💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
➲ቅድሚያ ለተውሂድ ቦታ እንስጥ!
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧አላህ ከእውቀቶች ሁሉ በቅድሚያ እንድንማረው ቦታ እንድንሰጠው ያዘዘን እርሱን በብቸኝነት ማምለክ ተውሂድን ነው!

«فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ»

«እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን፡፡»
[ሙሀመድ :19]


«إِنَّ اللّهَ لاَ يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَلِكَ لِمَن يَشَاءُ وَمَن يُشْرِكْ بِاللّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلاَلاً بَعِيدا»ً

«አላህ በርሱ የማጋራትን(ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡»
[ኒሳእ-116
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
⇠الحياء زينة المرأة وجمالها

➛ሀያዕ የሴት ልጅ ውበቷ ነው።
1⃣✍ አህለሱና ወልጀማአዎች የአላህ ስምና መገለጫ በማፅደቅ በኩል መልእክተኞች ከተላኩበት ሀቅ የማይዘነበሉትና የማያፈነግጡት ለምንድ ነው⁉️
Anonymous Quiz
4%
እንዲከተሉት የታዘዙበት ስለሆነ
5%
ከጥመት መዳኛ ብቸኛው መንገድ
6%
የተስተካከለና ቀጥ ያለ መንገድ ስለሆነ
86%
ሁሉም
•°•°• ሙስሊሟ እህቴ ሆይ! በጭቁን ማህበረሰብ ውስጥ ያደገ ጭቁን ሴት አትሁኝ •°•

" ተማሪ አንብቢ ደካማ ሳይሆን ጠንካራ ሁኝ በማይረባ ነገር ቢዚ
በሚያደርጉሽ ነገሮች ራስሽን ውጥረት ውስጥ አታስገቢ"


°•° በጠንካራ ማንነት ውስጥ እጅግ ውብ የሆነ ውበትን ትጎናፀፊያለሽ ከዚያ የሚሊዮኖች ምርጫ ትሆኛለሽ°•°

•°• ዲነሽ ከመማር ከማንበብ ከመፃፍ በጭራሽ አይከለክልሽም ግን ቁጥብ እና በሃያዕ የታጀብሽ እድትሆኚ ያዝሻል ደግሞ እዳዘነጊ "ሃያዕ" ራሱን የቻለ የተፈጥሮ ውብ ውበት መሆኑን°•°

•°• ጠንካራ ሴቶች የብዙ ለውጥ ባለቤቶች ናቸው በመሆኑም እኔም አንችም ጠንካራ መሆን ይጠበቅብናል•°•

Bint Ahmed aselefy
➲ልብ➝ በ6 ነገሮች ትበላሻለች

① ኢልም (እውቀት) ኖሮት አለመተግበር

② ስራን ያለ ኢኽላስ መስራት

③ የአሏህን ቀደር ( ዉሳኔ ) አለመውደድ

④ ተውበትን በመከጀል ሀጢያትን መዳፈር

⑤ የአሏህን ሪዝቅ (ሲሳይ) እየበሉ አለማመስገን

⑥ የሞተን ሠው እየቀበሩ አለማስተንተን

አሏህ ይጠብቀን!!!


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ②③➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➳መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➧ክፍል ሀያ ➢ሰለዋት ማውረድ ኢባዳ ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧እሳቸው ላይ ከምናወርደው የሰለዋት አይነቶች ውስጥ በላጩ እሳቸው ለሶሐባዎቻቸው በላጭ ነው ሲሉ ያስተማሩት ነው። ይህም የተለያዩ ቅርፆች ያሉት ሲሆን የሚከተለው አንዱ ነው፡- "اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على آل إبراهيم إنك حميد مجيد، وبارك على…
➣መንዙማ
➬➬➬➬➬

➩ክፍል ሀያ አንድ
➻➻➻➻➻➻➻

➲መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው
(ተቀባይነት አይኖረውም)” ሲሉ ካስጠነቀቁት ውስጥ እንወድቃለን
።


➧ሶለዋትን በተመለከተም ተመሳሳይ ቀመር ልንከተል ይገባል። እውነት አላህ በስራችን ምንዳን እንዲሰጠን እና ከቁጣው መራቅን ከፈለግን ሸሪዐው ባዘዘው መልኩ ልንፈፅም ይገባል። በሃገራችን የሚታየው ግን በብዙ መልኩ ከዚህ አደብ ጋር የሚፃረር ነው።

በመልክተኛው እና ቤተሰባቸው ላይ አላህ እዝነቱን፣ ሰላሙን፣ በረከቱን እንዲያወርድ በውዝዋዜና በጭፈራ አጅቦ ሲለመን ማየት ለአስተዋዮች ያሸማቅቃል።


➩ይባስ ብሎም ይህ ታላቅ አምልኮ ከሺርክ እየተቀላቀለ መፈፀሙ ነው። አንዳንዱ ቦታ ጭራሽ ወንድ እና ሴት የሚቀላቀሉበት ሁኔታም አለ። ይህ ተግባር የአላህን ቁጣ የሚያከናንብ፣ ምንዳን ሳይሆን ኪሳራ የሚያስከትል ጥፋት ነው።


➲አምልኮ እና ጭፈራ የተለያዩ ናቸው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ዛሬ ዛሬ በአምልኮታዊ ስንኞች እያጨበጨቡ የሚጨፍሩ መመልከት የተለመደ ሆኗል። አምልኮትን ለጭፈራና ዛዛታ ማዋል ሰቅጣጭ ጥፋት ነው። እስኪ አስቡት አንድ ሰው ቁርኣንን ለጭፈራ ሲጠቀምበት። ታዲያ ትልቁ ጥፋት እነዚህን በመንዙማም ሆነ በነሺዳ ስም የሚፈፀሙ ውዝዋዜዎች እንደ መቃረቢያ መቁጠራቸው ነው።


➩በዛዛታና በዘፈን የሚጨፍር ሰው “ተው” ተብሎ ሲመከር ወንጀል መሆኑን አውቆ “አላህ እንዲያላቅቀኝ ዱዓ አድርጉልኝ” ይላል እንጂ አጅር አገኝበታለሁ ብሎ አይሞግትም። በተገላቢጦሹ በሶለዋት ስም በየሰርጉ ላይ፣ በየሐድራው፣ በየመውሊዱ የሚሸበሸቡ ዜማዎች ግን እንደ መቃረቢያ ስለሚታሰቡ የሚጨፍሩት ሰዎች “ተዉ አላህን ፍሩ ሶለዋት ኢባዳ ነው፣ ኢባዳ (አምልኮ ደግሞ) በጭፈራ አይከናወንም” ሲባሉ አይደለም ዱዓ አድርግልኝ ሊሉ ቀርቶ ሸይጧን የሚሰሩትን ጥፋት አሳምሮላቸው


➧በሚቃወማቸው ሰው ላይ “የነብዩ ሙሃባ የሌላቸው”፣ “ወሃቢይ”፣... ወዘተ እያሉ ስም ይለጥፋሉ።ሰለፎቻችን “ቢድዓ ኢብሊስ ዘንድ ከወንጀል በላይ ይበልጥ ተወዳጅ ናት” ማለታቸው ምንኛ እውነት ነው?! የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እስኪ ግን እናስተውል!


➳ቁርኣን መቅራት፣ ዱዓ ማድረግ አምልኮ ናቸው ወይንስ አይደሉም? መልሳችንም “አዎ” እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ታድያ የአላህን ቃል ቁርኣን ስንቀራ አንድም ቀን ጨፍረን እናውቃለን?
ዱዓ ስናደርግስ ጨፍረን እናውቃለን? መልሳችን “ኧረ በፍፁም” ይሆናል።


➮ታድያ ለምን ይሆን ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ላይ ሰለዋት ስናወርድ የምንጨፍረው?
ሰለዋትስ አምልኮ (ዒባዳ) አይደለምን? መልሳችን እንዲያውም ከታላላቅ ዒባዳዎች መሃል ነው ይሆናል።



➲ስለዚህ የአላህ ባርያዎች ሆይ! የእውነት አላህን እንፍራ!! ሸይጧን እንዲጫወትብን እድል አንስጠው።
ሶሐባዎች ከማንም በላይ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ወዳጆች ናቸው። አላህ እና መልክተኛው ያላዘዙትን፣ ሶሐባዎች የማያውቁትን በሶለዋት ስም በሸሪዐ ያልተደነገጉ ሺርክ በተቀላቀለባቸው ስንኞች ማዜም፣ ማጨብጨብ፤ ማፏጨት እና መጨፈር ነገ ከአላህ ፊት እንዳንጠየቅበት በጊዜ ልንርቅ ይገባል።


➳ብልጥ ማለት በነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ሱና የተብቃቃ ነው። የመካ አጋሪያን ካዕባ ዙርያ ያፏጩና ያጨበጭቡ ነበር። ይህም አስወግዟቸዋል።
◉

◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➛ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

✅አድስ ተከታታይ ፅሁፍ
〰〰〰〰〰〰〰〰

➛ክፍል አንድ

➧በተስተካከለው ዲናችን ውስጥ እውቀት ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠው መሆኑ ለማንም የሚሰወር አይደለም፡፡ እውቀት የመጀመሪያው መሰረት ነው፡፡ በእውቀት ካልሆነ በቀር የሰው ልጅ ለእርሷ ሲባል የተፈጠረባት ፣ እርሷን ለማረጋገጥ ሲባል የተገኘባት አምልኮ ሊረጋገጥ ፣ እንዲሁም በአጠቃላይ ሸሪዓ በፍጹም የተስተካከለ ሊሆን አይችልም፡፡

➲እውቀት ፍጹም ሊቀር የማይገባ ፣ ሁሉም ነገር የሚጀመርበት ተቀዳሚው መሰረት ነው።አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡


فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ۗ

“እንሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም እወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምህረትን ለምን፡፡”
ሙሐመድ፡19

➳አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - በእውቀት ጀመረ፡፡ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ዘወትር ከሱብሂ ሶላት በኋላ ከሚያደርጉት ዱዓ መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፡፡

➧ኡሙ'ሰለማ ረድየላህ አንሃ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፋለች፡-“ረሡል صلى الله عليه وسلم ሱብሂ ሶላት ሰግደው ካሰላመቱ በኋላ የሚከተለውን ዱዓ ያደርጉ ነበር

"اللهم إني أسألك علما نافعا، ورزقا طيبا، وعمال متقبال"

ትርጉሙ፡ “አላህ ሆይ! ጠቃሚ የሆነ እውቀት ፣ መልካም የሆነ ሲሳይ ፣ተቀባይነት ያለውን ስራ እለምንሀለሁ፡፡” አህመድ፡ ኢብኑ ማጀህ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ ኢብኑ ማጀህ፡

➛ረሡል صلى الله عليه وسلم በየቀኑ ከሚያደርጉት ዱዓ ሁሉ ተቀዳሚ ያደረጉት እነዚህን ሶስት ዱዓዎች ነው፡፡ መልካም ሲሳይ ፣ ተቀባይነት ያለው ተግባር እና ጠቃሚ የሆነ እውቀት ናቸው፡፡

➧አንድ ሰው በጠቃሚ እውቀት ካልሆነ በቀር ከሲሳይ መልካሙን እና ቆሻሻውን
፣ ከስራም መልካሙንና መጥፎውን በፍጹም መለየት አይችልም፡፡
◉

◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➛አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ S H A R E
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➣መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➩ክፍል ሀያ አንድ ➻➻➻➻➻➻➻ ➲መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው (ተቀባይነት አይኖረውም)” ሲሉ ካስጠነቀቁት ውስጥ እንወድቃለን። ➧ሶለዋትን በተመለከተም ተመሳሳይ ቀመር ልንከተል ይገባል። እውነት አላህ በስራችን ምንዳን እንዲሰጠን እና ከቁጣው መራቅን ከፈለግን ሸሪዐው ባዘዘው መልኩ…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሀያ ሁለት

➭አምልኮ እና ጭፈራ የተለያዩ ናቸው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫


➧ሶሐባዎች ከማንም በላይ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ወዳጆች ናቸው። አላህ እና መልክተኛው ያላዘዙትን፣ ሶሐባዎች የማያውቁትን በሶለዋት ስም በሸሪዐ ያልተደነገጉ ሺርክ በተቀላቀለባቸው ስንኞች ማዜም፣ ማጨብጨብ፤ ማፏጨት እና መጨፈር ነገ ከአላህ ፊት እንዳንጠየቅበት በጊዜ ልንርቅ ይገባል። ብልጥ ማለት በነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ሱና የተብቃቃ
ነው። የመካ አጋሪያን ካዕባ ዙርያ ያፏጩና ያጨበጭቡ ነበር። ይህም አስወግዟቸዋል።


ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል፡


وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمْ عِندَ الْبَيْتِ إِلَّا مُكَاءً وَتَصْدِيَةً ۚ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

በቤቱ ዘንድም (በካዕባ) ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ (ይባላሉ)፡፡
አልአንፋል 35

➧ዛሬ ሰይጣን መጥፎ ስራቸውን አሳምሮ ያሳያቸው ሰዎች መስጂድ ውስጥ
ሲያጨበጭቡ የማንን ፈለግ ነው እየተከተሉ ያሉት?! አስተዋይ ልብ ይበል!!
እንዲህ አይነቱ አካሄድ ሃይማኖትን መዝናኛና መቀለጃ አድርጎ መያዝ ነው።

አላህ ውድ መልክተኛውን (صلى الله عليه وسلم (እነዚያ ሃይማኖታቸውን ቀልድ እና ጨዋታ አድርገው ከያዙ ሰዎች እንዲርቁ እንዲህ ሲል ያዛቸዋል፡

وَذَرِ الَّذِينَ اتَّخَذُوا دِينَهُمْ لَعِبًا وَلَهْوًا وَغَرَّتْهُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا ۚ
“እነዚያንም ሃይማኖታቸውን ጨዋታና ላግጣ አድርገው የያዙትን ቅርቢቱም ሕይወት ያታለለቻቸውን ተዋቸው።”
[አልአንዓም፡ 70]

➳ወገኖቼ! ለምንሰራቸው ስራዎች ጥሩ ኒያ መሰነቃችን ብቻውን እንዳይሸውደን።
አፈፃፀማችንም ከነብዩ (صلى الله عليه وسلم (አፈፃፀም ጋር የሚገጥም መሆኑን ከመፈተሽ እንዳንዘናጋ።አላህ እንዲህ ይላል

قُلْ هَلْ نُنَبِّئُكُم بِالْأَخْسَرِينَ أَعْمَالًا

«በሥራዎች በጣም ከሳሪዎቹን እንንገራችሁን» በላቸው፡
፡ አል ከህፍ 103


الَّذِينَ ضَلَّ سَعْيُهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَهُمْ يَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ يُحْسِنُونَ صُنْعًا

እነዚያ እነሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ሕይወት ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው
፡፡አልከህፍ 104

➲ስለዚህ ሃቅ ለእኛ የመሰለን ሳይሆን ሸሪዓ ያዘዘበት፤ መለኮታዊ ራዕይ
የወረደበት ነው። አላህን እንፍራ፣ በተለይ አሁን በየሰርግ ቤቱ በሶለዋት የሚጨፍሩ ሰዎች አላህን ፍሩ፣ ይህን መጥፎ መንገድ በማስተዋወቃችሁ፣ ሱናን በማጠልሸታችሁ ወደ አላህ በተውበት ካልተመለሳችሁ አደጋው ከባድ ነው።


ሰርግ ቤት፣ መውሊድ፣ ሀድራ የሚባለው ላይ የሚሰራው ስራ ሸር ለመሆኑ ምንም እነሱ ጥሩ አስበን ነው (የነቢ ውዴታ ይዞን ነው) ቢሉም የመልክተኛውን ፈለግ መቃረኑ ብቻ ጥመት ለመሆኑ በቂ ማሳያ ነው።

➛አምልኮ ሊፈፀም የሚገባው አላህ እና መልክተኛው ባዘዙት መልኩ ሶሐባዎች
በተረዱት አረዳድ ነው። መልካሙን ነገር ሁሉ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (አሳይተዋል። ከመጥፎ ነገሮች ሁሉ ከልክለዋል። ሶሓባዎች የተብቃቁበት ሱና ለእኛም ይብቃን።

◉
◉
◉
◉
✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➛ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን! ትጠቀማለህ

➳ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ②④➰
〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሀያ ሁለት ➭አምልኮ እና ጭፈራ የተለያዩ ናቸው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ሶሐባዎች ከማንም በላይ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ወዳጆች ናቸው። አላህ እና መልክተኛው ያላዘዙትን፣ ሶሐባዎች የማያውቁትን በሶለዋት ስም በሸሪዐ ያልተደነገጉ ሺርክ በተቀላቀለባቸው ስንኞች ማዜም፣ ማጨብጨብ፤ ማፏጨት እና መጨፈር ነገ ከአላህ ፊት እንዳንጠየቅበት…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➛ክፍል ሀያ ሶስት

➧በነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ላይ ሰለዋት መቼ እና እንዴት እናውርድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➫➫➫

➳ሰለዋት ማውረድ ማለት ምን እንደሆነ ከላይ አይተናል። አላህ በነብዩ ሙሐመድ(صلى الله عليه وسلم (ላይ የእዝነት ሰላምታውን እንዲያወርድባቸው እየጠየቅነው ነው።

➧ሱናውን ገጥመን በነብዩ صلى الله عليه وسلم ላይ ሰለዋት በምን አይነት ሁኔታዎች ላይ ነው የምናወርድባቸው? መስጊድ ስንገባ፣ ከመስጊድ ስንወጣ፣ ከአዛን በኋላ፣ ተሸሁድ (አተሒያቱ ላይ)፣ ዱዐ መክፈቻ፣ ዲን ትምህርት እየተማርን እና እያስተማርን ሐዲሳቸውን ስናነብ፣ ዱዐ ሲጠናቀቅ፣ ጁምዐ ቀን በበለጠ ሁኔታ፣ የዳዕዋ መክፈቻ ላይ የሳቸውን ስም እናነሳለን፣ ጁመዐ ኹጥባ ላይ፣ የሞተ ሰው ላይ ስንሰግድ፣ ወዘተ።

➲ ሀሙስ ማታ!
➫➫➫➫➫➫

➧በሃገራችን አንዳንድ አካባቢዎች ብዙ ቤቶች ላይ ሀሙስ ማታ “የአምዋት ቡና
(ለሞቱ ሰዎች የሚፈላ ቡና)” በማለት ጫት ተዘርግቶ፣ ቡና ተፈልቶ፣ እጣን እያጫጫሱ የሚያሳልፉ ሰዎች አሉ። ሌሎች ደግሞ በመስጊድ ደረጃ ሀሙስ ማታ ከመግሪብ እስከ ኢሻ በጀመኣ ሰለዋት እናወርዳለን የሚሉም አሉ
።

➧ ከዚህም አልፈው ሌሊቱን በቂምሃ
(በጫት መቃም) የሚያሳልፉት ብዙ ናቸው። በጣም የሚገርመው ቁጭ ብለው በጀመኣ ሲሉ የነበረውን
“ሶለዋት” ብለው የሚጠሩትን “መርሃባ ነቢ መርሃባ (እንኳን ደህና መጡ ነቢ እንኳን ደህና መጡ!)” የሚለው ላይ ሲደርሱ ከተቀመጡበት ብድግ የሚሉ መኖራቸው ነው።

➽በሰዓቱ ከሚባሉ የመንዙማ ስንኞች የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡-

➧“ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ” (በሀደሪኛ)
➧“አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢ” (በአማርኛ)
➧“ግቡልን የተንቢ” (በጉራጊኛ
)

➳ይህንንም የሚያደርጉት ነብዩ صلى الله عليه وسلم ይመጣሉ ብለው ስለሚገምቱ ነው። ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን! ነብዩ صلى الله عليه وسلم የትም አይመጡም። መዲና ተቀብረዋል። እኛ እሳቸው ላይ ሸሪአ ባዘዘው መልኩ ሰለዋት ስናወርድ መላኢካ ያደርስላቸዋል። ከዚያ ውጭ የትም አይመጡም።

➛ነብዩ صلى الله عليه وسلم አይደለም ሞተው በህይወት እያሉ እንኳን ሰው ከተቀመጠበት ሲነሳላቸው አይወዱም ነበር። ያው በዲን ላይ የሚጨመር ፈጠራ መጨረሻው ይህ ነው። ወደ አላህ እቃረባለሁ ብሎ ከአላህ መራቅ እና ቁጣውን መከናነብ። ነብዩ صلى الله عليه وسلم“የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው ተቀባይነት የለውም።”ብለዋል።

➛ በሃገራችን በተለምዶ “ኸሚስ” እየተባለ ሀሙስ ለጁሙዐ ሰዎች የሚሰባሰቡበት ምሽት ማስረጃ የማይደግፈው በሶሐባዎች ያልተፈፀመ ተግባር ነው።

➳ እንዲያውም ነብዩ صلى الله عليه وسلم በሐዲሣቸው ጁሙዐን ቀኑን በፆም ሌሊቱን በመቆም ከሌሎች ቀናት እንዳትለዩት ካሉት ማስረጃ ጋር የሚቃረን ነው። [ሙስሊም፡ 1144]
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ!ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➛ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ②⑤➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
☑️ ምቀኝነት
☑️ እዩልኝና ስሙልኝ
☑️ በራስ መገረምና ኩራት


https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru