💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
➧በአል-ኢህሳን መርከዝ የተነበበች ግጥም

➲ይደምቃል አል ኢህሳን!!
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸

አልሀምዱ ሊላሒ ይገባው ምስጋና፡
በመዘሀበል ሀቅ ታድመናልና፡
የአሏህ እዝነቱ ይውረድ በሙሀመድ፡
በተውሒዱ አርበኛ በኢማኑ ገመድ፡

~~
ሽንጣቸውን አስረው የስደት እርግቦች፡
ለእስልምና ሲባል ማሩን ሰጥተው ንቦች፡
መንጥቀው አምጥተው ከኢኽዋን መንጋጋ፡

ብዙ ክስተት አልፈው ቢደርስም አደጋ፡
በአሏህ እርዳታ በዕህቶች ልፋት፡
አያሌ ችግር ነው መርከዟን ያለፋት፡
ውድ ጌጣቸውን ወርቃቸውን ፈተው፡
ችግር መከራውን ሁሉን ለአሏህ ሰጥተው፡
መጋጌጥ መኳኳል መቀያየር ትተተው፡
ውድ ሀብታቸውን ለኸይር ነይተው፡
ያውና አየናቸው መርከዙን ገንብተው
፡
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
የአርሹ ባለቤት አሏህ ለኛ ፈቅዶ፡
በሰለፍያ ላይ አገናኘን ወዶ፡
በነቢ ሱና ላይ በዱንያ ላይ ቆመን፡
በአኸይራም ደግሞ በጀነት ያድመን፡
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
▸
እውቀትን ፍለጋ ካገር የወጣችሁ፡
ከእናትና ከአባት የተለያያችሁ፡
ወንዶችና ሴቶች ህፃናት ሆናችሁ፡
ከእቅዳችሁ በላይ ይፈፅምላችሁ፡
የመጣችሁበት እውቀቱም ይግራችሁ፡
~~~

ሀጃዊራ መጥቶ ከአጥር ጋር ቢጋጭም፡
ኢኽዋን ተደናብሮ ሀሳቡን ቢረጭም፡
መረጃ አልባ ተረት ሁሌ ቢያሰራጭም፡
የመርከዟ ስኬት ፈፅሞ አይቀጭጭም፡
ግባችን ትልቅ ነው በአጭሩ አንቀጭም
፡
```````

ከሁሉም አቅጣጫ ሒጂራ ያደረጉ፡
መሸቃውን ችለው ሀቅ የሚፈልጉ፡
አሉባልታን ትተው ወስነው የረጉ፡
ለሒዝብዮች ጩኸት የማይበረግጉ፡
ንፁህ ሰለፍዮች አሉን ጀግና ቆራጥ፡
አሏህን የፈሩ አስበው ለሲራጥ፡
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
ከላይም ከታችም ጠማሞች ሲዝቱ፡
ተውሒድን በተማርን ወሬ እሚወዝቱ፡
ጆሮ የማይሰጡ አሏት መርከዚቱ
፡
--------------------------------------
በትንሿ መርከዝ የተሰበሰቡ፡
ከዑስታዞቻቸው ኢልም የሚከስቡ፡
ኢስላምን ለመርዳት ሀቅን ያነገቡ፡
የሱናን ጎዳና ወስነው የገቡ፡
-----------------------------------

ፀንተው የሚጓዙ በተውሒድ በሱና፡
መስሚያ የሌላቸው ለፈሪ ልቦና፡
አሉን አናብስቶች ጎበዝና ጀግና፡
እንደሰው አስበው እንደ ዝሆን ገዝፈው፡
የዱንያን ስንክሳር ሹብሀውን ገፈው፡
አህባሽ ሱፍዮችን በመረጃ ገርፈው፡
ሐጃዊራወችን በሁጃ አወላክፈው፡
የኢኽዋንን መንጋ እስበሱ አጠላልፈው
፡
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
ይፀናሉ ብለን የምናስባቸው፡
ርቀው የመጡ ከቤተሰባቸው፡
ለአሏህ ስንል ከልብ የምንወዳቸው፡
ከሴት #ሉባኮወች ከወንዶችም ፅኑ፡
ሱናን ለመዘመር ቆርጠው የወሰኑ፡
~
በተውሒድ ጎዳና በቀደምቶች ልሳን፡
በሶሀቦች ፈለግ በጀዕፈር በሀሳን፡
ኢንሻዐ-ረቡና ይደምቃል አል ኢህሳን
፡
~~
👉#በኑረዲን_አል_አረቢ__!!
~~
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/AlihsanCharityAssociation
https://t.me/AlihsanCharityAssociation
Audio
✅ አዲስ የኪታብ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖➖

📚አቂደቱ አህሊሱነቲ ወልጀማኣ

【ክፍል፦ ⓶➂】

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
✍️ምክሮች ለሚስት

☞ ግትርነትን ተጠንቀቂ መልካም ትዳርን ያናጋል
☞ ሌሎችን አትመልከች፤ ይህ ድህነት ማለት ይህ ነው
☞ ዘውትር ውበትሽን ጠብቂ፤ የሴትነት መስህብሽ እሱ ነው
☞ ባለቤትሽ ለጀነት ወይም ለእሳት ምክኒያት ይሆናልና፤ ትኩረትሽን እንዳያጣ!

☞ ሙግትን ተጠንቀቂ፤ ሙግት በሽታ ነው!
☞ አቀባበልሽን አሳምሪ፤ የመጀመሪያው የፍቅር ማጠናከሪያ ነው!
☞ ለስላሳ ባህሪ ይኑርሽ፤ ኸይር ስታዪበት ቶሎ ተደሰቺ፤ ዘውድ የጫነች ንግስት ትሆኛለሽ!

©ተንቢሃት

https://t.me/https_Asselefya1
ሪዝቅ ማለት ገንዘብ ብቻ አይደለም!!
አላህን የምትፈራ እና የምታከብርህ

ሚስትም ትልቅ ሪዝቅ ናት!
▪️ነገረኛ አትበሉኝና አንዳንድ ወንዶች አሉ
ሚስታቸዉ ከአረብ ሀገር ተነቅባ ስትመለስ አሮጊት መስለሺ ከቤቴ አትገቢም በዛዉ ወደ አባትሺ ቤት የሚሉ።
በርበሬ ነበር ማጠን ዉይ ደግሞ በርበሬ ተወዷል ቅንጭብ በአይናቸዉ ማስገባት ነበር።


✍️የተወሰዴ!

➧ተመችቶኛል የምር ሓቂቃ የደዩስነት ጥግ ነዉኮ ማንም አያየኝ ያንተ ብቻ ልሁን አንተ ብቻ እየኝ ብትለዉ በሺዎች ካላዩሺ ነዉ የሚል
የደዩስ ጥግ አላሁመ ሙስተዓን!!


➲ይሄን የሚል ባል ያለሽ እዳለሺ ወደ አባትሺ ሂጂ በፍፁም ኒቃብሺ ለሱ ብለሺ የክብር መገለጫሺን አዉልቀሺ እዳትጥይ ሲፈልግ ራሱ ባሉ ጣይዉ አላህ ከሱ የተሻለ እንደሚሰጥሺ አትጠራጠሪ
ምክንያቱም አላህ ለሚፈራ ሰዉ ለሱ መዉጫ መንገድ ያዘጋጂለታል ካላሰበበት ቦታም ሲሳይ(ሪዝቅ)ይሰጠዋል ነዉና። በጌታሺ ትክክለኛ የቂን ይኑርሺ በአቋምሺ ፀኚ ዉዷዬ!!

(የሱና ቤት አይጠብም ተቀላቀሉን!)
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
👉ቁርኣን መንገድ የጠፋበትን ይመራል!

👉ቁርኣን ብቸኛን ልብ በፍቅር ይሞላ

👉ቁርኣን የተከዘን ልብ በደስታ እሴት ይሞላል!

👉ቁርኣን የተጨነቀን ይፈርጃል!


https://t.me/https_Asselefya1
ውዷ እህቴ !!!

በዚህ ዘመን ስለ ዲንሽ የምታስተምርሽ ጓደኛ ካገኘሽ አጥብቀሽ ያዣት

ይህ ዘመን መልካም እሚመኙ እና ወደ መልካም የሚያመልክቱ ሰዎች ያነሱበት ዘመን ነውና!!!


https://t.me/https_Asselefya1
🔊ምክር ለባሎች!!
➖➖➖➖➖➖

☞ሚስትህ በውበቷ እጅግ የተዋበች ቆንጆ ብትሆንም አይንህን ከወጣችውም ከወረደችውም ጋር እዚህም እዚያም የምታሳርፍና የምታንከራትት ከሆነ የሚስትህ ውበት በፍፁም አይታይህም።

☞አይንህን ሰበር አድርግ ከዛም ሚስትህን የምድር ውብ ሴት ሆና ታገኛታለህ። የተብቃቃ ሰው አሏህ ያብቃቃዋል። ጥብቅ የሆነ ሰው አሏህ ይጠብቀዋል።

☞መብቃቃት በገንዘብ ብቻ እንዳይመስልህ። በተሰጠችህ ሚስት፣ ልጆች፣ ትዳርህና በአጠቃላይ አምላክህ አሏህ እጅህ ላይ ባደረጋቸው ፀጋዎች ሁሉ መብቃቃትህ ከመብቃቃት ውስጥ ይካተታል። ስለዚህ አሏህን አመስግን።

☞የተሻለ አገኛለሁ ብለህ ከተንከራተትክ ተንከራተህ ትቀራለህ። ትዳርህ ደስታ ይርቀዋል። ቤትህ የተረጋጋ አይሆንም። ከትዳር አጋርህ እምነትን ታጣለህ። ደስታዋንም ትገፈዋለህ። ስለዚህ በእጅህ ያለችውን ፅጌረዳ ተንከባከባት!!


👉ተነካክቶ የተወሰዴ ባሎች ተመከሩበት


©ቴሌግራም አድራሻችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ©
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/https_Asselefya1
يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡


(አሕዛብ ፡ አያህ 59)


https://t.me/https_Asselefya1
🔊ነቃ በይ!

እህቴ እስኪ አሏህን ፍሪ
እወቂው እሱኑ ድንሽን ተማሪ
በሰለፎች መንሐጅ በፅናት ዘውትሪ

ከጀግኖቹ መንደር በሱናው እደሪ
ከደጋጎቹ ጋርም ውሎሽን አሳምሪ
ይህ ነው የኔ ምክር በጨርቅሽ ጫፍ ቋጥሪ!!

https://t.me/https_Asselefya1
Audio
✅ አዲስ የኪታብ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖➖

📚አቂደቱ አህሊሱነቲ ወልጀማኣ

【ክፍል፦ ⓶➃】

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
✅ ⭕ እናት አባቱን የሰደ ሰው ቅጣቱ ⭕ ✅

📌♻️ قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله :

📌♻️ ሸይሁል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ (አላህ ይዘንለትና) እንዲህ ብሏል።

📌《وإذا شتم الرجل أباه واعتدى عليه وجب أن يعاقب عقوبة بليغة تردعه وأمثاله .. قال تعالى :(فلا تقل لهما أف)فكيف يشتمهما ؟ 》
✅ 《አንድ ሰው እናት አባቱን የተሳደበና በነሱ ላይ ድምበር ያለፈ ከሆነ እሱና አምሳያው ከዚህ ድርጊት ሊመልስ የሚችል ድካ የደረሰ ቅጣት መቅጣት ያስፈልጋል። ምክንያቱም አላህ በቁርአኑ (እናት አባታችሁን
#ኡፍ "እጭ" እንዳትሏቸው) እያለ እንዴት ይሰድባቸዋል?》
📚 المستدرك (١١٢/٥)