💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ضوابط في الفتن…(13)
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
📚 ضوابط في الفتن يحتاجها كل مسلم
📚 ማንኛዉን ሙስሊም የሚያስፈልገዉ የሆነ የፈተና ግዜ መርሆዎች

الضابط الثالث عشر
إياك والظلم والشر والعذاب والزم العدل والخير والرحمة

አስራ ሶሦተኛዉ መርሆ
➧
በደልን ክፋትን ጨካኝ መሆንን ተጠንቀቅ!
➧እዝነትን መልካምን ፍትህን ያዝ!


▪️ክፍል አስራ ሶስት (①③)
〰〰〰〰〰〰〰
♦️የኪታቧን PDF ለማገኘት
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/Asselefya1/3376

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
t.me/abu_reyyis_arreyyis/4709
t.me/abu_reyyis_arreyyis/4709
➲ሐያእ (አይናፋርነት) ለሴት ልጅ ትልቁ ሀብቷና ውበቷ ነው!!
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
"
➧ሐያእ በመሰረቱ ወንዱም ሴቱም ጋር ሊኖር የሚገባው ተወዳጅ ምርጥ ባህሪ ነው። በተለይ መልኩ ግን ሴቶች ዘንድ ወሳኝነት አለው። ይሁን እንጂ ሐያእ (አይናፋርነት) የሚባለው ነገር አላህ ካዘነላቸው ጥቂት እንስቶች በስተቀር ብን! ብሎ የጠፋ ይመስላል።

➧ሴት ልጅ አይናፋርነት ከሌላት እንዲሁ ባህሪዋ ለባሏ እንኳ አይማርከውም፣ ምክንያቱም አይናፋርነት ለሴት ልጅ ከፈጣሪዋ የተሰጣት ልዩ ውበትና ግርማ ሞገሷ፣ ተፈጥሯአዊ የሆነ ስጦታዋ ነውና። ሀያእ (አይናፋርነት) የሚባለው ነገር ከብዙ ሴቶች ልብ ድራሹ ጠፍቶ በስመ ስልጣኔ ጋጠ-ወጥ ሴቶች አስባልቱን ከሞሉት ሰነባብቷል። እንዲያውም አንዳንዴ በተቃራኒው ሀያእ የሚባለው ነገር ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ዘንድ ይስተዋላል።
"

➲እህቴ ሆይ! ቁርኣን አንድን ነገር ሲጠቅስ ያለ ምክንያት አይደለም!። ይልቅ ከእኛ መተገበሩ ወይም መጠንቀቁ ተፍልጓል ማለት ነው። ለምሳሌ አላህ ስለ ነቢዩላህ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ስደት ላይ ሆኖ የገጠመውን ሲተርክ እንዲህ በማለት የአንዲትን እንስት አካሄድ አውስቷል:-

◀فَجَاءَتْهُ إِحْدَاهُمَا تَمْشِي عَلَى اسْتِحْيَاءٍ

«ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሐፍረት ጋር የምትሄድ ሆና መጣችው፡፡»
አል-ቀሰስ 25

➧ሸይኽ ናሲሩ ሰዕዲ (ረሂመሁላህ) ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ ተፍሲራቸው ላይ እንዲህ አሉ:- “ይህ የሚያመላክተው የመልካም ስነ-ምግባር ባለቤት መሆኗን ነው፣ ምክንያቱም አይናፋርነት በላጭ ከሆነው ከመልካም ስነ-ምግባር ነው!፣ በተለይ በሴቶች ላይ።” [ተፍሲሩ ሰዕዲ]

➧"ከሀፍረት ጋር የምትሄድ ሆነ…" በማለት አካሄዷን አውስቷል፣ አላህ ይህን አካሄድ አንቺም ከቤት የሚያስወጣሽ አስገዳጅ ነገር ሲኖር ተግባራዊ እንድታደርጊው ፈልጓል ማለት ነው። አለባበስሽ ሸሪዐው የሚፈልገው አይነት ሆኖ በጅልባብና ኒቃብ የተሰተርሽ ሆነሽ ብትወጪ እንኳን ይህ አይናፋርነት ፈፅሞ ሊለይሽ አይገባም!። ምክንያቱም ሀያእ ከፈጣሪሽ ዘንድ የተቸረሽ ትልቁ ሀብትሽና ውበትሽ ነው!።
"

➲የነዚያ ጋጠ-ወጦች ጩሃት ሸንግሎሽ በስመ ስልጣኔና ግልፀኝነት ሀያእሽን አትልቀቂው የአንቺ የሙስሊሟ እንስት የፈጣሪዋ ትልቅ ችሮታ ነው!!። ሀያእ የሚባለውን የተፈጥሮ ስጦታሽንና ሀብትሽን ለማቆየት ምናምንቴዎችን ትተሽ ጓደኝነትሽን ሀያእ ካላቸው እህቶችሽ ጋር አድርጊው!። ጓደኛሽ ሀያእ ከሌላት ሙተነቂብ መሆኗ አለያም ከአንቺ በላይ እውቀት ስላላት አትሸንግልሽ!፣ ከቻልሽ ሀያእ እንዲኖራት ምከሪያት! ካልተስተካከለች ግን ራቂያትና ሀያእ ያላቸውንና ዲናቸው ጠንካራ የሆኑ እህቶችሽን ጓደኛ አድርጊ!።
"
➧ወንድሜ ሆይ! ልታገባ ስታስብ ሀያእ ያላትን ሴት መምረጥ እንዳለብህ አትዘንጋ!። ልታገባት ያሰብካት ሴት ምናልባት ማሻ አላህ አለባበሷ ሸሪዐዊ የዲን እውቀቷም እንደዛው ሊሆን ይችላል፣ ግን ሀያእዋ እንዴት ነው?!። ምክንያቱም ሀያእ ትልቅ ዋጋ አለው!
በዚህ አስቸጋሪ ዘመን ሀያእ የሌላት እንስት ከራሷ የባሰ ሀያእ የሌለውን ትውልድ ቢሆን እንጂ ሀያእ ያለውን ትውልድ ልታፈራ አትችልም
!!።

➲ሀያእ እየጠፋ የመጣ የሙስሊም እንስቶች ትልቅ ሀብት ነው!! እህቴ ሆይ! ትልቁን ሀብትሽን ውበትሽን፣ የፈጣሪሽን ስጦታ ፈልገሽ አጥብቀሽ ያዢው!!

✍🏻ኢብን ሽፋ:

➧ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Al-Jinn
Fares Abbad
🌸ቁርአን የልብ መርጊያ💎

◉አል_ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚ ((ረሂመሁላህ)) እንዲህ ይላሉ◉

➩◉ልብ ፅናት እና ሰላምን ከምታገኝባቸው ምክንያቶች በጣም ትልቁ ነገር ➷ቁርአን መቅራትን ➷ማብዛት ነው!

➛ተጋበዙልኝ የማለዳ ቲላዋ🌹

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ⑥③➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዳን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
◾️በሽተኛና ፃም በዝርዝር ከነ መረጃው
◾️ሀይድና ኒፋሳ ደም ላይ ሴቶችና ፃም
◾️የሴት ልጅ ፊትና በወንዶች ላይ
◾️ማፍጠሪያ ትንሽ ደቂቃ ሲቀረው ሀይድ ቢመጣባት


《ክፍል 1⃣6⃣》
〰〰〰〰〰〰
🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➧መልካም ጓደኛ
➫➫➫➫➫➫

➻ሁለት ውብ የሂወት ኡደቶችን ይለግሰሀል… "አንደኛው እዚህ ዱንያ ላይ ሲሆን" "ሁለተኛው ደግሞ ጀነት ውስጥ ይሆናል"

➧መልካም ጓደኞች «ወደ አሏህ መንገድ… ይጠሩሀል…» «ከጠፋህባቸው… ይፈልጉሀል…» ከተዘናጋህ… አስታውሱሀል»

«…በዱአቸው ውስጥ…ያካቱሀል»
«ልክ እንደ ከዋክብቶች… መርከብህ መንገድ ከሳተች…ይመሩሀል
…» «ነገ ከአሏህ አርሽ ስር…ኢንሸአላህ…ይጠብቁሀል…» «ጀነት ውስጥ ፈልገውህ ካጡህ…

➧አሏህን ወደነሱ እንዲቀላቅልህ ይለምኑልሀል» "አሏህ ሶሊሆቹን አድርጎ ከሶሊሆቹ ያወዳጀን ከሶሊሆቹ ጓደኞቻችን አይነጥለን በያሉበት ይጠብቅልን "

#መንቁል

➛ያአላህ ምንኛ መታደል ነው እንደዚህ አይነት ጓደኛ ማገኘት አላህ ይወፍቀን እኛንም መልካሞች ያድርገን!!

➳ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
አርበዒን 47ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
ደርስ
~~~~

~ አርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር
~ ለመርከዘ ተውሒድ የቁርኣን ሒፍዝ ተማሪዎች የቀረበ
~ ሐዲሥ ቁጥር – 4️⃣7⃣
~ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ pdf መልክ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/1672
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ⑥④➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
▪️تلاوة طيبـة
▪️طهـــر مسمعــك وارح قلبـــك
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➛ክፍል አስር ➭➭➭➭➭➭➭ ➧የነብዩን صلى الله عليه وسلم ቋሚ የሆነ የሶላት አፈጻጸምን በተመለከተ ኢብን አልቀይም ራሂመሁላህ እንደሚከተለው አጠር አድርጎ ገልጾታል፡- ➭“ነብዩ صلى الله عليه وسلم በቀንና በሌሊት አርባ ረከዓዎችን ተጠባብቀው ይሰግዱ ነበሩ፡፡ አስራ ሰባት ፈርዶች ፣ አስራ ሁለት ራቲባ…
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➻ክፍል አስራ አንድ
➛➛➛➛➛➛➛➛

➲እያንዳንዱ ሙስሊም ይብዛም ይነስም ለመልካም ስራዎች አላህ ከገጠመው
በሰራው ስራ ሊሸነገል አይገባውም፡፡በተለይ የስራው ቁጥርና ጥራት ቢበዛም ሊታለል አይገባም፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ ስለሙእሚኖች ባህሪ የሚከተለውን ተናግሯል፡

وَالَّذِينَ يُؤْتُونَ مَا آتَوا وَّقُلُوبُهُمْ وَجِلَةٌ أَنَّهُمْ إِلَىٰ رَبِّهِمْ رَاجِعُونَ

“እነዚያም የሚሰጡትን ነገር እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መሆናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ሆነው የሚሰጡት፡፡” አል ሙእሚኑን፡ 60

➧የሙእሚኖች እናት ዓኢሻ ረድየላህ አንሁ ስለዚህ ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ጥያቄ ጠየቀች፡- “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ዝሙት ፣ ስርቆት አስካሪ መጠጥ የሚጠጡ ናቸውን?”

የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ፡-

▪️"لا يا بنت أبي بكر، أو لا يا بنت الصديق، ولكنه الرجل يصوم ويصلي ويتصدق وهو يخاف أن لا يقبل منه"

➧“የአቡበክር ልጅ ሆይ! ወይም የሲዲቅ ልጅ ሆይ! ነገሩ እንደዚያ አይደለም፡፡ ሰውየው እየጾመ ፣ እየሰገደ ፣ እየሶደቀ አላህ አይቀበለኝም ብሎ የሚፈራ ነው፡፡” አህመድ፡ 25705 ቲርሚዚይ፡3175 ኢብኑ ማጀህ፡ 4198 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል አስ ሶሂህ፡162

➧ረሡል صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

▪️"لن يدخل أحدا منكم عمله الجنة" قالوا: ولا أنت؟ يا رسول الله قال: "ولا أنا، إلا أن يتغمدني الله منه بفضل ورحمة"

“ከእናንተ ለአንዳችሁ ስራው ጀነት አያስገባውም” በማለት ረሡል صلى الله عليه وسلم ተናገሩ፡፡ “አንተም የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” በማለት ሶሃቦቹ ጠየቁ፡፡ “እኔም ብሆን ፤ አላህ በችሮታው እና በእዝነቱ እስካልሸፈነኝ ድረስ” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ ቡኻሪ፡5673 ሙስሊም፡2816

➲አንድ ሰው መልካም ስራ ስለሰራ መደነቅ ፣ መታለል የለበትም፡፡ይልቁንም መልካም ስራዎችን እያበዛ ፣ ዘወትር አላህ ስራውን እንዲወድለት ፣ እንዲቀበለው ለወደፊትም ለመልካም ስራ እንዲገጥመው ይማጸን፡፡

➧ለእያንዳንዱ ሙስሊም ከሞት በኋላ ያለው ሁለተኛው እድሜው ሊሰወርበት አይገባም፡፡ ይህ እድሜ አላህ የገጠመው ካልሆነ በቀር አብዛኛው አይነቃበትም፡፡ለአንድ ሰው ሁለተኛ እድሜ አለው፡፡እርሱም ከሞት በኋላ የሚገኝ ሁለተኛው የመልካም ስራ እድሜው ነው፡፡

▪️ይህን አስመልክቶ ረሡል صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

▪️"إذا مات الإنسان انقطع عنه عمله إلا من ثالثة: إلا من صدقة جارية، أو علم ينتفع به، أو ولد صالح يدعو له"

➧የሰው ልጅ ሲሞት ሶስት ነገሮች ሲቀሩ ስራው ሁሉ ይቋረጣል፡ ቋሚ (ቀጣይ) የሆነ ሶደቃ ፣ ወይም በእርሱ ተጠቃሚ የሚሆኑበት እውቀት ወይም ለእርሱ ዱኣ የሚያደርግለት ሷሊህ (ደግ) ልጅ” ሙስሊም፡1631

▪️وقال في الحديث الآخر "سبع يجر للعبد أجرهن من بعد موته، وهو في قبره: من علم علما، أو كرى نهرا، أو حفر بئرا، أو غرس نخلا، أو بنى مسجدا، أو ورث مصحفا، أو ترك ولدا يستغفر له بعد موته"
▪️በሌላ ሐዲስ፡ “ባሪያው ከሞተ በኋላ በቀብር ውስጥ የሰባት ነገሮቸ ምንዳ ይፈሱለታል፡፡ እውቀትን ያስተማረ ፣ ቆፍሮ ውሃ ያወጣ ወይም የጉድጓድ ውሃ የቆፈረ ወይም የተምር ዛፍ የተከለ ወይም መስጅድ የገነባ ወይም ኪታብ ወቅፍ ያደረገ ወይም ለእርሱ ከሞተ በኋላ ኢስቲግፋር የሚያደርግለት ልጅን የተወ” በዛር በሙስለዳቸው፡ 7289 ላይ አቡ ኑዓይም ደገሞ ሂልየቱ አል አውሊያእ፡2/343 ላይ ዘግበውታል ሐዲሱን አልባኒ ሐሰን ብለውታል ሶሂህ አል ጃሚዕ፡3602

〰 〰 〰 〰 〰 〰 〰

➭ ኢንሻ አሏህ ክፍል አስራ ሁለት ይቀጥላል◉◉◉✍

▪️ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】
〰 〰 〰 〰 〰 〰 〰

➧ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዳን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
◾️የእርጉዝና የምታጠባ ሴት ፃም
◾️ቀዷውን ሳያወጣ ረመዷን የገባበት
◾️የሌሎችን ህይወት ለማዳን ማፍጠር
◾️በህመም ምክንያት ያልፃማቸው ቀናቶችና ቀዷ ሳያወጣ የሞተ ሰው


《ክፍል 1⃣7⃣》
〰〰〰〰〰〰
🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ⑥⑤➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲ጊዜህን በቁም ነገር ላይ አውለው
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛

▪️ሸይህ ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ።

➧ጊዜውን ➴➴➴➴

➛አላህን በማውሳት (በዚክር)
➛ቁርአን በመቅራት
➛ከመልካም ሰዎች ጋር በመሆን
➛ከዝንጉና ከመጥፎ ጓደኞችን በመራቅ ያሳለፈ ሰው


➲ቀልቡ ያማረና የለሰለሰ ይሆንለታል።

📚 مجموع فتاوى ابن باز (5/244)

https://t.me/https_Asselefya1
قال صلى الله عليه وسلم :

(( أسعدُ النّاسِ بِشَفاعَتِي يَوْمَ القِيامَةِ مَنْ قالَ : لا إله إلاّ اللَّهُ خالِصاً مُخْلِصاً منْ قَلْبِهِ )).

📝 رواه البخاري
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➻ ክፍል አስራ ሶስት ➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧አንድ ሰው የመልካም ባህሪያት ሁሉ ከእርሱ ላይ ካልተሰባሰቡ ከኢማምነት ደረጃዎች ሊደርስ አይችልም፡፡ በመልካም ባህሪያቶች ለሰዎች አርአያ ሊሆን ይገባል፡፡ ➛የእውቀት አይነቶችን እየሰበሰበ ነገር ግን የተግባር ሰው ካልሆነ ይህ ሰው እርሱ እንዳልተጠቀመ ሁሉ በእውቀቱ ሌሎች…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➛ክፍል አስራ አራት
〰〰〰〰〰〰〰

➲ዘጠነኛው፡- በእውቀቱ ለመስራት አላህን መማጸን ነብዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ዱኣ ያዘወትሩ ነበር” ትላለች ኡመ ሰለማ ረዲየሏህ አንሃ

▪️"اللهم إني أسألك علما نافعا، ورزقا طيبا، وعمال متقبال"

“አላህ ሆይ! ጠቃሚ እውቀትን ፤ ተቀባይነት ያለውን ስራ እጠይቅሃለሁ፡፡” አህመድ፡(26521) ኢብኑ ማጀህ፡( 925) ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ ኢብኑ ማጀህ፡(762)

➲ይህን የተባረከ ዱዓ በቀኑ መጀመሪያ ላይ ማድረጉ ተስማሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ቀን የስራዎች ሜዳ በመሆኑ ነው። የሙስሊም አላማና ግቡ ደግሞ እነዚህ ሶስት ነገሮች ናቸው ፤ ሌላ አራተኛ የለም፡፡ ጠቃሚ እውቀት ፣ ተቀባይነተ ያለው ስራ ፣ መልካም የሆነ ሲሳይ ናቸው፡፡

➧ስለዚህ ፈጅርን ከሰገድክ በኋላ ይህን ዱዓ ማድረግህ በጣም የተስማማ ነው፡፡ በአላህ ታግዘሃል ፤ እውቀትን በመፈለግ ተማጽነሀል ፤ ለስራህ አላህ እንዲያግዝህ ለምነሀል ፤ ሲሳይን ለማግኘት ከአላህ እገዛን ጠይቀሃል፡፡ በቃ ከዚያም የቀን ስራህን በሰላም ትጀምራለህ ማለት ነው፡፡

➲አስረኛው፡- እውቀትን ወደስራ ያልቀየረ የተወገዘ ነው በስራ ላይ ያልተጠመደን ፣ ለስራ ትኩረት ያልሰጠን አካል ሰለፎች ያነወሩበት በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡ ከዚህ መካከል የሚከተለው የአቡሁረይራ ረዲየሏህ አንሁ ንግግር ነው፡-

▪️"مثل علم لا يعمل به كمثل كنز لا ينفق منه في سبيل الله"

➧“በእርሱ የማይሰሩበት እውቀት በአላህ መንገድ ወጭ እንደማይደረግ ድልብ ሐብት አምሳያ ነው፡፡” አል ኸጢብ ፊልኢቅቲዳ፡ (12) አልባኒ ሰነዱን መውቁፍ ነው ምንም አይልም በለውታል

➧ሀዲስን በብዛት ስለሚጽፍ ሰው ኢማም አህመድ -ረሂመሁሏህ- ተጠየቁ፡፡ከዚያም
የሚከተለውን መለሱ፡-


▪️"ينبغي أن يكثر العمل به على قدر زيادته في الطلب"

➧“እውቀትን በሚፈልግበት መጠን በእርሱ መሰራትን ሊያበዛ ይገባል፡፡” አል ኸጢብ ፊልኢቅቲዳ፡(12 )ከዚያም አያይዘው የሚከተለውን ተናገሩ፡-

▪️"سبل العلم مثل سبل المال، إن المال إذا ازداد ازدادت زكاته"

“የእውቀት መንገዶች ልክ የገንዘብ መንገዶችን አምሳያ ናቸው፡፡ ገንዘብ በጨመረ ቁጥር ዘካው እየጨመረ ይሄዳል፡፡”


➲ኸጢብ አልበግዳድይ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“ያለወጭ ገንዘብ እንደማይጠቅመው ሁሉ በእርሱ ለሰራበት፣ ዋጅቦችን ተጠባብቆ ለፈጸመ እንጅ እውቀትም እንዲሁ አይጠቅምም፡፡ አንድ ግለሰብ ነፍሱን ይመልከት ፤ወቅቱን ይጠቀምበት ፤ … ጉዞው ቅርብ ነው ፤ መንገዱ አስፈሪ ነው ፤ መታለሉ ብዙ ነው ፤ አደጋው ትልቅ ነው ፤… አላህ በመጠባበቂያ (ቦታ) ላይ ነው ፤ መመለሻው ወደርሱ ነው፡፡ አል ኸጢብ ፊልኢቅቲዳ፡(12)

➤አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

◀فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ ⓻وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ⓼

➧“የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል፡፡ የብናኝ ክብደት
ያክልም ክፉን የሰራ ሰው ያገኘዋል
፡፡” ዘልዘላህ፡(7_8)

▪️ሀሰን አልበስርይ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

◀"أنزل القرآن ليعمل به، فاتخذ الناس تالوته عمال"
“ቁርኣንን ያወረደው በእርሱ ሊሰሩበት ነው፡፡ ሰዎች ግን ማንበቡን ስራ አድርገው
ይዘውታል
፡፡” ይህን ንግግር ብን አልጀውዝ “ተብሊስ ወኢብሊስ” በሚባለው ኪታብ ከዘገበ በኋላ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

▪️"أنهم اقتصروا على التالوة، وتركوا العمل به"
➲"እነርሱ በንባቡ ብቻ ተገደቡ በእርሱ መስራትን ተው”
ተብሊስ ወኢብሊስ፡ ገፅ(137)

➧ለኢብራሂም ብን አድሀም -ረሂመሁሏህ- አንድ ሰው የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበላቸው፡- “አላህ በቁርኣኑ “እኔን ለምኑኝ እቀበላችኋለሁ” ጋፊር፡ (60) በማለት ተናግሮ ሲያበቃ እኛ ዱዓ እያደረግን ለምንድን ነው ዱዓችን ተቀባይነትን ያጣው?” በማለት
ጠየቃቸው
፡፡

➲ኢብራሂም ለዚህ ሰው የሚከተለውን መልስ ሰጡት፡-“ዱዓችን ተቀባይነት ያጣው በአምስት ምክንያቶች ነው” በማለት መልስ ሰጡት፡፡እርሱም “ምንድን ናቸው?!” በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም “አላህን አውቃችሁ
የእርሱን ሐቅ አለመወጣታችሁ
፡፡ ቁርኣንን አንብባችሁ በእርሱ አለመስራታችሁ፡፡ረሡልን صلى الله عليه وسلم እንወዳለን ብላችሁ ሱናቸውን በመተዋችሁ፤ ኢብሊስን እንራገማለን ትላላችሁ ነገር ግን እርሱን ትታዘዛላችሁ ፤ አምስተኛ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ የሰው ነውር ትከታተላላችሁ፡፡” ጃሚዑ በያኒ አል ዒልም፡(1220)

〰 〰 〰 〰 〰 〰 〰

➧ኢንሻአላህ ክፍል አስራ አምስት ይቀጥላል◉◉◉✍


➧ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‏ ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ ‏ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.


▪️وعن عبد اللَّه بن عمرو بن العــــــاص رَضِيَ اللَّهُ عَنهُما أنه سمع رَسُــول اللَّهِ ﷺ يقول: (من صلي عليّ صلاة صلى اللَّه عليه بها عشرا)

📖| رواه مسلم
.https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
‏‌‎
.