💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➻ ክፍል አስራ ሶስት ➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧አንድ ሰው የመልካም ባህሪያት ሁሉ ከእርሱ ላይ ካልተሰባሰቡ ከኢማምነት ደረጃዎች ሊደርስ አይችልም፡፡ በመልካም ባህሪያቶች ለሰዎች አርአያ ሊሆን ይገባል፡፡ ➛የእውቀት አይነቶችን እየሰበሰበ ነገር ግን የተግባር ሰው ካልሆነ ይህ ሰው እርሱ እንዳልተጠቀመ ሁሉ በእውቀቱ ሌሎች…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➛ክፍል አስራ አራት
〰〰〰〰〰〰〰

➲ዘጠነኛው፡- በእውቀቱ ለመስራት አላህን መማጸን ነብዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ዱኣ ያዘወትሩ ነበር” ትላለች ኡመ ሰለማ ረዲየሏህ አንሃ

▪️"اللهم إني أسألك علما نافعا، ورزقا طيبا، وعمال متقبال"

“አላህ ሆይ! ጠቃሚ እውቀትን ፤ ተቀባይነት ያለውን ስራ እጠይቅሃለሁ፡፡” አህመድ፡(26521) ኢብኑ ማጀህ፡( 925) ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ ኢብኑ ማጀህ፡(762)

➲ይህን የተባረከ ዱዓ በቀኑ መጀመሪያ ላይ ማድረጉ ተስማሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ቀን የስራዎች ሜዳ በመሆኑ ነው። የሙስሊም አላማና ግቡ ደግሞ እነዚህ ሶስት ነገሮች ናቸው ፤ ሌላ አራተኛ የለም፡፡ ጠቃሚ እውቀት ፣ ተቀባይነተ ያለው ስራ ፣ መልካም የሆነ ሲሳይ ናቸው፡፡

➧ስለዚህ ፈጅርን ከሰገድክ በኋላ ይህን ዱዓ ማድረግህ በጣም የተስማማ ነው፡፡ በአላህ ታግዘሃል ፤ እውቀትን በመፈለግ ተማጽነሀል ፤ ለስራህ አላህ እንዲያግዝህ ለምነሀል ፤ ሲሳይን ለማግኘት ከአላህ እገዛን ጠይቀሃል፡፡ በቃ ከዚያም የቀን ስራህን በሰላም ትጀምራለህ ማለት ነው፡፡

➲አስረኛው፡- እውቀትን ወደስራ ያልቀየረ የተወገዘ ነው በስራ ላይ ያልተጠመደን ፣ ለስራ ትኩረት ያልሰጠን አካል ሰለፎች ያነወሩበት በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡ ከዚህ መካከል የሚከተለው የአቡሁረይራ ረዲየሏህ አንሁ ንግግር ነው፡-

▪️"مثل علم لا يعمل به كمثل كنز لا ينفق منه في سبيل الله"

➧“በእርሱ የማይሰሩበት እውቀት በአላህ መንገድ ወጭ እንደማይደረግ ድልብ ሐብት አምሳያ ነው፡፡” አል ኸጢብ ፊልኢቅቲዳ፡ (12) አልባኒ ሰነዱን መውቁፍ ነው ምንም አይልም በለውታል

➧ሀዲስን በብዛት ስለሚጽፍ ሰው ኢማም አህመድ -ረሂመሁሏህ- ተጠየቁ፡፡ከዚያም
የሚከተለውን መለሱ፡-


▪️"ينبغي أن يكثر العمل به على قدر زيادته في الطلب"

➧“እውቀትን በሚፈልግበት መጠን በእርሱ መሰራትን ሊያበዛ ይገባል፡፡” አል ኸጢብ ፊልኢቅቲዳ፡(12 )ከዚያም አያይዘው የሚከተለውን ተናገሩ፡-

▪️"سبل العلم مثل سبل المال، إن المال إذا ازداد ازدادت زكاته"

“የእውቀት መንገዶች ልክ የገንዘብ መንገዶችን አምሳያ ናቸው፡፡ ገንዘብ በጨመረ ቁጥር ዘካው እየጨመረ ይሄዳል፡፡”


➲ኸጢብ አልበግዳድይ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“ያለወጭ ገንዘብ እንደማይጠቅመው ሁሉ በእርሱ ለሰራበት፣ ዋጅቦችን ተጠባብቆ ለፈጸመ እንጅ እውቀትም እንዲሁ አይጠቅምም፡፡ አንድ ግለሰብ ነፍሱን ይመልከት ፤ወቅቱን ይጠቀምበት ፤ … ጉዞው ቅርብ ነው ፤ መንገዱ አስፈሪ ነው ፤ መታለሉ ብዙ ነው ፤ አደጋው ትልቅ ነው ፤… አላህ በመጠባበቂያ (ቦታ) ላይ ነው ፤ መመለሻው ወደርሱ ነው፡፡ አል ኸጢብ ፊልኢቅቲዳ፡(12)

➤አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

◀فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ ⓻وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ⓼

➧“የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል፡፡ የብናኝ ክብደት
ያክልም ክፉን የሰራ ሰው ያገኘዋል
፡፡” ዘልዘላህ፡(7_8)

▪️ሀሰን አልበስርይ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

◀"أنزل القرآن ليعمل به، فاتخذ الناس تالوته عمال"
“ቁርኣንን ያወረደው በእርሱ ሊሰሩበት ነው፡፡ ሰዎች ግን ማንበቡን ስራ አድርገው
ይዘውታል
፡፡” ይህን ንግግር ብን አልጀውዝ “ተብሊስ ወኢብሊስ” በሚባለው ኪታብ ከዘገበ በኋላ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

▪️"أنهم اقتصروا على التالوة، وتركوا العمل به"
➲"እነርሱ በንባቡ ብቻ ተገደቡ በእርሱ መስራትን ተው”
ተብሊስ ወኢብሊስ፡ ገፅ(137)

➧ለኢብራሂም ብን አድሀም -ረሂመሁሏህ- አንድ ሰው የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበላቸው፡- “አላህ በቁርኣኑ “እኔን ለምኑኝ እቀበላችኋለሁ” ጋፊር፡ (60) በማለት ተናግሮ ሲያበቃ እኛ ዱዓ እያደረግን ለምንድን ነው ዱዓችን ተቀባይነትን ያጣው?” በማለት
ጠየቃቸው
፡፡

➲ኢብራሂም ለዚህ ሰው የሚከተለውን መልስ ሰጡት፡-“ዱዓችን ተቀባይነት ያጣው በአምስት ምክንያቶች ነው” በማለት መልስ ሰጡት፡፡እርሱም “ምንድን ናቸው?!” በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም “አላህን አውቃችሁ
የእርሱን ሐቅ አለመወጣታችሁ
፡፡ ቁርኣንን አንብባችሁ በእርሱ አለመስራታችሁ፡፡ረሡልን صلى الله عليه وسلم እንወዳለን ብላችሁ ሱናቸውን በመተዋችሁ፤ ኢብሊስን እንራገማለን ትላላችሁ ነገር ግን እርሱን ትታዘዛላችሁ ፤ አምስተኛ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ የሰው ነውር ትከታተላላችሁ፡፡” ጃሚዑ በያኒ አል ዒልም፡(1220)

〰 〰 〰 〰 〰 〰 〰

➧ኢንሻአላህ ክፍል አስራ አምስት ይቀጥላል◉◉◉✍


➧ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‏ ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ ‏ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.


▪️وعن عبد اللَّه بن عمرو بن العــــــاص رَضِيَ اللَّهُ عَنهُما أنه سمع رَسُــول اللَّهِ ﷺ يقول: (من صلي عليّ صلاة صلى اللَّه عليه بها عشرا)

📖| رواه مسلم
.https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
‏‌‎
.
የጁሙዓ ቀን ትሩፋቶችና ብይኖች
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
خُطْبَةُ الْجُمُعَةِ
የጁሙዓ ኹጥባ

فَضَائِلُ وَأَحكَامُ يَومٍ الجُمُعَةِ
የጁሙዓ ቀን ትሩፋቶች እና ብይኖች

🕌 ደሴ አል-አዝሓር መስጂድ

📅 يوم الجمعة 2 رجب 1443 الموافق 4/2/2022

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/4756
t.me/abu_reyyis_arreyyis/4756
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዳን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
◾️የኢባዳዎች መለያየት ሒክማው
◾️ሙሉ የአላህ ባርነት የሚረጋገጠው
◾️በአላህ ትእዛዝ ላይ ቀጥ ማለትን በተመለከተ ተዳሶበታል


《ክፍል 1⃣8⃣》
〰〰〰〰〰〰

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم
➧ሉቅማን ለልጁ ከሰጣቸው ምክሮች አንዱ

وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِى ٱلْأَرْضِ مَرَحًا ۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍۢ فَخُورٍۢ

«ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፡፡ በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ፡፡ አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድምና፡፡


⚘https://t.me/https_Asselefya1
【يَا لِسَانُ قُلْ خَيْرًا تَغْنَمْ واسْكُتْ عَنْ شَرٍّ تَسْلَمْ مِنْ قَبْلَ أَنْ تَنْدَمَ】

✅ አንተ ምላስ ሆይ‼️ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀትህ በፊት፦ መልካምን ተናገር ትርፋማ ትሆናለህ። ከመጥፎ ነገር ዝም በል ትድናለህ።
Audio
➡️ ሰሞኑ በሚዲያ እየተደረገ ያለው የትዳር ጫረታ በተመለከተ የተሰጠ ምክር

♦️የሀያእ አስፈላጊነት
♦️የተሳሳተ የትዳር መንገድ
♦️የሴት ውበት በአደባባይ መግለፅ


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➡️ ሰሞኑ በሚዲያ እየተደረገ ያለው የትዳር ጫረታ በተመለከተ የተሰጠ ምክር ♦️የሀያእ አስፈላጊነት ♦️የተሳሳተ የትዳር መንገድ ♦️የሴት ውበት በአደባባይ መግለፅ 🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
ውድ እህቶቼ ከልብ ሁናችሁ አዳምጡት እስኪ!!!

➧ሀቂቀተን በዚህ ሰሞን የምንሰማው ነገር በጣም ነው የሚያሳፍረው!

ለምን ግን እያወቀን ሀያዐችንን እርግፍ አድርገን እንጥላለን ለምን ያአላህ ውዷ እህቴ ሆይ አላህ ሱበሀኑሁ ወተአላ ለአንቺ ያልቀደረውን ያልፃፈውን ላታገኝው ለምን እራስሺን ታወርጃለሺ ታረክሻለሺ??

➲እረ ተው ልብ ግዙ እንደዚህ አይነቱ ትዳር ቅርት ቢልብሺስ ራስሺን አዋርደሺ ያገኘሺው ትዳር ትዳር ሆኖ የምትኖሪ ይመስልሻልን? አይምሰልሺ እራስሺን አስከብሪ በጌታሺ ላይ ሙዕሚን ሁኚ የጌታሺን ትዕዛዝ አክብሪ አላህ አንቺ ካሰብሺው በላይ ይሰጥሻል! ለሁሉም ነገር ከልብ ሁኚ ቁጥብ ሁኚ እራስሺን አታዋርጂ!! ልብ ግዙዙዙ........✍ምክሩ ለእራሴም ነው አላህ ሂድያ ይስጠን እህቶቼ!!!
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ⑥⑥➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
Audio
بلال بن محمود العشي
🎤• للقارئ • الشيخ
((
#بلال_بن_محمود_العشي ))
↪️ውብ ቲላዋ ተጋበዙ!!
〰〰〰〰〰〰〰
ቁረአን የልብ ብርሀን የዱኒያ የአሄራን ሂወት የሚያቀና ውብ የማይጠገብ የአላህ ቃል ነው


https://t.me/UmuUseyminAselfiya
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዳን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
◾️ፃም የተደነገገበት ዋና አላማ
◾️የጥጋብና የረሀብ ተፅእኖ


《ክፍል 1⃣9⃣》
〰〰〰〰〰〰

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
አርበዒን 48ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
ደርስ
~~~~

~ አርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር
~ ለመርከዘ ተውሒድ የቁርኣን ሒፍዝ ተማሪዎች የቀረበ
~ ሐዲሥ ቁጥር – 4️⃣8⃣
~ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ pdf መልክ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/1672
#ለእህቴ_አድርሱላት___!

#ምርጫ_እንድህ_አይደለም።
---------------------------------
አውቃለሁ ይከብዳል ያለ ትዳር ኑሮ፡
የህሌና ፀፀት የውስጥ እንጉርጉሮ፡
ቀን ባለፈ ቁጥር እድሜ ይጨምራል፡
ያውም በዚህ ዘመን ፊትናውም ያስፈራል፡
አወ ብቸኝነት እጂጉን ያስጠላል፡
ጊዜው ሲረዝምብሽ ሊመስልሽ ይችላል!!
--------------//--------------------------
#ቢሆንም_ግን_እህት__!!
የችግሩን ክብደት እኔ ብረዳሽም፡
በዚህ መጥፎ ተግባር አብሽሪ አልልሽም፡
ደግሞ ለአንችም ቢሆን አያስደስትሽም፡
ለሙስሊሟ ጀግና ይህ አይመጥንሽም፡
--------------------------------------------
ጆይን ብሎ ገብቶ በሊፍት ለመውጣት፡
የማይሆን አስቦ የያዙትን ማጣት፡
ሀፍረትሽን ጥለሽ በሚዲያ መምጣት፡
ተመከሪ እህቴ ይህ ለአንች ነው ቅጣት፡
ተቆጠቢ እባክሽ እህት ተመከሪ፡
ወንጀል አትሰብስቢ ተይ አሏህን ፍሪ!!
---------------------------------------------
ዩቲዩብ ላይ ቀርበሽ ትዳር ስትጠይቂ፡
ውበትሽ እንድታይ ደፍረሽ ስትስቂ፡
ፈታኝ መጥፎ ነገር ፎቶ ስትለቂ፡
ወንድን ለመፈተን ተጋልጠሽ ስትዘልቂ፡
ወንጀሉ ከባድ ነው እህት ተጠንቀቂ!!
---------------------------------------------
ባል ፍለጋ ብለሽ በሚዲያ አትውጭ፡
አሏህን ለምኝው በአደብ ተቀመጭ፡
ለኢኽዋን ለአህባሽ ልብሽን አትስጭ፡
ትዳር ቀልድ አይደለም ጀግናውን ምረጭ፡
ለኢኽዋን ብትነግሪው የትዳር ንድፍሽን፡
በውስጥ አይመክርሽም አያውቅም ልክሽን፡
ስልጣኔ መስሎት ያረክሳል ክብርሽን!!
---------------//-----------------------
#ስለዚህ_እህቴ__!!
ቂያማ እየቀረበ እየበዛ ፊትና፡
ሀቁ እየተተወ በዝቶ ፍልስፍና፡
መፍትሔው ተረስቶ ተውሒዲና ሱና፡
የትዳር ጣዕሙ ደስታው ተረሳና፡
ፋራነት ተደርጎ መፅናት እስልምና፡
መሀይሙ በዝቶ አዋቂ አንሷልና፡
ሀራም ግንኙነት ንቃት ሆኗልና፡
ይህ ደግሞ ለእህቴ አይመጥንምና፡
ታገሽ አሏህ አለሽ ፀልይ ለረበና፡
እውነተኛ ውበት ይሔ ነው ቁንጂና፡
አሏህ ይሰጥሻል የሀቅ ሰው ጀግና፡
ቁጥብ ሴት ሁኝ እንጂ አሞተ ቆፍጣና፡
ቀጥ ብለሽ ተጓዥ በኢስላም ጎዳና፡
#እንጂ_ምርጫ_እንድህ_አይደለም!
------------------------------------------
በተውሒድ በሱና በእውቀት የመጠቁ፡
በፀባይ በአደብ እጂጉን የላቁ፡
የሴትን ልጂ ክብር ጠንቅቀው ያወቁ፡
በመንሀጀ ሰለፍ በሀቅ የረቀቁ፡
ሚስትነትሽን አምነው የሚንከባከቡሽ፡
ሱናውን ጠብቀው በደሴታ እሚያገቡሽ፡
እንድህ አይነት ጀግና ጠንካሮች እያሉ፡
ኢኽዋንን ለማግባት ታስቢያለሽ አሉ!?
ፖለቲካ ሰብኮ ከሱና እሚያርቅሽ!?
ከጠማማወች ጋር ከሚያስተዋውቅሽ!?
ለሰላማዊ ሰልፍ ሜዳ ከሚያዘልቅሽ!?
ዘወትር ጧት ማታ ከሚጨቃጨቅሽ!?
ለውስን ቀን እንጂ ይህ ላያዛልቅሽ!?
ሽርክ ቢዲዐ እንጂ ተውሒድ ላይቀልብሽ፡
ተይው ከወድሁ ይሔ ሰው ይቅርብሽ።
                                
ሱሪ ከሚገትት አስመሳይ አልጫ፡
ከፖለቲካ ጋር ተጣብቆ እንደ ሙጫ፡
ከገባሽ በኋላ ከሚጨንቅሽ መውጫ፡
ልንገርሽ አሁኑ ይስተካከል ምርጫሽ፡
ለእውነተኛ ፍቅር ለዘላቂ ኑሮ፡
ሰለፍይ ማግባት ነው ሰለፍይ አፍቅሮ፡
ሱፍይ ኢኽዋን አህባሽ ያረጋል ደንቆሮ፡
#አወ_እንድህ_አይደለም.....!!
እየተነዛነዝሽ ከመኖር ዘላለም፡
ውጫዊ ገፅታ ውበትና ቀለም፡
ጭራሹን በድፍረት በሚዲያው አለም፡
ተሳሳትሽ እህቴ ምርጫ እንድህ አይደለም፡
---------------------------------------------
ከኑረዲን አል አረቢ 2014
➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
➲የሶሀባ ሚስቶች ለባላቸው የነበራቸው ልዩ ፍቅር
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ከእለታት አንድ ቀን አቡ ደርዳዕ ከሚስት ኡሙ ደርዳእ ጋር አብረው ተቀምጠው ሳሉ ኡሙ ደርዳእ እንዲህ አለች

➜ጌታዬ አላህ ሆይ ! ባለቤቴ አቡ ደርዳእ እዚህ ዱንያ ላይ እርሱ እኔን ለትዳር ጠይቆኝ አግብቶኛል ፡ እኔ ደግሞ እርሱኑ ጀነት ላይ እንድትድረኝ እለምንሃለሁ አለች፡

➧ከዛም አቡ ደርዳእ ይሄን ስትል እየሰማት ነበርና እንዲህ አላት

➻እሱ እንዲሳካልሽ የምትፈልጊ ከሆነ ምናልባት እኔ ካንቺ በፊት ከሞትኩ "አንቺ እስክትሞች ድረስ ፈፅሞ ሌላ ባል እንዳታገቢ አደራ" አላት

➺ከዚያም ከግዜያት ቡሀላ አቡ ደርዳእ ሞተ

➲ኡሙ ደርዳእ በጣም ውብና ቆንጆ ነበረችና ከአቡ ደርዳእ ሞት ቡሀላ ሙዓዊያ ኢብኑ አቢ ሱፍያን ለትዳር ሊጠይቃት ወደርሱዋ ይመጣል

➫አስቡት ሙዓዊያ በጊዜው የሙስሊሞች መሪ አስተዳደር ወይንም መንግስት ነበር፡

➺ከዛም ሙዓዊያ የትዳር ጥያቄ ሲያቀርብላት እንዲህ ብላ መለሰችለት

➧በፍፁም ወላሂ ዱንያ ላይ ከአቡ ደርዳእ ቡሀላ ማንም ወንድ ቢመጣልኝ አላገባም፡ አላህ በርሱ ፈቃድ ጀነት ላይ አቡ ደርዳእን እስኪድረኝ ድረስ እዚች ዱንያ ላይ ባል ሚባል በፍፁም አላገባም አለችው።

📒📘📕📙📔 ሒልየቱል አውሊያ (224-225-1)
🖊ሑሴን አሕመድ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w