💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
الوقوع_فريسة_للآخرين_من_أسباب
<unknown>
ينبغي على الزوجين أن يملئ البيت بالعاطفة والمحبة

#مقطع صوتي
للشيخ سليمان الرحيلي وفقه الله


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➽የተዘረጋው የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አስር ➲ቁርኣንን በፍጥነት አንብቦ ከመጨረስ ነፍስህን በእርሷ የምትፈውስበት ፣ አስተንትነህ ትርጉሟን በደንብ ተገንዝበህ የምታነባት አንዲት አንቀጽ በላጭና በጣም ጠቃሚ ናት፡፡ለዚህ ነው ሰለፎቹ ወይም ቀደምት ደጋጎች በአንዲት አንቀጽ ቆመው ሌሊቱን የሚያነጉት፡፡ ነብዩ صلى الله عليه وسلم በሚከተለው አንድ አንቀጽ ቆመው ሌሊቱን…
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➳ክፍል ⓫

➤አንተ ቁርኣንን ታነባለህ ነገር ግን በትዕዛዞች፣በክልከላዎች በማስጠንቀቂያዎች፣ በተግሳጾች እና ማስታወሻዎች እንዲሁ ዝም ብለህ ታልፋለህ፡፡ ታዲያ ከቁርኣን ለአንተ ያለህ ድርሻ ወይም እጣ ምን ይሆን?
ኢብን መስዑድ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"إذا سمعت الله يقول: "يأيها الذين ءامنوا" فأرعها سمعك ، فإنه إما خير يأمر به أو شر ينهى عنه"

➧አላህ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ!” በማለት ሲጣራ ከሰማህ ጀሮህን ሰጠህ በደንብ አድምጥ፡፡ አንድም መልካም ሊያዝህ ነው ወይም መጥፎ ከሆነው ነገር ሊከለክልህ ነው፡፡” ተፍሲር ኢብኑ አቢ ሓቲም፡1/196

➭ነገር ግን ልክ ንግግሩ ለሌላ ሰው እንደሆነ ጀሮህን ሰጠህ የማታዳምጥ ወይም ነገሩ እንደማይመለከትህ ዝም ብለህ የምታልፍ ከሆነ ከቁርኣን እንዴት ልትጠቀም ትችላለህ? የቁርኣን አሻራ በአንተ ላይ እንዴት ሊያርፍ ይችላል?
ስለዚህ አንድ ሙስሊም ነፍሱን ሊታገል ፣ የተከበረውን ቁርኣን ለመቅራት ከላይ
የተጠቀሱትን ሶስት መስፈርቶች ተግባራዊ ሊያደርግ ይገባል፡፡

➧እነዚህን ሶስት መስፈርቶች በቀላሉ እንዲገነዘብ አላህ ቁርኣንን ገርና ቀላል
አድርጎታል፡፡


وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን? አል ቀመር 17

➲ኢብን አል'ቀይም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"يسره للذكر ، ويسر ألفاظه للحفظ ، ومعانيه للفهم ، وأوامره ونواهيه للامتثال"

➽“ቁርኣንን ለማስታወስ ገር አደረገው ፣ በቃል ለመሸምደድ ቃላቶችን ገር አደረጋቸው፣ ትርጉማቸውን ለመገንዘብ ገር አደረገው ፤ ለመተግበር ያመች ዘንድ ትዕዛዝን እና ክልከላን ገር አደረጋቸው፡፡”
ሙኽተሶሩ ሰዋዒቅ አል ሙርሰላ፡ ገፅ 40

➠ይህ ቁርኣን ለደረቶች ፈውስ እንደሆነ በሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ግልጽ አደረገ፡፡

وَنُنَزِّلُ مِنَ الْقُرْآنِ مَا هُوَ شِفَاءٌ وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ ۙ وَلَا يَزِيدُ الظَّالِمِينَ إِلَّا خَسَارًا

ከቁርኣንም ለምእመናን መድኀኒትና እዝነት የኾነን እናወርዳለን፡፡ በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸውም፡፡
አል ኢስራዕ 82


هُوَ لِلَّذِينَ آمَنُوا هُدًى وَشِفَاءٌ ۖ
“እርሱ (ቁርኣን) ለእነዚያ ለአመኑት መምሪያና መፈወሻ ነው፡፡” ፉሲለት፡44

وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى

“(ቁርኣን) በደረቶች ውስጥ ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድሓኒት (ሲሆን በእርግጥ መጣላችሁ)” ዩኑስ፡57

➧ቀታዳህ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"إن القرآن يدلكم على دائكم ودوائكم ، أما داؤكم فذنوبكم ، وأما دواؤكم فالاستغفار"

➤“ቁርኣን በሽታችሁንም መድሓኒታችሁንም ይጠቁማል፡፡ በሽታችሁ ወንጀሎቻችሁ ናቸው፡፡ መድሓኒታችሁ ደግሞ ኢስቲግፋት (አላህን ይቅርታ መጠየቅ) ነው፡፡” በይሓቂይ ሹዓብ አል ኢማን፡ አስበሃኒ አት ተርጊብ ወት ተርሂብ 221

➢ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉✍

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ የተህሪፍ ትርጉምና አይነት
☑️ የአህባሾችና የየሁዶች መመሳሰል

➰ክፍል ①①➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➳ክፍል ⓫ ➤አንተ ቁርኣንን ታነባለህ ነገር ግን በትዕዛዞች፣በክልከላዎች በማስጠንቀቂያዎች፣ በተግሳጾች እና ማስታወሻዎች እንዲሁ ዝም ብለህ ታልፋለህ፡፡ ታዲያ ከቁርኣን ለአንተ ያለህ ድርሻ ወይም እጣ ምን ይሆን? ኢብን መስዑድ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግረዋል፡- "إذا سمعت الله يقول: "يأيها الذين ءامنوا" فأرعها…
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል ⓬

➭ልቦናን የሚያጠቁ በሽታዎች በርካታ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሁሉም የልቦና በሽታዎች ወደሁለት አይነት መጠቃለል ይችላሉ፡፡ አንደኛው የበሽታ ዓይነት ስሜትን ከመከተል የሚመጣ በሽታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በማህይምነት ምክንያት የሚመጣ የብዥታ በሽታ ነው፡፡ ለሁለቱም በሽታዎች ፍቱን መድሓኒት የተከበረው ቁርኣን ነው፡፡

➳ቁርኣን በውስጡ ለልቦችና ለደረቶች መድሓኒት አለው፡፡ ነገር ግን ፈውሱና መድሓኒቱ መቼ? እና እንዴት ነው የሚገኘው? በቁርኣን አማካኝነት ልቦና ፈውስ ማግኘት ይችላልን? ቁርኣንን አስመልክቶ የግለሰቦች ተጨባጭ ሁኔታ ከአንገት በላይ የዘለለ አይደለም፡፡ ልቡ ከእርሱ ተከልክሎ አንደበቱ ብቻ በእርሱ ይንቀሳቀሳል፡፡ ነገሩ ሲታይ በጣም የተራራቀ ነው፡፡ ቁርኣኑ ወደልቡ ሰርጾ ሊገባ ይገባል፡፡ በቁርኣን አንቀጾችና በትርጉሙ ልቦናው ሊንቀሳቀስ ግድ ይላል፡፡

➢በቁርኣን መልእክቶችና በውስጥ ባቀፈው ተግሳጽ እና ማስታዎሻዎች ልብ መንፈራገጥ አለበት፡፡በሽታዎቹና ቫይረሶቹ ሊወገዱና ሊጸዱ ዘንድ ልብ በእርሱ ሕያው መሆን አለበት፡፡የቁርኣን አንቀጹ ልብ ላይ በትክክል ካረፈ አስደናቂ የሆነ አሻራ ጥሎ ይሄዳል፡፡

➽ቡኻሪ በዘገቡት ጁበይር ብን ሙጥዒም ረድየሏሁ አንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ነብዩ صلى الله عليه وسلم በመግሪብ ሶላት ወጥ’ጡሪን ሲቀሩ ሰማሁ፡፡ ከሚከተለው አንቀጽ ላይ ሲደርሱ ልቤ ልትበር ቀረበች፡፡”

أَمْ خُلِقُوا مِنْ غَيْرِ شَيْءٍ أَمْ هُمُ الْخَالِقُونَ ◍أَمْ خَلَقُوا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ ۚ بَل لَّا يُوقِنُونَ◍أَمْ عِندَهُمْ خَزَائِنُ رَبِّكَ أَمْ هُمُ الْمُصَيْطِرُونَ
➧“ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን?
ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም፡፡ ወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?ወይስ እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን?
” ጡር 35_37 ቡኻሪ፡4854

➧እንደበሽታው መጠን በእርሱ ሊፈወሱበት ይገባል፡፡ ከአንድ ሰው ዘንድ ፍርሀቶች እና ብዥታዎች ካሉበት “ሌሊት ሌሊት እደነግጣለሁ ወይም እፈራለሁ ካለ” የሚከተለውን የአላህ ቃል አስተንትኖና ደጋግሞ በመቅራት ነፍሱን በቀላሉ መፈወስ ይችላል፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል

إِنَّمَا ذَٰلِكُمُ الشَّيْطَانُ يُخَوِّفُ أَوْلِيَاءَهُ فَلَا تَخَافُوهُمْ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

እንዲህ የሚላችሁ ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል፡፡ አትፍሩዋቸውም፡፡ ምእምናንም እንደኾናችሁ ፍሩኝ፡፡አል ኢምራን 175

➧ሰይጣን የጣለበት ፍርሀት ከልቦናው እስኪወገድ ድረስ ይህን አንቀጽ ደጋግሞ ይቅራ፡፡ ነፍሱ በአላህ ላይ እንዳትመካ ድክመት የሚሰማት ከሆነ የሚከተሉትን የአላህ አንቀጾች በማስተንተን ደጋግሞ ይቅራ፡፡

وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ ۚ
“በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡” አጥ ጦላቅ፡3

وَعَلَى اللَّهِ فَتَوَكَّلُوا إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
“ምእመናንም (አማኞችም) እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ተመኩ” አል ማኢዳህ፡23

ኢንሻአላህ ይቀጥላል✍◉◉◉◉◉◉

➤አንብብ!! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➳ ክፍል ስምንት ➲ዐብዱረሕማን ኢብን ዘይድ ኢብን አስለም ደግሞ “በአላህ ላይ አንድም የሚያጋራ የለም አላህ ጌታው፣ አላህ ፈጣሪው እና ሲሳይ ሰጪው መሆኑን እያወቀ እና እያመነ ቢሆን እንጂ። ኢብራሂም ምን እንዳሉ አታይምን وَاجْعَلْنِي مِن وَرَثَةِ جَنَّةِ النَّعِيمِ◆وَاغْفِرْ لِأَبِي إِنَّهُ كَانَ مِنَ الضَّالِّينَ◆وَلَا…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ዘጠኝ

وَأَنَّ ٱلْمَسَٰجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدًۭا

እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡

➧በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ይህ አንቀጽ አምልኮ ለአላህ ብቻና ብቻ እንደሚገባ ከሚያመለክቱ ዋና ዋና አንቀጾች ውስጥ አንዱ ነው።አንቀጹ ላይ መስጅድ ለተባለው ከተሰጡት ትርጉምች ውስጥ በጥቂቱ

➳ሰባቱ የሱጁድ አካላት (ፊት፣ ሁለት እጆች፣ሁለቱ ጉልበቶች፣እና ሁለቱ እግሮች )ማለት ተፈልጎበት ነው ተብሏል።

➳በአላህ ቤቶች ወይንም መስጅዶች ሽርክ አትፈጽሙባቸው።ልብ ሊባል የሚገባው የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም ሽርክን በሁለም አይነቱ ነው ።የተዋጉት!

➲ወንድሜ ሙሀመድ አህመድ ኢብኑ መነወር የሽርክ ቡላና ዳልቻ የለውም፣ብሏል!!

➧በብቸኛው ፈጣሪ አላህ ጅብሪልም፣ሚካኢልም፣ኢሳም፣መርየምንም፣ነብዩመሀመድም ፣አልይም፣ ሁሴንም፣ጸሀይም ፣ጨረቃ፣ጅንም ፣ሚታይም፣ማይታይም ፣ባጠቃላይ ፍጡራን ቢመለክ ሽርክ ነው። ማንኛውም ፍጡር ማምለክ ሽርክ ነው።

➲ለአላህ ብቻ የሚገባውን አምልኮ ከአላህ ውጭ ላለ ለማንም አካል የሰጠ አጋሪ ነው።

➲በአላህ ላይ እያጋሩ የተሰራ ስራ ተቀባይነት የለውም። ጭራሽ ሌሎች በአላህ ላይ ሳያጋሩ የተሰሩ ስራዎችን ሁሉ ድምጥማጤቸውን ያጠፋል።


➲በአላህ ላይ እያጋራ የሞተሰው መኖሪያው ጀሀነም ነው።ለበደለኞች ምንም ረዳት የላቸውም ።አላህ ከሽርክ ይጠብቀን።

➲ ነብያዊ መልእክት ወደ የመን
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ነብዩ (صلى الله عليه وسلم ባልደረባዎቻቸውን መልእክትን አስይዘው ወደ ተለያዩ ህዝቦች ይልኳቸው ነበር። ከላኳቸው ባልደረባዎች ውስጥ የዚህ ኡማ ሃላል እና ሀራሙን የሚያውቅ የተባለላቸው ሙዓዝ ኢብን ጀበል (ረድየላሁ አንሁ) አንዱ ናቸው።

➧የአላህመልክተኛ (صلى الله عليه وسلم (ሙአዝን ወደ የመን ሲልኳቸው እንዲህ ነበር ያሏቸው፡

◆ إِنَّكَ تَقدَمُ عَلى قَومِِ مِن أَهلِ الكِتَابِ فَليَكُن أَوَّلَ ماتَدعُوهُم إِلَى أَن يُوَحِّدُوا اللّٰهَ تَعَالَى فَإِذَا عَرَفُوا ذَلِكَ فَأَخبِرهُم أَنَّ اللَّهَ فَرَضَ عَلَيهِم خَهسَ صَلَوَاتِِ فِي يَومِهِم وَلَيلَتِهِم فَإِذَا صَلُّوا فَأَخبِرهُم أَنَّ اللَّهَ افتَرَضَ عَلَيهِم زَكَاةً فِي أَموَالِهِم تُؤخَذُ مِن غَنِيِّهِم فَتُرَدُّ عَلَى فَقِيرِهِم......

➤“አንተ ከመፅሐፉ ባለቤቶች የሆኑ ሰዎች ዘንድ ትሄዳለህ። የመጀመሪያ የምትጠራቸውአላህን በብቸኝነት እንዲያመልኩ ነው። ይህንን ካወቁ በሌሊትና በቀናቸው ውስጥ አላህ አምስት ሶላቶችን እንደደነገገባቸው ንገራቸው። ከሰገዱ ከሃብታሞቻቸው ላይ ተወስዶለድሆቻቸው የሚሰጥ ሰደቃ (ዘካን) አላህ ግዴታ እንዳደረገባቸው ንገራቸው።…” [ቡኻሪ፡1458፣ ሙስሊም፡ 19]

➭ከዚህ ሐዲሥ እንደምንረዳው አህለል ኪታቦች ተውራት እና ኢንጂል የወረደላቸው “የመጸሀፍቱ ባለቤቶች” ተብለው ቢጠሩም የተውራት እና የኢንጂል ዋና መልክት የሆነውን ተውሒድ በሺርክ እና በኩፍር ስለ ለወጡት አላህ መልክተኛውን(صلى الله عليه وسلم (ልኮ ወደ ሁሉ ነብያት መንገድ እንዲመለሱ ጥሪ እንዲደረግላቸው አዘዘ። ለዚያም ነው ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ሙዓዝን ወደ መጸሀፍቱ ባለቤቶች የላኩት።

➛ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉✍

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰ

📖አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ዘጠኝ وَأَنَّ ٱلْمَسَٰجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدًۭا እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ ➧በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ይህ አንቀጽ አምልኮ ለአላህ ብቻና ብቻ እንደሚገባ ከሚያመለክቱ ዋና ዋና አንቀጾች ውስጥ አንዱ ነው።አንቀጹ ላይ መስጅድ ለተባለው ከተሰጡት ትርጉምች ውስጥ በጥቂቱ ➳ሰባቱ…
➧መንዙማ
➬➬➬➬➬

እውነታው፡አደጋዎቹና መዘዞቹ

➧ክፍል አስር

➤ከዚህ ሐዲሥ እንደምንረዳው አህለል ኪታቦች ተውራት እና ኢንጂል
የወረደላቸው “የመጸሀፍቱ ባለቤቶች” ተብለው ቢጠሩም የተውራት እና የኢንጂል ዋና መልክት የሆነውን ተውሒድ በሺርክ እና በኩፍር ስለ ለወጡት አላህ መልክተኛውን (صلى الله عليه وسلم (ልኮ ወደ ሁሉ ነብዩ መንገድ እንዲመለሱ ጥሪ እንዲደረግላቸው አዘዘ።

➧ለዚያም ነው ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ሙዓዝን ወደ መጸሀፍቱ ባለቤቶች የላኩት። ዛሬም አለም ላይ አላህ ካዘነላቸው ውጭ አብዛኛው ሰው እራሱን ሙስሊም ነኝ እያለም፣ ቁርኣን እና ሀዲስ እንደሚከተል እያስተጋባም፣ የነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ተከታይ ነኝ እያለም፣ ቁርኣን እና ሀዲስ የእስልምና ምንጮች እንደሆኑ እያመነም፣ ትክክለኛውን የነብያት መንገድ ተቃርኖ የሺርክ አምልኮ ውስጥ ገብቷል።

➲በዚህ ሀዲስ መሰረት ከምንም ነገር በፊት እምነትን የማስተካከል ነገር ይቀደማል። ወደ አላህ መንገድ እንጣራለን የሚሉ ሁላ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ለሙኣዝ የሰጡትን ትእዛዝ፣ ሙአዝ በተግባር ያሳዩትን መንገድ ተቀብሎ ወደ ተውሒድ ጥሪ ከምንም በፊት ሊያደርግ ይገባዋል።


➳እምነቱ ያልተስተካከለ ሰው የሰራውን ያህል ቢሰራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት
የለውም።
ለዚህም ማስረጃው ኢማሙ ሙስሊም የዘገቡት ታሪክ ነው። የሆኑ ሰዎች ከበስራ (ኢራቅ) አካባቢ ለሀጅ መጡ። ሶሐባው ዐብደላህ ኢብን ዑመርን (ረድየላሁ ዐንሁማ) አገኙ። ከዚያም በአካባቢያቸው ቀደርን (የአላህን ውሳኔ) የሚያስተባብሉ ሰዎች እንዳሉ ነገሯቸው።

➧በዚህን ጊዜ ኢብኑ ዑመር “ንገሯቸው እኔም ከነሱ አይደለሁም፣ እነሱም ከእኔ አይሉም። በቀደር እስከሚምኑ ድረስ በአላህ መንገድ ላይ የኡሁድ ተራራን የሚያክል ወርቅ ቢሰጡ አላህ አይቀበላቸውም” በማለት መለሱላቸው።

➲ይህ ታሪክ የሚያስረዳን እምነት ሳይስተካከል የተሰራ ስራ የኡሁድ ተራራን የሚያክል ወርቅ በአላህ መንገድ ላይ ቢለግሱ እንኳን ተቀባይነት እንደሌለው ነው። ለዚህም ነው ከምንም በፊት እምነትን፣ አቂዳን፣ ተውሒድን ማስተካከል ግድ የሆነበት
ምክንያት። መልካምን ነገር ሌላ መልካም ነገር ይበልጠዋል።


➳የመልካም ነገሮች ሁሉ ቁንጮ
ተውሒድ እምነትን ማስተካከል ስለሆነ የመጀመሪያው ጥሪ የተደረገው በዚህ ጉዳይ ላይ ነው።
ከዚያም ነብዩ (صلى الله عليه وسلم” (ይሄን እሺ ካሉህ” በማለት ወደ ሁለተኛው መልካም ትእዛዝ
ጠቆሙ። መልካም ስራዎች ሁሉ የሚገነቡት ተውሒድ የሚባለው ታላቁ መሰረት ሲስተካከል ነው::



➧ለዚያም ነው “የመጀመሪያ የምትጠራቸው ከአላህ በስተቀር (እውነተኛ) አምላክ እንደሌለ እና እኔም የአላህ መልክተኛ መሆኔን እንዲመሰክሩ” በሌላ ዘገባ “አላህን በብቸኝነት በአምልኮ እስኪነጥሉት ድረስ” የሚል ነብያዊ ተእዛዝ ለሙአዝ የተላለፈው። እሱም እንደታዘዘው የፈጸመው።

✍ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል◉◉◉◉

📚መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል{ሀፊዘሁሏህ} የተወሰደ

📖አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል።

➤ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ ተእጢል፣ ተሽቢህና ተምሲል
☑️ አህባሾችና ተሽቢህ
☑️ የአላህ መገለጫ በተመለከተ
መርሆ

➰ክፍል ①②➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲የሰዎች ውዴታና ጥላቻ ከሀቅ እንዳያዘነብልህ!!
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

◾️قَال العلاَّمة صَالِح الفُوزَان حفِظهُ اللّٰه:
➭ሸሕ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ብለዋል።

【 «تَمسَّك بِدِينك وَلو ضَلَّ أكثَرُ النَّاس ولَو أصبَحتَ غَريبًا بَين النَّاس، اصبِر علىٰ هَذا مَا دام أنَّك علىٰ الحقِّ لا يَهمُّك أن تُرضي فَلانًا أو تُغضِب فُلانًا لا عَليْك»】
✅
አብዘሀኛው ሰው ቢጠም (ከሀቅ ቢዘነበል) ወይም ብቸኛ ተደርገህ በሰዎች መሀከል እንግዳ ብትደረግም እንኳ ዲንህን አጥብቀህ ያዝ። በሀቅ ላይ እስካለህ ድረስ በዛው ላይ ታገስ (ፅና)። ይህም በማድረግህ እገሌ ይወድልኛል ወይም ይጠላኛል ብለህ አትጨነቅ። የፈለገው ቢወድ የፈለገው ቢጠላ አንተ ምን ነገር የለብህም።
📚شَرح كِتَاب الفِتَن والحَوادِث (ص١٩٢)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ዘጠኝ وَأَنَّ ٱلْمَسَٰجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدًۭا እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ ➧በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ይህ አንቀጽ አምልኮ ለአላህ ብቻና ብቻ እንደሚገባ ከሚያመለክቱ ዋና ዋና አንቀጾች ውስጥ አንዱ ነው።አንቀጹ ላይ መስጅድ ለተባለው ከተሰጡት ትርጉምች ውስጥ በጥቂቱ ➳ሰባቱ…
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ⓭

➽ባዕድ ሴቶችን በመመልከት የተፈተነ ወይም በሴቶች ፈተና ቅዥት ውስጥ የገባ ሰው የሚከተለውን የአላህ ቃል ከልቡ እስኪሰርጽ ድረስ በደንብ አስተንትኖ ያንብብ፡፡

قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ

“ለምእመናንም ንገራቸው ፡-ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤
ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው ፤ አላህ በሚሰሩት ሁሉ
ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡
” አን ኑር፡30

➛ወላጆቹን በድሎ ወይም ሐቃቸውን አጓድሎ ከሆነ አሁንም በደንብ ትርጉሙን
በማስተንተንና ከልቡ ውስጥ ሰርጾ እስኪገባ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ ደጋግሞ ያንብብ፡


۞ وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا ۚ إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِندَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا ◍وَاخْفِضْ لَهُمَا جَنَاحَ الذُّلِّ مِنَ الرَّحْمَةِ وَقُل رَّبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا

➧“ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ በወላጆቻችሁም
መልካምን ስሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን
ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው፡፡አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው፡፡ ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፡፡“ጌታዬ ሆይ! በህጻንነቴ (በርህራሄ) እንዳሳደጉኝ እዘንላቸውም” በል
፡፡”አል ኢስራእ፡23_24

➲ድክመት ከነፍሱ ውስጥ ከተገኘ ኢማን የሚጨምሩ የቁርኣን አንቀጾችን ደጋግሞ
በማንበብ ፈውስ ያግኝ፡፡ አንቀጾቹ ልብ ውስጥ መስረጻቸውን ያረጋግጥ፡፡ ልቡ ውስጥ ተመቻችተው እንዲቀመጡ ከፍተኛ ጥረት ያድርግ፡፡ አንቀፁዋ ልቡ ውስጥ ሰርጻ ከደረሰች ፈውስ ያገኛል ፣ በአላህ ፈቃድ ምንዳው ይረጋገጣል፡፡

➧ የሁሉ ችግር ቁርኣን ወደልቦና ሰርጾ አለመግባቱ ነው፡፡ አንቀጹ ከልብ ከደረሰ ማንም ይሁን ማን በሽታው በቀላሉ ይወገዳል፡፡ በሽታው በአላህ ክህደት ከሆነ መድሓኒቱ ወደኢስላም ተጸጽቶ
መመለስ ነው፡፡ በሽታው ኒፋቅ ከሆነ ፈውሱ ወደኢማን መዞር ነው፡፡
በሽታው የአመጽ፣ የወንጀል ፣ የሐጢያት ከሆነ ደግሞ መድሓኒቱ በዲን ላይ ቀጥ ማለት ፣ ወደቅኑ ጎዳና ተመልሶ አላህን በብቸኛነት ማምለክ ነው፡፡

➽ቁርኣንን በማስተንተን ከልብ በማድመጥና በእርሱም በመስራታቸው ምክንያት ከህመማቸው ፈውስ ያገኙ ሰዎችን ቁጥር አላህ እንጅ ማንም ቆጥሮ አይዘልቀውም፡፡እንዲህ አይነት ሰዎች ታሪካቸው ሲወራ በጣም ትንግርት ነው፡፡ ከሰዎች በርካታዎቹ ወደቅኑ መንገድ የተመሩት አንዲትን አንቀጽ አድምጠው ከልባቸው ውስጥ ሰርጾ እስኪገባ ደጋግመው በመቅራታቸው እና ለእርሷ ታላቅ ቦታ በመስጠታቸው እንደሆነ
ይገልጻሉ፡፡


ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉✍

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ የአህባሾች ማምታቻ
☑️ የ"ليس كمثله شيئ" መልእክት
☑️ የአላህ መገለጫዎች ከፍጡር መገለጫ ጋር በፍፁም አይመሳሰልም


➰ክፍል ①③➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
አርበዒን 40ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
↪️አድስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር

↪️ ሐዲሥ ቁጥር – 4⃣0⃣

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w