💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የላኢላ_ሃኢለሏህ መስፈርቶች ሰባት ናቸዉ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ⓹ ➠7ኛው መስፈርት መዉደድ ከትላቱ የቀጠለ፦ ስለዚህ መስፈርቶች ስናወራ ዋናዉ የሚፈለገዉ ነገር በተጨባጭ መልዕክታቸዉን ማስገኛት እንጂ እንዲሁ በጭንቅላት ሸምዲዶ በምላስ መዘርዘሩ አይደለም። ስንት መስፈርቶቿን መቁጠር ሳይችል ላኢላ ሀኢለሏህን በሚገባ የሚያስገኝ አለ?! ➧ስንት በምላሱ…
የላኢላ ሃኢለላህ መስፈርቶች ሰባት ናቸዉ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ክፍል ስድስት

የሰባተኛው መስፈርት ማጠቃለያ ነጥቦች
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

➧አብዘሃኛዉ ወገናችን የላኢላ_ሃኢለላህ መልዕክት በሚገባ አለመረዳቱ በግልፅ የሚታይ ነዉ።

ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦''ለዚች መልካም ቃል ላኢላ ሃኢለላህ ካላቸዉ ብልሹ ግንዛቤ አንፃር ሲታይ ዛሬ ላይ ያሉ በርካታ ሙስሊሞች በተጨባጭ እዉነታ ከቀደመዉ የአረቦች የጨለማዉ ዘመን የከፍ ነዉ።ምክንያቱም እነዚያ አጋሪዎች አረቦች የላኢላ ሃኢለላህን መልዕክት ይረዱ ነበር፣ አያምንባቱም እንጂ

ብዙሃኑ የዘመናችን ሙስሊሞች ግን የሚያምኑበትን ነዉ የሚያስተጋቡትናት 'ላኢላ ሃኢለላህ 'ይላሉ። በተጨባጭ ግን በመልዕክቷ አያምኑም።(አትተዉሒዲ አዉወለን፡14)

እንዲያዉም ላኢላ ሃኢለላህ የምትለዋን ምስክርነት አንሻፎ የሚረዳዉ ተራዉ ህዝብ ብቻ አይደለም። በተዉሒድ ስም ኪታብ የሚፀፉት ሳይቀሩ ''ላኢላ ሃኢለላህ ማለት ከአላህ በቀር የሚፈጥር ፣የሚረዝቅ፣ የሚያቀናብር፣የለም ማለት ነዉ''የሚሉት ቀላል አይደሉም

ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦''ከሚደንቀዉ ዘግይተዉ ከመጡት በተዉሒዲ እዉቀት ላይ መፀሃፍ ከሚያዘጋጁት ዉስጥ አብዘሃኞቹ የሚያተኩሩት የአላህን ጌትነት በሚያትተዉ -ተዉሒዲ አርሩቡብያ -ላይበመሆኑ ነዉ። ልክ የጌታን መኖር የሚክዱ ሰዎችን የሚያናግሩ ይመስል። ምንም እንኮን የጌታን መኖር የሚክዲ ቢኖርም ነገር ግን በአምልኮት ሺርክ ላይ የወደቁ ሙስሊሞች ምንኛ የበዙ ናቸዉ። (አልቀዉሉል ሙፊዲ ፡8)

ስለዚህ በፈጣሪ መኖር የሚያምኑ ሰዎችን የምናናግርበት ቋንቋ ከነጭራሹ በፈጣሪ ህልዉና የካዱ ሰዎችን በምናናግርበት መልኩ መሆን የለበትም።በፈጣሪ ህልዉና ማመንማ እነሱ ጋር የሚገኝ ተዉሒዲ ነዉ።መሆን የሚገባዉ ይህ ቢሆንም በተጨባጭ የሚታየዉ ግን ከዚህ ተቃራኒ ነዉ።

አሁንም ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ ይላሉየሚያሳዝነዉ ዛሬ በዚህ ርዕስ ስር የሚፀፉ በርካቶችን ብትመለከት ስለ ተዉሒዲ ሲናገሩ ከተዉሒዲ አርሩቡቡያ ባለፈ ሲያሰፍሩ አይታይም። ይሄ ስህተት ነዉ። ከባዲ ክፍተት!! ከተዉሂዲ አርሩቡቡያ በበለጠ ከሙስሊሞች ልቦና ዉስጥ ተዉሒዱል ኡሉሂያን ልንተክል የግዲ ይለናል። ምክንያቱም ተዉሒዱ አርሩቡቡያ የሐቂቃ የሆነ መካዲን አንዲም አልካደዉምና!! ታዲያ ይሄን በህሌና የሚታወቅ ተፈጥሯዊ ጉዳይ ብቻ እያፀደቅን ስሜት በእጂጉ የሚገባበትን ጉዳይ ፀጥ ማለታችን በርግጥም ከባዲ ክፍተት ነዉ።(አልቀዉሉል ሙፊዲ:8)

በዚህ ተጠናቀቀ

📚ተዉሒዲ የሁለት ሃገር ስኬት ከሚለዉ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁሏህ መፀሃፍ የተወሰዴ

✍️أم عثيمين
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ አላህ ከአርሽ በላይ ስለመሆኑ
☑️ ይህንን ለሚያስተባብሉ ምላሽ


ክፍል ①⑤


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
سورة الرحمن _ Surah Rahmān بصوت أحمد خضر
<unknown>
❖┅━℘❦⇣❦℘━┅❖
تلاوة هادئة رائعة
سورة الرحمن
القارئ: احمد خضر
❖┅━℘❦⇣❦℘━┅❖
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ⓮ ➤ከታቢዒዮች መካከል ታላቅ መሪ የሆኑት ፉዶይል -ረሂመሁሏህ- ጸጸት ከማድረጋቸው በፊት ግማሽ የሆነውን ህይዎታቸውን ያሳለፉት በዘረፋ ተግባር ወይም በሽፍትነት ነው፡፡አርባ አመት እስኪሞላቸው ድረስ የአካባቢው ህብረተሰብ በጣም ይሰጋቸው ነበር፡፡“ሲየር አዕላም አን’ኑበላእ” በተባለው ኪታብ ዘህብይ -ረሂመሁሏህ- የእርሳቸውን የጸጸት…
የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

የመጨረሻው ክፍል
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➛ይህን አስመልክቶ አንድ ሰው በቁርኣን ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ ኢብን አል'ቀይም - ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ህግና መርሆ አውስተዋል፡-

➧“በቁርኣን መጠቀም ከፈለግክ በምታነብና በምታደምጥ ጊዜ ልብህን ሰብስብ ፣ በእርሱ አላህ እንደሚያነጋግርህ አውቀህ ጀሮህን ስጥ፡፡” አል ፈዋኢድ፡ ገፅ 5

ይህ በቁርኣን ለመጠቀምና በእርሱም ለመፈወስ ታላቅና በጣም ጠቃሚ የሆነ መንገድ ነው፡፡ ተጠቃሚ ለመሆን የቁርኣን አንቀጽን ቆም ብሎ እያስተነተኑ ማንበብ እንጅ እርሱን እንደማይመለከተው ሁሉ አይቶ እንዳላየ ማለፍ ተገቢ አይደለም፡፡

በደንብ ያስተውል ፣ ያስተንትን በተፍሲር ኪታቦችና በእውቀት ባለቤቶች ንግግር
ይታገዝ፡፡ አንቀጹ ከልቡ ውስጥ ከደረሰና ከተመቻቸ መድሓኒትነቱ በአላህ ፈቃድ
ይረጋገጣል
፡፡ ይህም “ወሽፋኡን ሊማ ፊ ሱዱር” (በደረቶች ውስጥም ላለው
መድሓኒት)
የሚለው የአላህ ቃል ትርጉም ነው፡፡

የአላህን የተከበረ ንግግር ሳይገነዘቡና ሳያስተነትኑ በፍጥነት ማንበብ በዚህ ታላቅ የአላህ ኪታብ ሊገኝ የሚችለው መልካም ፍሬና ፋይዳ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡

በዚህ ጉዳይ መይሙን ብን ሚህራን -ረሂመሁሏህ- እንደተናገረው ተቃራኒ ከመሆን ይጠንቀቅ፡፡

እርሱ በዳይ ሆኖ በሚሰግድበት ሰዓት የሚከተለውን ቁርኣን በማንበብ ነፍሱን
ይራገማል

أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ

“ንቁ የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ይሁን”
አልአዕራፍ፡44 )) ተፍሲር ኢብኑ አቢ ሓቲም፡ 8484

ይህ ፣ ስለቁርኣን ንግግር ፣ ስለተሰጠው ደረጃ ፣ ስለሚያስገኘው ፍሬ ፣ ውጤቱ ፣ ስለኣዳቦቹ ፣ ከእርሱ ጋር ባሪያው ሊኖረው ስለሚገባው ስርዓት ያብራራንበት ነው፡፡

በጣም ሰፊ ከመሆኑ አኳያ በዚህ መጠን ካወሳን መልካም ጠቀሜታ - በአላህ ፈቃድ ይኖረዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

የተከበረውን ቁርኣን የልቦናችን ጨፌ ፣ የደረቶቻችን ብርሃን ፣ የሀዘናችን ፣ የሀሳባችን እና የጭንቀታችን መወገጃ እንዲያደርግልን ፣ በቁርኣን ተጠቃሚ ፣ የእርሱም ባለቤትና የአላህም ወዳጆች እንዲያደርገን ፤ ቁርኣንን ለእኛ መረጃ እንጅ በእኛ ላይ መረጃ እንዳያደርግብን ፣ እርሱ በሚወደው ሁኔታ ለማስተንተን ፣ በእርሱም ለመስራት እንዲገጥመን ፣ በዚህ ምድራዊ ዓለምም ይሁን በወዲያኛው ዓለም የመልካም ባለቤቶች እንዲያደርገን በመልካም ስሞቹ ፣ በከፍተኛ ባህሪያቶቹ ፣ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለው በመሆኑ የታላቁን ዓርሽ ባለቤት እማጸናለሁ።

ኪታቧ በዚህ ተጠናቀቀች አላህ በአወቅነው እውቀት ተጠቃሚዎች ያድርገን ጠቀሚ እውቀትን ይወፍቀን የአርሹ ጌታ ቁረአንን የልባችን ብረሀን ያድርግልን እያልኩኝ ትንሿ እህታችሁን መምከር ከስህተቷ ለማስተካከል ለምትፈልጉ ከታች ባለው አድራሻ ማሳወቅ ትችላላችሁ!
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
@Sunayenuhmerkbnat_bot

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
=
https://t.me/https_Asselefya1
سورة الكهف | بصوت القارئ الشيخ على عبد الرحمن الحذيفى
تذكيــــــــــــر

▪️ بـــ قراءة سورة الكهف.

عن أبي سَعيدٍ الخُدريِّ -رضي الله عنه- عنِ النبيِّ -صلَّى اللهُ عليه وسلَّم- أنَّه قال: "مَن قَرَأَ سورةَ الكَهفِ يومَ الجُمُعةِ أضاءَ له من النورِ ما بَينَ الجُمُعتينِ".

📘[صحيح الجامع (٦٤٧٠)].

▪️ والإكثار من الصلاة على النبي -ﷺ-

قالَ رسولُ اللَّه -ﷺ-: "إنَّ مِن أَفْضلِ أيَّامِكُمْ يَوْمَ الجُمُعةِ، فَأَكْثِرُوا عليَّ مِنَ الصلاةِ فِيهِ، فإنَّ صَلاتَكُمْ معْرُوضَةٌ علَيَّ فقالوا: يَا رسول اللَّه، وكَيْفَ تُعرضُ صلاتُنَا عليْكَ وقدْ أرَمْتَ؟ قال: يقولُ: بَلِيتَ، قالَ: إنَّ اللَّه حَرم عَلَى الأرْضِ أجْساد الأنْبِياءِ".

📘[رواهُ أَبُو داود بإسنادٍ صحيحِ].

وآخر ساعة من يوم الجمعة.

 عَن أبي هريرة -رضي الله عنه- أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ -ﷺ- ذَكَرَ يَوْمَ الجُمُعَةِ، فَقَالَ: "فِيه سَاعَةٌ لا يُوَافِقها عَبْدٌ مُسلِمٌ، وَهُو قَائِمٌ يُصَلِّي يسأَلُ اللَّه شَيْئًا، إِلاَّ أَعْطَاهُ إِيَّاه وَأَشَارَ بِيدِهِ يُقَلِّلُهَا".

📘[متفقٌ عليه].
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስከ መጨረሻው ተከታተሉት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

👉ቁርአንን አስተካክሎ በተጅዊድ ማንበብ ትልቅ ኒእማ ነው።

◾️እናታችን ኣኢሻ (رَضي اللَّه عنها) እንዳስተላለፈችው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

【يقول النبي ﷺ: الماهر في القرآن مع السفرة الكرام البررة، والذي يقرأ القرآن ويتتعتع فيه وهو عليه شاق له أجره مرتين】

 ➲ቁርአንን አሳምሮ የሚያነብና የሚጠባቀው የሆነ ሰው ከነዛ ከተከበሩ፣ ከላቁና ታዛዥ ከሆኑት መላኢካዎች ይሆናል። ያ እየተኮላተፈ፣ እየተቸገረና እየከበደው ቁርአንን ለሚቀራ ደሞ ሁለት አጅር አለው። በመቅራቱና በመቸገ‼️
📚 متفق عليه
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➳ክፍል ⓵⓶ ➧ይራባሉ፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (በአንድ አጋጣሚ እሳቸው፣ አቡበክር እና ኡመር (ረድየላሁ ዐንሁማ) ተርበው ነበር። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ ግን የሚመግብ እና የማይመገብ ነው። ➧ይተኛሉ፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (እንቅልፍ ወስዷቸው ፈጅር ሰላት አምልጧቸው ያውቃሉ።አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ…
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል ⓵

➭ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ደግሞ ጌታችንን አላህ እንዲህ ሲሉ ያወድሱታል፣ ይለምኑታል።

يَا حيُّ يَاقَيُومُ بِرَحمَتِكَ أَستَغِيثُ أَصلِح لِي شَأْنِي كُُلَّهُ ولا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طرْفَةَ عَيْنِِ

➧“ህያው የሆንከው፣ ፍጡራንህን የምታብቃቃው በራስህ የምትብቃቃው (አላህ) በእዝነትህ እርዳታን እለምንሃለሁ። ሁለመናዮን አሳምርልኝ። እኔን ለነፍሴ ለቅጽበት ታክልእንኳን አትተወኝ።”
[ሰሂህ አ-ተርጊብ ወተርሂብ፡ 661]

➳ሁሉም ጠፍተው የልቅና እና የክብር ባለቤት የሆነው አላህ እንደሚቀር እንዲህ ሲል ይነግረናል፡-


كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ ◉وَيَبْقَىٰ وَجْهُ رَبِّكَ ذُو الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ

“በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው። የልቅናና የልግሥና ባለቤትየሆነው የጌታህ ፊትም ይቀራል።” [
አርረሕማን፡ 26-27]

ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ሁሉም ፍጡራን ሞተው አላህ ብቻውን እንደሚቀር እና “እነዚያ አምባ ገነኖች እነዚያ ኩራተኞች የት አሉ?” እንደሚል ነግረውናል። [ሙስሊም፡ 2788]

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ስለዚህ አምልኮ የሚገባው ህያው ለሆነው አላህ እንጂ ለሞቱት ወይም ለሚሞቱት ኢሳ ዐለይሂ-ስሰላም ወይንም ለሞቱት ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم(፣ መርየም፣ ፋጢማ (ረድየላሁ አንሃ)፣ አልይ (ረድየላሁ አንሁ)፣ ሁሴን (ረድየላሁ
አንሁ) እና መሰሎቻቸው አይደለም። እነዚህን ታላላቅ የአላህ ባሪያዎች የጠቀስኩት ለምሳሌነት ነው። እነሱን ከአላህ ውጭ ማምለክ ካልተቻለ፣ ሌሎቹንማ ይበልጥ አይቻልም
። አንድ አንቀፅ ልጨምር:-

وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا

“በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ። ከማመስገንም ጋር አጥራው። በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂነት በእርሱ በቃ።”
[አል ፉርቃን፡ 58]

➧በየትኛውም ዘመን ከአላህ ውጭ የሚመለኩት ሁሉ ይህንን የሚያሟሉ አይደሉም። ሁሉም የአላህ ፍጡሮችናቸው፣ ሁሉም ሟቾች ናቸው፣ ሁሉም ጠፍተው የልቅናና የልግሥና ባለቤት የሆነው የጌታ አላህ ፊት ይቀራል።

አላህ የሚመግብ እና የማይመገብ ነው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አምልኮ የሚገባው ሁሉን መጋቢ ለሆነው ፈጣሪ እንጂ ለተመጋቢ ፍጡራን አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል፡

قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ ۗ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው፡፡ «እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን (ተብያለሁ)» በላቸው፡፡ አል አንዓም 14

ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ያነበበ ተጠቀመ!!

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ የመልእክተኛች እውነተኝነት
☑️ ሳሂር፣ ጠንቋይ፣ ኮከብ ቆጣሪ

ክፍል ①⑥


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ይችን አያ የሚያስተነትን አዕምሮ ያለው ሰው እንደት አላህን ያመፃል?


كَيْفَ تَكْفُرُونَ بِاللَّهِ وَكُنتُمْ أَمْوَاتًا فَأَحْيَاكُمْ ۖ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

ሙታን የነበራችሁ ስትኾኑ ሕያው ያደረጋችሁ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ሲኾን ከዚያም ወደርሱ የምትመለሱ ስትኾኑ በአላህ እንዴት ትክዳለችሁ!

➛አላህ ባማረውና ውብ በሆነው ቃሉ ልባችንን ያርጥብልን! የእኛ ነገር ያሳዝናል
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➳ክፍል ⓵⓶ ➧ይራባሉ፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (በአንድ አጋጣሚ እሳቸው፣ አቡበክር እና ኡመር (ረድየላሁ ዐንሁማ) ተርበው ነበር። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ ግን የሚመግብ እና የማይመገብ ነው። ➧ይተኛሉ፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (እንቅልፍ ወስዷቸው ፈጅር ሰላት አምልጧቸው ያውቃሉ።አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ…
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል ⓵

ፈጣሪ እና ፍጡሮቹ
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

የሁሉ ጌታ፣ ብቸኛው ፈጣሪ አንድ አምላክ አላህ ብቻ ነው። አላህ ከእርሱ ውጭ ያሉትን ሁሉ የፈጠረ የአለማቱ ሁሉ ጌታ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ الفاتحة: ٢

“ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለሆነው።” [አልፋቲሐህ፡ 2]

የሰው ልጅ ፈጣሪውን ትቶ ልክ እንደሱ ፍጡር የሆኑትን ቢያመልክ የኪሳራዎች
ሁሉ ከባድ ኪሳራ ውስጥ ወድቋል።

ያለመውንም ሳያገኝ ከጌታውም ጋር ተጣልቷል።ምክንያቱም ፍጡራን ከላይ እስከ ታች ሁሉም ከአላህ ከጃዮች ናቸውና። ደግሞም ደረጃቸው ቢለያይም ሁሉም የፍጡር ድንበርን የማይሻገሩ ባርያዎች ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፡


أَمْ خُلِقُوا مِنْ غَيْرِ شَيْءٍ أَمْ هُمُ الْخَالِقُونَ

ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን? አጥጡር 35


إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

➧“እነዚያ ከአላህሌላ የምትገዟቸው (እነሱም) ብጤዎቻችሁ ተገዢዎች (ባሪያዎች) ናቸው።እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ፤ (መመለስ ግን
አይችሉም)።”
[አልአዕራፍ፡ 194]

ጂብሪል (ዐለይሂ-ስሰላም) የመላእክቶች አለቃ ነው። ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ደግሞ የነብያት ሁሉ ኢማም ናቸው። ሁለት የፍጡራን ቁንጮዎች። ከመሆኑም ጋር ነብዩ(صلى الله عليه وسلم (ጂብሪል “ምን ነው እንደበፊቱ ቶሎ ቶሎ አትመጣም?” ብለው ሲጠይቁት እንዲህ ነበር ያለው


وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا

(ጂብሪል አለ) «በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም
፡፡መርየም 64

➧ተመልከቱ እንግዲህ የመለእክቶች አለቃ ጂብሪል ካለበት ቦታ ያለ አላህ ፍቃድመንቀሳቀስ አይችልም።

ህያው የማይሞት አላህ እና ሙታን ፍጡሮቹ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➫➫➫➫➫➫➫

አላህ ከምንም በፊት መጀመሪያ የነበረ ነው። ሁሉም ሞተው ብቻንም ቀሪ ነው።
ነብዩን (صلى الله عليه وسلم (የየመን ሰዎች “እንዴት ይሁ ሁሉ ነገር ጀመረ?” ብለው ጠየቁ። ነብዩም(صلى الله عليه وسلم (እንዲህ አሉ፡- “መጀመሪያ አላህ ነበር። ከእርሱም ጋር ምንም ነገር አልነበረም።


አርሹም ውሃው ላይ ነበር። ከዚያም ሰማያትእና ምድሮችን ፈጠረ።” ቡኻሪ ዘግበውታል

እንግዲህ አላህ ስለ እራሱ እንዲህ ሲል ይነግረናል

اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ۚ

“አላህ ከእርሱበቀር ሌላ አምላክ የለም። ሕያው ራሱን ቻይ ነው።” [
አልበቀራህ፡ 255]



ኢንሻአላህ ይቀጥላል......

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

https://t.me/https_Asselefya1
أذكار الصباح كاملة بصوت العفاسي بدقة عالية (2020) جديد
🌹اذكار الصباح🌹

🌸የጧት ዚክር🌸

አስጊና አሰቃቂ አስፈሪ ጨለማ
መብራት የሌለበት ቲንሸየ ሻማ
ማይነጋ መሳይ የሀሳብ ቀጠሮ
በመከጀል ተስፋ ነገን ዛሬ ቋጥሮ
መንጋቱን ታያለክ ባሳብ ተወጥሮ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

ክፍል ①⑦


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ⓵⓷ ➭ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ደግሞ ጌታችንን አላህ እንዲህ ሲሉ ያወድሱታል፣ ይለምኑታል። يَا حيُّ يَاقَيُومُ بِرَحمَتِكَ أَستَغِيثُ أَصلِح لِي شَأْنِي كُُلَّهُ ولا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طرْفَةَ عَيْنِِ ➧“ህያው የሆንከው፣ ፍጡራንህን የምታብቃቃው በራስህ የምትብቃቃው (አላህ)…
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል አስራ አምስት

قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ ۗ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው፡፡ «እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን (ተብያለሁ)» በላቸው፡፡ (አል:አንዓም 14)

እነሱ “መቃረቢያ” ሲሉት፣ አላህ ሺርክ ሲል ጠራው።

የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَالَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ مَا نَعْبُدُهُمْ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَا إِلَى اللَّهِ زُلْفَىٰ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ فِي مَا هُمْ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي مَنْ هُوَ كَاذِبٌ كَفَّارٌ

እነዚያም ከእርሱ ሌላ ረዳቶች የያዙት “ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም” (ይላሉ)።” [አዝዙመር፡ 3]
ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን አላህ ከክፉ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ፡-

ሺርክን ለመስራት አላሰቡም ነበር። አላማቸውም አልነበረም። እነሱ አምልኮን ማሟያ ለመፈጸም እና በዚህም ወደ አላህ ለመቃረብን ብቻ ነበር ያሰቡት። ሸይጧን የአደም ልጆችን ለማሳሳት እንዴት እንደሚቀርባቸው እና ከሰው ሰይጣናት ውስጥ የሆኑት የአደም ልጆችን እንዴት ይህንን (የሺርክ) ተግባር አሳምረው እንደሚያቀርቡላቸው ተመልከት።

እኛም እንላቸዋለን፡- ጣኦቶቹን በቀጥታ ላታመልኩ ትችላላችሁ። ነገር ግን ጻድቃንን በናንተ እና በአላህ መካከል (ድልድይ) አድርጋችኋል። ይህም ቢሆን አላህ ዘንድ ሺርክ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ ۚ قُلْ أَتُنَبِّئُونَ اللَّهَ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ። “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። “አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን?” በላቸው። ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም።” [ዩኑስ፡ 18]

ተመልከቱ አላህ “አላህ ከሁሉም ጠራ፤ ላቀም” ሲል ከነሱ እና ከተግባራቸው እራሱን ነጻ እንዳደረገ። “ከሚያጋሩት” ሲል ደግሞ ተግባራቸውን ሺርክ ብሎ እየጠራው ነው።የሸይኽ ፈውዛን ንግግር እዚህ ላይ አበቃ።
ዛሬ ሺርክ የሚፈጽሙ ሰዎች ይህንኑ ነው ማማካኛ አድርገው የሚወስዱት። ተመሳሳይ ጥፋት። ተመሳሳይ ማመካኛ።
የአላህ ወልይ ማን ነው?

ወልይነት (ወዳጅነት ረዳትነት)፡- የጠላትነት ተቃራኒ ነው። የወልይነት መሰረቱ መውደድ እና መቃረብ ነው።

የጠላትነት መሰረቱ መጥላት እና መራቅ ነው። “ዊላያ” በሙያዊ ፍቺው አንድ ባርያ አላህን በመታዘዙ አላህ ያን ባርያ መቅረቡ ነው። ወልይነት ኢማን እና አላህን መፍራት የተባሉትን ሁለት መስፈርቶች ይጠይቃልአላህ አንዲህ ይላል፡-

أَلَا إِنَّ أَوْلِيَاءَ اللَّهِ لَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
الَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ


ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም። (እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው።” [ዩኑስ፡ 62-63]


➩ስለዚህ አንድ ሰው በአላህ አምኖ አላህን እስከፈራ ድረስ ወልይ ነው። በመስፈርቱ መሰረትም፡-
አባት፡- በአላህ አምኖና እሱን ፈርቶ በስሩ የሚተዳደሩትን ቤተሰቦች በአግባቡ ከያዘ ይህ የአላህ ወልይ ነው።

ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ያነበበ ተጠቀመ!!

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1