💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

የአየተል ኩርስይ ትርጉም
የአየቱል ኩርስይ ትሩፋት

ክፍል ②①


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➛መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➲ክፍል አስራ ስምንት ➧ከዚህ ውጭ ያለውና ከሱና ባፈነገጡት ሺአዎች የተጀመረው የሺርክ መነሀሪያ የሆነው መውሊድ ግን ቢድአ ነው። እዚሁ መውሊድ የሚሉት ላይ “ሀድራ”፣ “መንዙማ"እየተባለ እዚሁ መፅሀፍ ላይ ወደ ፊት የምናያቸው በርካታ ጥፋቶች ይፈፅማሉ:: ➲ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፡- “ከንግግር ሁሉ በላጭ የአላህ ንግግር ነው፣ ምርጥ የሚባለው መመሪያ…
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል ⓵⓽

መንዙማ ድሮ እና ዘንድሮ
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➮

እውነታው ግን አዲስ እየተባሉ የወጡ መንዙማዎች አብዛኛዎቹ ግጥማቸውም ይሁን ዜማቸው ከድሮዎቹ የተቀዱ ናቸው። ስለዚህ የድሮዎቹ ላይ ችግር እንዳለ ከታመነ በተጨባጭ ከነችግራቸው እየተወረሱ ነው።“ድቤም ቢኖረው ከሺርክ የጸዳ ነው” የሚሉትም ከእውነት የራቀ ነው። ለዚህ በምዕራፍ ሁለት ብዙ ምሳሌዎችን እንመለከታለን።

በየሰርግ ቤቱ በየአጋጣሚው የሚባሉ የሺርክ ስንኞችን ድሮም ይባሉ ዘንድሮ፣ በድቤም ይሁን በእንጉርጉሮ፣ ስቱድዮ ውስጥም ይሁኑ መስጂድ ውስጥ ከአላህ ውጭ ያሉ አካላት እስከተጠሩበት ድረስ ሁሉም ሺርክ ነው። አብዛኛው እዚህ መፀሃፍ ላይ የሰበሰብኳቸው የሺርክ ስንኞች 70 ፐርሰንቱ ያህል በዚህ ዘመን ነሺዳ፣ እንጉጉሮ እየተባሉ ከሚለቀቁት ላይ ነው።

➛“ሺርክና የሙዚቃ መሳሪያ የሌለበት” የሚሉት ነሺዳም ይሁን መንዙማ ሙስሊሙን ኡማ ቁርኣንን ከመቅራት፣ ቁርኣንን ከመስማት፣ ቁርኣንን ከመሀፈዝ፣ በሸሪዓ የተደነገጉ ዚክሮችን ከመዘከር እና ሸሪኣዊ እውቀትን ከመፈለግ አዘናግቷል

ይህም የጥፋት መንገድ ለመሆኑ ከበቂ በላይ ነው። ሸይኽ አልባኒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል“…..ነሺዳ ሀራም በሆኑ ላይ ሁለት ነገር ማስረጃ ማድረጋችን በቂ ነው።

አንደኛው ሰለፉነ ሷሊህ በዚህ መንገድ አይጠቀሙም ነበር።

ሁለተኛው በተጨባጭ የማየው እና
የምመሰክረው እሱም ቢሆን አደገኛ ነገር ነው። ይህም የሙስሊም ወጣቶች የሚረኩት በኢስላማዊ ነሺዳ ነው። በእሷም ይዘፍናሉ። … ሁል ጊዜ። ይህም ተግባራቸው ቁርኣን ከመቅራት፣ አላህን ከማውሳት፣ ነብዩ ላይ ሶለዋት ከማውረድ አዘናጋቸው።….”


📝ምንጭ አልበያን አል-ሙፊድ አን ሁክሚ አተምሲሊ ወል አናሺድ ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን ሀፊዘሁላህ ያዩለት የአብደላህ አስ-ሱለይማኒ መፀሀፍ።

ሰለዋት ማውረድ ኢባዳ ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ሰለዋት ማውረድ ታላቅ አምልኮ ነውነብዩ (صلى الله عليه وسلم (እኛ ላይ ካላቸው መብቶች አንዱ እሳቸው ላይ ሰለዋት ማውረዳችን ነው። ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (እንዲህ ይላሉ “በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእሱ ላይ አስር ያወርድበታል።” [ሙስሊም፡ 384] በሳቸው ላይ ሰለዋት እንድናወርድ አላህም እንዲህ ሲል ያዘናል

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡[አልአሕዛብ፡ 56]

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ተመልከቱ የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم (አላህ ዘንድ ያላቸው ደረጃ እና ማዕረግ በጣም ታላቅ መሆኑን ከዚች አንቀጽ እንገነዘባለን። አላህ እና መላእክቱ የሚያደርጉት ሰለዋት ምንድን ነው? ታላቁ ሰለፍ አቡል ዐሊያ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡-

➳ሶለዋት “ከአላህ ሲሆን አላህ በላይኛው ነዋሪዎች (መላእክቶች) ዘንድ ነብዩን ማወደሱ ነው።”
➳የመላእክት ሶለዋት ደግሞ “ዱዐ ማድረጋቸው ነው
።” [ቡኻሪ፡ 6/120]



ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
ኢብኑል ጀውዝይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

የሚደርስብህ ፊትና (በላእ) ልክ ከአላህ ዘንድ እንደመጣ እንግዳ ነው።
የዚህን እንግዳ አቀባበል አሳምር


በሰላም ከቤትህ በመውጣቱ ነገ የውመል ቂያማ ምንዳ በሚሰጥበት ቀን አንተን አመስጋኝ እንጂ ወቃሽ እንዳይሆንብህ በሶብር ላይ ጥረት አድርግ።

📖| المدهِش ٣٧٤

https://t.me/Asselefya1
الشيخ الحصري - سورة الكهف (مرتّل)
Convert To Voice
🔁 سورة الكهف 🔁

🔺ማራኪ የሱረቱል ከህፍ ቂርአት

🎙القارئ محمد خليل الحصري

➲ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
➯➯➯➯➯➯➯➯➯


↪️ ገላን መታጠብ
↪️ ሽቶ መቀባት
↪️ ሲዋክ መጠቀም
↪️ ጥሩ ልብስ መልበስ
↪️ ሱረቱ ከህፍን መቅራት
↪️ በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
↪️ በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት
➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩


قَالَ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ
"من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَين"
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል"

📚
صحيح الجامع - رقم : (6470)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
1⃣ የአላህ መልዕክተኛ በሚሞቱበት ጊዜ "ኡነሊል መውቲ ለሰከራት" ይሉ ነበር ትርጉሙ ምን ማለት ነው⁉️
Anonymous Quiz
10%
ሞት ጥፍጥና አለው
6%
ሞት አስለቃሺ ነው
79%
ሞት ስካር አለው
5%
ሞት በጣም ቀላል ነው
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➭መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ⓵⓽ ➻መንዙማ ድሮ እና ዘንድሮ ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➮ ➧እውነታው ግን አዲስ እየተባሉ የወጡ መንዙማዎች አብዛኛዎቹ ግጥማቸውም ይሁን ዜማቸው ከድሮዎቹ የተቀዱ ናቸው። ስለዚህ የድሮዎቹ ላይ ችግር እንዳለ ከታመነ በተጨባጭ ከነችግራቸው እየተወረሱ ነው።“ድቤም ቢኖረው ከሺርክ የጸዳ ነው” የሚሉትም ከእውነት የራቀ ነው። ለዚህ በምዕራፍ ሁለት ብዙ ምሳሌዎችን እንመለከታለን።…
መንዙማ
➬➬➬➬➬

ክፍል ሀያ

➢ሰለዋት ማውረድ ኢባዳ ነው

➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧እሳቸው ላይ ከምናወርደው የሰለዋት አይነቶች ውስጥ በላጩ እሳቸው ለሶሐባዎቻቸው በላጭ ነው ሲሉ ያስተማሩት ነው። ይህም የተለያዩ ቅርፆች ያሉት ሲሆን የሚከተለው አንዱ ነው፡-

"اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على آل إبراهيم إنك حميد مجيد، وبارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على آل إبراهيم إنك
حميد مجيد"

➳አላህ ሆይ! በኢብራሂምና በቤተሰቦቻቸው ላይ እዝነትህን እንዳሰፈንከው ሁሉ በሙሀመድና በቤተሰቦቻቸው ላይም እዝነትህን አስፍን፣ አንተ ምስጉንና የላቅክ አምላክ ነህ። አላህ ሆይ! በኢብራሂምና በቤተሰቦቻቸው ላይ በረከትህን እንዳሰፈንክ ሁሉ በሙሀመድና በቤተሰቦቻቸው ላይም በረከትህን አዉርድ። አንተ ምስጉንና የላቅክ አምላክ ነህ።”
[ቡኻሪ፡ 3369፣ ሙስሊም፡ 406]

ስለዚህ በመልእክተኛው (صلى الله عليه وسلم) ላይ ሰለዋት ማውረድን የሚሻ ሰው በማስረጃ በመጣው መሰረት ሊያደርገው ይገባል። ምክንያቱም አምልኮ ተውቂፊይ ነውና።

ተውቂፊይ ማለት ምን ማለት ነው?
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

አምልኮ ተውቂፍይ ነው ሲባል አላህ እና መልክተኛው (صلى الله عليه وسلم) ባዘዙበት መልኩ ብቻ የሚፈጸም ነው ማለት ነው። ለምሳሌ ሰላትን ብንወስድ የምንሰግደው በመልእክተኛው (صلى الله عليه وسلم) በታዘዝነው መሰረት ነው

ለዚህም እራሳቸው “ስሰግድ እንዳያችሁኝ ስገዱ” ማለታቸው ዋቢ መሆን ይችላልልክ ሶላታችንን እሳቸው ባስተማሩት መልኩ ሳይሆን እኛን ባሰኘን መልኩ እንደማንፈፀምው ሌሎች ዒባዳዎችንም ስለአፈፃፀማቸው በመጡት ማስረጃዎች ላይ ተገድበን ልንፈፅም ይገባል።

ያለበለዚያ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው
(ተቀባይነት አይኖረውም)” ሲሉ ካስጠነቀቁት ውስጥ እንወድቃለን።
ሶለዋትን በተመለከተም ተመሳሳይ ቀመር ልንከተል ይገባል። እውነት አላህ በስራችን ምንዳን እንዲሰጠን እና ከቁጣው መራቅን ከፈለግን ሸሪዐው ባዘዘው መልኩ ልንፈፅም ይገባል። በሃገራችን የሚታየው ግን በብዙ መልኩ ከዚህ አደብ ጋር የሚፃረር ነው።


በመልክተኛው እና ቤተሰባቸው ላይ አላህ እዝነቱን፣ ሰላሙን፣ በረከቱን እንዲያወርድ በውዝዋዜና በጭፈራ አጅቦ ሲለመን ማየት ለአስተዋዮች ያሸማቅቃል። ይባስ ብሎም ይህ ታላቅ አምልኮ ከሺርክ እየተቀላቀለ መፈፀሙ ነው። አንዳንዱ ቦታ ጭራሽ ወንድ እና ሴት የሚቀላቀሉበት ሁኔታም አለ። ይህ ተግባር የአላህን ቁጣ የሚያከናንብ፣ ምንዳን ሳይሆን ኪሳራ የሚያስከትል ጥፋት ነው።
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

ኢንሻአላህ ይቀጥላል ◉ ◉ ◉ ◉

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

በተለያዩ እውቀቶች ይጠቀሙ ዘንድ ወደ ግሩፖችን ይቀላቀሉ!!

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

ክፍል ②②


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሰህል ቢን ሰእድ አስሳኢድይ እንዳስተላለፈው አንድ ሰው ወደ አላህ መልእክተኛ በመምጣት እንዲህ በማለት ጠየቃቸው።

◾️የአላህ መልእክተኛ ሆይ፦ ተግብሬው የአላህና የሰዎች ውዴታ የማገኝበት ስራ ጠቁመኝ አላቸው።

እሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱለት

ከዱንያ ችላ በል፦ አላህ ይወድሀል።
➳ሰዎች ዘንድ ካለው ነገር ችላ በል፦ ሰዎች ይወዱሀል።


📚(ኢብኑ ማጃህ ዘግቦታል)

https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
ቅድሚያ ለተውሂድ ቦታ እንስጥ!
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

አላህ ከእውቀቶች ሁሉ በቅድሚያ እንድንማረው ቦታ እንድንሰጠው ያዘዘን እርሱን በብቸኝነት ማምለክ ተውሂድን ነው!

«فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ»

«እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን፡፡»
[ሙሀመድ :19]


«إِنَّ اللّهَ لاَ يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَلِكَ لِمَن يَشَاءُ وَمَن يُشْرِكْ بِاللّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلاَلاً بَعِيدا»ً

«አላህ በርሱ የማጋራትን(ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡»
[ኒሳእ-116
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
⇠الحياء زينة المرأة وجمالها

ሀያዕ የሴት ልጅ ውበቷ ነው
1⃣ አህለሱና ወልጀማአዎች የአላህ ስምና መገለጫ በማፅደቅ በኩል መልእክተኞች ከተላኩበት ሀቅ የማይዘነበሉትና የማያፈነግጡት ለምንድ ነው⁉️
Anonymous Quiz
4%
እንዲከተሉት የታዘዙበት ስለሆነ
5%
ከጥመት መዳኛ ብቸኛው መንገድ
6%
የተስተካከለና ቀጥ ያለ መንገድ ስለሆነ
86%
ሁሉም