💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Forwarded from Deleted Account
✔️ ሞትና ቀጣይ ሂደቶች

- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣

- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ

ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡

1- ልብሴን ያወልቃሉ፣

2- ያጥቡኛል፣

3- ይከፍኑኛል፣

4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣

5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣

6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣

7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡

ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡

8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል

- ቁልፎቼ 🔑🗝

- መጽሐፎቼ 📚

- ጫማዎቼ 👟

- ልብሦቼ 👖👔…..

በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣

- የዓለም 🌍 እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣

- የኢኮኖሚው 💰 ቀውስም አልተፈጠረም፣

- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ🧾 ይወጣል፣

- ንብረቴ 💸🏠🚘 የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣

- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤

- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል

- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤



ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …

በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ

1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ

2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣

3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣

የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ

ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!

1- መልክህ፣

2- ሀብትህ፣

4- ጤናህ፣

5- ልጅህ፣

6- ቪላህ፣

7- ዝናህ፣

8- ሚስትህ/ባልሽ

ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ

እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ

ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡

እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ

1- በግዴታዎች፣

2- በሱንና ነገሮች፣

3- በድብቅ መፅውት፣

4- መልካም ሥራ አብዛ፣

5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣

ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡

መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡
☘☘☘☘☘☘
"ውዷ _እህቴ"

⏭ትግስትን ሶብርን ስንቅሺ!
የአላህን ቃል ቁርአንን ጓደኛሺ!
ተወኩልን ተስፋሺ አድርገሺ ይዘሺ
"ኢልምን ከመፈለግ አትሰልቺ"!!
#ሴት_እህቶቻችን_ለሴት_እህቶቻችን_ሊጨነቁላቸው_ይገባል!

┈┈••••○○❁❁○○••••┈┈•
#ሸይኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሃዲ አልዋዲዒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–
"ይህ ኢስላማዊው ማህበረሰብ ሙስሊም እህቶቿን የጥፋትና የማጥፋት ተጣሪዎች እንዳይወስዷቸው (ወደጥፋት እንዳይነጥቋቸው) ዘንድ በጣም የሚያሳስባት ሴት ያስፈልገዋል!"
[📚 አልኢንቲሳር ሊሑቁቂ:’ልሙእሚናት ገፅ 6 📚]

የሚያሳዝነው የአጥፊዎቹ ተጠናክሮ መስራት ሳይሆን የአልሚዎቹ ማንቀላፋት ነው!

የነቃሽ እህቴ ሆይ ለሌላው ሙስሊም እህትሽ አስቢላት ኢስላምን በጥልቅ እንድትረዳ የበኩልሽን አስተዋፅኦ አበርክቺ! ቢያንስ መሰረታዊ የዲን እውቀት ይኖራት ዘንድ ጥረት አድርጊ! "ያወቀ ይነቃል" ነውበማሳወቅ ላይ በርቺ ተበራቺ!! አደራሽን ከእዝነት ከርህራሄ የመነጨ አካሄድን ተላበሺ ያኔ የሸፈተች እህትሽን ልብ መግዛት ትችያለሽ!!

አላህ ባለሽበት የኢስላም ገፅታን የምታስወቢ ሌሎች እህቶችሽን ለማቅናት የምትለፊ የዲን ጀግና ያድርገሽ!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
#ሰለፎቻችን_የሴቶችን_ፈተና_ምን_ያክ_ይጠነቀቁ_ነበር!?? እንመልከት
፠በበይተል ማል ተቆጣጣሪ ተደርጌ ብሾም ታማኝ ሁኜ እገኛለሁ፤በሴት ልጅ ግን ነፍሴን አላምናትም። ዐጧዕ ረሂመሁሏህ
ምንጭ ሲየር አዕላም አንኑበላዕ 5/87-87
፠ሸይጧን በሴት ልጅ መቶ እስኪፈትን ድረስ ተስፋ አይቆርጥም።
ሰኢድ ኢብኑ ሙሰየብ
ምንጭ ሲየር አዕላም አንኑበላዕ 4/237
፠ሰኢድ ኢብኑ ሙሰየብ አንድ አይናቸው ጠፍቶ 84 አመት ሁኗቸው ይሄን ተናግረዋል፦
-እኔ ዘንድ እንደ ሴት ያለ አስፈሪ ነገር የለም።
-ሴት ልጅ ባንተ በኩል ከመጣች እስከምታልፍ ድረስ አይንህን ጨፍን። አነስ ረዲየሏሁ አንሀ
፠ሁመይድኢብኑ ሂላል እንዳወሩት፡ አስወድ ኢብኑ ኩልሱም የሚባል ሰው ነበር ከቤቱ ወጥቶ ጉዞ በሚጀምር ጊዜአይኑን ከእግሩ አይነቅለልም ነበር።አንዳንድ ሴቶች ፀጉራቸውን ገልጠው ተቀምጠው እሱ ካለፈ ባትሸፍኝ ችግር የለውም ሰውየው እኮ አስወድ ኢብኑ ኩልሱም ነው ይሉ ነበር። ምንጭ አዝ ዙህድ 256
፠ሀሳን ኢብኑ ሲናን ለኢድ ሶላት ወጥተው ሲመለሱ ባለቤታቸው"ዛሬ ስንት ቆነጃጂት ሴቶችን ተመለከትክ?"አለቻቸው።ይሄንኑ ጥያቄ ስትደጋግምባቸው"ወየውልሽ ከቤቴ ወጥቼ እስክመለስ ድረስአውራ ጣቴን እንጂ አላየሁም" አሏት።ምንጭ አል ወረዕ ሊብኒ አቢ ዱንያ
፠ወደ መጥፎ ነገር (ባጢል) መመልከት ማዘውተር ሀቅን ከማወቅ ይከለክላል።ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም ምንጭ ሂልየቱል አውልያዕ 2/8
አሏህ ከሚጠቀሙት ያድርገን።

✍كوني سلفية على الجادة
▪️قال ابن القيم رحمه الله تعالى:

((إن في القلب قسوة لا يذيبها إلا ذكر الله تعالى، فينبغي للعبد أن يداوي قسوة قلبه بذكر الله. ))

📙 [الوابل صيب(١٠٧)]

🔺ልብ ውስጥ አሏህን ማስታወስ እንጂ የማያቀልጣት ድርቀት አለች

አንድ ሰው ልቡን አሏህን በማስታወስ ሊያክም ይገባል
ወጣቶች እንደሚተናኮሏትና እንዳስቸገሯት በመናገር
ለወንድሟ አቤት ያለችውን እህት! ኢስላማዊ አልባሳት መሸጫ ወስዶ ለፊትና የማያጋልጥ ኢስላማዊ ልብስ ገዛላትና መልበስ ጀመረች። ከተወሰነ ጊዜ በኃላ አሁንም ወጣቶቹ ያስቸግሩሻል? በማለት ጠየቃት። የእህቱ ምላሽ፤ "በአላህ ይሁንብኝ ይህንን ልብስ ከገዛህልኝ ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ያከብረኛል" የሚል ነበር። ወንድሟ ይህን ሲሰማ እንዲህ አላት « የሚፈታተን ልብስ በመልበስ አንቺ ነበርሽ ማለት ነው የምትለክፊያቸው። እነሱ ቢሆኑ ኖሮ የጨዋ ልብስ ከለበስሽ በኃላም ማስቸገራቸውን ይቀጥሉ ነበር»።

[ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ اﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﻗُﻞ ﻷَِّﺯْﻭَاﺟِﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺗِﻚَ ﻭَﻧِﺴَﺎءِ اﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﻳُﺪْﻧِﻴﻦَ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻦَّ ﻣِﻦ ﺟَﻼَﺑِﻴﺒِﻬِﻦَّ ۚ ﺫَٰﻟِﻚَ ﺃَﺩْﻧَﻰٰ ﺃَﻥ ﻳُﻌْﺮَﻓْﻦَ ﻓَﻼَ ﻳُﺆْﺫَﻳْﻦَ ۗ ﻭَﻛَﺎﻥَ اﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭًا ﺭَّﺣِﻴﻤًﺎ] الأحزاب 59

«አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» አል አህዛብ 59

አላህ ሆይ! እህቶቻችንን የፊትና ምክኒያት ከመሆን ጠብቃቸው። ከሸይጣን ወታደሮች ሁሉ ሰትራቸው። የትክክለኛ ሒጃብን ውበት አሳያቸው። በሀያእ አስጊጣቸው!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሶላቱን ከማይሰግድ በአላህ እጠበቃለሁ !

እህቴ ሆይ!

➻ሰላት የጋብቻ ዋነኛ መስፈርትሽ ይሁን!!

➻ለፈጠረው አምላክ ያልተናነሰ፣ ለነብሱ ያላዘነና ትእዛዝን ያላከበረ ሰው ላንቺ የሚያስብና የሚራራ አይሆንም!!

➻አላህን ከወደድሽ ወዳጆቹን ትወጃለሽ ለትእዛዛቱ እጅ የማይሰጡ ፋሲቆችን ትጠያለሽ፣ ትርቂያለሽም!!
ሰው እንደውሎው ነው!!

© ተንቢሀት።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሙሓደራ 74 የቀልብ በሽታና መደኃኒቱ በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር አልአሩሲ አል-አይመሮ المحاضرة…
በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር ሀሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁሏህ)
📌 አዲስ ሙሀደራ

🔶  دَاءُ الْقَلْبِ وَدَوَاؤُهُ

🔶 የቀልብ በሽታና መደኃኒቱ

🎙 الأُسْتَاذُ أَبُو مُسْلِمٍ عُمَرُ بنُ حَسَنٍ الْعَرُوسَيّ

🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን  አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)  
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሙሓደራ 091 ረድ በሙሓመድ ሱሩር ላይ
Ustaz Kedir Ahmed
ሙሓደራ 091
ረድ በ ሙሓመድ ሱሩር ላይ ለቀጠፈው ቅጥፈት እና ጅሕልናው የተብራራበት
በመረጃ የተደገፈ አጥጋቢ እና በቂ መልስ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
የዩሱፍ ፊልም እና መሰል ታሪኮችን ኢስላማዊ ፊልም በሚል ስያሜ
ፊልም አዘጋጅተው የማያቀርቡት
እውን ኢስላማዊ ነውን ወይም ደግም ኢስላማዊ ድራማ የሚባል አለን?

ከቀረበለት ጥያቄ ጋር በማያያዝ አብራርቶታል።

🎙 በኡስታዝ ኸድር አህመድ አልኬሚሴ ሀፊዘሁሏህ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎ሴት ልጅ ድምፅን ከፍ ተደርጎ የሚሰገዱ ሰላቶችን ስትሰግድ á‹ˆáŠ•á‹śá‰˝ አካባቢው ላይ አለመኖራቸውን ካረጋገጠች ድምፇን ከፍ አድርጋ መስገድና ማሰገድ ትችላለች??

➧ሸይኽ ዓብድልዓዚዝ ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና 《ሴት ልጅ ደምፅ ከፍ ተደርገው የሚሰገዱ ሰላቶችን (እንደ ዒሻእ መግሪብና ሱብሂ)  ወንዶች በምትሰግድበት አካባቢ አለመኖራቸውን ካረጋገጠች ድምፇን ከፍ አድርጋ መስገድ ትችላለች??? ተብለው ተጠይቀው 

🌺ሲመልሱ:

➧《ሴት ልጅ ድምፅ ከፍ ተደርገው የሚሰገዱ ሰላቶችን  ወንዶች በሌሉበት ቦታ  ሴቶችን ኢማም ሆና እያሰደገደች ከሆነ የምታሰግዳቸው ሴቶች የቂርአቷን ንባብ በማድመጥ እንዲጠቀሙ ደምፇን ከፍ አድርጋ በመቅራት ማሰገድ ትችላለች።

➧ለብቻዋ እየሰገደች ከሆነ ግን ለራሷ ብቻ እንዲሰማት ያህል ነው መቅራት ያለባት።

➧ከኢማሟ ጋር የምትሰግደው አንዲት ሴት ብቻ ከሆነች ኢማሟ ከቀኝ ጎን አበራት ትቁም።

➧ከአንድ በላይ ሴት ሰጋጆች ከኢማሟ ጋር አብረው ከሰገዱ ከኢማሟ ከቀኝና ከግራ ጎኗ አብረዋት ይቁሙና ኢማሟ መሀከል ላይ ትቁምና ታሰግዳቸው።

📚የሼኹ መጅሙዓል ፈታዋ መፅሀፍ ቁጥር 12 ገፅ 131።

🖋𝓪𝓫𝓾 𝓲𝓫𝓻𝓪𝓱𝓲𝓶𝓮

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
ትዳርን ለምንድነው የምትፈሩት?
♻️በኡስታዝ ከድር አህመድ(አቡ ጅወይርያ)አል_ኬሚሴ

✔️በኢብኑ አባስ መርከዝ የተደረገ ሙሃደራ።
〰〰〰
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
✅✅ ኡሱሉ ሰላሳ👉 ክፍል አምስት⑤

👉 ካፊሮችን ወዳጅ አድርጎ መያዝ ያለው አደጋ

🎙¶¶ አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ¶¶
Audio
✅✅ ሀያእ የውበት መገለጫ ነው ✅

👉 የሴት ልጅ ውበቷ አይናፋርነቷ ነው
👉 ሀያእ ከመጥፎ ስራ ግርዶሽ ይሆናል
👉 ሀያእ ያላት ሴት ሁሌም በመልካም ባህርይ ላይ ናት ወደ መልካም ይገፋፋታል
👂👂👂👂👂
🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
《 هل الأفضل للمرأة أن تصلي في بيتها جماعة مع أهلها أم تصلي منفردة ؟ 》

▪️الشـيخ العلامـة
سليمـان بن سليـم الرحيلـﮯ
- حفظـہ اللّـہ تـعالـﮯ -

•┈┈••••○○❁🌷❁○○••••┈┈•

نسـأل اللــہ ان ينفــ؏ بهـذا المقـطـ؏ الجميـ؏ .
ሼህ ሱለይማን ኢብን ሰሊም አል-ራሄሊ እድህ ይላሉ ሴት ልጅ እቤትዋ ውስጥ ትስገድ ይህ የተወደደ ነው ከአይን አርቃ ትስገድ ጀመአ ይስገዱ የተወደደ ነው