💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
➧ለአል ኢህሳን ጀግና እህቶቻችን ማስታወሻ ትሁንልኝ

➲ጀግና ነሽ ብርቅየ


❖ሰለፍይ ጀግና በሱና ያጌጥሽው
በሱሀቦች ፋና ኒቃብ የለበስሽው
ተውሂድን በመማር ጊዜ የፈጀሽው
የመንሀጅ እህቴ ኢስላምን ያወቅሽው


በአል ኢህሳን መርከዝ የተገናኘነው
ከእንቁ ኡሰስታዞች በደርስ የተጣድነው
በመንሀጀ ሰለፍን የተረዳዳነው
ድንገት ስንለያይ ቀዘፈኝ እንባየ
እጅጉን ተሰማኝ መጣ ትዝታየ
እንባ ስታፈሽ እህትሽ ስትሄድ
ባጃጅ ስትሳፈር ስትገባ መንገድ
ስተትዘያየሩ በኒቃብ አምራችሁ
በጣም ገራሚ ነው ያስቀናል ፍቅራችሁ

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷

ታሪክ አይረሳውም የሰራሽው ስራ
በተውሂድ ጠንክሪ ምርትሽ ፍሬ ያፍራ
በቀጣይ ትውልዱ ደጋግሞ ይወራ
አንች ውዷ እህቴ መንሀጅ ያገናኘን
እንደ እድል ሆነና ሀገር ያለያየን
አላህ በእዝነቱ በዱኒያ ሰብስቦን
በእንቁ ኡስታዞች ለመማር ወፍቆን
በአል ኢህሳን መርከዝ ወስኖ አሰባስቦን
ደግሞ በውሳኔው ድንገት ያለያን
እንባ እየተራጨን እየተሸኛኘን
መለያየታችን እጅጉን ቢያመኝም
ውሳኔው የአላህ ነው ምንም አናረግም


እኔ ግን እህቴ ብዙ ተምሬ አለሁ
የሴቶች አለቃ መሆንሽ  ተረዳሁ
ቆራጥና አስተዋይ አርቆ አሳቢ ነሽ
ለድንሽ አሳቢ  እንቁ ጀግና የሆንሽ
የተውሂድ ዘበኛ የሱና ነበልባል
ሽርክን አራጋፊ የቢድአ እስክንፋል
መሆንሽ ግልፅ ነው ስራሽ ይናገራል
ለአህባሽ ለሱፍይ የእግር እሳታቸው
ለኢኽዋን ቡቃያ በእውቀት ገራፊያቸው
ሀዳድይ ሀጁሪን አንገት አስደፊያቸው
ለሙብተዲእ ሁሉ የእራስ ምታታቸው
አንች ነሽ እህቴ እኔ አይቸሻለሁ
ከምነግርሽ በላይ ብዙ ሰምቻለሁ
በአላህ ውሳኔ ዛሬ ብንለያይ
ኢንሻኡ ረቡና ብዙ አመት ሳንቆይ
እንገናኛለን በተውሃድ ዳእዋ ላይ
አንች ብቻ በርቺ በጅልባብ በኒቃብ
በአቂዳሽ ኑረሽ በሱናሽ በመዋብ
የነቢን ትእዛዝ ተግብረሽ በአግባብ
በሶብር ላይ ቆይ  እስኪሻ ጌታየ
እስከምንገናኝ አይናችን እያየ
የሁለት ሀገር ውብ ብርቅየ



✍ገጣሚ ወንድማችን አቡ ሹራ አህመድ
አልብኪይ

➷ለአል ኢህሳን መርከዝ ሴት ተማሪወች ማስተዋሻ የተነበበች
እህቶቸ በርቱልኝ አልሀምዱሊላህ የአላህ ውሳኔ ሆኖ ብንለያይም
እንደነገርኳችሁ ትእግስት አድርጉ
፡

➷የእኔ ውዶች በሰላም ግቡልኝ➷
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ 🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ?! ➬➬➬➬➬➬➬➬ ➲ክፍል ሰባት ➤የመልካም ጓደኛን ባህሪ እያየን ነበር እናም በዝህ ክፍላችን የመልካም ጓደኛ ባህሪዎች በትንሹ እንቋጫለን በቀጣዩ ክፍላችን ደግሞ የመጥፎ ጓደኛ ባህሪዎች ምንድናችሁ የሚለውን እናያለን ኢንሻ አላህ ። ❶❹➛ለአላህ ታማኝነት ያለው!! ➲ይህ ማለት ምን ማለት መሰለህ ወንድሜ አንድ ሰው ለአላህ ታማኝ ካልሆነ ላንተም…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ

🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ?!
➬➬➬➬➬➬➬➬

➲ክፍል ስምንት


➤እስከዛሬው ክፍላችን በአላህ ፍቃድ የተወሰኑ የመልካም ጓደኛን ባህሪዎች አይተን ነበር ከዝህኛው ክፍላችን ጀምረን ደግሞ የመጥፎ ጓደኛ ባህሪዎችን የምንመለከት ይሆናል ።

➲ይህንን ስናይ ግን ልታውቁልኝ የምፈልገው ነገር ይህንን የመጥፎ ጓደኛ ባህሪዎች ካላወቅን ልንርቀውና ልንጠነቀቀው ስለማንችል ነው ኸይር የምጠቅሰው ምክኒያቱም አንድን ነገን ለመራቅና ለመጠንቀቅ ግዴታን የሱን ምንነት ልናውቀው ይገባናል ።


⓵➮ዓቂዳው የተበላሸ ተውሂድ የለለው!!

➲ወንድሜ ሆይ ከሁሉም በፊት አንተ ለምን እንደተፈጠርክ እውቅ የተፈጠርክበትን አላማ ስታውቅ ግዜና ያኔ ለተውሂድ ያለህ ቦታ ከፍተኛ ይሆናል ማለት ነው ለተውሂድ ሰዎች ቦታ ትሰጣለህ ያኔ ።

➲ከጓደኛ ሁሉም መጥፎ ጓደኛ ማለት ዓቂዳው የተበላሸ ምንም የተውሂድ ብርሀን የለለው ነው በሽርክና በኹራፋት የተጨማለቀ ከሆነ ይህ በፍፁም ላንተ ጓደኛ ሊሆንክ አይችልም #በፍፁም !!

▪ዓቂዳው የተበላሸ ሰው ለአላህ ራሱ ስላልታዘዘ ምንም ላንተም ጓደኛ ሊሆንክ አይችልም እናም እንዲህ አይነትን ሰው በፍፁም እንዳትቀርብ ከአላህ ውጭ !!

➺ከአላህ ውጭ ላለ ከሰገደ
➺ከአላህ ውጭ ባለ ከተመካ
➺ከአላህ ውጭ ያለን እርዱኝ ካለ
➺ከአላህ ውጭ ያለን ከተጣራ
➺ከአላህ ውጭ ካለ ከከጀለ
➺ከአላህ ውጭ ለቀብር ካረደ

እና ሌሎችም የመሳሰሉትን ታላላቅ ወንጀሎችን ከተዳፈረ ይህ ሰው ላንተ ጠላትህ እንጅ ወዳጅህ አይደለም እናም ተጠንቀቅ ።

⓶➮ በቢድዓህ ባህር ውስጥ የሚዋኝ!!

➤ እንደሚታወቀው ዲናችን ሙሉ ነው #አልሀምዱሊላህ ስለዝህ አንዲስ ነገር ዲናችን አይቀበልም መጤ ነገር ሁሉም ጥመት ነው ይህ ጥመት ደግሞ የጀሀነም ነውና ።


➲ሱናው አልበቃ ብሎት ከሱናው አንድትን እንኳ ሳይሰራና ሳያውቅ በድዓው ባህር ከዋኘ ይህም ትልቅ ቂልነት ይሉካል ይህ ነውና አንተንም ቂል እንዳያደርግህ ተጠንቀቅ ።

▪ሱናውን ትቶ በተለያዩ የቢድዓህ አይነቶች ከገባ ይህ ሰው ለምሳሌ ፦
👇👇👇👇👇👇👇👇
➧የሽርክ መናኸሪያ የሆነውን መውሊድ ካከበረ
➧በነሺዳህ ስም ከጨፈረ ከደነሰ
➧በፊልም ስም ሓራምን ካየ
➧ ጫት የዱዓ መሳሪያ ነው ካለ
➧ በአደባባይ እናፍጥር እያለ ከበጠበጠ

እናም መሰል የቢድዓህ አይነቶች ላይ የሚዋኝ ከሆነ ይህን ሰው እንዳትጎዳኝ!!

➤ አደራህን የሱናው ወንድሜ ሆይ ይህ ሰው ብጥብጥና ሁከትን እና ቢድዓን እንጅ ሌላ አያወስክም ስለዝህ ቆም ብለክም አስብ ።

➲ አንድ ቢድዓን ማምጣት ትልቅ ወንጀል ነው
#ዲንም አልሞላም ብሎ ማሰብ ነውና ይህም ትልቅ ጥፋት ነው ዲናችንን ሙሉ ነው ቢድዓን አይቀበልም ኸይር አላህ ለሁላችንም በሱና ያስውበን ።

➧ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል ኢንሻ አላህ.........🖋

✍️አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/https_Asselefya1
▪️የሴት ልጅ መስተካከልና መበላሸት በባሏ ላይ ተፅእኖ ያሳድራሉ!!

➡️ሀሰኑል በስሪይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–

“መካ ውስጥ ልብስ ሻጭ የሆነ ሰው ዘንድ ከርሱ ልብስ ለመግዛት ቆምኩኝ፣ እየማለ ልብሱን ማወደስ ጀመረ፣ ከርሱ መግዛቱን ተውኩት፣ ከእንደዚህ አይነት ሰው መግዛቱም ተገቢ አይደለም አልኩና ከሌላ ሰው ገዛሁኝ። ከዚያም  ከሁለት አመት በኋላ (ወደዚያው) ጉብኝት  አደረግኩ፣ እርሱ ዘንደም ቆምኩኝ እየማለም እያወደሰም ሆኖ አላገኘሁትም፣ ለርሱም እንዲህ አልኩት:– ያ  ከአመታት በፊት ያገኘውህ ሰው አይደለህምን? አዎ ነኝ አለ፣ ከዚህ በፊት ከነበርክበት ሁኔታ ወደ ምመለከትህ ሁኔታ ምን አወጣህ? እየማልከና እያወደሰክም ሆነህ አላይህም፣ አልኩት።
እንዲህ አለ:–


⓵➞ለኔ አንዲት ሚስት ነበረችኝ፣ ትንሽ ነገር ይዤ ስገባ የምታመናጭቅና አሳንሳ የምታይ፣ ብዙ ይዤ ስገባ አሳንሳ ተየዋለች፣ ከዚያም አላህ ወደ አኼራ ወሰዳት (ሞተች)።

⓶➞ከርሷ በኋላ ሌላ ሴት አገባሁ፣ ወደ ሱቅ መውጣት ስፈልግ ልብሴን ይዛ ከዚያም እገሌ ሆይ! አላህን ፍራ ጥሩ ነገር እንጂ አትመግበን፣ ትንሽ ብታመጣልን ብዙ አድርገን እንቆጥረዋለን/እናብዛዘዋለን፣ ምንም ይዘህ ባትመጣ እንኳን እናግዝሃለን፣ ትለኛለች።”

ምንጭ:– አል ሙጃለሰቱ ወጀዋሂር አል ዒልም 5/251📚

👉ጥያቄ ለእህቶቼ:– ለመሆኑ እናንተ ከየትኛዋ ሴት ናችሁ ከመጀመሪያዋ ወይስ ከሁለተኛዋ???
መልሱን……… ለአላህ ብላችሁ ከልባችሁ ለራሳችሁ መልሱትና ራሳችሁን ገምግሙበት!!
ከመጀመሪያዋ የሆናችሁ አላህን (ተባረከ ወተዓላ) ፈርታችሁ ተፀፅታችሁ ወደ ሁለተኛዋ ተመለሱ!!
ከሁለተኛዋ የሆናችሁ ሸይጧን ድንበር እንዳያሳልፋችሁ ነፍሳችሁን ዝቅ እንድትልና
ከጌታዋ ከጃይ እንድትሆን አድርጓት! አላህ ፅናት እንዲሰጣችሁም የዘውትር ዱዓችሁ ይሁን!! ምክንያቱም ይህ እጅግ በጣም ከባድ ነዉና!!

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/abuUseyminabdurehman
የአንዳድ እህቶች ስህተት ባል ችላ የምትለዉን የሚወድ የምትንከባከበዉ አይወድም የምትሉ?!

እረ ሴቶችዬ ነቃ በሉ ባሎች የሚንከባከባቸዉ
የሚያግዛቸዉ አይዞህ የሚላቸዉ የሚወዱ
!!

ችላ እያልሺ ይወደኛል ብለሺ የምትንከባከበዉ ችላ የማትለዉ ፍልጋ ጥሎሺ እንዳይሄድ ዋ!

ይልቅ ነቃ ብለሺ ተንከባክበሺ ያዢ!
ኋላ ወይኔ ወየዉ ማፊ ፍይዳ እህቴ
ዋ!


https://t.me/https_Asselefya1
👉ምርጥ ወንድ ማለት በፍቅር ሰበብ አመታት በሀራም እንድትዘወትሪ ያደረገሽ ሳይሆን
አላህን ፈርቶ ለሀላል የጋበዘሽ ነው::



👌ይሰማል ለወደፊት ኒካ እያሉ መጃጃል ይቅር!
ትክክለኛ ፈላጊ ቀን አይቆጥርም ቶሎ ሀላል የሚያደርግ።ተመከሩ አትጃጃሉ ኋላ ልታለቅሱ!


👉ያለ መጃጃልኮ ሰላም ኑሮ አለ ጎበዝ
በቃ ከወንድ ካልተወራ ይሞታልዴ?

👉ሓቂቃ ራሳችን እንፈትሺ በትክክለኛዉ መስመር
ከመጣ ዳይ ወደ ሀላል ነገር ግን አጥር ላጥር
ከመጣ በብሎክ ክተችዉ ግዜሺ አታቃጥይ!!

👉ነገርኩሺ ትንሺ ትንሺ እያለ ያችኑ ያለችሺ
ኢማን አሟጦ አጥፍቶ ባዶሺ ሊያስቀርሺ ነዉ።
ተጠንቀቂ እህቴ ተጠንቀቂ ከኒካ በፊት ወሬ ከወንድ መጃጃል ተጠንቀቂ!!መጨረሻሺ አደጋዉ የከፍ ነዉና።

👌አድበሺ እየሸቀልሺ ቂርአትሺ ቅሪ የሚያዋጣሺን
የወደፊቴ እያልሺ አትጃጃይ!!!

✍️ቢንት አራጋዉ

https://t.me/https_Asselefya1
👉እህቴ_ሆይ

➧ተረጋግተሽ አግቢ አትሯሯጭ በሶሻል ሚዲያ

✍ዑስማን ኢብኑ አልዓሲ አስ-ሰቀፊ እንዲህ በማለት ለልጆቹ ምክር ሲሠጥ የተደመጠው

يا بنيّ ! الناكح مغترس، فلينظر امرؤ حيث يضع غرسه، والعِرْق السوء قَلَّمَا يُنجب، فتخيروا ولو بعد حين
“ልጆቼ ሆይ! ጋብቻ አዝመራ ነው። አንድ ሰው ተክሉን የት እንደሚተክል ያስተውል። መጥፎ ዘር ፍሬ አያፈራም። ጊዜ የሚወስድባችሁም ቢሆን ጥሩ ነገር ምረጡ።”

ታላቁ ኸሊፋ ዑመር ኢብኑ አልኸጧብ የሆኑ ልጆች አንድ ልጅ በአባቱ ላይ ያለውን መብት በጠየቁት ጊዜ
“እናቱን መምረጥ፣ መልካም ሥም ማውጣት፣ ቁርዓንን ማስተማር” በማለት መልሰውላዋቸል።

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
👉ውዷ እህቴ!

ይህ ምድር ጊዜያዊ መሸጋገሪያ ነውና የሰው ልጅ የፈለገውን ሁሉ አያገኝበትም፤ ስለሆነም ከአላህ መልካምን ነገር መጠበቅ ተገቢ ነው፤

እርግጠኛ ሁኚ! ያለፈሽ ኸይር ሁሉ የምታገኝው አልነበረም፤ ያገኘሽውም የምታጪው አልነበረም፡፡ አላህ በጥበቡ ለሁሉም ጉዞ ምህዋር አድርጎለታል፡፡ የፈለግሽው ሁሉ ላንቺ የሚጠቅምሽ አይደለምና መቅረቱ መልካም ሊሆን ይችላል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፤

ْ {{وَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ وَعَسَىٰ أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ}} البقرة /216

"አንዳች ነገርን እርሱ ለናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት
መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም ነገር እርሱ ለናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም (የሚሻላችሁን) ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም፡፡"


አልበቀራህ /216
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
አጂብ  አስተዋይነት!!

አንዱ ሷሊሕ ሲናገሩ:–
አላህን ለምኘው ከተሳካልኝና ከፈፀመልኝ አንዴ እደሰታለሁ። ከከለከለኝ ደግሞ አስር ጊዜ እደሰታለሁ አሉ።
ለምን? ሲባሉ እሳቸውም:–
አላህን ለምኘው ካሳካልኝ እኔ የፈለግሁትን አገኘሁ ማለት ነው።
ካላሳካልኝ ደግሞ እሱ አልፈለገልኝም ማለት ነው።


ከኔ ፍላጎት የጌታዬ ምርጫ አስር እጅ የተሻለ በመሆኑና የሱን ምርጫ ስለማስቀድም ደስታዬም እጥፍ ድርብ ይሆናል በማለት መለሱ።
አላህን ለምነን ባይሳካልን ወይ ከእኛ ዘንድ የጎደለ ነገር ኑሮ ነው: ካልሆነም አላህ በተሻለ ነገር ሊቀይርልን ፈቅዶ ነው እንጂ ጌታችን አላህ ዘንድ  የለም የሚባል ነገር የለም።


➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
ላንቺ ነው ውዷ/إليكي يا غالية

ቢቻልሽ ከወንዶች ጋ ንግግርን አታብዢ
ያወራሽ እንደሆንም በንግግርሽ ቁጥብ ሁኚ
አብዛኞች  ወሬሽንን ሳይሆን  …

ማንነነትሽንና አንቺነትሽን አድማጭ ሲሆኑ
ሴትነትሽን ገማችና ለኪዎች በመሆን
ኃላ የሚንቁሽ ብዙዎች ናቸውና
ቁጥብ ሁኚ ያኔ ውድ ትሆኛለሽ❗️


نصيحة لآختي المسلمة/ምክር ለሙስሊማ

https://t.me/https_Asselefya1
♻️ወሎ_ነው_ሀገሬ__!!
▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
ለሁሉም ግልፅ ይሁን፤
ወሎ ፍቅር እንጅ ክፋት አያቀውም፡
ሁሉም ዘመዱ ነው፤
ከማንም ይስማማል ሴራ ሸፍጥ የለውም፡
የአሏህ ውሳኔ እንጂ፤
የማንም ቀረርቶ የማንም ፉከራ አያሸንፈውም፡
በርግጥ ይገባኛል፤
ወሎየ ነኝ ስለው ውስን ሰው አይወድም፡
ግን ደግሞ ሀቅ ነው፤
እኔ ወሎዬ ነኝ ይህንን አልክድም፡
በተረዳሁት ልክ፤
#የዘረኝነት_ጥል ወሎ ገብቶ አያውቅም፡
ግን ደግሞ ግድ ነው፤
ቤተሰቡ ሲሞት ማንንም ሰው አይስቅም፡
-----------------------------------------------
እናት ስታነባ፤
ልጅህ ስትተክዝ አባትህ ሲገደል፡
እንደት ሰው ይችላል፤
ይህን ሁሉ ሴራ ይህን ሁሉ በደል!!
ወሎዬ_ነኝ_ስልህ
፤
በነገር አሻጥር በወሬ እምታስረኝ!?
ማን እንድሆን ፈለክ፤
ከወሎየነት ውጭ በል እስኪ ንገረኝ!?

▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
እውነት ለመናገር፤
#ዘረኝነት ይዞን ማንንም አንጠላም፡
ይህ ፀያፍ ክስተት ነው፤
አሏህ ከልክሎናል በእምነታችን ኢስላም፡
ይህን ህግ ደግሞ፤
ያለምንም ክስተት የወሎ ህዝብ ያምናል፡
ግን ባንድ ወገን ጥረት፤
በአንድ እጅ ጭብጨባ ይህ እንደት ይሆናል
!!
▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
ዛሬም እንላለን፤
ማንም አይሙትብን ማንም አይታረድ፡
ከሰው አንጠብቅም፤
የአለሙ ጌታ አሏህ ሰላም ይፍረድ፡
እኛ እንፈልጋለን፤
ያለ ምንም በደል ያለ መጠራጠር፡
ለዘላቂ ልማት፤
ነገ ዛሬ ሳይል ህዝቡ ሰላም ይፍጠር፡
ወሎ ገራገር ነው፤
ሰው ወዳድ ነው ህዝቤ፡
እኔም ወሎዬ ነኝ፤
የመልካምነትን ሀቅ ተገንዝቤ፡
የትኛውም ቦታ፤
መኖር እችላለሁ ማንንም አክብሬ፡
በፍቅር በመውደድ፤
በተቀደሰ ሀሳብ ደስታ አነባብሬ፡
👉ዘረኛ_አይደለሁም፤
አማኞችን መውደድ እንድህ ነው ነገሬ፡
ይህን ግን አልክድም፤
እኔም ወሎዬ ነኝ ወሎ ነው ሀገሬ፡

▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
✍️በኑረዲን_አል_አረቢ
▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
▴▴
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
متن أصول الثلاثة ۹
Abu Useymin
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖

📚ኪታብ ኡሱሉ ሰላሳ

            ➧ክፍል 
❞

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1

@abuUseyminabdurehman
¶ሓቂቃ ራሳቸዉን ከፊትና ጠብቀዉ ቁርአን የሚያቀሩ ኡስታዞች አላህ ያብዛቸዉ ይጠብቃቸዉ!

¶ተጂዊዱ ጠብቀዉ ተማሪዎች የሚያርሙ ኡስታዞችም አላህ ያብዛቸዉ ይጠብቃቸዉ!

➧አሁን ላይ የፊትና በር ከፍችና ዝም ብለዉ መቅራታቸዉ ብቻ የሚያዩ ተማሪዎች ተጂዊድ
ሳይስተካከል ቶሎ ለማስከተም በሚል የሚሰባብሩ ዝም ብለዉ የሚያሳልፉ በዝተዋል!


➧አላህ ሂድያ ይስጣችሁ ሓቂቃ ለዛዉ ብር ተከፍሏቸዉ እንድህ መጫወት ሲጀመር ባይከፈልስ ለምን የአላህ ቃል እየተሰባበረ ሲቀራ ዝም ይባላል ጎበዝ አቅማችሁ ካልደረሰ አድባችሁ ተቀመጡ ዓሊሞች ዘንድ ቁጭ ብላችሁ ቅሩ አንደየ ስለተከተመ ብቻ አቀራለሁ ብሎ ቁርአን ማበላሸት ምን አይነት ደዩስነት ነዉ

➧አረ አላህን ፍሩ ለራሳችሁ የምሰባብሩት አንሶ ሰዎች ቁርአን እንድሰባብሩ አታድርጉ አቅማችሁ አዉቃችሁ እደሩ!!ቦታዉ ለዓሊሞች ልቀቁ!!

➧አንዳዶችም አሉ ስለሚያሳልፏቸዉ ብቻ እዛ የሚቀሩ በተጂዊድ አሳምሮ የሚያቀራትማ እሱ ያጠብቃል እያለች የምትሸሺ ወደት ነዉ ሽሽት አስተካክለሺ ከቀራሺኮ እሱም አንችን እንድትደጋግሚ አይነግርሺም ለአንቺ በማዘነዉ
የሚመላልስሺ አስተካክለሺ እንድትቀሪ ስለዚህ ተመከሪ አጥብቆ የያዘሺ አጥብቀሺ ያዢ!

➧ያ ዝም ብሎ የሚለቅሺ እየሰባበርሺ ወዳ ጣይ
ሰባብረሺ ቀርተሺ ምንም አትጠቀሚ አስተካክለሺ ከቀራሽዉ ግን ሁለየ ትጠቀሚያለሺ ሰዎችንም ትጠቅሚያለሺ!!

✍️ቢንት አራጋዉ የዑሰይሚን ማሚ

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
✍️ወሎ_ሁኖ_አያውቅም!!
----------------------------
በሀበሻ ታሪክ በዚህች ሀገር ክስተት፡
ባንዳ ሆኖ አያውቅም ወሎ በስህተት፡
ወደ ኋላ ሳይዞር ሳያወልቅ ጥምጣም፡
#ምሽግ_ሰባሪ_ነው_የወሎ_ሽርጣም፡
በሚዲያ ወጥተህ ጠላት ከመለመን፡
በገንዘብ ከመስራት ጠላትክን ከማመን፡
#የወሎን_ሳተና_ጀግንነቱን_እመን!?

------------------------------------------
▪️ወሎ_በጠላት_ፊት_አያቀረቅርም፡
ዘር ስለማይቆጥር ሰፈር አያፈቅርም፡
አቅራሪው ፎካሪው ፊኛ ቢወጥርም፡
ወሎ
#በባንዳነት አይጠረጠርም፡
ህዝቤ ድምፅ ይሆናል ለእነዚያን ወንድሞች፡
መቀበሪያ ላጡት
#የትግራይ ሙስሊሞች፡
የኢስላም ልጆችን እኖዳቸዋለን፡
ድሮስ ከነርሱ ጋር እኛ መች ፀብ አለን!!

----------------------------------------
የዚህች ሀገር ጠላት የታሪክ ጠባሳ፡
የጥቁር አሻራ ደግሞም የሀበሳ፡
በጭካኔ ድርጊት የግፍ ፍርደኛችን፡
አንተና እሱ ናችሁ የሀገር ባንዳችን፡
ጨክን የወሎ ልጅ ምረር እንደ ኮሶ፡
በየደረስክበት ንፁህ ደምህ ፈሶ፡
እንደት ትሆናለህ ሞትህ ተደግሶ፡
የፌስ ቡክ አርበኛ
#ባንዳ ነህ እያለህ፡
ጠላት ጋር አብሮ ደፍሮ እያስገደለህ፡
የቱ ነው ጠላትህ ስንቱን ትችላለህ፡
ህዝቤ ቂም አታውቅም
#ወሎ ትለያለህ፡
--------------------------------------------
ለፈሪ ፉከራ ለባንዳው ቀረርቶ፡
ይሸኘዋል እንጂ የሰራውን ሰርቶ፡
አያሸረግድም #ኤጁ ትጥቁን ፈቶ፡
ወሎ ሲጠናከር ተው አይንህን አትሽ፡
ባንዳው ራስህ ነህ ማንነትክን ፈትሽ፡

👉ወሎ____
ፍቅር ደግነት ጋር ልቡ ላይ ፀድቆበት፡
ውልደቱና እድገቱ ጀግንነት ሆኖበት፡
ሀብት እየዘረፈ የኖረ ሲለቅም፡
በፌስቡክ አርበኛ
#ወሎዬ አይናቅም፡
ቀርቦ አብሮት ያልኖረ ይህን ህዝብ አያውቅም፡
ወሎ ፍቅር እንጂ ጥላቻ አይሰንቅም፡
የራሱን ሀቅ እንጂ የሰው አይናፍቅም፡
ደፍሮ ለወረረው ርስቱን አይለቅም፡
ሀገር አፍራሽ ባንዳ ወሎ ሁኖ አያውቅም፡

------------------------------------------------
#ወሎ_ታሪክህ_ይመስክር!!
-------------------------------------------
✍️ኑረዲን_አል_አረብ

http://t.me/nuredinal_arebi