💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
سورة الكهف | بصوت القارئ الشيخ على عبد الرحمن الحذيفى
تذكيــــــــــــر

▪️ بـــ قراءة سورة الكهف.

عن أبي سَعيدٍ الخُدريِّ -رضي الله عنه- عنِ النبيِّ -صلَّى اللهُ عليه وسلَّم- أنَّه قال: "مَن قَرَأَ سورةَ الكَهفِ يومَ الجُمُعةِ أضاءَ له من النورِ ما بَينَ الجُمُعتينِ".

📘[صحيح الجامع (٦٤٧٠)].

▪️ والإكثار من الصلاة على النبي -ﷺ-

قالَ رسولُ اللَّه -ﷺ-: "إنَّ مِن أَفْضلِ أيَّامِكُمْ يَوْمَ الجُمُعةِ، فَأَكْثِرُوا عليَّ مِنَ الصلاةِ فِيهِ، فإنَّ صَلاتَكُمْ معْرُوضَةٌ علَيَّ فقالوا: يَا رسول اللَّه، وكَيْفَ تُعرضُ صلاتُنَا عليْكَ وقدْ أرَمْتَ؟ قال: يقولُ: بَلِيتَ، قالَ: إنَّ اللَّه حَرم عَلَى الأرْضِ أجْساد الأنْبِياءِ".

📘[رواهُ أَبُو داود بإسنادٍ صحيحِ].

وآخر ساعة من يوم الجمعة.

 عَن أبي هريرة -رضي الله عنه- أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ -ﷺ- ذَكَرَ يَوْمَ الجُمُعَةِ، فَقَالَ: "فِيه سَاعَةٌ لا يُوَافِقها عَبْدٌ مُسلِمٌ، وَهُو قَائِمٌ يُصَلِّي يسأَلُ اللَّه شَيْئًا، إِلاَّ أَعْطَاهُ إِيَّاه وَأَشَارَ بِيدِهِ يُقَلِّلُهَا".

📘[متفقٌ عليه].
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስከ መጨረሻው ተከታተሉት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

👉ቁርአንን አስተካክሎ በተጅዊድ ማንበብ ትልቅ ኒእማ ነው።

◾️እናታችን ኣኢሻ (رَضي اللَّه عنها) እንዳስተላለፈችው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

【يقول النبي ﷺ: الماهر في القرآن مع السفرة الكرام البررة، والذي يقرأ القرآن ويتتعتع فيه وهو عليه شاق له أجره مرتين】

 ➲ቁርአንን አሳምሮ የሚያነብና የሚጠባቀው የሆነ ሰው ከነዛ ከተከበሩ፣ ከላቁና ታዛዥ ከሆኑት መላኢካዎች ይሆናል። ያ እየተኮላተፈ፣ እየተቸገረና እየከበደው ቁርአንን ለሚቀራ ደሞ ሁለት አጅር አለው። በመቅራቱና በመቸገ‼️
📚 متفق عليه
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➳ክፍል ⓵⓶ ➧ይራባሉ፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (በአንድ አጋጣሚ እሳቸው፣ አቡበክር እና ኡመር (ረድየላሁ ዐንሁማ) ተርበው ነበር። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ ግን የሚመግብ እና የማይመገብ ነው። ➧ይተኛሉ፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (እንቅልፍ ወስዷቸው ፈጅር ሰላት አምልጧቸው ያውቃሉ።አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ…
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል ⓵

➭ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ደግሞ ጌታችንን አላህ እንዲህ ሲሉ ያወድሱታል፣ ይለምኑታል።

يَا حيُّ يَاقَيُومُ بِرَحمَتِكَ أَستَغِيثُ أَصلِح لِي شَأْنِي كُُلَّهُ ولا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طرْفَةَ عَيْنِِ

➧“ህያው የሆንከው፣ ፍጡራንህን የምታብቃቃው በራስህ የምትብቃቃው (አላህ) በእዝነትህ እርዳታን እለምንሃለሁ። ሁለመናዮን አሳምርልኝ። እኔን ለነፍሴ ለቅጽበት ታክልእንኳን አትተወኝ።”
[ሰሂህ አ-ተርጊብ ወተርሂብ፡ 661]

➳ሁሉም ጠፍተው የልቅና እና የክብር ባለቤት የሆነው አላህ እንደሚቀር እንዲህ ሲል ይነግረናል፡-


كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ ◉وَيَبْقَىٰ وَجْهُ رَبِّكَ ذُو الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ

“በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው። የልቅናና የልግሥና ባለቤትየሆነው የጌታህ ፊትም ይቀራል።” [
አርረሕማን፡ 26-27]

ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ሁሉም ፍጡራን ሞተው አላህ ብቻውን እንደሚቀር እና “እነዚያ አምባ ገነኖች እነዚያ ኩራተኞች የት አሉ?” እንደሚል ነግረውናል። [ሙስሊም፡ 2788]

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ስለዚህ አምልኮ የሚገባው ህያው ለሆነው አላህ እንጂ ለሞቱት ወይም ለሚሞቱት ኢሳ ዐለይሂ-ስሰላም ወይንም ለሞቱት ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم(፣ መርየም፣ ፋጢማ (ረድየላሁ አንሃ)፣ አልይ (ረድየላሁ አንሁ)፣ ሁሴን (ረድየላሁ
አንሁ) እና መሰሎቻቸው አይደለም። እነዚህን ታላላቅ የአላህ ባሪያዎች የጠቀስኩት ለምሳሌነት ነው። እነሱን ከአላህ ውጭ ማምለክ ካልተቻለ፣ ሌሎቹንማ ይበልጥ አይቻልም
። አንድ አንቀፅ ልጨምር:-

وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا

“በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ። ከማመስገንም ጋር አጥራው። በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂነት በእርሱ በቃ።”
[አል ፉርቃን፡ 58]

➧በየትኛውም ዘመን ከአላህ ውጭ የሚመለኩት ሁሉ ይህንን የሚያሟሉ አይደሉም። ሁሉም የአላህ ፍጡሮችናቸው፣ ሁሉም ሟቾች ናቸው፣ ሁሉም ጠፍተው የልቅናና የልግሥና ባለቤት የሆነው የጌታ አላህ ፊት ይቀራል።

አላህ የሚመግብ እና የማይመገብ ነው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አምልኮ የሚገባው ሁሉን መጋቢ ለሆነው ፈጣሪ እንጂ ለተመጋቢ ፍጡራን አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል፡

قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ ۗ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው፡፡ «እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን (ተብያለሁ)» በላቸው፡፡ አል አንዓም 14

ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ያነበበ ተጠቀመ!!

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ የመልእክተኛች እውነተኝነት
☑️ ሳሂር፣ ጠንቋይ፣ ኮከብ ቆጣሪ

ክፍል ①⑥


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ይችን አያ የሚያስተነትን አዕምሮ ያለው ሰው እንደት አላህን ያመፃል?


كَيْفَ تَكْفُرُونَ بِاللَّهِ وَكُنتُمْ أَمْوَاتًا فَأَحْيَاكُمْ ۖ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

ሙታን የነበራችሁ ስትኾኑ ሕያው ያደረጋችሁ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ሲኾን ከዚያም ወደርሱ የምትመለሱ ስትኾኑ በአላህ እንዴት ትክዳለችሁ!

➛አላህ ባማረውና ውብ በሆነው ቃሉ ልባችንን ያርጥብልን! የእኛ ነገር ያሳዝናል
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➳ክፍል ⓵⓶ ➧ይራባሉ፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (በአንድ አጋጣሚ እሳቸው፣ አቡበክር እና ኡመር (ረድየላሁ ዐንሁማ) ተርበው ነበር። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ ግን የሚመግብ እና የማይመገብ ነው። ➧ይተኛሉ፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (እንቅልፍ ወስዷቸው ፈጅር ሰላት አምልጧቸው ያውቃሉ።አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ…
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል ⓵

ፈጣሪ እና ፍጡሮቹ
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

የሁሉ ጌታ፣ ብቸኛው ፈጣሪ አንድ አምላክ አላህ ብቻ ነው። አላህ ከእርሱ ውጭ ያሉትን ሁሉ የፈጠረ የአለማቱ ሁሉ ጌታ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ الفاتحة: ٢

“ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለሆነው።” [አልፋቲሐህ፡ 2]

የሰው ልጅ ፈጣሪውን ትቶ ልክ እንደሱ ፍጡር የሆኑትን ቢያመልክ የኪሳራዎች
ሁሉ ከባድ ኪሳራ ውስጥ ወድቋል።

ያለመውንም ሳያገኝ ከጌታውም ጋር ተጣልቷል።ምክንያቱም ፍጡራን ከላይ እስከ ታች ሁሉም ከአላህ ከጃዮች ናቸውና። ደግሞም ደረጃቸው ቢለያይም ሁሉም የፍጡር ድንበርን የማይሻገሩ ባርያዎች ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፡


أَمْ خُلِقُوا مِنْ غَيْرِ شَيْءٍ أَمْ هُمُ الْخَالِقُونَ

ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን? አጥጡር 35


إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

➧“እነዚያ ከአላህሌላ የምትገዟቸው (እነሱም) ብጤዎቻችሁ ተገዢዎች (ባሪያዎች) ናቸው።እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ፤ (መመለስ ግን
አይችሉም)።”
[አልአዕራፍ፡ 194]

ጂብሪል (ዐለይሂ-ስሰላም) የመላእክቶች አለቃ ነው። ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ደግሞ የነብያት ሁሉ ኢማም ናቸው። ሁለት የፍጡራን ቁንጮዎች። ከመሆኑም ጋር ነብዩ(صلى الله عليه وسلم (ጂብሪል “ምን ነው እንደበፊቱ ቶሎ ቶሎ አትመጣም?” ብለው ሲጠይቁት እንዲህ ነበር ያለው


وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا

(ጂብሪል አለ) «በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም
፡፡መርየም 64

➧ተመልከቱ እንግዲህ የመለእክቶች አለቃ ጂብሪል ካለበት ቦታ ያለ አላህ ፍቃድመንቀሳቀስ አይችልም።

ህያው የማይሞት አላህ እና ሙታን ፍጡሮቹ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➫➫➫➫➫➫➫

አላህ ከምንም በፊት መጀመሪያ የነበረ ነው። ሁሉም ሞተው ብቻንም ቀሪ ነው።
ነብዩን (صلى الله عليه وسلم (የየመን ሰዎች “እንዴት ይሁ ሁሉ ነገር ጀመረ?” ብለው ጠየቁ። ነብዩም(صلى الله عليه وسلم (እንዲህ አሉ፡- “መጀመሪያ አላህ ነበር። ከእርሱም ጋር ምንም ነገር አልነበረም።


አርሹም ውሃው ላይ ነበር። ከዚያም ሰማያትእና ምድሮችን ፈጠረ።” ቡኻሪ ዘግበውታል

እንግዲህ አላህ ስለ እራሱ እንዲህ ሲል ይነግረናል

اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ۚ

“አላህ ከእርሱበቀር ሌላ አምላክ የለም። ሕያው ራሱን ቻይ ነው።” [
አልበቀራህ፡ 255]



ኢንሻአላህ ይቀጥላል......

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

https://t.me/https_Asselefya1
أذكار الصباح كاملة بصوت العفاسي بدقة عالية (2020) جديد
🌹اذكار الصباح🌹

🌸የጧት ዚክር🌸

አስጊና አሰቃቂ አስፈሪ ጨለማ
መብራት የሌለበት ቲንሸየ ሻማ
ማይነጋ መሳይ የሀሳብ ቀጠሮ
በመከጀል ተስፋ ነገን ዛሬ ቋጥሮ
መንጋቱን ታያለክ ባሳብ ተወጥሮ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

ክፍል ①⑦


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ⓵⓷ ➭ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ደግሞ ጌታችንን አላህ እንዲህ ሲሉ ያወድሱታል፣ ይለምኑታል። يَا حيُّ يَاقَيُومُ بِرَحمَتِكَ أَستَغِيثُ أَصلِح لِي شَأْنِي كُُلَّهُ ولا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طرْفَةَ عَيْنِِ ➧“ህያው የሆንከው፣ ፍጡራንህን የምታብቃቃው በራስህ የምትብቃቃው (አላህ)…
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል አስራ አምስት

قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ ۗ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው፡፡ «እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን (ተብያለሁ)» በላቸው፡፡ (አል:አንዓም 14)

እነሱ “መቃረቢያ” ሲሉት፣ አላህ ሺርክ ሲል ጠራው።

የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَالَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ مَا نَعْبُدُهُمْ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَا إِلَى اللَّهِ زُلْفَىٰ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ فِي مَا هُمْ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي مَنْ هُوَ كَاذِبٌ كَفَّارٌ

እነዚያም ከእርሱ ሌላ ረዳቶች የያዙት “ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም” (ይላሉ)።” [አዝዙመር፡ 3]
ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን አላህ ከክፉ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ፡-

ሺርክን ለመስራት አላሰቡም ነበር። አላማቸውም አልነበረም። እነሱ አምልኮን ማሟያ ለመፈጸም እና በዚህም ወደ አላህ ለመቃረብን ብቻ ነበር ያሰቡት። ሸይጧን የአደም ልጆችን ለማሳሳት እንዴት እንደሚቀርባቸው እና ከሰው ሰይጣናት ውስጥ የሆኑት የአደም ልጆችን እንዴት ይህንን (የሺርክ) ተግባር አሳምረው እንደሚያቀርቡላቸው ተመልከት።

እኛም እንላቸዋለን፡- ጣኦቶቹን በቀጥታ ላታመልኩ ትችላላችሁ። ነገር ግን ጻድቃንን በናንተ እና በአላህ መካከል (ድልድይ) አድርጋችኋል። ይህም ቢሆን አላህ ዘንድ ሺርክ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ ۚ قُلْ أَتُنَبِّئُونَ اللَّهَ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ። “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። “አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን?” በላቸው። ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም።” [ዩኑስ፡ 18]

ተመልከቱ አላህ “አላህ ከሁሉም ጠራ፤ ላቀም” ሲል ከነሱ እና ከተግባራቸው እራሱን ነጻ እንዳደረገ። “ከሚያጋሩት” ሲል ደግሞ ተግባራቸውን ሺርክ ብሎ እየጠራው ነው።የሸይኽ ፈውዛን ንግግር እዚህ ላይ አበቃ።
ዛሬ ሺርክ የሚፈጽሙ ሰዎች ይህንኑ ነው ማማካኛ አድርገው የሚወስዱት። ተመሳሳይ ጥፋት። ተመሳሳይ ማመካኛ።
የአላህ ወልይ ማን ነው?

ወልይነት (ወዳጅነት ረዳትነት)፡- የጠላትነት ተቃራኒ ነው። የወልይነት መሰረቱ መውደድ እና መቃረብ ነው።

የጠላትነት መሰረቱ መጥላት እና መራቅ ነው። “ዊላያ” በሙያዊ ፍቺው አንድ ባርያ አላህን በመታዘዙ አላህ ያን ባርያ መቅረቡ ነው። ወልይነት ኢማን እና አላህን መፍራት የተባሉትን ሁለት መስፈርቶች ይጠይቃልአላህ አንዲህ ይላል፡-

أَلَا إِنَّ أَوْلِيَاءَ اللَّهِ لَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
الَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ


ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም። (እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው።” [ዩኑስ፡ 62-63]


➩ስለዚህ አንድ ሰው በአላህ አምኖ አላህን እስከፈራ ድረስ ወልይ ነው። በመስፈርቱ መሰረትም፡-
አባት፡- በአላህ አምኖና እሱን ፈርቶ በስሩ የሚተዳደሩትን ቤተሰቦች በአግባቡ ከያዘ ይህ የአላህ ወልይ ነው።

ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ያነበበ ተጠቀመ!!

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

ክፍል ①⑧


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ማንኛውም በዱንያ ላይ ለሚደርስብን መከራ፣ ስቃይ፣ ችግር፣ ሙሲባና ስብራት መጠገኛውና መካሻው ጀነት ውስጥ ነው። ብቻ በሶብር ላይ እንበርታ!
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➳መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አስራ አምስት قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ ۗ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ «ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው…
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል ⓵⓺

እናት፡- በአላህ አምና እና እሱን ፈርታ፣ የባሏን ሃቅ ጠብቃ፣ ልጆቿን በስነ ስርዐት ካሳደገች የአላህ ወልይ ናት።

ልጅ፡- ልጆች በአላህ አምነውና እሱን ፈርተው፣ ለወላጆቻቸው ታዝዥ ሆነው፣
ወላጆቻቸውን ካገዙ የአላህ ወልዮች ናቸው።

ነጋዴው፡- ኢማንና ተቅዋን አስገኝቶ ንግዱን በአግባቡ ነግዶ፣ ከሃላል ከስቦ፣ ዘካውን ካወጣ ይህ የአላህ ወልይ ነው። ወዘተ….

ደግሞም ወልዮች የሚበላለጡት በኢማናቸው እና ለአላህ ባላቸው ፍራቻ ነው።

ታላላቆቹ የአላህ ወልዮች ነብዮች ናቸው። ከነብዮቹም ውስጥ መልክተኞቹ ናቸው።ከመልክተኞቹም ውስጥ አምስቱ የቁርጠኝነት ባለቤቶች የሚባሉት ቁንጮዎች ናቸውከአምስቱ የቁርጠኝነት ባለቤቶች ውስጥ ደግሞ የሁሉ ቁንጮ የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ ናቸው።صلى الله عليه وسلم ለምን ይህን አርእስት እዚህ መጸሀፍ ላይ ማንሳት አስፈለገ? ምክንያቱም አገራችን
ላይ በብዛት ከአላህ ውጭ አምልኮ የሚፈጸምላቸው “ወልዮች” ተብለው የሚገመቱ ሰዎችን ነው።
አንዳንዶች በድፍረት “ወልዮች ነብያትን ይበልጣሉ” ሁሉ ይላሉ። ይሄ የሰዎቹ ቅጥፈትና ድፍረት የት እንደደረሰ የሚያሳይ ነው

ዛሬ በተገላቢጦሹ ማህበረሰባችን ዘንድ ከእምነት ክፍል ብዙ የሚያጓድሉ፣ክህደትን እና ሺርክን (ለምሳሌ የሚጠነቁሉና ትንቢት ተናጋሪ ነን የሚሉ፣ የሚያጓሩ) እያጨማለቁ፣ በኢስላም ንፅህና የኢማን ግማሽ ሆኖ ሳለ በተገላቢጦሽ ንፅህናቸውን
የማይጠብቁ፣ ሶላት ወይ ከነጭራሹ የማይሰግዱ ወይም ደግሞ ጀመአ የማይገኙ ወልይ ተብለው የሚገመቱ ብዙ ወንበዴዎች አሉ።


እንዲህ አይነቱ የሰይጣን ወልይ እንጂ
በፍፁም የአላህ ወልይ አይደለም።

ረመዳንን ምንዳውን ምን ያጓድለዋል?
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት ውስጥ አንዱ ነው። ረመዳን የቁርኣን
ወር ነው። ረመዳን የሰደቃ ወር ነው። ረመዳን ተራዊህ የሚሰገድበት ወር ነው። ረመዳን ብዙ መልካም ስራዎች የሚሰሩበት ወቅት ነው። ረመዳን ቁርኣን የወረደበት ወር ለመሆኑ አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል


شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ

የረመዳን ወር ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት)
ከሚለዩም ገላጮች ሲሆን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው።
” [አልበቀራህ: 185]

በዚህ በተከበረ የቁርኣን ወር የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم (ከጂብሪል ዐለይሂ-ስሰላም ጋር አንድ ጊዜ እየተቃሩ ሙሉ 30 ጁዝ ቁርኣንን ይጨርሱ ነበር። የሞቱ አመትም ሁለት ጊዜ ጨርሰዋል።



ኢንሻአላህ ይቀጥላል..........

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➤ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴
➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1