💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
🎀ከጥሩ ሚስት መገለጫዎች🌸💎
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➧የትም ብትሆን አላህን ትፈራለች፣ በሁሉም ነገር የነቢዩን ሱና ትከተላለች

➧ባሏ ያዘዛትን በሙሉ -ከዲን ጋር የሚጋጭ እስካልሆነ ድረስ- ትታዘዛለች

➧ከሷ ጥሩን ነገር እንጂ እንዳያይ፣ እንዳይሰማና እንዳያሸት ጥረት ታደርጋለች

ቤትና ንብረቱን እንዲሁም
ቤተ-ሰቦቹን ትጠብቃለች

➧እሱ የማይፈልገውን ሰው
አትጠጋም አታስጠጋምም


➧ባሏን ሳታሳውቅ ሱና ጾም አትጾምም
ከቤትም አትወጣም


የባሏንና የቤቷን ሚስጥር
በሚገባ ትጠብቃለች


➧ባሏን በመልካም ነገር ላይ
ታግዛለች ሲሰንፍ ታበረታታዋለች፣
ሲረሳ ታስታውሳለች


ሐላል ከስብ እንዲከስብ ሐራምን እንዲርቅ ዘወትር ትገፋፋዋለች፣ለእሷና
ለቤቱ ብሎ ዲኑ የማይፈቅደውን
ስራ እንዳይሰራም ታሳስበዋለች


➧ደስታና ሃዘኑን ትጋራለች፥
እርሱ ሐሳብና ጭንቀት ውስጥ ሆኖም እሷ አትስቅም፣ እሱ ማረፍና መደሰት በሚፈልግበት ወቅት ላይም እሷ በተቃራኒው ተከፍታ አታስከፋውም

➧በሚያደርግላት ነገር በሙሉ
ይብዛም ይነስ ታመሰግነዋለች

➧ቤቷን እያቀዘቀች የሰው ቤት አታሞቅም ቤቷንም እያፈረሰች የሰው ቤትአትገነባም!

አላህ የሰጣትን ልጆች በኢስላም ስርዓት ቀርጻ ታሳድጋለች ትልቁ የእሷ
ስራም ይህ እንደሆነ በማወቅ በስራዋ ትኮራለች
! ልጅም ያጣች እንደሆነ ታግሳ ተስፋ ሳትቆርጥ ጌታዋን ትለምናለች
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
አዲስ የኪታብ ቂርአት


📚አቂደቱ አህሊሱነቲ ወልጀማኣ

ክፍል፦ ⓷

🎙አቡአብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
◾️ሸህ ሷሊህ አልፈውዛን "አላህ ይጠብቃቸው" እንዲህ ብለዋል።

ዱአ ካደረጉ በኋላ ፊትን ማበስ በሸሪአችን ያልፀደቀ መሰረት የሌለው ተግባር ነው።

📕[إغاثة اللهفان 27-06-1438 هـ]
ፍቅር...

➛ፍቅር ማለት በትንሽ ፊደሎች የተዋቀረ ነገር ግን ትርጉሙ ሰፊ የሆነ ሳያስፈቅድ በልብ ውስጥ ሰርፆ የሚገባ የራሱ የሆነ ግፊት ያለው የፈጣሪ ፀጋ ነው።

➛ፍቅር ማለት ላፈቀሩት ሰው መኖር ማለት ነው። ፍቅር ከቃላት ድርደራ በላይ ተግባራዊ ገለፃን የሚሻ ልዩ ገፀ በረከት ነው።

➛ፍቅር መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ላፈቀሩት ሰው ራስን አሳልፎ እስከመስጠት የሚደርስ የሀይል ባለቤት ነው።


➛ፍቅርን በቃል መግለፁ ቀላል ነው ፍቅርን መኖር ግን ከባድ እና ትዕግስትን የመፈታተን ልምድ ያለው ነው።

➛ እውነተኛ አፍቃሪ የሚያፈቅረው ሰው 75% ስህተት ቢኖርበትም 25% መልካምነቱን ብቻ የሚያሳይ ልዩ መነፀር ያለው ነው።


➛ፍቅርን የሚዘምሩ ብዙዎች ናቸው የሚኖሩት ግን ጥቂቶች ናቸው።

➛እውነተኛ አፍቃሪ ፍቅርን በመስጠት የሚሽቀዳደም እንጂ ለመቀበል ሁሌ የሚጓጓ አይደለም።


➛በፍቅር ዐለም ውስጥ መሸነፍ በራሱ ማሸነፍ ነው።ለፍቅር መሸነፍህን ከውርደት የምትቆጥር ከሆነ ለአቅመ ፍቅር አልደረስክም ማለት ነው


➛ስለ ፍቅር በመሸነፍ ውስጥ ትልቅ የሆነ ማሸነፍ አለ።

➛እውነተኛ ፍቅር መቀመጫው ልብ ላይ እንጂ ምላስ ላይ አይደለምና የምላስ አፍቃሪ ሆነክ የልብ አፍቃሪዎችን እንዳትጎዳ ተጠንቀቅ!...


➛ብቻ ፍቅርን መግለፅ ከባድ ነውና አፍቅራችሁ ተረዱት።

✍️አላህ ሆይ ፍቅርን ከሚያወሩት ብቻ ሳይሆን ከሚኖሩት ከእውነተኛ አፍቃሪዎች አድርገን።

✍️@ተነካክቶ የተወሰዴ!!

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
🖋ከሚስትም ጠላት አለ‼️
➛➛➛➛➛➛➛➛➛


✍️ሀያሉ አምላካችን የዚህች የቅርቢቱ ዐለም ህይወታችን የተሟላ እንዲሆን ከጎምዛዛና ስልቹ የብቸኝነት እስር ቤት ወጥተን ጣፋጭ የሆነ በመተሳሰብና በመተጋገዝ ላይ የተመሰረተ የሰመረ ህይወት እንዲኖረን ትዳር እንድንመሰርት አዞናል ። ይህም ህይወት ፍሬ አፍሮቶ በልጆች ደምቆ ለቀጣዩ ዐለም የስኬት ህይወት የሚያዘጋጅ እንዲሆን የምታገባት የትዳር አጋርህ አላህን የምትፈራ በኢማን የተዋበች በቁርኣን ያጌጠች በሐዲስ ተኮትኩታ በሱና የታነፀች መሆን እንድትችል መልፋት ይኖርብሃል ። የዚህ አይነትዋ ሚስት የልጆችህ እናት ናት ። ሀላፊነታቸውን ትወስዳለች አንተ ወደ አኼራ ብትሄድም እሷ ልጆችህን ለቁም ነገር ታበቃለች ። አባታችን አላህ ይዘንለት እንዲሉ ትጥራለች ይህ የሚሆነው ግን አንተ በሷ ላይ ከምርጫህ ጀምሮ እስከ መጨረሻው በምትከፍለው ዋጋ ነው ። በተቃራኒው በዲኗ ላይ ካረዳሀት በዱንያዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ ካቶከርክ የቸልታህ ውጤት የሷ ጠላትነት ሊሆን ይችላል ። ለዚህ ነው አላህ ከሚስቶች ውስጥ ጠላት የሚሆኑ እንዳሉ እንዲህ በማለት የነገረን :–

" يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ مِنْ أَزْوَاجِكُمْ وَأَوْلَادِكُمْ عَدُوًّا لَّكُمْ فَاحْذَرُوهُمْ ۚ وَإِن تَعْفُوا وَتَصْفَحُوا وَتَغْفِرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيم ٌ"
التغابن ( 14 )

" እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተጓጎል) ለናንተ ጠላቶች የኾኑ አልሉ ፤ ስለዚህ ተጠንቀቋቸውይቅርታ ብታደርጉ ብታልፏቸውም ብተምሩዋቸውም አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው።

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➠በድኑ ጠንካራ የሆነ ጀግና እየተመኛሺ አንቺ ግን ገና ቃኢዳም አልጨረሺ እቴዋ አንች የምትመኚዉ አይነትኮ እሱም ይመኛል እ?!

➠so ምኞቱ ጥሩ ሆኖ ሳለ በተቻለ አቅም ራስሽንም ጠንካራ ጀግና ለመሆን ጣሪ።

➠ከአንቺ ሙከራ ጋር የተመኛሺዉ አይነት አላህ ይወፍቅሻል እናም ጠንክሪ ለማለት ያክል ነዉ።

✍️ኡሙ ዑሰይሚን

https://t.me/https_Asselefya1
ድክመትሽን የጥንካሬሽ ጉልበት አድርጊው!
ብልህነት ያንቺ ነውና
...ውድቀትሽ ለስኬት
መድረሻ የሚሆን ሙካራ መማረያ ልምድ
አርገሽ ቁልፍ አድርጊው ጥንካሬ ያንቺ ነውና
!

አንቺ ለውድቀት አልተፈጠርሽም
ምንም እንኳን ሂይወት ብትጠብሽ
ጠንክሪ ጥሎ የማይጥል አንድ አሏህ አለሽ!!!

https://t.me/https_Asselefya1
➧እህቶችዬዋ

👉እንደዉ ይች
👉አልችልም👈የምትባል አማረኛ ስንቶቻችንን አስራ አስቀመጠችን ካሰብንበት እንዳንደርስ ለመሆኑ እኛ ከሞከርነዉ የማንችለዉ ነገር ከአላህ ጋር ምን አለ?! እስከዛሬስ ሞክረዉ ያልቻልነዉ ምን አለ?!

👉እናም እህቶችዋዬ ይች አማረኛ ከላያችን ላይ አዉልቀን ጥለን 👉እችላለሁ👈 የምትለዋ አጥብቀን ይዘን ወደፊት እንጓዝ በአላህ ፍቃድ ካሰብንበት እንደርሳለን!!

✍️أم عثيمين بنت أراغاو

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
የሙሓመድ አወል መንዙማ ( 10 )
Abu Useymin
➡️ ተከታታይ ሙሐደራ
➛➛➛➛➛➛➛

የሙሐመድ አወል መንዙማ!!

የሽርክ ስንኞቹ ከራሱ ድምፅ ጋር!

➡️ ክፍል አስር

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

https://t.me/abuUseyminabdurehman/7287

https://t.me/https_Asselefya1
لماذا يركز الاعداء على المرأة؟
ج/ الإمام ابن عثيمين
➡️ ለምንድ ነው የዲን ጠላቶች ሴቶች ላይ ትኩረት የሚያደርጉት? እውነት ለነሱ አዝነው ነው?

♦️አጭር ድንቅ ምክር♦️

🎙الشيخ العلامة الإمام محمد بن صالح العثيمين رحمه الله تعالى

📼 مدة المقطع: 🔊 ٠٦:٠٦
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Audio
አዲስ የኪታብ ቂርአት


📚አቂደቱ አህሊሱነቲ ወልጀማኣ

ክፍል፦ ④

🎙አቡአብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1