💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Muhammad al Muqit سورة الدخان - محمد المقيط | AD-DUKHAN (THE SMOKE)…
Quran Cure for the Hearts
➧ትልቅ ቅጣት ማለት ባንተና በቁርአን መረዳት መካከል እገዳ መኖር ነው!

﴿وَجَعَلْنَا عَلَى قُلُوبِهِمْ أَكِنَّةً أَنْ يَفْقَهُوهُ وَفِي آذَانِهِمْ وَقْراً﴾

" በልቦቻቸውም ላይ እንዳያውቁት ሺፋኖችን በጆሮዎቻቸውም ላይ ድንቁርናን አደረግን ፡፡"
[አንዓም 25]

➧ቁርአንን ልክ ንፁህ ያልሆነ ሰው
እንደማይነካው


➮ንፁህ ልብ የሌለውም የቁርአንን መረዳትና ጥፍጥናውን አያገኝም

➮የምንሰራቸው ወንጀሎች ከቁርአን እያራቁንና ልቦቻችንን አድርቀው
እያቆሸሹብን ይገኛሉ
ኢስቲግፋር ወደ አላህ መመለስ እናብዛ አላህ ወደርሱ ይመልሰን ።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌹ተጋበዙልኝ🌹

➲ቁረአንን ላስተነተነው ሰው የማይጠገብ የአላህ ፀጋ ልብን የሚያረጋጋ ሀሳብን የሚያስረሳ ያአላህ ... የአርሹ ጌታ ልባችንን በዚህ በማይጠገበው ቃሉ ያለምልምልን ይሙላልን ሀቂቃ ለአወቀው ሰው እኮ እንደ ቁረአን የደስታ ሰበብ የለምምምም!
ጠፊዋ ዱኒያ የማይጠገበውን የአላህ ፀጋ ጀነትን እንዳታሳጣን ጌታችንን እንለምነው ወደ ጌታችን እንመለስ!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
✅የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمእንድህ አሉ፣

▪️የመጨረሻ ሶላታችሁን በለሊት ዊትር አድርጉ !
📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ①⑨➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
۞ أَتَأْمُرُونَ النَّاسَ بِالْبِرِّ وَتَنسَوْنَ أَنفُسَكُمْ وَأَنتُمْ تَتْلُونَ الْكِتَابَ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ሥራ ታዛላችሁን? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን? (የሥራችሁን መጥፎነት) አታውቁምን?

📚ሱረቱል በቀራ 44
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➽መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ⓵⓺ ➲እናት፡- በአላህ አምና እና እሱን ፈርታ፣ የባሏን ሃቅ ጠብቃ፣ ልጆቿን በስነ ስርዐት ካሳደገች የአላህ ወልይ ናት። ➛ልጅ፡- ልጆች በአላህ አምነውና እሱን ፈርተው፣ ለወላጆቻቸው ታዝዥ ሆነው፣ ወላጆቻቸውን ካገዙ የአላህ ወልዮች ናቸው። ➛ነጋዴው፡- ኢማንና ተቅዋን አስገኝቶ ንግዱን በአግባቡ ነግዶ፣ ከሃላል ከስቦ፣ ዘካውን ካወጣ ይህ የአላህ ወልይ ነው።…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➭ክፍል ⓵⓻

➢አላህ ሙሉ ምንዳ የሚከፍለው ረመዳንን አምኖ፣ ሂሳቤን አላህ ይከፍለኛል ብሎ፣ መልካምን በመስራት ከአልባሌ ነገሮች በመራቅ ነው። የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم )እንዲህ ብለዋል፡

قَالَ رَسُوْل اللّٰه صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم :- مَن لَم يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ والعَمَلَ بِهِ فَلَيْسَ لِلَّهِ حاجَةٌ فِي أَنْ يَدَع طَعَامَهُ وَشَرَابَهُ

➧“አንድ ባሪያ የቅጥፈት ወሬን እና በሱ መስራትንም ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን ከመተው አላህ ደንታ የለውም።”
አል- ቡኻሪ

➮ተራ ቅጥፈቶች ለዚህ የሚዳርጉ ከሆነ ሺርክ እና ቢድአ ደግሞ ከነዚህ ሁሉ የባሰ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው። ይህ ሆኖ ሳለ ዛሬ በሃገራችን በተውሒዱ ወር በረመዳን ሰው ቁርኣን እየቀራ እንዳያሳልፍ መንዙማ ባዮች በየቋንቋው ሺርክ፣ ጭፈራ እና ብዙ ጉድ ያለባቸውን መንዙማዎች ይዘው በየመስጂዱ እና ገበያ ቦታ ላይ ከታላቅ ማስታወቂያ ጋር ብቅ ይላሉ። ሀስቡነላህ ወኒእመል ወኪል። ይሄ እንደዋዛ ሊታይ የማይገባው አደገኛ ጥፋት ነው።

➳ብዙዎቻችን ግን ጥፋቱ ከመንሰራፋቱ፣ ዘወትር ከመሰማቱ የተነሳ ጆሯችን ለምዶት ውስጣችን እስከማይደፈርስ ደርሷል።

➧ሌላው አገራችን ላይ አንዳንድ መስጊዶች ለአፍጥር ሰኣት 30 ደቂቃ ሲቀረው በሚያሳዝን ሁኔታ ማይክሮፎን ከፍተው በአላህ ላይ የማጋራትን ንግግር በአንድነት በዜማ ሲያስተጋቡ ይስተዋላሉ። ለምሳሌ እንዲህም ይላሉ፡-

“ኹዝ ቢየዲ ያረሱለላሀ፣ አጊስና ያረሱለላህ”

➛ትርጉሙም


➛“አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! እጄን ያዙኝ። አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርዱን (አጠጡን?)።”ፆሞ ውሎ በሺርክ ማፍጠር ምንኛ ልብ ያደማል?!

➲መንዙማ እና መውሊድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧መውሊድ ማለት የአንድን ግለሰብ የተወለደበት ቀን አመት ጠብቆ ማክበር ማለት ነው። የነብያት ሁሉ ሃይማኖት እስልምና የማንም ግለሰብ የልደት በአል እንዲከበር አልደነገገም።

➠ በእስልምና አንድ ሰው ልጅ ሲወለድለት ለጌታው ምስጋና ለማቅረብ እና ደስታውን ለመግለጽ ልጅ በተወለደለት በሰባተኛው ወይንም በአስራ አራተኛው ወይንም በቻለ ጊዜ ወንድ ከተወለደለት ሁለት በግ ወይንም ፍየል፣ ሴት ከተወለደለት አንድ በግ ወይንም ፍየል ያርዳል። ከወዳጅ ከዘመዶቹም ጋር በጋራ ይመገበዋል።

➳ አላህ የደነገገው እንግዲህ ይህን ነው።ከዚህ ውጭ ያለውና ከሱና ባፈነገጡት ሺአዎች የተጀመረው የሺርክ መነሀሪያ የሆነው መውሊድ ግን ቢድአ ነው። እዚሁ መውሊድ የሚሉት ላይ “ሀድራ”፣“መንዙማ” እየተባለ እዚሁ መፅሀፍ ላይ ወደፊት የምናያቸው በርካታ ጥፋቶች ይፈፀማሉ።
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📖መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➧ ጥሩ ፀሐፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!

📩ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
በሀላል መንገድ ኒካህ ማሰር አጅር የሚያስገኝና ሪዝቅን የሚያሰፋ ሲሆን በተቃራኒው ከኒካህ በፊት የሚደረግ የሀራም ግኑኝነት ግን ወንጀል ሲሆን ሪዝቅንም ያጠባል።

አላህ ሆይ! በነገራቶች ሁሉ ሀላሉን ወፍቀን ከሀራም ጠብቀን
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➖የሱረቱል ኢህላስ ትርጉም
➖የሱረቱል ኢህላስ ትሩፋት
➖ኢስባትና ነፍይ በተመለከተ

➰ክፍል ②∅➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (MuhammedSirage MuhammedNoor)
የሰዎች ኢስላምና ተውሒድ አላጠግብህ ብሎት የዘር ሃረጋቸውን መመዘኛ ያደረገ ሁሉ በጉዳዩ ላይ የታላቁን ነብይ ሳይሆን የታላቁን ከሃዲ የአቡ ጀህልን ና የመሠሎቹን ኮቴ በመከተል ላይ ነው!
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ⓵⓻ ➢አላህ ሙሉ ምንዳ የሚከፍለው ረመዳንን አምኖ፣ ሂሳቤን አላህ ይከፍለኛል ብሎ፣ መልካምን በመስራት ከአልባሌ ነገሮች በመራቅ ነው። የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم )እንዲህ ብለዋል፡ قَالَ رَسُوْل اللّٰه صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم :- مَن لَم يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ والعَمَلَ بِهِ…
➛መንዙማ
➬➬➬➬➬

➲ክፍል አስራ ስምንት

➧ከዚህ ውጭ ያለውና ከሱና ባፈነገጡት ሺአዎች የተጀመረው የሺርክ መነሀሪያ የሆነው መውሊድ ግን ቢድአ ነው። እዚሁ መውሊድ የሚሉት ላይ “ሀድራ”፣ “መንዙማ"እየተባለ እዚሁ መፅሀፍ ላይ ወደ ፊት የምናያቸው በርካታ ጥፋቶች ይፈፅማሉ::

➲ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፡-
“ከንግግር ሁሉ በላጭ የአላህ ንግግር ነው፣ ምርጥ የሚባለው መመሪያ
የሙሐመድ صلى الله عليه وسلم መመርያ ነው፤ ከነገሮች ሁሉ የከፋው (በዲን ላይ) ፈጠራ ነው፤ ፈጠራ
የተባለ ሁሉ ቢድዐ ነው፤ ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።”
[ሙስሊም፡ ]867

➧ሰርጋችን እስልምና ውብና የተሟላ የህይወት መመሪያ ነው። ትልልቅ የህይወታችን ክፍሎች ቀርቶ ትንንሽ የሚባሉት እራሱ ዝርዝር መመሪያ ተቀምጦላቸዋል። አንዳንዶች ግን ይህን እውነታ በመዘንጋት ወይም ችላ በማለት ከሸሪአው መመሪያ ወጥተው በራሳቸው ሲጓዙ ያጋጥማሉ። ለምሳሌ ሰርግን ብንወስድ ምን መምሰል እንዳለበት፣ ምን መባል እንዳለበት፣ ሙስሊሞች በሰርግ ላይ እንዴት መደሰት እንዳለባቸው ሸሪአ ጠቁሞናል።

➩ሆኖም ግን ዛሬ ከሳቸው ንግግር እና ከኢስላም በተቃራኒ ኢስላማዊ ዲጄ እየተባለ፣ የሺርክ መንዙማዎች እየተዜሙ፣ ወንዶች እየጨፈሩ እና እያጨበጨቡ፣ ሴቶች ባልተፈቀደላቸውየሙዚቃመሳሪያእየጨፈሩ፣ሴትእናወንድ ተቀላቅለው እየጨፈሩ፣ እያፏጩ ወዘተ ታላቁን የደስታ ቀን አላህን በማመጽ የሚያሳልፉት አሉ።

➲የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ይህን ታላቅ የደስታ ቀን ኒካሁ እንደታሰረ ለሙሽራው እና ለሙሽሪቷ “ባረከላሁ ለኩማ ወባረከ አለይኩማ ወጀመኣ በይነኩማ ፊ ኸይር” ተብሎ ዱአ እንደሚደረግላቸው ከውዱ ነብይ (صلى الله عليه وسلم) ፈለግ ተምረናል። ይህንን ዱአ ያደረጉት ለኡመቱ ታማኝ እና አዛኝ መካሪ የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم) ናቸው።

➧ልብ እንበል! አሁንም ይህንኑ ዱአ በሙዚቃ መሳሪያ እና በጭፈራ “ባረከላሁ ለኩማ” ብለን ካልቀወጥነው “ለቅሶ ቤት እኮ አይደለም የመጣነው”፣ “የእነ እገሌ ዘፋኝን ከመስማት አይሻልም ወይ?” የሚሉ አሉ። ይሄ አደብ የቀለለው አነጋገር ነው። ሙስሊም ማለት ለፈጣሪው ህግ እጅ የሚሰጥ ነው። ሙስሊም ማለት የሶሐቦችን አርአያ የሚከተል ነው። ሶሐቦች ሰርጋቸውን የጋጠ ወጦች አይነት ካላደረግን “ለቅሶ ቤት” ይሆንብናል የሚሉ ግብዞች አልነበሩም።

➲የደስታ ቀንን እንዴት ጌታቸውን እያመሰገኑ ማሳለፍ እንዳለባቸው ስለሚያውቁ በነብዩ ሱና መሰረት ነው የተጓዙት። صلى الله عليه وسلم

➣መንዙማ ድሮ እና ዘንድሮ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭አብዛኞች ከሚሸወዱባቸው ነገሮች ውስጥ “የድሮ መንዙማ እና የአሁን መንዙማ ይለያያሉ”፣“የድሮመንዙማዎችሺርክአለባቸው”፣“ድቤአላቸው”፣“የአሁኖቹ ደግሞ እንጎርጉሮ የሆነም አለ”፣ “ድቤ ያለውም ከሽርከ የጸዳ ነው” የሚሉ አሉ።

◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል......

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➳አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

በተለያዩ እውቀቶች ይጠቀሙ ዘንድ ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ!!

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➖የአየተል ኩርስይ ትርጉም
➖የአየቱል ኩርስይ ትሩፋት

➰ክፍል ②①➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➛መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➲ክፍል አስራ ስምንት ➧ከዚህ ውጭ ያለውና ከሱና ባፈነገጡት ሺአዎች የተጀመረው የሺርክ መነሀሪያ የሆነው መውሊድ ግን ቢድአ ነው። እዚሁ መውሊድ የሚሉት ላይ “ሀድራ”፣ “መንዙማ"እየተባለ እዚሁ መፅሀፍ ላይ ወደ ፊት የምናያቸው በርካታ ጥፋቶች ይፈፅማሉ:: ➲ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፡- “ከንግግር ሁሉ በላጭ የአላህ ንግግር ነው፣ ምርጥ የሚባለው መመሪያ…
➭መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ⓵⓽

➻መንዙማ ድሮ እና ዘንድሮ
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➮

➧እውነታው ግን አዲስ እየተባሉ የወጡ መንዙማዎች አብዛኛዎቹ ግጥማቸውም ይሁን ዜማቸው ከድሮዎቹ የተቀዱ ናቸው። ስለዚህ የድሮዎቹ ላይ ችግር እንዳለ ከታመነ በተጨባጭ ከነችግራቸው እየተወረሱ ነው።“ድቤም ቢኖረው ከሺርክ የጸዳ ነው” የሚሉትም ከእውነት የራቀ ነው። ለዚህ በምዕራፍ ሁለት ብዙ ምሳሌዎችን እንመለከታለን።

➮በየሰርግ ቤቱ በየአጋጣሚው የሚባሉ የሺርክ ስንኞችን ድሮም ይባሉ ዘንድሮ፣ በድቤም ይሁን በእንጉርጉሮ፣ ስቱድዮ ውስጥም ይሁኑ መስጂድ ውስጥ ከአላህ ውጭ ያሉ አካላት እስከተጠሩበት ድረስ ሁሉም ሺርክ ነው። አብዛኛው እዚህ መፀሃፍ ላይ የሰበሰብኳቸው የሺርክ ስንኞች 70 ፐርሰንቱ ያህል በዚህ ዘመን ነሺዳ፣ እንጉጉሮ እየተባሉ ከሚለቀቁት ላይ ነው።

➛“ሺርክና የሙዚቃ መሳሪያ የሌለበት” የሚሉት ነሺዳም ይሁን መንዙማ ሙስሊሙን ኡማ ቁርኣንን ከመቅራት፣ ቁርኣንን ከመስማት፣ ቁርኣንን ከመሀፈዝ፣ በሸሪዓ የተደነገጉ ዚክሮችን ከመዘከር እና ሸሪኣዊ እውቀትን ከመፈለግ አዘናግቷል።

ይህም የጥፋት መንገድ ለመሆኑ ከበቂ በላይ ነው። ሸይኽ አልባኒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል“…..ነሺዳ ሀራም በሆኑ ላይ ሁለት ነገር ማስረጃ ማድረጋችን በቂ ነው።

➧አንደኛው ሰለፉነ ሷሊህ በዚህ መንገድ አይጠቀሙም ነበር።

➧ሁለተኛው በተጨባጭ የማየው እና
የምመሰክረው እሱም ቢሆን አደገኛ ነገር ነው። ይህም የሙስሊም ወጣቶች የሚረኩት በኢስላማዊ ነሺዳ ነው። በእሷም ይዘፍናሉ። … ሁል ጊዜ። ይህም ተግባራቸው ቁርኣን ከመቅራት፣ አላህን ከማውሳት፣ ነብዩ ላይ ሶለዋት ከማውረድ አዘናጋቸው።….”


📝ምንጭ አልበያን አል-ሙፊድ አን ሁክሚ አተምሲሊ ወል አናሺድ ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን ሀፊዘሁላህ ያዩለት የአብደላህ አስ-ሱለይማኒ መፀሀፍ።

➲ሰለዋት ማውረድ ኢባዳ ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ሰለዋት ማውረድ ታላቅ አምልኮ ነው። ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (እኛ ላይ ካላቸው መብቶች አንዱ እሳቸው ላይ ሰለዋት ማውረዳችን ነው። ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (እንዲህ ይላሉ “በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእሱ ላይ አስር ያወርድበታል።” [ሙስሊም፡ 384] በሳቸው ላይ ሰለዋት እንድናወርድ አላህም እንዲህ ሲል ያዘናል

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

➭አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡[አልአሕዛብ፡ 56]

➧የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ተመልከቱ የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم (አላህ ዘንድ ያላቸው ደረጃ እና ማዕረግ በጣም ታላቅ መሆኑን ከዚች አንቀጽ እንገነዘባለን። አላህ እና መላእክቱ የሚያደርጉት ሰለዋት ምንድን ነው? ታላቁ ሰለፍ አቡል ዐሊያ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡-

➳ሶለዋት “ከአላህ ሲሆን አላህ በላይኛው ነዋሪዎች (መላእክቶች) ዘንድ ነብዩን ማወደሱ ነው።”
➳የመላእክት ሶለዋት ደግሞ “ዱዐ ማድረጋቸው ነው
።” [ቡኻሪ፡ 6/120]
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➲ኢብኑል ጀውዝይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

➠ የሚደርስብህ ፊትና (በላእ) ልክ ከአላህ ዘንድ እንደመጣ እንግዳ ነው።
የዚህን እንግዳ አቀባበል አሳምር
።

በሰላም ከቤትህ በመውጣቱ ነገ የውመል ቂያማ ምንዳ በሚሰጥበት ቀን አንተን አመስጋኝ እንጂ ወቃሽ እንዳይሆንብህ በሶብር ላይ ጥረት አድርግ።

📖| المدهِش ٣٧٤

https://t.me/Asselefya1
الشيخ الحصري - سورة الكهف (مرتّل)
Convert To Voice
🔁 سورة الكهف 🔁

🔺ማራኪ የሱረቱል ከህፍ ቂርአት

🎙القارئ محمد خليل الحصري

➲ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
➯➯➯➯➯➯➯➯➯


↪️ ገላን መታጠብ
↪️ ሽቶ መቀባት
↪️ ሲዋክ መጠቀም
↪️ ጥሩ ልብስ መልበስ
↪️ ሱረቱ ከህፍን መቅራት
↪️ በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
↪️ በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት
➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊


قَالَ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ
"من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَين"
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል"

📚
صحيح الجامع - رقم : (6470)
〰〰〰〰〰〰
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w