች የአቋም መንሸራተት ኢብኑ መስዑዶችን መረጃ አድርጎ ማቅረቡ ኢብኑ መስዑዶች አሁንም ዶክተር ሰለፍይ ነው ብለው ማወደሳቸውና የመሳሰሉ ነጥቦች የተዳሰሱበት

🎙በኡስታዝ ባሕሩ ተካ (ሀፊዘሁሏህ ተዓላ)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
የኔዎች
~
ዘር ያላጎራበተን … በደም ያልተዛመድን
ኢስላም ብቻ ያገናኘን … በሱና፞ የተጋመድን
የልቦቻችን ስስቶች … የፍቅራችን አሻራ
ከስልጤ፣ ከጉራጌ … ከኦሮሞ፣ ከአማራ
ከትግሬ፣ ከሱማሌ … ከአፋር፣ ከአርጎባ
ከበርታ፣ ከወለኔ … ከአደሬ፣ ከሀላባ
•
•
•
በዘር ነውጥ ያልተናጡ … ለኢስላም እጅ የሰጡ
በሱና፞ የሚለኩ … በሱና፞ የሚቆርጡ
ለልባችን የቀረቡ … አእላፍ ወዳጆች አሉ
ለአላህ ሲሉ የሚወዱ … ለአላህ ሲሉ የሚጠሉ።
አሉኝ "የኔ" የምላቸው … በምስራቅ በምእራብ
ከወንድም፣ ከእህቶቼ … በሰሜኑም በደቡብ።

Ibnu Munewor[ኢብኑ ሙነወር]
🌸‏أخـتي كريمة

‏تحبيـن آلَلَهّ..؟!

➷ሂጃብሽ ጅልባብሽ አላህ እንደሚወድልሽ ነው አለባበስሽ⁉️

➷ወይንስ ነፍስያሽ እንደፈለገችው ነው አለባበስሽ⁉️

~ እራስሽን ፈትሺ እህቴ ስሜትሽን መከተልን ተጠቀቂ ካቺ ስሜት የጌታሽ ትዛዝ ይበልጣልና።


✍ام فلان
♡..ሐያእ የሚያመጣው ጥሩ ነገር ብቻ ነው።
▼⇨ሐያእ የእምነት አካል ነው
▼⇨ ሐያእ እውነትኛ ውበት ነው
▼⇨ አላህ ሆይ! የሐያዕን ካባ አላብሰን

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w

═══ ¤❁✿❁¤ ═══
سورة الكهف ___ بصوت
الفنان غير معروف
ሱረቱ -ካህፍ⤴️⤴️⤴️🌹🌹
───────────────
🌸ጣፋጭ ቲላዋ ተጋበዙልኝ📚📚

🎤°•القارئ ⁖ ⟨ فـارس_عـبـاد ⟩

🎤ቃሪእ፦ ፋሪስ አባድ

💎🌹📚ሊደመጥ የሚገባው ወሳኝ ትምህርት መልእክት ለእህቶች🖋
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

የሙስሊም ሴት ስብእናሴት ሙስሊም እህት ( ሙስሊም እህት) በምንበምን

አይነት ባህሪ ወይም በምን አይነት አኽላቅ

መታነጽ እንዳለባት በሚል እርእስ

የተዳሰሰ ትምህርት ሊደመጥ የሚገባው ሙሀደራ(( በኡስታዝ አህመድ አደም))
📚ኢብኑ ተይሚያ የሱንዬች መድረክ
https://chat.whatsapp.com/H1N5Ugqz9O6GwIBtCOnxZ4
➧ይህ ጽሁፍ ኢን ሻአ አላህ ለነዚያ አላህ እና መልክእከተኛውን ለሚወዱና ጀነትና ፀጋዎቿን ማግኘትን ለሚሹ ሆነው ሳለ ማንነታቸውን ረስተው ከኢስላም ለራቁ እህቶች ነው፡፡

💎እህቴ ሆይ !

➧ይህንን አስደናቂ እና አስገራሚ የአንድሉስ (የስፔይን) ታሪክ ሰምተሻልን ???

➧በታሪኩ ወቅት የነበረው የአንደሉስ ከሊፋ ወንድ ልጁን የሚያገባለት ሰው ይፈልጋል !!!

➧የሚፈልጋትም ሴት እንደማንኛውም ከተማው ላይ እንዳሉት ሴቶች ሳይሆን ምርጥ የተባለችውን ሴት ነበርና ቁርጡባ በተባለቸው ከተማ አዋጅን እንዲህ ብሎ አስነገረ

➧“ በቤቱ ውስጥ ለጋብቻ የደረሰች፣ ሙሉውን የአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን ቃል ቁርአንን በቃሏ የያዘች ልጅ ያለው ሰው … ዛሬ ማታ መስኮቱ አጠገብ ሻማ ይለኩስ ”
➧ያኔ ቁርጡባ ከተማ በብርሃን ደምቃና ተጥለቅልቃ አደረች።

➧ምክንያቱም ከተማው ላይ ብዙ የአላህን ቃል የሀፈዙ ልጃገረዶች ነበሩና !!

➧በማግስቱ ንጉሱ ድጋሚ ሌላ አዋጅ አስነገረ።

➧“ ለጋብቻ የደረሰች፣ የአላህን ቃል ቁርአንን በሙሉ እንዲሁም ከማለኪይ የፊቂህ መዝሀብ አንድ ኪታብ የሀፈዘች ልጅ ያለው ሰው … ዛሬ ማታ መስኮቱ ላይ ሻማን ይለኩስ ”

➧በድጋሚ ሙሉ ከተማዋ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በብርሃን ተጥለቅልቃ አነጋች፡፡

➧አሁንስ ከኛ መሀል ለጋብቻ የደረሰች፣ የአላህን ቃል በሙሉ እና ከማሊኪይ የፊቅህ መዝሀብ አንድ ኪታብ የሀፈዘች ትኖር ይሆን ??

➧ይሄ ጥያቄ እኛ ዘንድ ቢጠየቅ ያንዳችን መስኮት ላይ ሻማ አይኖርም ነበር።

➧የእህቶቻችን መጠንከር የኡማው መጠንከር ነው፡፡ ወንዶች ይማሩ ይሆናል ግና ለትክክለኛው የኡማው መጣፈጥ ሴቶቻችንም መማር አለባቸው።

➧ዛሬ ዛሬ ብዙሃኑን የህብረተሰብ ክፍል ስንመለከት እህቶቻችን መስጂድን የማይረግጡበት፤ መድረሳም የማይሄዱበት፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ጭራሽ እድሉ ቀርቦላቸውም ንቀው የተዉበትና ሌሎች ደግሞ እድሉን አጥተው የተቀመጡበት ሁኔታ ይስተዋላል።

➧ይህንን ድክመት ለመቀየርም እህቶቻችን የግድ መማር አለባቸው። ምክንያቱም እነርሱ የኡማው ምስሶ ናቸውና !!!

➧እህቶቼ ባሁኑ ወቅት ድራማዎችን፣ የቱርክ ፊልምን እና የመሳሰሉትን በመከታተል ግዜያቸውን ያባክናሉ እንጂ ቁርኣን እና ሀዲስን አያውቁትም ።

➧ይህ ደግሞ አደጋ ነው ። አንደሉስ (ስፔይን) በኡማው ታሪክ ከመታወስ የማትጠፋው ብዙ የተማሩ እህቶች ስለነበሯት ነው፡፡

➧እህቴ ሆይ አንቺም ተማሪ ፣ ስለ እስላም ተረጂ።

➧እህቴ ሆይ አንቺ የወደፊቷ እናት ነሽና ኢስላምን ካላወቅሽ ምንን ይሆን ለልጆችሽ የምታስተላልፊው ?

➧አሁን ላይ ባብዛኛው እህቶች ለኢስላም የሚያውቁት ነገር የለም። ወንድሞችም ደግሞ ብዙ ይቀረናል::
ይህንን ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ መቀየር አለብን። ልንማር ይገባል። ስለ ኢስላም እንወቅ።

💎እህቴ ሆይ !

➧ለዱኒያም ለኣኺራም የማይጠቀምሽን ነገሮች ትተሽ ለኢስላም ለመልፋት ሞክሪ።

➧እስልምናሽን ተግተሽ እወቂና አላህ ካንቺ ኢሰላምን በመማር የሚጠቀሙ፣ የኢስላምን ባንዲራ ከፍ የሚያደርጉ ልጆችን ይሰጥሽም ዘንድ አላህ ይወፍቅሽ።

🌸ተንቢሃት

💎https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
🗓ربيع الأول ٢٧ /١٤٤٢

♦️በኩጥባው ውስጥ የተጠቀሱ ዋና ዋና ሃሳቦች

📌አላህ ከዋለልን ትልቁ ኒእማ እስልምና ነው

📌አንድ ልንሆንና ልንስተሳሰር የምንችለው በተውሂድና በሱና ብቻና ብቻ ነው

📌ለዱንያ ቢሳቢስቲ ብለን ከትክክለኛው ጥሪ ወዳሁዋላ ልንል አይገባም


🎙አቡ አዩብ

ወደቻናሉ ጆይን ለማለት
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
https://telegram.me/abutoiba
🔺🔺🔺🔺🔺🔺

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
♻️🔺❗️ላስተዋለው ትልቅ ሙሲባ❗️🔺♻️

✅ قال الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله:
〰 〰 〰 〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
📌♻️ሸህ አብዱረዛቅ ቢን አልበድር አላህ ይጠብቃቸው እንዲህ ብለዋል።

📌♻️ كثير من الناس عنده استعداد يجلس ساعات طويلة ليتعلم أمرا دنيويا، ويمكن يُفني أو سنتين ثلاث ما عنده مشكلة، وينفق أموال طائلة في سبيل تعلمه
📌♻️ብዙ ሰዎች ዱንያዊ ጥቅም ብቻ የሚገኝበትን ትምህርትና እውቀት ለማግኘት በሚገባ ይዘጋጃሉ። ለዚህም ሲሉ ሳይሰለቹ ለብዙ ሰአታት ቁጭ ብለው ይማራሉ። በዚህም ላይ ሁለትና ሶስት ከዚህም በላይ የሆነን ሰአት ይሰጣሉ። ከዚህም አልፎ ይህንን አላማው ይሳካ ዘንድ ብዙ የሆነን ወጪ ያወጣሉ። ብዙ ገንዘብንም ይመድባሉ።

📌♻️ لكن التوحيد الذي هو الغاية التي خلق لأجلها وأوجِد لتحقيقها، ربما يستكثر على نفسه «ربع ساعة» يجلسها لتعلُّم التوحيد، هذه مصيبة

📌♻️ ነገር ግን በዋናነት ሊያረጋግጠው የተፈጠረለት አላማና እዚህ ምድር የመምጣቱ ዋና ምክንያት የሆነውን #ተውሂድ ግን እንደዛ አይማርም። አንዳንዴ ይህ ዋናው ጉዳይ ተውሂድን ለመማር የሰጣትን #እሩብ_ሰአት ብዙ እንደሆነ ያስባል። ሀቂቃ ይህ #ትልቅ_ሙሲባ ነው።

📘دروس وفوائد من آية الكرسي الدرس: -٥- (46:55)
🔸ረሱል-ﷺ-እንዲህ አሉ:-አንድ አካል ለሌላ አካል ሱጁድ እንዲወርድ ባዝ ኖሮ፡ሚስት ለባሏ ሱጁድ እንድትወርድ ባዘዝኳት ነበር፡በአላህ ስም እምላለሁ ሚስት የባሏን ሀቅ እስካልተወጣች ድረስ የጌታዋን ሀቅ አትወጣም።
ምንጭ፦ ኢብኑ ማጀህ (1853)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
በ Ibnu Munewor
~~~~ለሴቶች!
በርካታ እህቶቻችን በዲን አስተማሪዎች እንደሚበደሉ ይወራል። "ዲኔን ያስተምረኛል"፣ "አላህን ይፈራል" ያሉት ሰው ለህይታቸው መዘባረቅ ሰበብ ሲሆን ያጋጥማል። እኔ ለዚህ ችግር ቀዳሚ ሰበብ የራሳቸው የእህቶቻችን አለማስተዋል ይመስለኛል። በርግጥ ዲንን መስፈርት አድርገው ልባቸው ሰፍ ቢል አይፈረድባቸውም። ኧረ እንዲያውም የሚደነቁበት ነው።
ነገር ግን ከዲን ጎን ለጎን የሰውየው ስነ ምግባር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። አንድን ሰው ደዕዋ ላይ መሳተፉ፣ ዒባዳ ማብዛቱ፣ ወዘተ ጥሩ ነገር ሆኖ ሳለ አብሮ ለመኖር የሚያስችል ወሳኝ ቅመም ግን ሊጎድለው ይችላል። ስነ ምግባር። ለዚህም ነው ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ዲኑንና ስነ ምግባሩን የምትወዱለት ሰው ከመጣችሁ (ልጃችሁን) ዳሩት" ያሉት። 
ስነ ምግባር ከዲን ጋር በተጓዳኝ እንደተገለፀ ያስተውሉ።
እናም እህቶች ሆይ!
ዲንን እንደ መስፈርት ስታስቡ አኽላቅንም አትርሱ። በምትችሉት መንገድ ሁሉ አጣሩ። መስፈርታችሁን በጣም ጥብቅ አታድርጉት። ጭራሽም አታላሉት። በልክ።

ግልባጭ:– ለወንዶች! እባካችሁን ፀባያችሁን አሳምሩ። ካልሆነ ግን ህ
ሀ/ ጥሩ ሚስት ያመልጥሀል
ለ/ ጥሩ ህይወት ያመልጥሀል
ሐ/ ጥሩ እድል ያመልጥሀል።



https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
🎤 ቀልድ በእስልምና ይፈቀዳል?

ዛሬ ዛሬ ቀልዶች በዝተዋል ሚቀለድበትም ነገር በዝቷል እስኪ እስልምና ስለ ቀልድ ምን ይላል
1) ቀልድ በመሰረቱ ይፈቀዳል።ግን ለራስነቱ ቀልድ ስለሆነ ተብሎ ሚፈለግ ተግባር አደለም ።
- ራስን ነቃ ለማድረግ ፣ ነሻጣ ለማምጣት፣ ሌሎች ሙስሊም ወንድሞቻችንን ለማስደሰት ( ሙስሊም ወንድምን ማስደሰት ኢባዳ ነው) ሸሪያዊ መርሆን ሳይፃረር ሊቀለድ ይችላል።
👉ነገር ግን አንድ ሰው በቀልድ መታወቅ የለበትም ።ይህ ዳኢ ቀላጅ ነው ተብሎ ሰዎች ዘንድ በሙሉ እስኪታወቅ ድረስ መቀለድ ተገቢ አደለም።ምክንያቱም ይህ እስላማዊ አደብ አደለም ከጨዋ ሰውም ሚጠበቅ አደለም ሰለፎችም እንዲህ አልነበሩም
2)የአላህ መልእክተኛ ከሰሀቦች፣ከቤተሰባቸው እና ከህፃናት ጋር በተለያየ አጋጣሚ እንደቀለዱ ተረጋግጧል።
3)ቀልድ በፍፁም ውሸት ያለበት መሆን የለበትም
የአላህ መልእክተኛ እርሶ ይቀልዳሉ እንዴ ተብለው ሲጠየቁ
: " لا أقول إلا حقا "
እውነት እንጂ አልናገርም ብለዋል
👉ስለዚህ ለቀልድም ቢሆን መዋሸት አይቻልም
💎በሌላ ሀዲስ ላይ እንዲህ ብለዋል
‏وقد وعد عنه صلى الله عليه وسلم أنه قال: " ويل للذي يكذب ليضحك الناس ويل له ويل له "
"ወየሁለት ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ የሚዋሽ ወየሁለት ወየሁለት።
4)የክህደት ቃላትን እየተጠቀሙ መቀለድ ከእስልምናም ያስወጣል።
ጌታችን እንዲህ ይላል
قال تعالى {ولئن سألتهم ليقولن إنما كنا نخوض ونلعب ..} الآيات.
"ብትጠይቃቸው እኛማ ስንቀልድ እና ስንጫወት ነበር ይሉሀል።በአላህ በመልእክተኛው እና በአንቀፆቹ ነው ምታላግጡት በላቸው።ምንም ኡዝር አታቅርቡ ከእምነታችሁ በሇላ ክዳችሇል በላቸው።
5) የሙስሊም ወንድሙን ክብር በሚነካ መልኩ መቀለድ፣ወይም በቀልድ አድርጎ የሙስሊም ወንድሙን ቀልብ መስበርም አይፈቀድለትም።
6)በእስልምና ድንጋጌ መቀለድም አይፈቀድም።ለምሳሌ; በሂጃብ፣በፂም ፣በሰላት፣ በሀጅ ፣በፆመ ....በመሳሰሉት
7)በኡለሞች መቀለድም ከባድ ወንጀል ነው
8)እየተሳደቡ ወይም እየተማቱ መቀለድም አይፈቀድም
9)ሰዎች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ እየፈጠሩ ሚደረግም ቀልድ አይፈቀድም።መኪናውን ሰርቆ በማስደንገጥ ሚደረግ ቀልድን ይመስል
10)ሙስሊም ወንድሙ ላይ የጦር መሳሪያ በመደቀን የሚደረግ ቀልድ የተከለከለ በመሆኑ ላይ ሀዲስ መጥቷል
11) የሚፈቀደውን ቀልድም ቢሆን ማብዛት ተገቢ አደለም ። ቀልድ ሲበዛ ቀልብ ያደርቃል

‏قال عمر بن ؚبد العزيز : " اتقوا المزاح، فإنه حمقة توع؍ الضغينة "

👉👉👉👉👉👉
ቀልድ ልክ እንደ ጨው ነው።መግባት ባለበት ቦታ እና ሰአት ይገባል።ሲበዛ ማጣፈጡን ትቶ ያበላሻል


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w