💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم
➧ሉቅማን ለልጁ ከሰጣቸው ምክሮች አንዱ

وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِى ٱلْأَرْضِ مَرَحًا ۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍۢ فَخُورٍۢ

«ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፡፡ በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ፡፡ አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድምና፡፡


⚘https://t.me/https_Asselefya1
【يَا لِسَانُ قُلْ خَيْرًا تَغْنَمْ واسْكُتْ عَنْ شَرٍّ تَسْلَمْ مِنْ قَبْلَ أَنْ تَنْدَمَ】

✅ አንተ ምላስ ሆይ‼️ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀትህ በፊት፦ መልካምን ተናገር ትርፋማ ትሆናለህ። ከመጥፎ ነገር ዝም በል ትድናለህ።
Audio
➡️ ሰሞኑ በሚዲያ እየተደረገ ያለው የትዳር ጫረታ በተመለከተ የተሰጠ ምክር

♦️የሀያእ አስፈላጊነት
♦️የተሳሳተ የትዳር መንገድ
♦️የሴት ውበት በአደባባይ መግለፅ


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➡️ ሰሞኑ በሚዲያ እየተደረገ ያለው የትዳር ጫረታ በተመለከተ የተሰጠ ምክር ♦️የሀያእ አስፈላጊነት ♦️የተሳሳተ የትዳር መንገድ ♦️የሴት ውበት በአደባባይ መግለፅ 🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
ውድ እህቶቼ ከልብ ሁናችሁ አዳምጡት እስኪ!!!

➧ሀቂቀተን በዚህ ሰሞን የምንሰማው ነገር በጣም ነው የሚያሳፍረው!

ለምን ግን እያወቀን ሀያዐችንን እርግፍ አድርገን እንጥላለን ለምን ያአላህ ውዷ እህቴ ሆይ አላህ ሱበሀኑሁ ወተአላ ለአንቺ ያልቀደረውን ያልፃፈውን ላታገኝው ለምን እራስሺን ታወርጃለሺ ታረክሻለሺ??

➲እረ ተው ልብ ግዙ እንደዚህ አይነቱ ትዳር ቅርት ቢልብሺስ ራስሺን አዋርደሺ ያገኘሺው ትዳር ትዳር ሆኖ የምትኖሪ ይመስልሻልን? አይምሰልሺ እራስሺን አስከብሪ በጌታሺ ላይ ሙዕሚን ሁኚ የጌታሺን ትዕዛዝ አክብሪ አላህ አንቺ ካሰብሺው በላይ ይሰጥሻል! ለሁሉም ነገር ከልብ ሁኚ ቁጥብ ሁኚ እራስሺን አታዋርጂ!! ልብ ግዙዙዙ........✍ምክሩ ለእራሴም ነው አላህ ሂድያ ይስጠን እህቶቼ!!!
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ⑥⑥➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
Audio
بلال بن محمود العشي
🎤• للقارئ • الشيخ
((
#بلال_بن_محمود_العشي ))
↪️ውብ ቲላዋ ተጋበዙ!!
〰〰〰〰〰〰〰
ቁረአን የልብ ብርሀን የዱኒያ የአሄራን ሂወት የሚያቀና ውብ የማይጠገብ የአላህ ቃል ነው


https://t.me/UmuUseyminAselfiya
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዳን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
◾️ፃም የተደነገገበት ዋና አላማ
◾️የጥጋብና የረሀብ ተፅእኖ


《ክፍል 1⃣9⃣》
〰〰〰〰〰〰

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
አርበዒን 48ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
ደርስ
~~~~

~ አርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር
~ ለመርከዘ ተውሒድ የቁርኣን ሒፍዝ ተማሪዎች የቀረበ
~ ሐዲሥ ቁጥር – 4️⃣8⃣
~ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ pdf መልክ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/1672
#ለእህቴ_አድርሱላት___!

#ምርጫ_እንድህ_አይደለም።
---------------------------------
አውቃለሁ ይከብዳል ያለ ትዳር ኑሮ፡
የህሌና ፀፀት የውስጥ እንጉርጉሮ፡
ቀን ባለፈ ቁጥር እድሜ ይጨምራል፡
ያውም በዚህ ዘመን ፊትናውም ያስፈራል፡
አወ ብቸኝነት እጂጉን ያስጠላል፡
ጊዜው ሲረዝምብሽ ሊመስልሽ ይችላል!!
--------------//--------------------------
#ቢሆንም_ግን_እህት__!!
የችግሩን ክብደት እኔ ብረዳሽም፡
በዚህ መጥፎ ተግባር አብሽሪ አልልሽም፡
ደግሞ ለአንችም ቢሆን አያስደስትሽም፡
ለሙስሊሟ ጀግና ይህ አይመጥንሽም፡
--------------------------------------------
ጆይን ብሎ ገብቶ በሊፍት ለመውጣት፡
የማይሆን አስቦ የያዙትን ማጣት፡
ሀፍረትሽን ጥለሽ በሚዲያ መምጣት፡
ተመከሪ እህቴ ይህ ለአንች ነው ቅጣት፡
ተቆጠቢ እባክሽ እህት ተመከሪ፡
ወንጀል አትሰብስቢ ተይ አሏህን ፍሪ!!
---------------------------------------------
ዩቲዩብ ላይ ቀርበሽ ትዳር ስትጠይቂ፡
ውበትሽ እንድታይ ደፍረሽ ስትስቂ፡
ፈታኝ መጥፎ ነገር ፎቶ ስትለቂ፡
ወንድን ለመፈተን ተጋልጠሽ ስትዘልቂ፡
ወንጀሉ ከባድ ነው እህት ተጠንቀቂ!!
---------------------------------------------
ባል ፍለጋ ብለሽ በሚዲያ አትውጭ፡
አሏህን ለምኝው በአደብ ተቀመጭ፡
ለኢኽዋን ለአህባሽ ልብሽን አትስጭ፡
ትዳር ቀልድ አይደለም ጀግናውን ምረጭ፡
ለኢኽዋን ብትነግሪው የትዳር ንድፍሽን፡
በውስጥ አይመክርሽም አያውቅም ልክሽን፡
ስልጣኔ መስሎት ያረክሳል ክብርሽን!!
---------------//-----------------------
#ስለዚህ_እህቴ__!!
ቂያማ እየቀረበ እየበዛ ፊትና፡
ሀቁ እየተተወ በዝቶ ፍልስፍና፡
መፍትሔው ተረስቶ ተውሒዲና ሱና፡
የትዳር ጣዕሙ ደስታው ተረሳና፡
ፋራነት ተደርጎ መፅናት እስልምና፡
መሀይሙ በዝቶ አዋቂ አንሷልና፡
ሀራም ግንኙነት ንቃት ሆኗልና፡
ይህ ደግሞ ለእህቴ አይመጥንምና፡
ታገሽ አሏህ አለሽ ፀልይ ለረበና፡
እውነተኛ ውበት ይሔ ነው ቁንጂና፡
አሏህ ይሰጥሻል የሀቅ ሰው ጀግና፡
ቁጥብ ሴት ሁኝ እንጂ አሞተ ቆፍጣና፡
ቀጥ ብለሽ ተጓዥ በኢስላም ጎዳና፡
#እንጂ_ምርጫ_እንድህ_አይደለም!
------------------------------------------
በተውሒድ በሱና በእውቀት የመጠቁ፡
በፀባይ በአደብ እጂጉን የላቁ፡
የሴትን ልጂ ክብር ጠንቅቀው ያወቁ፡
በመንሀጀ ሰለፍ በሀቅ የረቀቁ፡
ሚስትነትሽን አምነው የሚንከባከቡሽ፡
ሱናውን ጠብቀው በደሴታ እሚያገቡሽ፡
እንድህ አይነት ጀግና ጠንካሮች እያሉ፡
ኢኽዋንን ለማግባት ታስቢያለሽ አሉ!?
ፖለቲካ ሰብኮ ከሱና እሚያርቅሽ!?
ከጠማማወች ጋር ከሚያስተዋውቅሽ!?
ለሰላማዊ ሰልፍ ሜዳ ከሚያዘልቅሽ!?
ዘወትር ጧት ማታ ከሚጨቃጨቅሽ!?
ለውስን ቀን እንጂ ይህ ላያዛልቅሽ!?
ሽርክ ቢዲዐ እንጂ ተውሒድ ላይቀልብሽ፡
ተይው ከወድሁ ይሔ ሰው ይቅርብሽ።
                                
ሱሪ ከሚገትት አስመሳይ አልጫ፡
ከፖለቲካ ጋር ተጣብቆ እንደ ሙጫ፡
ከገባሽ በኋላ ከሚጨንቅሽ መውጫ፡
ልንገርሽ አሁኑ ይስተካከል ምርጫሽ፡
ለእውነተኛ ፍቅር ለዘላቂ ኑሮ፡
ሰለፍይ ማግባት ነው ሰለፍይ አፍቅሮ፡
ሱፍይ ኢኽዋን አህባሽ ያረጋል ደንቆሮ፡
#አወ_እንድህ_አይደለም.....!!
እየተነዛነዝሽ ከመኖር ዘላለም፡
ውጫዊ ገፅታ ውበትና ቀለም፡
ጭራሹን በድፍረት በሚዲያው አለም፡
ተሳሳትሽ እህቴ ምርጫ እንድህ አይደለም፡
---------------------------------------------
ከኑረዲን አል አረቢ 2014
➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
➲የሶሀባ ሚስቶች ለባላቸው የነበራቸው ልዩ ፍቅር
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ከእለታት አንድ ቀን አቡ ደርዳዕ ከሚስት ኡሙ ደርዳእ ጋር አብረው ተቀምጠው ሳሉ ኡሙ ደርዳእ እንዲህ አለች

➜ጌታዬ አላህ ሆይ ! ባለቤቴ አቡ ደርዳእ እዚህ ዱንያ ላይ እርሱ እኔን ለትዳር ጠይቆኝ አግብቶኛል ፡ እኔ ደግሞ እርሱኑ ጀነት ላይ እንድትድረኝ እለምንሃለሁ አለች፡

➧ከዛም አቡ ደርዳእ ይሄን ስትል እየሰማት ነበርና እንዲህ አላት

➻እሱ እንዲሳካልሽ የምትፈልጊ ከሆነ ምናልባት እኔ ካንቺ በፊት ከሞትኩ "አንቺ እስክትሞች ድረስ ፈፅሞ ሌላ ባል እንዳታገቢ አደራ" አላት

➺ከዚያም ከግዜያት ቡሀላ አቡ ደርዳእ ሞተ

➲ኡሙ ደርዳእ በጣም ውብና ቆንጆ ነበረችና ከአቡ ደርዳእ ሞት ቡሀላ ሙዓዊያ ኢብኑ አቢ ሱፍያን ለትዳር ሊጠይቃት ወደርሱዋ ይመጣል

➫አስቡት ሙዓዊያ በጊዜው የሙስሊሞች መሪ አስተዳደር ወይንም መንግስት ነበር፡

➺ከዛም ሙዓዊያ የትዳር ጥያቄ ሲያቀርብላት እንዲህ ብላ መለሰችለት

➧በፍፁም ወላሂ ዱንያ ላይ ከአቡ ደርዳእ ቡሀላ ማንም ወንድ ቢመጣልኝ አላገባም፡ አላህ በርሱ ፈቃድ ጀነት ላይ አቡ ደርዳእን እስኪድረኝ ድረስ እዚች ዱንያ ላይ ባል ሚባል በፍፁም አላገባም አለችው።

📒📘📕📙📔 ሒልየቱል አውሊያ (224-225-1)
🖊ሑሴን አሕመድ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን


➰ክፍል ⑥⑦➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
أنس الجهني - قل هل ننبئكم بالأخسرين أعمالا
[ تلاوات خاشعة ▫️ tvquran@ ]
▫️• قُلْ هَلْ نُنَبِّئُكُمْ بِالْأَخْسَرِينَ أَعْمَالًا •▫️

• 🎙القــارئ ؛
#أنس_الجهني


🍀ጣፍጭ ቲላዋ🍀

🍃ከልባችሁ አድምጡት ልብን ይነካል

🍃 ደስታን ይፈጥራል ግፊት ያደርጋል

🍃የሙስሊም ህይወት ያለ ቁርአን ከባህር
እንደወጣ አሳ ነው::

https://t.me/UmuUseyminAselfiya
Audio
♦️አድስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

↪️ኪታቡ ዘዋጅ. الزواج
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➲ለ መርከዝ አቡ አዩብ online ተማሪዎች የሚሰጥ ደርስ

▪️ክፍል አምስት
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አዩብ ሙሀመድ ሰኢድ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➧ይድረስ 💎ለሱና እህቴ 💎

➷ እብደት ነው ጤንነት ምንድን ነው ነገሩ¿
የተፈጥሮን ውበት በአመድ መቀየሩ


➷ አንች እኮ ልዩ ነሽ ውብ አድርጎ ፈጥሮሻል
እርሱው በጥበቡ አሟልቶ ሰጥቶሻል

➷ ያአንች መዋቢያሽ በቀን 5ጊዜ ውዱእ እያለልሽ
በቻይና ዱቄት ምነው መለቅለቅሽ ጊዜ ማባከንሽ


➷ ኮስሞቲክ ሜካፑ ምን ያደርግልሻል
ተፈጥሮሽ ልዩ ነው ሁሌም ያምርብሻል።

መንቁል!

https://t.me/https_Asselefya1
➧ወንድ ልጅ ሴትን መውደዱ #ተፈጥሯዊ ነው
ነገር ግን እሷን መሰተሩና መጠበቁ ደግሞ
#ወንድነት ነው።

https://t.me/https_Asselefya1
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዳን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
◾️ፃም የተደነገገበት ጥበቦች ውስጥ
◾️ነፍስያን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል


《ክፍል 2⃣0⃣》
〰〰〰〰〰〰

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w