💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሀያ ስምንት 〰〰〰〰〰〰 ➭“ለኸልቁ ገበያ መድሀኒት ነበር፣ የቸገረው ሄዶ የለውም ማፈር፣ ከሀያቱ በልጧል ውለታው በቀብር፣ ወዲያልኝ የሱ ጉድ አያልቅም ይቅር” ➭ “ጌታው ሰይድ አህመድ የደባቱ ኑር፣ ዶላል ያስፈቀተው የዲኑ ጨረር፣ ስፍር ቁጥር የለው ስንቱ በእጁ ሻረ፣ አላህ ዘንድ ነበር ተናግሮ የማያፍር፣ ቢያለብስም ቢገፋም…
➧መንዙማ
➫➫➫➫➫

➭ክፍል ሀያ ዘጠኝ

➲የአላህ ውድ ባሪያ ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ለራሳቸው ጥቅም ማምጣት፣ ከራሳቸው ላይ ጉዳትን መከላከል አይችሉም። የሩቅንም አያውቁም። አላህ ነብዩንصلى الله عليه وسلم ይህን አስመልክቶ ግልፅ እንዲያደርጉ እንዲህ ሲል ያዛቸዋል

قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ الْغَيْبَ لَاسْتَكْثَرْتُ مِنَ الْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِيَ السُّوءُ ۚ إِنْ أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

“አላህ የሻውን በስተቀር ለእራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም። ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር። እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም” በላቸው።

[አልአዕራፍ፡ 188]

وَإِن يَمْسَسْكَ اللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُ إِلَّا هُوَ ۖ وَإِن يَمْسَسْكَ بِخَيْرٍ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
“አላህም በጉዳት ቢነካህ ለእርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም። በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።” [አልአንዓም፡17

لَهُ دَعْوَةُ الْحَقِّ ۖ وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِهِ لَا يَسْتَجِيبُونَ لَهُم بِشَيْءٍ إِلَّا كَبَاسِطِ كَفَّيْهِ إِلَى الْمَاءِ لِيَبْلُغَ فَاهُ وَمَا هُوَ بِبَالِغِهِ ۚ وَمَا دُعَاءُ الْكَافِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَالٍ

“እውነተኛ አምልኮ ለአላህ ብቻ ነው። እነዛ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው በምንም ነገር ምላሽ አይሰጧችሁም። ከአላህ ሌላ የሚያመልኩ ሰዎች ምሳሌያቸው እጁን ወደ ውሀ እነደሚዘረጋ ወደ አፉ ለማድረስ ፈፅሞ ማድረስ አይችልም።” [
አርረዕድ፡ 14]

➧አላህ አሁንም ለሰው ልጆች አዛኝ ነውና በሚገባቸው መልክ ከእርሱ ውጭ
የሚመለኩት እንደ አምላኪዎቻቸው ፍጡር መሆናቸውን እንዲህ ሲል ይነግረናል

إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

“እነዛ ከአላህ ውጭ የምትጠሯቸው እንደናንተው ባሪያዎች ናቸው ጥሯቸው እስኪ በእውነት እሺ ይበሏችሁ
።” [አእራፍ 194]

حُنَفَاءَ لِلَّهِ غَيْرَ مُشْرِكِينَ بِهِ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ السَّمَاءِ فَتَخْطَفُهُ الطَّيْرُ أَوْ تَهْوِي بِهِ الرِّيحُ فِي مَكَانٍ سَحِيقٍ

“ለአላህ ታዛዦች በርሱ የማታጋሩ ሆናችሁ (ከሀሰት ራቁ) በአላህም የሚያጋራ ሰው ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ነፋስ እርሱን በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ብጤ ነው።
” [አልሐጅ 31]

➭የሚከተሉት ስንኞች መንዙማ ባዮች የአላህን መብት (አምልኮ) ከእሱ ላይ አንስተው ለነብዩ (صلى الله عليه وسلم እና ለሌሎች ፍጡራን የሰጡበት ነው። አንባቢ እነዚህን የመንዙማ ስንኞች ብዙ ቦታ እንደሚሰማቸው እጠብቃለሁ።

➲ የኢስላም አካልም ተደርገው ይወሰዳሉ። ነገር ግን እንዲህ ዝርዝር ብለው ሲቀመጡ ምን ያህል ከምንወደው ጌታችን ጋር ሊያጣሉን እና ሊያራርቁን የሚችሉ በኢስላም ስም የመጡ ግን የሰይጣን ወጥመዶች መሆናቸውን እንረዳለን።

➧“በዝቶብኛልና አያሌ ነገር፣
አቤት ብየ ልጩህ እባሮቹ በር፣
ቀልቤን ወዳሳቸው አድርጌ ሰንዘር፣
አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር፣
ከሙስጠፋ ይዤ እስከ አቡል በሸር፣
አምቢያ ሙርሰልም አንድ እንኳን ሳይቀር”

➛አማኝ የፈለገውን ያህል ችግር ቢበዛበት ሁሉን ነገሩን እንዲያገራለት የሚለምነው ሁሉን ቻይ የሆነውን አጋር የሌለው አንድ አምላክ አላህ ብቻና ብቻ ነው።
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➭አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል አራት ➲ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡- "من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين" “በእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን ያስገነዝበዋል” ቡኻሪ፡ 71ሙስሊም፡1037 ➧“ኸይረን” የሚለው ቃል በነኪራ (ሁሉን በሚያካትት ቃል) መምጣቱ…
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ክፍል አምስት

➛የእውቀት አላማው ተግባር ለመሆኑ ከማስረጃ ጋር በማስደገፍ የተወሰኑ ነጥቦችንመጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡

➠የመጀመሪያው፡ እውቀትና ተግባር ሰዎች የተፈጠሩለት አላማ ነው ሁለቱ ፍጡራን የተፈጠሩበት አላማ ሲሆን የእውቀት አስፈላጊነቱ ለተግባር ነው፡፡
አላህ ፍጡራንን ሊያውቁት እና ሊግገዙት ፈጠረ፡፡ለመጀመሪያው ማስረጃ የሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ነው፡

اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ وَمِنَ الْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ يَتَنَزَّلُ الْأَمْرُ بَيْنَهُنَّ لِتَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا
“አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፡፡ ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሯል)
በመካከላቸው ትዕዛዙ ይወርዳል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አላህም
በነገሩ ሁሉ በእውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ
)፡፡”
አጥ ጦላቅ፡12

➭እውቀት ፍጡራን የተፈጠሩበት አላማ ነው ለሚለው ደግሞ ማስረጃው የሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ነው፡

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም
፡፡

➧እውቀትና አምልኮ ሁሉም ሰዎች የተፈጠሩበት አላማ ነው፡፡ ወደአላህ የሚያቃርብ በሆነ ጠቃሚ እውቀት ካልሆነ በቀር አምልኮት አምልኮ ሊሆን አይችልም፡፡ አውቆ የሰራ የተፈጠረበትን አላማ በትክክል አሳክቷል፡፡

➳በዚህ ምክንያት የእውቀት ባለቤቶች የሚከተለውን ይናገራሉ፡-
➧“ለእርሱ ሲባል የተፈጠርንበት ፣ እርሱን ለማረጋገጥ የተገኘንበት ተውሂድ ሁለት ጎኖች አሉት፡፡ የእውቀት ጎንና የተግባር ጎን ናቸው፡፡

➲በእውቀት የምናጸድቀው የተውሂድ ክፍል እና በተግባር ተፈጻሚና ተፈላጊ የሆነው የተውሂድ ክፍል ናቸው፡፡ አምልኮ በተገቢው ሁኔታ ሊረጋገጥ ፣ ባሪያው ለአላህ ትክክለኛ ታዛዥ ይሆን ዘንድ የግድ ሁለቱ መኖርአለባቸው፡፡”

➠ያለተግባር የእውቀት ባለቤት ቢሆን በአላህ ቁጣ ይመለሳል፡፡ ምክንያቱም
የእውቀትን አላማ በትክክል አላረጋገጠም፡፡ ያለእውቀት የተግባር ባለቤት ከሆነ ደግሞ ቀጥተኛ ከሆነው የአላህ መንገድ ይንሻፈፋል፡፡


➭ለዚህ ነው ታላላቅ ዱዓዎችን በውስጧ የሚገኝባትን ፋቲሃ ዘወትር በየሶላታችን
እንድንቀራት በሸሪዓ የተደነገገው፡፡


اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ ⓺صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ⓻


“ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡ የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ
ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን ፤ በሉ
)፡፡”አል ፋቲሃ ፡6_7

➠በእነርሱ ላይ ጸጋውን የዋለላቸው ሰዎች የእውቀትና የተግባር ባለቤቶች ናቸው፡፡በእነርሱ ላይ አላህ የተቆጣባቸው ሰዎች ደግሞ ተግባር የሌላቸው የእውቀት ባለቤቶች ናቸው፡፡ የተሳሳቱ የተባሉት ደግሞ ያለእውቀት የሚሰሩ ሰዎች ናቸው፡፡
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ③②➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ③③➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ሀያ ዘጠኝ ➲የአላህ ውድ ባሪያ ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ለራሳቸው ጥቅም ማምጣት፣ ከራሳቸው ላይ ጉዳትን መከላከል አይችሉም። የሩቅንም አያውቁም። አላህ ነብዩንصلى الله عليه وسلم ይህን አስመልክቶ ግልፅ እንዲያደርጉ እንዲህ ሲል ያዛቸዋል قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا…
➧መንዙማ
➫➫➫➫➫

➛ክፍል ሰላሳ

➲ተመልከቱ ይህንን ቆሻሻ ንግግር “አቤት ብዬ ልጩህ እባሮቹ በር” ሁሉም ባሪያዎች ከአላህ ከጃይ ደሃዎች ናቸው። ቢጮህባቸው ምንም ማድረግ የማይችሉትን በመለመን ሁለት አገር መክሰር ይልሃል ይህ ነው። “አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር (ሁለንተናችንን ለእናንተ ተገዢ አድርገናል)” ሱብሃነላህ! ሁለንተናችንን አምልኮን ለእርሱ በማጥራት ልንሰጥ የሚገባው ለአላህ ብቻ ነው።

➭ነብያት ምን መልክት ይዘው እንደመጡ አያውቅምን? አኡዙቢላሂ ነብያት አይደለም ከአላህ ሌላ ሊያመለኩ፣ እነሱ እራሳቸው ከአላህ ሌላ አታምልኩ አላህንም በብቸኝነት አምልኩ በማለት ላይ ነው ህይወታቸውን ያሳለፉት።

➧ከዚህ ሁሉ በላይ የሚያሳዝነው ታላቁን የተውሒድ አስተማሪ ነብዩን صلى الله عليه وسلم እከተላለሁ እያሉ እሳቸው ይዘውት የመጡትን ዋና መልክት ማንኮታኮታቸው ነው።

“በዘመን ያላችሁ ሳዳቶች አኽያር፣
ቀኝ እጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀር፣
ሺሊላህ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር፣
መቼም ያለናንተ ሁሉም አያምር፣
በናንተ የሸሸ ምንም አያፍር፣
ጌቶቼ አትለፉኝ አደቤም ባያምር፣
አደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር፣
ባሪያ ሲባል ማጥፋት እለት ነው እድር፣
ለናንተ ይገባል ያጠፋን መማር።”


➧ከአላህ ውጭ የሚለምን እማ ወድቆ
የቀረ ውዳቂ ነው። ሁለት አገር ባርያዎቹን ጥሎ የማይጥለው አላህ ብቻ ነው። አዎን እንዲህ አይነት በሺርክ የተሞላ መንዙማን የሚል ሰው ከኢብራሂም መንገድ ያፈነገጠ ቂል እና አደበ ቢስ ነው። ከአላህ ውጭ ወንጀልን የሚምር የለም።

➠ የስነስርዓት ባለቤት የሆኑት ነብዩ صلى الله عليه وسلم ጌታችንን አላህ እንዲህ ሲሉ ምህረትን ይለምኑታል“አላህ ሆይ! ነፍሴን ብዙ በደል በድያለሁ እነሆ ካንተ ውጭ ወንጀልን የሚምር የለም ማረኝ”

“አልሀምዱሊላሂ ይመስገን ገፋር፣
ቀልቤን ያዞረልኝ ወደናንተ በር፣
በናንተ የሸሸ ያገኛል ሹም ሽር፣
ሊለግስ ነው መሰሌ ዳመናው ዟዟረ፣
የስልካችሁ ንባብ ይሰማ ጀመረ።”


➲አላህ ልባችንን ወደሱ እንድናዞር ነው ያዘዘን። አላህ በሺርክና በኩፍር አያዝም። መንዙማ ባዩ አላህን እየወነጀለ ነው። አላህ ወደ እሱ እንድንሸሽ ነው ያዘዘን። መሾም መሻር የአላህ ስልጣን ብቻ ነው። ሰጪውም ለጋሹ የሁሉ ባለቤት አላህ
ብቻ ነው።


“ሁሉም ባንድ ሆነው ከሙስጠፋ ጋር፣
ዛሬ ይድረሱልን ላገኘን ችጋር”

➧ነብዩ صلى الله عليه وسلم እና የተቀሩት ነብያት በጠቅላላ ከመላእክቶች ከጂኖች ጭምር ቢሰበሰቡ ለማንም ሊደርሱ አይችሉም። አላህ እንዲህ ይላል፡

وَإِن يَمْسَسْكَ اللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُ إِلَّا هُوَ ۖ وَإِن يُرِدْكَ بِخَيْرٍ فَلَا رَادَّ لِفَضْلِهِ ۚ

“አላህም ጉዳትን ቢያደርስብህ ከርሱ ሌላ ለርሱ ገላጭ የለውም። በጎንም ነገር ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ የለውም።”
[ዩኑስ፡ 107]

“አብድ ብሎ እስኪሉ ቃድር፣
እርዳታው አይውል አያድር።”

➧አላህ ደግሞ ከሱ ውጭ የሚጠሩ አካላት እንኳን እንዲህ ፈጣን መልስ ሊሰጡ ይቅርና ዘላለም መልስ መስጠት አይችሉም። እንዲህ አይነት ዝንጉዎችን እንደሚማፀን ሰው ጠማማ የለም ይላል። ይሄውና

وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُو مِن دُونِ اللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَن دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ

“እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስም ለርሱ የማይመልስለትን ከአላህ ሌላ ከሚጣራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው።” [አልአሕቃፍ፡ 5]


➧ኡንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉✍


📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
ወንጀልና አመጽ በግለሰብና በማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ, በወንድም ሪድዋን ዳውድ (03-04…
محضراة جديدة

بعنوان: "آثار الذنوب والمعاصي على الفرد والمجتمع"

لأخ الفاضل رضوان داود حفظه الله

بالمسجد البخاري بمدينة بحر دار

تاريخ جماد الأولى ٨ \ ١٤٤٣ه‍
አዲስ ሙሓዶራ

ርዕስ – "ወንጀልና አመፅ በግለሰብና በማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ"

በወንድም ሪድዋን ዳውድ ሃፊዞሁሏህ

ታህሳስ ‐ 03 ‐ 2014

በመስጅደል ቡኻሪ (ባህር ዳር)

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧አትራፊ የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ሁለት ➲ኢማንና መልካም ስራ በቁርኣን ውስጥ ተቆራኝተው መምጣታቸው ሁለቱ የጠበቀ ቁርኝት እንዳላቸው ይጠቁማል፡፡ የቁርዓን አንቀጾችን በደንብ ከተከታተልን አንዳንድ ቦታ ኢማን ለመልካም ስራ መስፈርት ሆኖ ይመጣል፡፡ አንዳንድ ቦታ ደግሞ መልካም ስራ ለኢማን መስፈርት ሆኖ ይመጣል፡፡ ➭ኢማን ለመልካም ስራ መስፈርት የሆኑባቸው የቁርኣን አንቀጾች…
➧አትራፊው የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➻ክፍል ሶስት

➲የመልካም ስራ ፍሬዎችና አሻራዎች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➧በዱንያም ይሁን በአኼራ የሰው ልጅ የመልካም ስራ ፍሬዎቹና አሻራዎቹ በጣም በርካታ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ይህችን ዓለም በሚለቅበት ጊዜ ንብረቶች ፣ ገንዘቦች ፣ዘመዶች ንግዶች..ተከትለውት እንደማይሄዱ ይወቅ፡፡ ቀብር ውስጥ ተከትሎት የሚገባው መልካምም ይሁን መጥፎ ፣ ስራው ብቻ ነው፡፡

➧በቡኻሪና ሙስሊም በተዘገበ ሐዲስ አነስ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

"يتبع الميت ثالثة، فيرجع اثنان ويبقى معه واحد: يتبعه أهله وماله وعمله، فيرجع أهله وماله ويبقى عمله"

“ሟችን ሶስት ነገሮች ይከተሉታል ፤ ሁለቱ ይመለሳሉ አንዱ ብቻ ይቀራል ፤ ቤተሰቦቹ ፣ገንዘቡ እና ስራው ይከተሉታል ፤ ቤተሰቡና ገንዘቡ ይመለሳሉ ስራው ብቻ ይቀራል፡፡” ቡኻሪ፡6514 ሙስሊም፡2960

➠ቀብሩ ውስጥ ተከትሎት የሚገባው ስራው ብቻ ነው፡፡ልጅ የፈለገውን ያክል አባቱን ቢያፈቅር ለተወሰነ ደቂቃ እንኳ ቢሆን ቀብር ውስጥ አብሮት መቆየት አይችልም፡፡ ምን የበዛ ሐብትና ንብረት ቢኖረው ቀብር ውስጥ ተከትሎት አይገባም፡፡

➛በይሐቅይ “ሹዓቡል ኢማን” በሚባለው ኪታባቸው አቡሁረይራ ረድየላህ አንሁ ያስተላለፉትን ሀዲስ እንደሚከተለው ዘግበዋል፡፡

"مثل ابن آدم وماله وعمله مثل رجل له ثالثة أخالء ، قال له أحدهم : أنا معك ما
دمت حيا ، فإذا مت فلست مني ولا أنا منك ، فذلك ماله ، وقال الآخر : أنا معك فإذا بلغت إلى قبرك فلست مني ولست لك ، فذلك ولده ، وقال الآخر : أنا معك حيا وميتا فذلك عمله"


➲“የሰው ልጅ ገንዘቡ እና ስራው ልክ እንደሚዋደዱ ሶስት ጓደኛሞች ነው። ከመካከላቸው አንዱ “አንተ እስካለህ ድረስ አብሬህ ነኝ ፤ አንተ ከሞትክ ግን አንተ ከእኔ ፣ እኔም ከአንተ አይደለሁም፡፡” ይለዋል ፤ ይህ ገንዘቡ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ “እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ፤ ቀብር የደረስክ ጊዜ አንተም ከእኔ ፣ እኔም ከአንተ አይደለሁም፡፡” ይለዋል ፤ ይህ ደግሞ ልጁ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ፡ “እኔ በህይዎትም ይሁን በሞትህ ጊዜ ከአንተ አልለይም” ይለዋል ፤ ይህ ደግሞ ስራው ነው፡፡ በይሐቅይ ሹዓቡል ኢማን፡9993 ፣ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ በለውታል አስ ሶሂህ፡ 2481

➭ኢብን አል'ቀይም ረሂመሁላህ አንድ ጥበበኛ ተጠይቆ የሰጠውን ምላሽ “ረውዶቱል ሙሂቢን” ከሚባለው ኪታባቸው ላይ አስፍረውታል፡-
“ከጓደኞችህ መካከል የትኛው ነው ለአንተ በጎ የሚሰራልህ?” ተብሎ ጥበበኛው ሰው ተጠየቀ፡፡ “መልካም ስራ” የሚል ምላሽ ሰጠ፡፡ መልካም ስራ በጎ የሆነ ጓደኛ ነው፡፡ ብርቱና ከባድ በሆነው ቀብር ውስጥ በምትጋደምበት ጊዜ አብሮህ የማይለየው የሰራሃው በጎ ስራ መሆኑን አስተውል!
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ


➳ሄን ፅሁፍ በታከታታይ ለመገኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲ሀያእ ለሴት ልጅ ብቻ ሳይሆን ለወንድ ልጅም አስፈላጊ ነው! ወንድ ልጅ ሀያእ ሲኖረው አሳዳጊውን ያስመሰግናል! ሴቶች ለሱ ያላቸው ፍላጎትም እየጨመረ ይሄዳል!!!

( الكلم الطيبة189)
💎🌸💎🌸💎🌸💎🌸
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➛ክፍል ሰላሳ ➲ተመልከቱ ይህንን ቆሻሻ ንግግር “አቤት ብዬ ልጩህ እባሮቹ በር” ሁሉም ባሪያዎች ከአላህ ከጃይ ደሃዎች ናቸው። ቢጮህባቸው ምንም ማድረግ የማይችሉትን በመለመን ሁለት አገር መክሰር ይልሃል ይህ ነው። “አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር (ሁለንተናችንን ለእናንተ ተገዢ አድርገናል)” ሱብሃነላህ! ሁለንተናችንን አምልኮን ለእርሱ በማጥራት ልንሰጥ የሚገባው ለአላህ…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሰላሳ አንድ
➻➻➻➻➻➻➻➻

➢“ታመን ነበር ፈወሱን፣
ተርበን ነበር አጎረሱን፣
ታርዘን ነበር አለበሱን፣
ነብዩ የኛ ወለላ፣
የፍጡራን ሁሉ ጥላ፣
ጨለማ ውስጥ ላሉ ብርሀን፣
በሽርክ ለተጎሳቆሉ ኢማን፣
ለተሰቃዩ መጠጊያ፣
ለዋለሉት ሁሉ መርጊያ፣
በርሳቸው ጭንቀት በረካ፣
ዓለም በእስልምና ፈካ።”


➲የታመመን የሚያድነው አላህ ነው። የተራበን የሚያጎርሰው አላህ ነው። የታረዘን የሚያለብሰው አላህ ነው። አላህ እንዲህ ይላል “ሁላችሁም የተራባችሁ ናችሁ እኔ ያበላሁት ሲቀር። አብላን በሉኝ አበላችኋለሁ። ሁላችሁም የታረዛችሁ ናችሁ እኔ ያለበስኩት ሲቀር። አልብሰን በሉኝ አለብሳችኋለሁ”። የፍጡራን ሁሉ መጠጊያ አላህ ነው።

➧አላህ የሰማያትና የምድር አብሪ ነው። ጨለማ ውስጥ ያሉትን በሺርክ የተጎሳቆሉትን ወደ ብርሃኑ የሚመራው አላህ ብቻ ነው። የባርያዎች ልብ የሚገለባብጠው፣ የዋለሉትን በፍቃዱ የሚያረጋው አላህ ብቻ ነው።

“አብሽር ወንድሜ ግባ በቶሎ፣
ማነው ያፈረው ያነቢ ብሎ”
“አንቱን ጠርቼ ምን አጥቼ፣
ልሙት ፈንድቼ ልዮትና፣
አህመድ ሙሽራ የመዲና”
“የቦረናው ደግየ፣
እርዱኝ አባብየ”


“ሰለፍም ኸለፍም ማወረአል ባህር፣
በሁለም ሸሸሁኝ አንድ እንኳን ሳይቀር፣
ከዛፍ ከቅጠሉ በዝቶብኛል ነውር፣
እሜዳው ላይ ሆኜ ወድቄ በዱር፣
መግቢያ በር አጥቼ ታግቼ ባጥር፣
አልሄድ ወደፊት ወደኋላ አልበር፣
በቀኝ በግራየ እሳት ገደል ባህር፣
አቤት ጠራኋችሁ ጌቶቼ ዱስቱር፣
ረዳቴ ማንነው ከናንተ በቀር”

“እኚህ የእኛ ወንድሞች ብዙ ነው ሲርራቸው፣
እኚህ የእኛ ወንድሞች ሀያል ነው ትርፋቸው፣
እኝህ የእኛ ቅምጥሎች እኝህ የእኛ ሉሎች ሃያል ነው ትርፋቸው፣
ለቸገረን ሁላ ዛሬ ጠራናቸው፣
በአምስት ተግዝቶ እልፍ አእላፍ ትርፋቸው።”

“የአርባው ልጅሁ፣
ቆሟል ከደጅሁ፣
ስጡት በእጅሁ፣
ከእዛ ከጉርጅሆ (ከካዝናዎ)”
“ጀሚእ አውሊያ ሁላ ወልዮቹ ሁሉ፣
በወራት ያላችሁ ወራት የኳላችሁ፣
ቸግሮናል እና እርዱን እባካችሁ፣
ለታመመው ወራት መድሃኒት ይዛችሁ፣
ታጥቀን ተሸምረን ዛሬ ጠራናችሁ፣
መቼም ለእርዳታ ነው ጀሊል ሲፈጥራችሁ።”


“እኝህን ሳዳቶች ድረሱ አንበላቸው፣
እሱ ወደደና እሱ መረጣቸው፣
እመሀባው ባህር ሺህ አመት አስዋኛቸው፣
እሱ ወደዳቸው በፊት ሳይሰራቸው፣
ዩሂቡሁም ወዩሂቡነሁ አላቸው ጀባሩ፣
አቤት እርዱኝ ይላል የቤት ልጅ አሽከሩ፣
በናንተ የሸሸ የቂን ነው ማማሩ፣
ጥላቸው ጠባቂ በሁለት አገር”

“የፍቅርህን ጥም አይበርድም በውሃ፣
አንተን የወደደ አይባልም ደሃ፣
ትረዳ የለም ወይ ከየትስ በረሃ፣
ሊጋባ ነህ አሉ ያረሱል ያጣሃ”


➭እነዚህን አካላት የሚጣራ ሁሉ ያለጥርጥር ጠላት ነው እያፈራ ያለው።

➢ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉✍

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል


➛ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✅የጁሙዓ ቀን ሱናዎች
〰〰〰〰〰〰〰〰
①) ገላን መታጠብ
②) ሲዋክ መጠቀም
③) ጥሩ ልብስ መልበስ
④) ሱረቱል ከህፍን መቅራት
⑤) ሽቶ መቀባት (ለወንዶች)
⑥)
ሑጥባ በጥሞና ማዳመጥ
⑦) በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ
⑧) በነብዩ ﷺ ላይ ሶላትና ሰለዋት ማብዛት
⑨) ዱአ ተቀባይነት ያለበትን ሰአት ስላለ መጠባበቅ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ክፍል አምስት ➛የእውቀት አላማው ተግባር ለመሆኑ ከማስረጃ ጋር በማስደገፍ የተወሰኑ ነጥቦችንመጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡ ➠የመጀመሪያው፡ እውቀትና ተግባር ሰዎች የተፈጠሩለት አላማ ነው ሁለቱ ፍጡራን የተፈጠሩበት አላማ ሲሆን የእውቀት አስፈላጊነቱ ለተግባር ነው፡፡ አላህ ፍጡራንን ሊያውቁት እና ሊግገዙት ፈጠረ፡፡ለመጀመሪያው ማስረጃ የሚከተለው…
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል አምስት
➭➭➭➭➭➭➭➭

▪️ሱፍያን ብን ዑየይናህ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"من فسد من علمائنا ففيه شبه من اليهود ، ومن فسد من عبادنا ففيه شبه من النصارى"
➧“ከዑለማዎቻችን የተበላሹት ከአይሁድ ጋር መመሳሰል አላቸው። ከዓቢዶቻችን(ያለጥልቅ እውቀት አላህን የሚገዙት) የተበላሹት ደግሞ ከክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል አላቸው፡፡”
ምክንያቱም አይሁዶች እውቀት አላቸው ግን አይሰሩበትም
፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡


مَثَلُ الَّذِينَ حُمِّلُوا التَّوْرَاةَ ثُمَّ لَمْ يَحْمِلُوهَا كَمَثَلِ الْحِمَارِ يَحْمِلُ أَسْفَارًا ۚ

“የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት (ያልሰሩባት) ሰዎች
ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ቢጤ ነው፡፡” አል ጁሙዓ፡5

➧“ለም የህሚሉሃ” የሚለው የቁርኣን ቃል በእርሷ ያልሰሩ ማለት ነው፡፡ሸምድደዋታል ፣እርሷ የጠቆመችውን መልእእክት ተገንዝበዋል ነገር ግን በእርሷ ሊሰሩ አልቻሉም፡፡

➭ከዑባዶቻችን - ጥልቅ እውቀት የሌላቸው - ደግሞ የተበላሹት ከክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል አላቸው፡፡ ክርስቲያኖች የአዲስ ፈሊጥና ፈጠራ ፣ አላህ ለባሮች ማስረጃ ያላወረደለትን የአምልኮ አይነት በአዲስ መልክ የማምጣት (የመስራት) ባለቤት
ናቸው፡፡


➲ሁለተኛው፡ - አንድ ባሪያ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት ይጠየቃል
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➧ረሡል صلى الله عليه وسلم ሰዎች የትንሳኤ ቀን ባገኙት እውቀት ምን እንደሰሩበት? ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡

▪️አቡ በርዘት ረድየላህ አንሁ ከረሡል صلى الله عليه وسلم ሰምቶ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡-

"لا تزول قدما عبد يوم القيامة حتى يسأل عن أربع – وذكر منها عليه الصالة
والسالم - : عن علمه ماذا عمل به"

“የትንሳኤ ቀን ከአራት ነገሮች ሳይጠየቅ የባሪያው እግር ካለበት ቦታ አይነቃነቅም - ከእነርሱ መካከል የአላህ መልእክተኛ የሚከተለውን አወሱ - ከእውቀቱ ምን
እንደሰራበት
፡፡” ቲርሚዚይ፡ 2417 አድ ዳሪሚይ፡ 554 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አት ቲርሚዚይ፡2417

▪️አቡ ደርዳእ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"إنما أخشى يوم القيامة أن يناديني ربي على رؤوس الخالئق ، فيقول : يا عويمر!
ماذا عملت فيما علمت؟

➽“እኔ የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጥረታቱ መካከል ጠርቶ 'አንተ ኡወይሚር ሆይ! በአወከው ምን ሰራህበት?' ብሎ እንዳይጠይቀኝ ነው የምፈራው
፡፡” ኢትሐፉል ኸይረቲ አል ሚህረቲ፡8/161

➧ይህ አስደንጋጭና አደገኛ የሆነ ቦታ ነው፡፡ ማንኛውም ባሪያ ከታነጸው እውቀት
“በአወቅከው ነገር ምን ሰራህበት?” ተብሎ የትንሳኤ ቀን መጠየቁ አይቀርም፡፡ምክንያቱም የማወቃችን ትልቁ አላማ ተግባር ነው፡፡ ለዚህ ነው ማንኛውም ሰው ከተማረው ትምህርት የሚጠየቀው፡፡
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w