💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
አትራፊ የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ተከታታይ አድስ ፅሁፍ


ክፍል አንድ

➛በዚህ ምድራዊ ዓለም በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርቶ ለመነገድና ትርፍ ለማትረፍ ሁሉም ደፋ ቀና ይላል ፤ ይሽቀዳደማል፡፡ ሁሉም በግዥና በሽያጭ ላይ ተሰማርቶ ይታያል፡፡ ነፍሱን ለሽያጭ አቅርቦ ሁሉም ማልዶ ከቤቱ ይወጣል፡፡

መልካም ስራ በመስራት ነፍሱን ከቅጣት ነጻ የሚያደርግ አለ ፤ በአንጻሩ የአላህን ትዕዛዝ በመንቀፍ ነፍሱን ለጥፋት የሚያጋልጥ አለ፡፡ በዚህ ኪታብ ውስጥ የምንነጋገረው አብዛኛው ሰው የዘነጋው ፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው ሊሽቀዳደምበት የሚገባ በዱንያ መልካም ህይዎትን በአኼራ ደግሞ ዘላለማዊ ህይዎትን የሚያወርስ የሆነውን “አትራፊ የንግድ ማዕከላት”ነው፡፡

በመልካም ስራ ትርፍ የሚገኝበት የአኼራ ንግድ የሶላት ንግድ ነው ፤ የጾም ንግድ
ነው ፤ የሶደቃ ንግድ ነው ፤ ባሪያው ወደጌታው የሚቃረብበት በአጠቃላይ የመልካም ስራ ንግድ ነው፡፡ በዱንያ ንግድ ውስጥ ትርፍና ኪሳራ እንዳለ ሁሉ በአኼራውም ንግድ ትርፍና ኪሳራ አለ፡፡

በአላህ አምኖ መልካምን ስራ የሰራ ታላቅ ምንዳ ይኖረዋል ፤ከኢማን እና ከመልካም ስራ የራቀ ግልጽ የሆነ ኪሳራ ይገጥመዋል

የመልካም ስራ ደረጃ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫

መልካም ስራ በቁርኣን ውስጥ ከሰማንያ በላይ የተወሳ ሲሆን ከኢማን ጋር ተጣምሮ ሰባ ሶስት ቦታዎች ላይ ተወስቷል፡፡ መልካም ስራ ከኢማን ጋር ተቆራኝቶ በመጣበት የቁርኣን አንቀጽ እንኳ በመልካም ስራ የሚገኘው ምንዳ በስፋት ተወስቷል፡፡

መልካም ስራ የአላህን ምህረት ፣ እዝነት እና ውዴታ እንደሚያስገኝ ፤ በመልካም ስራ ምድር ላይ የፍስሃና የደስታ ህይዎት እንደሚያስገኝ ይገልጻል፡፡ መልካም ስራ ሰርተው ያለፉ አማኞች በዚህ ምድራዊ ዓለም ያሳረፉትን መልካም አሻራ ያወሳል፡፡

➭ይህ ሁሉ በግልጽ የሚጠቁመው መልካም ስራ በዲናችን ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ እንዳለው ነው፡፡ ባሪያው ይህን ሲሰማ ለመልካም ስራ ፊቱን ያዞራል ፤ ፍላጎቱም ይጨምራል ፤ የመነቃቃት ስሜት ይታይበታል፡፡ ሙስሊም የመልካም ስራ ጥቅሞችን ፣ ፍሬዎችን ፣ ፋይዳዎችንና መልካም አሻራዎችን ከተገነዘበ ፍላጎቱ የላቀ ፣ በማሕበራዊ ህይዎቱ ውስጥ የመልካም ስራ ሚናው ከፍተኛ ይሆናል፡፡

ለመልካም ስራ ቸልተኛነት ካሳየህ ደካማ ትሆናለህ ፤ በማይጠቅሙ ነገሮች ትጠመዳለህ፡፡ አንድ ሰው ከመልካም ስራ ተዘናግቶ ህይዎቱን ካጠናቀቀ ጸጸት በማይጠቅምበት ቀን ተጸጻች ይሆናል፡



🖊ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
♦️ تلاوة من سورة الأحقاف
♦️ القارئ: #صالح_الطوالة
•••━══❁✿❁══━•••
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➻ክፍል ሀያ አምስት ➛➛➛➛➛➛➛➛ ➤ነብዩ صلى الله عليه وسلم በህይወት በነበሩ ጊዜ አይደለም የሁሉ ቀላቢ የራሳቸውም ቀላቢ አልነበሩም። እሳቸውንም ሆኑ ፍጡራኑን ሁሉ የሚቀልበው፣ ከእርሳቸው በፊትም ይሁን ከእርሳቸው በኋላ ያሉትን ፍጡሮቹን የሚቀልበው አላህ ብቻ ነው። የሁሉ ቀላቢ የሆነው አላህ እንዲህ ይላል፦ ۞ وَمَا مِن دَابَّةٍ…
መንዙማ
➬➬➬➬


ክፍል ሀያ ስድስት

አቡል ጀበል ካልነበር የተገኘ ነውና ጥንት አልነበረም። ፍጡር ነውና ይሄው ሞቷል። ዛሬም የለም። አላህ ከቀብር እስከሚቀሰቅሰው ድረስም ቂያማ ድረስ አይኖርም።


ታዲያ “ይኖራል ነግሶ አለምን ገዝቶ” ማለት ምን የሚሉት ቅጥፈት ነው?!! አይደልም አቡል ጀበል ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) እንኳን ሞተዋልኮ።

የልቅናው እማ አሁን ልፈስረው፣
የአላህ ሹም እኮ ነው ሸልሞ የፈጠረው፣ በፊት የሰራው ጉድ አሁን ልናገረው፣ የአደም ጭቃ ነው እጁን ያጠቆረው፣ ነበር ያሳመረ ሌሎች አቡል ጀበል ግርማ አለው ለመልኩ”


ኢንና ሊላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን!! እስቲ አሁን ይሄ ብልግና አይደለም ወይ?!!

‎كَبُرَتْ كَلِمَةً تَخْرُجُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ ۚ إِن يَقُولُونَ إِلَّا كَذِبًا

ከአፎቻቸው የምትወጣውን ቃል ምን አከበዳት! ውሸትን እንጂ አይናገሩም፡፡
(ሱረቱ አል ከህፍ፡-5) አላህ ግን አደምን (ዐለይሂ-ስሰላም) በሁለት እጆቹ እንደፈጠረ እንዲህ ሲል ይነግረናል።

قَالَ يَا إِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَيَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ الْعَالِينَ

➩(አላህም) «ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ (በኃይሌ) ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ? (አሁን) ኮራህን? ወይስ (ፊቱኑ) ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡
(ምዕራፍ ሱረቱ ሷድ-75)

አቡል ጀበል አይደለም አደም ሲፈጠር ሊኖር ቀርቶ የራሱንም አፈጣጠር አላየም። ለዚህም ማስረጃችን የሚከተለው የጌታችን አላህ ቃል ነው

۞ مَّا أَشْهَدتُّهُمْ خَلْقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَا خَلْقَ أَنفُسِهِمْ وَمَا كُنتُ مُتَّخِذَ الْمُضِلِّينَ عَضُدًا

የሰማያትንና የምድርን አፈጣጠር አላሳየኋቸውም፡፡ የነፍሶቻቸውንም አፈጣጠር (እንደዚሁ)፡፡ አሳሳቾችንም ረዳቶች አድርጌ የምይዝ አይደለሁም፡፡[አልከህፍ፡ 51]

ሌላው ደግሞ እንዲህ ይላል፡-
“ይመነጥቁታል ያወጡታል ከጭንቅ” እውን ከጭንቅ የሚያወጡት እነሱ ናቸው?

أَمَّن يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَاءَ الْأَرْضِ ۗ أَإِلَـٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ

➳ወይስ ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ጥቂትን እንጂ አትገሰፁም
?” [አንነምል፡ 62]

የቦረናው ጌታ ነው እንደ ጡላጊ፣
ትንሹን ጠቃሚ ትልቅ አሳዳጊ”
ትንሹን ጠቃሚ ትልቁን አሳዳጊ አላህ ብቻ ነው
። አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-

قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَاءُ ۖ بِيَدِكَ الْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

➧(ሙሐመድ ሆይ!) በል፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ (በችሎታህ) ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡»[አሊ ዒምራን፡ 26]

ይሄ ስንኝ በግልፅ የአላህን መብት አሳልፎ ለቦረናው ሸይኽ እየሰጠ ነው።
ጠቃሚ ጎጂ፣ ሰጪ ነሺ አላህ ብቻ ነው።




ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➛ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
ምርጥ የማለዳ የቲላዋ ግብዧ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ቁረአን ማንበብና እንድሁም በትኩረት ማዳመጥ ትልቅ ኢባዳ ነው!

♦️ تلاوة من سورة الحشر
♦️ القارئ: #مختار_الحاج
•••━══❁✿❁══━•••
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
በኢማን ላይ መጠራጠር
እና ወስዋስ (ጉትጎታ ) የተለያዩ ነገሮች ናቸው
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

ክፍል ②⑧


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➭የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሶስት ➲የዓሊምን ደረጃና ቦታ በተመለከተ “ሙስነድ” እና ሌሎች የሐዲስ መዛግብት ላይ የሰፈሩ ሐዲሶች አብራርተውት ይገኛሉ፡፡ረሡል صلى الله عليه وسلم አጠቃላይና ታላቅ በሆነው ሐዲሳቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡- ➧“እውቀትን ፍለጋ የተጓዘ ሰው ፤ ወደጀነት የሚወስደውን መንገድ ያመቻችለታል፡፡ የሚሰሩትን ስራ በመውደዳቸው…
የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ክፍል አራት

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين"

በእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን ያስገነዝበዋል” ቡኻሪ፡ 71ሙስሊም፡1037

➧“ኸይረን” የሚለው ቃል በነኪራ (ሁሉን በሚያካትት ቃል) መምጣቱ ክብደትን እና
ልቅናን እንዲሁም በአላህ ዲን የታነጸ ሰው የሚለቅመው ጠቃሚ ፍሬ ከፍተኛ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ዕውቀትን በመፈለግ ላይ እንቅስቃሴ ከጀመረ አላህ መልካሙን እንደሻለት የሚያመክት ነው ማለት ነው፡፡

ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-“በዚህ ሐዲስ የተፈለገው ተግባርን ያጣመረ የዲን እውቀት ነው፡፡ ከተግባር ነጻ የሆነ
እውቀትን የፈለገ ሰው አላህ መልካም ሽቶለታል ማለትን አያመላክትም፡፡”

➭ይህ ማለት ፣ ዲንን ሊገነዘብና ወደተግባር ሊቀይረው ይገባል ማለት ነው፡፡ የመማሩ ዋናው አላማ ከራሱ ላይ ማህይምነትን ማስወገድ ፣ በእውቀት ላይ ተንተርሶ አምልኮን ለአላህ ብቻ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ አይነት ባህሪ ላይ ከሆነ መልካምን ለማግኘት ተገቢ ይሆናል ማለት ነው፡፡


ለተግባር እውቀት በጣም ተፈላጊ ነው፡፡ እውቀት ፣ አምልኮን ፍጹም ለአላህ ብቻ ለማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህ ነው ከተግባር በፊት እውቀት ተቀዳሚ የሆነው፡፡ ተግባር፣ አምልኮ ፣ ወደአላህ መቃረብ ከአላህ ኪታብና ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱና በመነጨ ጠቃሚ እውቀት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ሚፍታህ ዳሪ አስ ሳዓዳ፡1/65

በዚህ ታላቅ ርዕስ ዙሪያ ጥቅል መረጃዎችን እና ታላላቅ የሰለፎችን ንግግር ያካተተኢቅቲዷኡል ዒልም አልዓመልየተባለ ምርጥ መጽሐፍ ኸጢብ አል'በግዳድይ -ረሂመሁሏህ - ጽፈዋል፡፡

➲“ኢቅቲዷኡል ኢልም አልዓመል” የተባለው ኪታብ የእውቀት አላማው ተግባር እንደሆነ ፣ በእውቀትና በማስረጃ ላይ በመንተራስ አምልኮን ፍጹም ለአላህ ብቻ ማረጋገጥ እንደሚገባ ትኩረት ይሰጣል፡አንድ ባሪያ እውቀት ኖሮት ስራ ከሌለው ፣እንዲሁም ያለእውቀት ተግባር ብቻ ከሆነም አምልኮ በትክክል ተረጋግጧል ማለት አይቻልም፡፡

የአላህ አምልኮ በሁለት ነገሮች ካልሆነ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ በጠቃሚ እውቀት እና በመልካም ተግባር፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَىٰ وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ

እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልእክተኛው (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡” አት ተውባህ፡33

➭“ሁዳ” ፡ ማለት ጠቃሚ እውቀት ማለት ነው፡፡ ዲኑል ሐቅማለት ደግሞ ወደአላህ የሚያቃርብ መልካም ተግባር ማለት ነው፡፡ዲኑል ሐቅ” ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲሁም አጠቃላይ ነብያቶች የተላኩበት ነው፡፡



እንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

ክፍል ②⑨


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➳መንዙማ ➬➬➬➬ ➧ክፍል ሀያ ስድስት አቡል ጀበል ካልነበር የተገኘ ነውና ጥንት አልነበረም። ፍጡር ነውና ይሄው ሞቷል። ዛሬም የለም። አላህ ከቀብር እስከሚቀሰቅሰው ድረስም ቂያማ ድረስ አይኖርም። ➧ታዲያ “ይኖራል ነግሶ አለምን ገዝቶ” ማለት ምን የሚሉት ቅጥፈት ነው?!! አይደልም አቡል ጀበል ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) እንኳን ሞተዋልኮ። የልቅናው እማ አሁን ልፈስረው፣…
መንዙማ
➬➬➬➬➬

ክፍል ሀያ ሰባት

➲ይሄ ስንኝ በግልፅ የአላህን መብት አሳልፎ ለቦረናው ሸይኽ እየሰጠ ነው።
ጠቃሚ ጎጂ፣ ሰጪ ነሺ አላህ ብቻ ነው።

ይሁንቦት በነሰይድ ዳና፣ መደሻችን (መደሰቻችን) ይሁን ያለንበት ዘመን፣ ቆሞ ቀር ሆነናል ባለንበት ዘመን፣እኩሉን ሞሽሩን እንዳንቀር ተርበን” ከአላህ ተዓምር ውስጥ ወንድ እና ሴትን ማጋባቱ በመካከላቸው ውዴታና መተዛዘንን ማድረጉ ነው።

➧ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) እንኳን ትዳር የሰጣቸው አላህ ነው። ዛሬ ግን ይሄው እዚህ ላይ እንደምናየው “እኩሉን ሞሽሩን” ብለው ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) ዳሩን ሲል፤ ከአላህ ውጭ ይጠይቃሉ። አላህ ብቻ ሊያደርገው በሚችለው ጉዳይ ፍጡራንን መጥራት ሺርክ እና ኩፍር ነው

➲የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) “ከአላህ ውጭ ያለን እየጠራ የሞተ እሳት ገባ” ብለዋል። አላህ ከፍጡሮቹ ስልጣኑን አሳልፎ የሰጠው አለን?

የአላህ ጌትነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከላይ አሳልፈናል። አገራችን ላይ ካሉ መንዙማዎች ውስጥ ለምሳሌነት የሚከተሉት አላህ ስልጣኑን ለፍጡራኑ አሳልፎ እንደሰጠ ይዋሻሉ። ጥያቄው አላህ ምን ሆኖ ነው ስልጣኑን ለፍጡራኑ አሳልፎ የሚሰጠው? ጌታችን አላህ ማለት ህያው፣ የማይሞት፣ በራሱ የተብቃቃ ፍጡራኑን የሚያብቃቃ፣ አሸናፊ፣ የማይተኛ፣ የማያንቀላፋ፣ ሿሚ፣ ሻሪ፣ የፍጡራኑ ሁሉ መጠጊያ ነው።

አላህ ከእርሱ ውጭ የሚመለኩት በሰማይም በምድርም ምንም እንደማይችሉ፣ ሽርክናም እንደሌላቸው፣ አጋዦቹም እንዳልሆኑ፣ እርሱ ከፈቀደ በኋላ ቢሆን እንጂ እንደማያማልዱም እንዲህ ሲል ይነግረናል፡-

قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِ اللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِن شِرْكٍ وَمَا لَهُ مِنْهُم مِّن ظَهِيرٍ

«እነዚያን ከአላህ ሌላ (አማልክት ብላችሁ) የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም፤» በላቸው፡፡[ሰበእ፡ 22]


وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ ۚ حَتَّىٰ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ ۖ قَالُوا الْحَقَّ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ


ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፡፡ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጸም ጊዜ (ተማላጆቹ) «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ፡፡ (አማላጆቹ) «እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው» ይላሉ፡፡ [ሰበእ፡ 23]

የሚከተሉት ስንኞች ላይ አላህ ስልጣኑን ለፍጡራኑ አሳልፎ እንደሰጠ ተደርጎ ይቀጠፍበታል። አላህ ላይ መዋሸት ደግሞ ከባድ ቅጥፈት ነው።
እስኪ አላህ ይህንን እንዳለ ምን አሳወቀው

أَطَّلَعَ الْغَيْبَ أَمِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا

ሩቁን ምስጢር ዐወቀን ወይስ አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን ያዘ [
መርየም፡78]

ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➛አንብብ ያነበበ ተጠቀመ!

➧ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
وَعِبَادُ الرَّحْمَٰنِ الَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى الْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ الْجَاهِلُونَ قَالُوا سَلَامًا

የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡
وَالَّذِينَ يَبِيتُونَ لِرَبِّهِمْ سُجَّدًا وَقِيَامًا

እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው፡፡

وَالَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا اصْرِفْ عَنَّا عَذَابَ جَهَنَّمَ ۖ إِنَّ عَذَابَهَا كَانَ غَرَامًا

እነዚያም «ጌታችን ሆይ! የገሀነምን ቅጣት ከእኛ ላይ መልስልን ቅጣቷ የማይለቅ ነውና» የሚሉት ናቸው፡፡


إِنَّهَا سَاءَتْ مُسْتَقَرًّا وَمُقَامًا

እርሷ መርጊያና መቀመጫ በመኾን ከፋች! (ይላሉ)፡፡

وَالَّذِينَ إِذَا أَنفَقُوا لَمْ يُسْرِفُوا وَلَمْ يَقْتُرُوا وَكَانَ بَيْنَ ذَٰلِكَ قَوَامًا

እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑ የማይቆጥቡትም ናቸው፡፡ በዚህም መካከል (ልግስናቸው) ትክክለኛ የኾነ ነው፡፡

وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል፡፡
➛ከቁረእን ጋር እንኑር!!
አቡ ሁረይራ አለቀሰ !

እንዲህ ሲባልም ተጠየቀ

يا أبا هُريرة.. أتبكي على الدُّنيا !
አቡ ሁረይራ ሆይ በዱንያ ላይ ታለቅሳልህ?

- لا والله، دُنياكم هذهِ لا تُبكيني ..

አይደለም በአላህ ይሁንብኝ ይህች ዱንያችሁ አታስለቅሰኝም

إنَّما أبكي مِنْ ثِقَلِ الحِمْلِ ، وسوء الرفيق ، وَمِنْ قلَّةِ الزَّاد ، وُبعدِ الطَّريق..


እኔ ማለቅሰው ከሸክሙ ክብደት ከመጥፎ ጓደኛ ከምግብ ማነስ ከመንገዱ ርዝመት ነው ።

أبكي خوفًا مِن أسقُط يوم القيامة مِن على الصراط ولا أدخُل الجنَّة..

ኣለቅሳለው የቂያም ቀን ከሲራጥ ከወደቅኩኝ ጀነትን አልገባመ ብዬ

وَدِدتُ أنِّي لَم أُخلق.

ባልተፈጠርኩ ብዬ ተመኘሁኝ


📚 ሲየር አእላም አኑበላእ
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

ክፍል ③∅


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧አትራፊ የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ተከታታይ አድስ ፅሁፍ ➧ክፍል አንድ ➛በዚህ ምድራዊ ዓለም በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርቶ ለመነገድና ትርፍ ለማትረፍ ሁሉም ደፋ ቀና ይላል ፤ ይሽቀዳደማል፡፡ ሁሉም በግዥና በሽያጭ ላይ ተሰማርቶ ይታያል፡፡ ነፍሱን ለሽያጭ አቅርቦ ሁሉም ማልዶ ከቤቱ ይወጣል፡፡ ➭ መልካም ስራ በመስራት ነፍሱን ከቅጣት ነጻ የሚያደርግ አለ ፤…
አትራፊ የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ክፍል ሁለት

ኢማንና መልካም ስራ በቁርኣን ውስጥ ተቆራኝተው መምጣታቸው ሁለቱ የጠበቀ ቁርኝት እንዳላቸው ይጠቁማል፡፡ የቁርዓን አንቀጾችን በደንብ ከተከታተልን አንዳንድ ቦታ ኢማን ለመልካም ስራ መስፈርት ሆኖ ይመጣል፡፡ አንዳንድ ቦታ ደግሞ መልካም ስራ ለኢማን መስፈርት ሆኖ ይመጣል፡፡

ኢማን ለመልካም ስራ መስፈርት የሆኑባቸው የቁርኣን አንቀጾች የሚከተሉት ናቸው፡
فَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَا كُفْرَانَ لِسَعْيِهِ وَإِنَّا لَهُ كَاتِبُونَ
“እርሱ ያመነ ሆኖ በበጎ ስራዎች ማንኛውንም የሚሰራም ሰው ፤ ምንዳውን አይነፈግም፡፡
አል አንቢያእ፡94


مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

“ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ይሰሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን
፡፡” አን ነህል፡97


وَمَنْ أَرَادَ الْآخِرَةَ وَسَعَىٰ لَهَا سَعْيَهَا وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَٰئِكَ كَانَ سَعْيُهُم مَّشْكُورًا

“መጨረሻይቱንም ዓለም የፈለገ ሰው እርሱ አማኝ ሆኖ ለርሷ (ተገቢ) ስራዋን የሰራም ሰው እነዚህ ስራቸው የተመሰገነ ይሆናል፡፡”
አል ኢስራእ፡19

መልካም ስራ ለኢማን መስፈርት የሆኑባቸው የቁርኣን አንቀጾች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡
وَمَن يَأْتِهِ مُؤْمِنًا قَدْ عَمِلَ الصَّالِحَاتِ فَأُولَٰئِكَ لَهُمُ الدَّرَجَاتُ الْعُلَىٰ
“በጎ ስራዎችን በእርግጥ የሰራ ምእመን ሆኖ የመጣውም ሰው እነዚያ ለእነሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አሏቸው
፡፡” ጧሃ፡75

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ

“እነዚያ ያመኑ፡፡ መልካም ስራዎችንም የሰሩ፡፡” አል በቀራህ፡277

إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ

“ግን እነዚያ ያመኑት መልካሞችንም የሰሩት” አት ቲን፡6

إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ
“እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት”
አል ዓስር፡3

በልብ ውስጥ ትክክለኛ እና ጤናማ የሆነ እምነት ሳይኖር መልካም ስራ ብቻውን ምንም ጥቅም አይሰጥም።አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል
وَمَن يَكْفُرْ بِالْإِيمَانِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ

“ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ስራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎች ነው፡፡”
አል ማኢዳህ፡5

አንድ ሰው ኢማን ኖሮት መልካም ስራ ከሌለው ከኢስላም ባለቤቶች ሊሆን አይችልም።ምክንያቱም የኢስላምና የኢማን ባለቤቶች አምነው መልካምን ስራ የሰሩት ብቻ ናቸው፡፡ ሁለቱ - ኢማንና መልካም ስራ- ተያያዥ ነገሮች ናቸው፡፡

ከልቡ በትክክል ካረጋገጠና ካመነ መልካም ስራ በአካሉ ላይ ይፋ ይሆናል። የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"ألا وإن في الجسد مضغة إذا صلحت صلح الجسد كله، وإذا فسدت فسد الجسد كله، ألا وهي القلب"

➲“ንቁ! በአካል ውስጥ አንዲት ቁራጭ ስጋ ትገኛለች፡፡ እርሷ ከተስተካከለች አካል ሁሉ ይስተካከላል፡፡ እርሷ ከተበላሸች አካል በሙሉ ይበላሻል፡፡ ንቁ! እርሷ ልብ ነች፡፡”
ቡኻሪ፡52 ሙስሊም፡1599



ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w