💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ወንጀልና አመጽ በግለሰብና በማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ, በወንድም ሪድዋን ዳውድ (03-04…
محضراة جديدة

بعنوان: "آثار الذنوب والمعاصي على الفرد والمجتمع"

لأخ الفاضل رضوان داود حفظه الله

بالمسجد البخاري بمدينة بحر دار

تاريخ جماد الأولى ٨ \ ١٤٤٣ه‍
አዲስ ሙሓዶራ

ርዕስ – "ወንጀልና አመፅ በግለሰብና በማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ"

በወንድም ሪድዋን ዳውድ ሃፊዞሁሏህ

ታህሳስ ‐ 03 ‐ 2014

በመስጅደል ቡኻሪ (ባህር ዳር)

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧አትራፊ የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ሁለት ➲ኢማንና መልካም ስራ በቁርኣን ውስጥ ተቆራኝተው መምጣታቸው ሁለቱ የጠበቀ ቁርኝት እንዳላቸው ይጠቁማል፡፡ የቁርዓን አንቀጾችን በደንብ ከተከታተልን አንዳንድ ቦታ ኢማን ለመልካም ስራ መስፈርት ሆኖ ይመጣል፡፡ አንዳንድ ቦታ ደግሞ መልካም ስራ ለኢማን መስፈርት ሆኖ ይመጣል፡፡ ➭ኢማን ለመልካም ስራ መስፈርት የሆኑባቸው የቁርኣን አንቀጾች…
አትራፊው የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ክፍል ሶስት

የመልካም ስራ ፍሬዎችና አሻራዎች


➧በዱንያም ይሁን በአኼራ የሰው ልጅ የመልካም ስራ ፍሬዎቹና አሻራዎቹ በጣም በርካታ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ይህችን ዓለም በሚለቅበት ጊዜ ንብረቶች ፣ ገንዘቦች ፣ዘመዶች ንግዶች..ተከትለውት እንደማይሄዱ ይወቅ፡፡ ቀብር ውስጥ ተከትሎት የሚገባው መልካምም ይሁን መጥፎ ፣ ስራው ብቻ ነው፡፡

በቡኻሪና ሙስሊም በተዘገበ ሐዲስ አነስ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

"يتبع الميت ثالثة، فيرجع اثنان ويبقى معه واحد: يتبعه أهله وماله وعمله، فيرجع أهله وماله ويبقى عمله"

ሟችን ሶስት ነገሮች ይከተሉታል ፤ ሁለቱ ይመለሳሉ አንዱ ብቻ ይቀራል ፤ ቤተሰቦቹ ፣ገንዘቡ እና ስራው ይከተሉታል ፤ ቤተሰቡና ገንዘቡ ይመለሳሉ ስራው ብቻ ይቀራል፡፡” ቡኻሪ፡6514 ሙስሊም፡2960

ቀብሩ ውስጥ ተከትሎት የሚገባው ስራው ብቻ ነው፡፡ልጅ የፈለገውን ያክል አባቱን ቢያፈቅር ለተወሰነ ደቂቃ እንኳ ቢሆን ቀብር ውስጥ አብሮት መቆየት አይችልም፡፡ ምን የበዛ ሐብትና ንብረት ቢኖረው ቀብር ውስጥ ተከትሎት አይገባም፡፡

በይሐቅይ “ሹዓቡል ኢማን” በሚባለው ኪታባቸው አቡሁረይራ ረድየላህ አንሁ ያስተላለፉትን ሀዲስ እንደሚከተለው ዘግበዋል፡፡

"مثل ابن آدم وماله وعمله مثل رجل له ثالثة أخالء ، قال له أحدهم : أنا معك ما
دمت حيا ، فإذا مت فلست مني ولا أنا منك ، فذلك ماله ، وقال الآخر : أنا معك فإذا بلغت إلى قبرك فلست مني ولست لك ، فذلك ولده ، وقال الآخر : أنا معك حيا وميتا فذلك عمله"


➲“የሰው ልጅ ገንዘቡ እና ስራው ልክ እንደሚዋደዱ ሶስት ጓደኛሞች ነው። ከመካከላቸው አንዱ “አንተ እስካለህ ድረስ አብሬህ ነኝ ፤ አንተ ከሞትክ ግን አንተ ከእኔ ፣ እኔም ከአንተ አይደለሁም፡፡” ይለዋልይህ ገንዘቡ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ “እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ፤ ቀብር የደረስክ ጊዜ አንተም ከእኔ ፣ እኔም ከአንተ አይደለሁም፡፡” ይለዋል ፤ ይህ ደግሞ ልጁ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ፡ “እኔ በህይዎትም ይሁን በሞትህ ጊዜ ከአንተ አልለይም” ይለዋል ፤ ይህ ደግሞ ስራው ነው፡፡ በይሐቅይ ሹዓቡል ኢማን፡9993 ፣ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ በለውታል አስ ሶሂህ፡ 2481

ኢብን አል'ቀይም ረሂመሁላህ አንድ ጥበበኛ ተጠይቆ የሰጠውን ምላሽረውዶቱል ሙሂቢንከሚባለው ኪታባቸው ላይ አስፍረውታል፡-
“ከጓደኞችህ መካከል የትኛው ነው ለአንተ በጎ የሚሰራልህ?” ተብሎ ጥበበኛው ሰው ተጠየቀ፡፡ “መልካም ስራ” የሚል ምላሽ ሰጠ፡፡ መልካም ስራ በጎ የሆነ ጓደኛ ነው፡፡ ብርቱና ከባድ በሆነው ቀብር ውስጥ በምትጋደምበት ጊዜ አብሮህ የማይለየው የሰራሃው በጎ ስራ መሆኑን አስተውል!



ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ


ሄን ፅሁፍ በታከታታይ ለመገኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሀያእ ለሴት ልጅ ብቻ ሳይሆን ለወንድ ልጅም አስፈላጊ ነው! ወንድ ልጅ ሀያእ ሲኖረው አሳዳጊውን ያስመሰግናል! ሴቶች ለሱ ያላቸው ፍላጎትም እየጨመረ ይሄዳል!!!

( الكلم الطيبة189)
💎🌸💎🌸💎🌸💎🌸
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➛ክፍል ሰላሳ ➲ተመልከቱ ይህንን ቆሻሻ ንግግር “አቤት ብዬ ልጩህ እባሮቹ በር” ሁሉም ባሪያዎች ከአላህ ከጃይ ደሃዎች ናቸው። ቢጮህባቸው ምንም ማድረግ የማይችሉትን በመለመን ሁለት አገር መክሰር ይልሃል ይህ ነው። “አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር (ሁለንተናችንን ለእናንተ ተገዢ አድርገናል)” ሱብሃነላህ! ሁለንተናችንን አምልኮን ለእርሱ በማጥራት ልንሰጥ የሚገባው ለአላህ…
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል ሰላሳ አንድ
➻➻➻➻➻➻➻➻

➢“ታመን ነበር ፈወሱን፣
ተርበን ነበር አጎረሱን፣
ታርዘን ነበር አለበሱን፣
ነብዩ የኛ ወለላ፣
የፍጡራን ሁሉ ጥላ፣
ጨለማ ውስጥ ላሉ ብርሀን፣
በሽርክ ለተጎሳቆሉ ኢማን፣
ለተሰቃዩ መጠጊያ፣
ለዋለሉት ሁሉ መርጊያ፣
በርሳቸው ጭንቀት በረካ፣
ዓለም በእስልምና ፈካ።”


የታመመን የሚያድነው አላህ ነው። የተራበን የሚያጎርሰው አላህ ነውየታረዘን የሚያለብሰው አላህ ነው። አላህ እንዲህ ይላል “ሁላችሁም የተራባችሁ ናችሁ እኔ ያበላሁት ሲቀር። አብላን በሉኝ አበላችኋለሁ። ሁላችሁም የታረዛችሁ ናችሁ እኔ ያለበስኩት ሲቀር። አልብሰን በሉኝ አለብሳችኋለሁ”። የፍጡራን ሁሉ መጠጊያ አላህ ነው።

አላህ የሰማያትና የምድር አብሪ ነውጨለማ ውስጥ ያሉትን በሺርክ የተጎሳቆሉትን ወደ ብርሃኑ የሚመራው አላህ ብቻ ነው። የባርያዎች ልብ የሚገለባብጠው፣ የዋለሉትን በፍቃዱ የሚያረጋው አላህ ብቻ ነው

አብሽር ወንድሜ ግባ በቶሎ፣
ማነው ያፈረው ያነቢ ብሎ”
“አንቱን ጠርቼ ምን አጥቼ፣
ልሙት ፈንድቼ ልዮትና፣
አህመድ ሙሽራ የመዲና”
“የቦረናው ደግየ፣
እርዱኝ አባብየ”


ሰለፍም ኸለፍም ማወረአል ባህር፣
በሁለም ሸሸሁኝ አንድ እንኳን ሳይቀር፣
ከዛፍ ከቅጠሉ በዝቶብኛል ነውር፣
እሜዳው ላይ ሆኜ ወድቄ በዱር፣
መግቢያ በር አጥቼ ታግቼ ባጥር፣
አልሄድ ወደፊት ወደኋላ አልበር፣
በቀኝ በግራየ እሳት ገደል ባህር፣
አቤት ጠራኋችሁ ጌቶቼ ዱስቱር፣
ረዳቴ ማንነው ከናንተ በቀር”

እኚህ የእኛ ወንድሞች ብዙ ነው ሲርራቸው፣
እኚህ የእኛ ወንድሞች ሀያል ነው ትርፋቸው፣
እኝህ የእኛ ቅምጥሎች እኝህ የእኛ ሉሎች ሃያል ነው ትርፋቸው፣
ለቸገረን ሁላ ዛሬ ጠራናቸው፣
በአምስት ተግዝቶ እልፍ አእላፍ ትርፋቸው።”

የአርባው ልጅሁ፣
ቆሟል ከደጅሁ፣
ስጡት በእጅሁ፣
ከእዛ ከጉርጅሆ (ከካዝናዎ)”
“ጀሚእ አውሊያ ሁላ ወልዮቹ ሁሉ፣
በወራት ያላችሁ ወራት የኳላችሁ፣
ቸግሮናል እና እርዱን እባካችሁ፣
ለታመመው ወራት መድሃኒት ይዛችሁ፣
ታጥቀን ተሸምረን ዛሬ ጠራናችሁ፣
መቼም ለእርዳታ ነው ጀሊል ሲፈጥራችሁ።”


እኝህን ሳዳቶች ድረሱ አንበላቸው፣
እሱ ወደደና እሱ መረጣቸው፣
እመሀባው ባህር ሺህ አመት አስዋኛቸው፣
እሱ ወደዳቸው በፊት ሳይሰራቸው፣
ዩሂቡሁም ወዩሂቡነሁ አላቸው ጀባሩ፣
አቤት እርዱኝ ይላል የቤት ልጅ አሽከሩ፣
በናንተ የሸሸ የቂን ነው ማማሩ፣
ጥላቸው ጠባቂ በሁለት አገር”

የፍቅርህን ጥም አይበርድም በውሃ፣
አንተን የወደደ አይባልም ደሃ፣
ትረዳ የለም ወይ ከየትስ በረሃ፣
ሊጋባ ነህ አሉ ያረሱል ያጣሃ”


እነዚህን አካላት የሚጣራ ሁሉ ያለጥርጥር ጠላት ነው እያፈራ ያለው

➢ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል


ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጁሙዓ ቀን ሱናዎች

①) ገላን መታጠብ
②) ሲዋክ መጠቀም
③) ጥሩ ልብስ መልበስ
④) ሱረቱል ከህፍን መቅራት
⑤) ሽቶ መቀባት (ለወንዶች)
⑥)
ሑጥባ በጥሞና ማዳመጥ
⑦) በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ
⑧) በነብዩ ﷺ ላይ ሶላትና ሰለዋት ማብዛት
⑨) ዱአ ተቀባይነት ያለበትን ሰአት ስላለ መጠባበቅ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ክፍል አምስት ➛የእውቀት አላማው ተግባር ለመሆኑ ከማስረጃ ጋር በማስደገፍ የተወሰኑ ነጥቦችንመጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡ ➠የመጀመሪያው፡ እውቀትና ተግባር ሰዎች የተፈጠሩለት አላማ ነው ሁለቱ ፍጡራን የተፈጠሩበት አላማ ሲሆን የእውቀት አስፈላጊነቱ ለተግባር ነው፡፡ አላህ ፍጡራንን ሊያውቁት እና ሊግገዙት ፈጠረ፡፡ለመጀመሪያው ማስረጃ የሚከተለው…
የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ክፍል አምስት
➭➭➭➭➭➭➭➭

▪️ሱፍያን ብን ዑየይናህ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"من فسد من علمائنا ففيه شبه من اليهود ، ومن فسد من عبادنا ففيه شبه من النصارى"
➧“ከዑለማዎቻችን የተበላሹት ከአይሁድ ጋር መመሳሰል አላቸው። ከዓቢዶቻችን(ያለጥልቅ እውቀት አላህን የሚገዙት) የተበላሹት ደግሞ ከክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል አላቸው፡፡”
ምክንያቱም አይሁዶች እውቀት አላቸው ግን አይሰሩበትም
፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል


مَثَلُ الَّذِينَ حُمِّلُوا التَّوْرَاةَ ثُمَّ لَمْ يَحْمِلُوهَا كَمَثَلِ الْحِمَارِ يَحْمِلُ أَسْفَارًا ۚ

“የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት (ያልሰሩባት) ሰዎች
ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ቢጤ ነው፡፡” አል ጁሙዓ፡5

➧“ለም የህሚሉሃ” የሚለው የቁርኣን ቃል በእርሷ ያልሰሩ ማለት ነው፡፡ሸምድደዋታል ፣እርሷ የጠቆመችውን መልእእክት ተገንዝበዋል ነገር ግን በእርሷ ሊሰሩ አልቻሉም፡፡

ከዑባዶቻችን - ጥልቅ እውቀት የሌላቸው - ደግሞ የተበላሹት ከክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል አላቸው፡፡ ክርስቲያኖች የአዲስ ፈሊጥና ፈጠራ ፣ አላህ ለባሮች ማስረጃ ያላወረደለትን የአምልኮ አይነት በአዲስ መልክ የማምጣት (የመስራት) ባለቤት
ናቸው፡፡


ሁለተኛው፡ - አንድ ባሪያ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት ይጠየቃል
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
ረሡል صلى الله عليه وسلم ሰዎች የትንሳኤ ቀን ባገኙት እውቀት ምን እንደሰሩበት? ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡

▪️አቡ በርዘት ረድየላህ አንሁ ከረሡል صلى الله عليه وسلم ሰምቶ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡-

"لا تزول قدما عبد يوم القيامة حتى يسأل عن أربع – وذكر منها عليه الصالة
والسالم - : عن علمه ماذا عمل به"

“የትንሳኤ ቀን ከአራት ነገሮች ሳይጠየቅ የባሪያው እግር ካለበት ቦታ አይነቃነቅም - ከእነርሱ መካከል የአላህ መልእክተኛ የሚከተለውን አወሱ - ከእውቀቱ ምን
እንደሰራበት
፡፡” ቲርሚዚይ፡ 2417 አድ ዳሪሚይ፡ 554 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አት ቲርሚዚይ፡2417

▪️አቡ ደርዳእ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"إنما أخشى يوم القيامة أن يناديني ربي على رؤوس الخالئق ، فيقول : يا عويمر!
ماذا عملت فيما علمت؟

➽“እኔ የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጥረታቱ መካከል ጠርቶ 'አንተ ኡወይሚር ሆይ! በአወከው ምን ሰራህበት?' ብሎ እንዳይጠይቀኝ ነው የምፈራው
፡፡” ኢትሐፉል ኸይረቲ አል ሚህረቲ፡8/161

➧ይህ አስደንጋጭና አደገኛ የሆነ ቦታ ነው፡፡ ማንኛውም ባሪያ ከታነጸው እውቀት
በአወቅከው ነገር ምን ሰራህበት?” ተብሎ የትንሳኤ ቀን መጠየቁ አይቀርም፡፡ምክንያቱም የማወቃችን ትልቁ አላማ ተግባር ነው፡፡ ለዚህ ነው ማንኛውም ሰው ከተማረው ትምህርት የሚጠየቀው፡፡



ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ኒቃብን የተመለከተ ምክር


የኒቃብ አስፈላጊነት
ኒቃብ ለማይለብሱ ምክር
ኒቃብና አንዳንድ ስነስርአቶቹ
ኒቃብ በተመለከተ ብዥታዎች

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማንኛውም የሚደርስብን ስቃይና መከራ የስራችን ውጤት ነው

➧አላህ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ብሏል።

ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ
◾️ሰዎች በእጆቻቸው በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት ብልሽት (መከራ) በየብስና በባሕር ይፋ ሆነ (ተሰራጨ)፡፡
لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
◾️(ይህም የሆነው) የሠሩትን ስራ የከፊሉን ቅጣት ያቀምሳቸው ዘንድ ነው። (በዚህም ሰበብ ወደ አላህ) ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡

📚(ሱረቱ አል-ሩም - 41)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

🔹የአህባሾች ማምታቻ

ክፍል ③④


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ኒቃቤ ክብሬ ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫

ንግስት ለመባል ዘውድ አልሻም እኔ
ኒቃቤን ስለብስ ንግስት ነኝ ያኔ

↷⇣❪🌹❫⇣↶

መኖሬን መረጥኩኝ በሱና ታቅቤ አልደራደረም መቼም በኒቃቤ!!💎

የሂቡ ማም
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧አትራፊው የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➻ክፍል ሶስት ➲የመልካም ስራ ፍሬዎችና አሻራዎች ➧በዱንያም ይሁን በአኼራ የሰው ልጅ የመልካም ስራ ፍሬዎቹና አሻራዎቹ በጣም በርካታ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ይህችን ዓለም በሚለቅበት ጊዜ ንብረቶች ፣ ገንዘቦች ፣ዘመዶች ንግዶች..ተከትለውት እንደማይሄዱ ይወቅ፡፡ ቀብር ውስጥ ተከትሎት የሚገባው መልካምም ይሁን መጥፎ ፣…
አትራፊ የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ክፍል አራት
➻➻➻➻➻➻

➧“ሙስነድ ኢማም አህመድ” ኪታብ ላይ በራእ ብን ዓዚብ ረድየላህ አንሁ ካስተላለፈው ረጅም ሐዲስ ውስጥ የሚከተለው የረሡል صلى الله عليه وسلم ንግግር ይገኝበታል፡-

▪️"ويأتيه رجل حسن الوجه حسن الثياب طيب الريح، فيقول: أبشر بالذي يسرك هذا يومك الذي كنت توعد، فيقول له: من أنت فوجهك الوجه يجيء بالخير؟ فيقول: أنا عملك الصالح"

➭“በመልካም ፊት ፣ በመልካም ልብስ ፣ ሽታው አሪፍ በሆነ (ሁኔታ) አንድ ሰው (ቀብር ውስጥ) ይመጣል፡፡” ፤ “በዚህ በሚያስደስትህ ፣ በዚህ ስትቀጠረው በነበረው ቀን አብሽር” ይለዋል፡፡ ሟች ፡ “በመልካም ፊት የመጣሃው ሰው ማን ነህ?” በማለት ግለሰቡን ይጠይቀዋል፡፡ “እኔ መልካም ስራህ ነኝ” በማለት ይመልስለታል፡፡
አህመድ፡ 18534 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል አህካሙ አል ጀናኢዝ፡ ገፅ 159

▪️وجاء في "الصحيح" عن النبي صلى الله عليه وسلم: أنه قال: "إذا وضعت الجنازة، فاحتملها الرجال على أعناقهم فإن كانت صالحة قالت: قدموني، وإن كانت غير صالحة قالت: يا ويلها، أين يذهبون بها"

በትክክለኛ ሐዲስ ነብዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “ጀናዛዋ የተቀመጠች ጊዜ ፤ ሰዎች በጫንቃዎቻቸው ይሸከሟታል ፤ መልካም ከሆነች አስቀድሙኝ ትላለች ፤ ከመልካም ውጭ ከሆነች ደግሞ “ወይ ጥፋቷ! የት ነው ይዘዋት የሚሄዱት?” ትላለች፡፡ ቡኻሪ፡1314

የመልካም ስራ ታላቅነትን የሚጠቁሙ መረጃዎች በርካታ ናቸው፡፡ ለመልካም ስራ አላህ የገጠማቸው ሰዎች የአትራፊ ንግድ ባለቤቶች ናቸው፡፡ ከእነርሱ ውጭ ያሉ ከሀዲዎች ደግሞ አጓዳዮች ጸጸት በማይጠቅምበት ቀን በታላቅ ጸጸት ውስጥ ይሆናሉ፡፡

ብልህ እና አስተዋይ የሚባለው ነፍሱን የተቆጣጠረ ፣ ከሞት በኋላ ላለው ህይዎቱ የሚሰራ ነው ፤ ደካማ ማለት ደግሞ የነፍሱን ስሜት የሚከተል ፣ በአላህ ላይ ከንቱ ምኞትን የሚመኝ ነው፡፡

በዚህ ትርጉም ላይ ዓልይ ብን አቢጧሊብ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተኗግሯል፡-

▪️"ارتحلت الدنيا مدبرة، وارتحلت الآخرة مقبلة، ولكل واحدة منهما بنوه، فكونوا منأبناء الآخرة، ولا تكونوا من أبناء الدنيا، فإن اليوم عمل ولا حساب، وغدا حساب ولا عمل"

➧“ዱንያ ፊቷን አዙራ ወደኋላ ተመለሰች ፣ አኼራ ደግሞ ፊት ለፊት ተጓዘች ፤ ለእያንዳንዳቸው ልጆች አሏቸው ፤ ከአኼራ ልጆች ሁኑ ፣ ከዱንያ ልጆች አትሁኑ ፤ ዛሬ ሂሳብ የለም የስራ ቀን ብቻ ነው ፣ ነገ ደግሞ ሂሳብ እንጅ ስራ የለም፡፡”
ኢማም አል ቡኻሪ ኪታቡ አር ሪቃቅ ባቡን ፊል አመሊ ወጡሊሂ በተዕሊቅ ዘግበውታል

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡
لِمِثْلِ هَٰذَا فَلْيَعْمَلِ الْعَامِلُونَ

“ለዚህ ብጤ ሰሪዎች ይስሩ፡፡”
አስ ሷፋት 61

ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ


➳ሄን ፅሁፍ በታከታታይ ለማገኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

🔹የአላህ እዝነት በተመለከተ

ክፍል ③⑤


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሸይኽ ፈውዛን - አላህ ከክፉ ይጠብቃቸውና - ዒልም ፈላጊ ተማሪዎችን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፦

እውቀትን ከመፈለግ አትሰልች።
አያያዝህ ትንሽ ቢሆን እንኳ እውቀትን ፈልግ። መልካም ስራ ከመስራት ጋር ሲሆን ትንሹም በረካ አለበት።


እውቀት ፍለጋ ላይ መቀጠል ያለጥርጥር ኸይር ነው። እውቀት ፍለጋ ዒባዳ ነው።እውቀት ፍለጋ ግዴታ ካልሆኑ ዒባዳዎች የበለጠ ነው።"

[አልኢጃባቱል ሙሃማህ፡ 84]