💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
አርበዒን 35ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
↪️ደርስ

↪️አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር
↪️ሐዲሥ ቁጥር 3️⃣5⃣

↪️ የኪታቡን በ pdf ለማገኘት⤵️ https://t.me/IbnuMunewor/1672
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➳ክፍል አምስት ➤ተውሂድ ሩቡቢያ ➫➫➫➫➫➫➫➫ ➠ሙሺሪኮች ከላይ በተገለጸው ሁሉ አረጋጋጭ ናቸው፡፡ በብርቱ ጊዜ ዱዓን ፍጹም ለአላህ ብቻ ያደርጋሉ፡፡ምክንያቱም ጣዖቶቻቸው ከጥፋት ምንም የማዳን ችሎታ እንደሌላቸው ፤ አላህ እንጅ ከብርቱ ችግር የሚያድን አንድም አካል እንደሌለ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ➛አላህ በተከበረው…
➲"ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ"
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➻ክፍል ስድስት

➠ተውሂድ ኡሉህያ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴

➢ቁርኣን ተውሂድ አርሩቡብያን የሚያወሳው በከሀዲዎች ላይ ማስረጃን ለማቅረብ ነው፡፡ እነርሱ ባመኑበት ያላመኑበትን እንዲያምኑበት ለማድረግ ነው፡፡ ሩሡሎች “እናንተ ከሀዲዎች ሆይ! አላህ ብቸኛው ፈጣሪ ፣ መጋቢ ፣ ከጥፋት የሚያድን መሆኑን ካረጋገጣችሁ ለምንድን ነው የማይፈጥር ፣ ሲሳይ የማይሰጥ ፣ ከነገሩ ምንም አይነት መብት የሌለው ፣ ምንም የማያስተናብር ፣ የማይፈጥር ወደሆነ አካል "የምታዘነብሉት?” የሚል መልእክት ነው ለሙሽሪኮች የሚያስተላልፉት፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


◆أفَمَن يَخْلُقُ كَمَن لَّا يَخْلُقُ ۗ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ


“የሚፈጥር እንደማይፈጥር ነውን? አትገሰጹምን?” (አን’ነህል፡ 17

➠ስለዚህ ተውሂድ አልኡሉሁያ ሩሡሎች ወደርሱ ጥሪ ያደረጉበት ፣ ከህዝባቸው
ምላሽ የፈለጉበት የተውሂድ ክፍል ነው፡፡ በተውሂድ ባለቤቶች እና በጥመት ባለቤቶች መካከል በዚህ የተውሂድ ክፍል የተፈጠረው ውዝግብ እስካሁን ድረስ ቀጥሏል፡፡


➳የሰላማዊ ዓቂዳ ባለቤቶች ፡ ከዚህ የተውሂድ ክፍል የተጣመሙትን ፣ ወደሙሽሪኮች እምነት የተዘነበሉትን ፣ በቀብር ውስጥ ያሉ ሙታንን በማምለክና ወሰን ያለፈ ውዳሴ በማወደስ የአላህን መብት ቆርሰው የሚሰጡ ሰዎችን ወደትክክለኛው ዓቂዳ እንዲመለሱ ፤ በአምልኮ አላህን ብቻ እንዲነጥሉ ፤ ከገቡበት አደገኛ ሁኔታ እንዲወጡና የጣዖት አምልኮን እርግፍ አድርገው እንዲተው ይፈልጋሉ፡፡ ምክንያቱም
ይህ የጃሂልያ እምነት ነው
፡፡

➠ ከጃሂልያዎችም የበረታ እምነት ነው፡፡ ምክንያቱም የጃሂልያ አማኞች በደስታ ካልሆነ በቀር ብርቱ ችግር በሚገጥማቸው ጊዜ አላህን ብቻ
ነበር አጥርተው የሚግገዙት
፡፡

➳እነዚህ ሙሽሪኮች - የጥመት ባለቤቶች - ግን ሽርካቸው በደስታም በብርቱም ጊዜ ነው፡፡ እንዴውም ሽርካቸው በብርቱ ችግር ጊዜ ይበረታል፡፡ ውጥረት ውስጥ በገቡ ጊዜ የሚያመልኳቸውን ወልዮች ድረሱልን ይላሉ፡፡ መቃብር ውስጥ የሚገኙ ሙታኖችን ሲማጸኑ ትሰማለህ፡፡ የበፊት ሙሽሪኮች ግን ጉዳት በነካቸው ጊዜ ዱዓን ለአላህ ብቻ ነበር የሚያጠሩት፡፡
ይህ ነው ፣ መልእክተኞች አምልኮን ፍጹም ለአላህ እንዲያረጋግጡ ለህዝቦቻቸው ቅስቀሳ ያደረጉበት የተውሂድ ክፍል ነው
፡፡

➳ይህ የተውሂድ ክፍል ነው በመካከላቸው ልዩነት እንዲፈጠር ያደረገው፡፡ ይህ የተውሂድ ክፍል እንዲረጋገጥ ነው ረሡል صلى الله عليه وسلم
ሙሽሪኮችን የተጋደሉት
፡፡

➠ይህ የተውሂድ ክፍል የ “ላአላሃ ኢልለሏህ” ትርጉም ነው፡፡ “ኢላህ” ማለት
የሚመለክ ማለት ነው፡፡ “ላኢላሃ ኢልለሏህ” ከሚለው ቃል ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም የሚለውን ትርጉም እንይዛለን፡፡

➳“ኢላህ” ማለት አንዳንድ የጥመት ባለቤቶች በመፍጠር ላይ ቻይ የሚል ትርጉም እንደሚሰጡት አይደለም፡፡ ይህ አይደለም ትክክለኛ ትርጉሙ፡፡ “ኢላህ” ማለት የሚመለክ ማለት ነው …

ኢንሻአላህ
ይቀጥላል

=
https://t.me/https_Asselefya1
تلاوة رااااائعة.. علي جابر .رحمه الله
<unknown>
«قُل لَّن يُصِيبَنَا إِلَّا مَا كَتَبَ اللَّهُ لَنَا هُوَ مَوْلَانَا ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ»

«አላህ ለኛ የጻፈልን ነገር እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ እርሱ ረዳታችን ነው፡፡ ሙእሚኖች በአላህ ላይ ይመኩ» በላቸው፡፡

🎙القارئ الشيخ علي جابر رحمه اللّٰه
➲የጁሙዓ ሶላትን መተዉ አደጋ!

عن عبدالله بن عمر وأبي هريرة رضي الله عنهم أنهما سمِعا رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول على أعوادِ مِنبَره:

[ لَيَنْتَهِيَنَّ أَقْوَامٌ عَنْ وَدْعِهِمُ الجمُعَاتِ أَوْ لَيَخْتِمَنَّ الله على قُلُوبِهمْ ،ثُمَّ ليَكُونُنَّ مِنَ الغَافِلينَ]

📚رواه مسلم

➠ከዐብደላህ ቢን ዑመር እና አቢ-ሁረይረህ (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሚንበራቸው እንጨት ላይ ቆመው እንዲህ ሲሉ ሰምተናል አሉ:-

[ሕዝቦች የጁመ ሶላቶችን ከመተው ይከልከሉ። ወይም አላህ ልቦቻቸው ላይ ያትምባቸዋል። ከዛም (አላህን ባለማውሳት) ከዘንጊዎች ይሆናሉ።]

📚ሙስሊም ዘግበዉታል

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
በውሃ ቀጠነ የሚፈርሰው የዘመኑ ትዳር
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር "ሃፊዘሁላህ"
➡️ ያለ ወልይ ኒካህ ማሰር
➡️ በውሃ ቀጠነ የሚፈርስ ትዳር
➡️ መቼ ነው ቃዲ ኒካህ የሚያስረው

🌐ሴቶች በትኩረት አዳምጡት

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
“በገንዘቦቻችሁ እና በነፍሶቻችሁ በርግጥ ትፈተናላችሁ፡፡ ከነዚያም ከናንተ በፊት መፅሀፍን ከተሰጡትና ከነዚያ ከሚያጋሩትም ብዙን ማሰቃየት ትሰማላችሁ፡፡”
አዎ የሚደርስብን የደረሰባቸው ነው፡፡ ካለንበት ለመውጣት የታዘዝንበት ብልሃትም የታዘዙበት ነው፡፡
(وَإِن تَصۡبِرُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ فَإِنَّ ذَ ٰ⁠لِكَ مِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ)
“ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነው” ብሎናል፡፡ [አሊ ዒምራን፡ 186]
ፈተናው ሊከብድ ስቃዩ ሊጨምር ይችላል፡፡ ግና መለኮታዊ አዋጁን እንስማ፡
(أَمۡ حَسِبۡتُمۡ أَن تَدۡخُلُوا۟ ٱلۡجَنَّةَ وَلَمَّا یَأۡتِكُم مَّثَلُ ٱلَّذِینَ خَلَوۡا۟ مِن قَبۡلِكُمۖ مَّسَّتۡهُمُ ٱلۡبَأۡسَاۤءُ وَٱلضَّرَّاۤءُ وَزُلۡزِلُوا۟ حَتَّىٰ یَقُولَ ٱلرَّسُولُ وَٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ مَتَىٰ نَصۡرُ ٱللَّهِۗ أَلَاۤ إِنَّ نَصۡرَ ٱللَّهِ قَرِیبࣱ)
“በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (ምእመናን መከራ) ብጤ ሳይመጣችሁ ጀነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልእክተኛውና እነዚያ ከርሱ ጋር ያመኑት 'የአላህ እርዳታ መቼ ነው?' እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው፣ ተርበደበዱም፡፡ 'ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው' (ተባሉም፡፡)” [አልበቀራ፡ 214]
አዎ የአላህ እርዳታ ቅርብ ነው፡፡ ግና የአላህን ትእዛዝ ማክበር ይጠይቃል፡፡ ፈረጃው ይፈጥን ዘንድ የአላህን ህግጋት እንጠብቅ፡፡ ጌታችን “አላህን ብትረዱ ይረዳችኋል” ይላል፡፡ አላህን መርዳት ማለት ትእዛዙን መጠበቅ እና ክልከላውን መራቅ ነው። ለውጥ ከፈለግን እራሳችንን እንለውጥ፡፡
(إِنَّ ٱللَّهَ لَا یُغَیِّرُ مَا بِقَوۡمٍ حَتَّىٰ یُغَیِّرُوا۟ مَا بِأَنفُسِهِمۡۗ)
“በርግጥም አላህ በህዝቦች ዘንድ ያለውን (ገፅታ) በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚቀይሩ ድረስ አይለውጥም፡፡) [አረዕድ፡ 11]
“እስከመቼ” አትበለኝ፡፡ “የአላህ ውሳኔ እስከሚመጣ ድረስ” እልሃለሁ፡፡ ለመሆኑ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም እስከመቼ ነው ፊርዐውንን የታገሱት? ነብዩ ﷺ እስከመቼ ነው ደናቁራን አጋሪዎችን የታገሱት? ረጋ ብለህ አስተውል፡፡ የያኔው ሰቀቀን ከዛሬ እጥፍ ድርብ የከፋ ሰቀቀን ነው፡፡ የያኔው መፍተሄ የዛሬም መፍተሄ ነው፡፡ ይልቅ እወቅ! “አላህን ጠብቅ ይጠብቅሃል፡፡ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህን ታገኘዋለህ፡፡ ስትለምን አላህን ለምን፡፡ ስትታገዝ በአላህ ታገዝ፡፡ እወቅ! ህዝቦች በሙሉ በሆነ ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አላህ ላንተ በፃፈልህ እንጂ አይጠቅሙህም፡፡ በሆነ ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ በፃፈው እንጂ አይጎዱህም፡፡ ብእሮቹ ተነስተዋል! መዝገቦቹም ደርቀዋል፡፡” “እወቅ! የሳተህ ነገር የሚያገኝህ አልነበረም፡፡ ያገኘህም ነገር የሚስትህ አልነበረም፡፡ እወቅ!!! ድል ከትእግስት ጋር ነው። ግልግል ከጭንቅ ጋር ነው። ከከባድም ነገር ጋር ገር ነገር አለ።” ወሶለላሁ ዐላ ነቢይና ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊሂ ወሶሕቢሂ ወሰለም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 28/2007)
(ተነካክቶ በድጋሚ የተለጠፈ)
የቴሌግራም አድራሻ፦

https://t.me/IbnuMunewor
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲"ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ" ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➻ክፍል ስድስት ➠ተውሂድ ኡሉህያ ➴➴➴➴➴➴➴➴➴ ➢ቁርኣን ተውሂድ አርሩቡብያን የሚያወሳው በከሀዲዎች ላይ ማስረጃን ለማቅረብ ነው፡፡ እነርሱ ባመኑበት ያላመኑበትን እንዲያምኑበት ለማድረግ ነው፡፡ ሩሡሎች “እናንተ ከሀዲዎች ሆይ! አላህ ብቸኛው ፈጣሪ ፣ መጋቢ ፣ ከጥፋት የሚያድን መሆኑን ካረጋገጣችሁ…
➲ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ"
➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯

➳ክፍል ሰባት

➠ተውሂድ አል'አስማእ ወስ'ሲፋት
➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯

➳የተውሂድ አል'አስማእ ወስ'ሲፋት ትርጉሙ ምንም ሳናጣምም ፣ ሳናራቁት ፣ አኳኋንን ሳንገልጽ እና ከፉጡራን ጋር
ሳናመሳስል አላህ ለነፍሱ ያጸደቀውን ወይም ረሡል صلى الله عليه وسلم ለአላህ ያጸደቁትን ስምና መገለጫዎች ማጽደቅ ፤ አላህ ከነፍሱ እንዲሁም ረሡል صلى الله عليه وسلم ከአላህ ላይ ያራቆቱትን ጎደሎና ነውር ባህሪያት ማራቅ ማለት ነው፡፡


አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

◆لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

“የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው
፡፡” አሽ ሹራ፡ 11

◆فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

➥“ለአላህም አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ አላህ (መሳይ እንደሌለው) ያውቃል እናንተ ግን አታውቁም፡፡”
አን ነሕል፡ 74

➻በአየተል ኩርስይ ፣ በሱረቱል ኢኽላስ ፣ በአብዛኛው የመካ ምዕራፎች ፣ መዲና
በወረዱ ምዕራፎች የአላህን ስምና መገለጫዎች አስመልክቶ የመጡ መረጃዎች በርካታ ናቸው
፡፡

➳ቁርኣን የአላህን ስሞች እና መገለጫዎች ከማውሳት ያገለለ አይደለም

➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➻ከእያንዳንዱ ምዕራፍ መጀመሪያ ላይ የሚገኘውን “ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም” ብንመለከት አላህ አዛኝ በጣም ሩህሩህ መሆኑን ያጸድቃል፡፡ አላህ ነፍሱን በባህሪያት ይገልጻል ፤ ነፍሱን በስሞች ይጠራል፡፡ ስለዚህ እኛም እርሱ በኪታቡ ያጸደቀውን ማመን እና የማጽደቅ ግዴታ አለብን፡፡

➢በዚህ ጉዳይ አቅላችን ጣልቃ ሊገባ አይገባም፡፡ በራሳችን ስሜት ትርጉሙን መቆልመም አይገባም፡፡ የራሳችንን አመለካከት በአላህ ላይ ወሳኝ ልናደርግ መሞከር ትክክል አይደለም፡፡ ምክንያቱም አላህ ከሌላው ስለነፍሱ አዋቂ ነውና፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል

◆يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِهِ عِلْمًا

“በስተፊታቸው ያለውን በስተኋላቸውም ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በእርሱም
እውቀትን አያካብቡም ፤ (አያውቁም
)፡፡” ጦሃ፡ 110

◆اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ۚ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ ۚ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ ۚ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ ۖ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِّنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ ۚ

➤“አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ህያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢሆን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡በሻውም ነገር እንጅ ከእውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡” አል በቀራህ፡255

➠ኢንሻአላህ
ይቀጥላል


🖊ام فاروق
=
https://t.me/https_Asselefya1
{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا الرِّبَا أَضْعَافًا……
القارئ فايز السيحاني |تلاوة خاشعة
ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡
{አል ኢምራን}
አርበዒን 36ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
↪️ደርስ አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር

↪️ሐዲሥ ቁጥር – 3️⃣6️⃣

↪️PDF ለማገኘት⤵️⤵️
https://t.me/IbnuMunewor/1672
⤵⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ጀነት በአንድ ቆሪ ገንፎ
Sheki Muhammad Zayn
➲ኛን ካገለገልክ ተይዘንሀል❌

ጀነትን በአንድ ቆሪ ገንፎ ትገባለህ❌

🎙ሸህ ሙሀመድ ዘይን ሸኽ አደም

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ" ➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯ ➳ክፍል ሰባት ➠ተውሂድ አል'አስማእ ወስ'ሲፋት ➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯ ➳የተውሂድ አል'አስማእ ወስ'ሲፋት ትርጉሙ ምንም ሳናጣምም ፣ ሳናራቁት ፣ አኳኋንን ሳንገልጽ እና ከፉጡራን ጋር ሳናመሳስል አላህ ለነፍሱ ያጸደቀውን ወይም ረሡል صلى الله عليه وسلم ለአላህ ያጸደቁትን ስምና መገለጫዎች ማጽደቅ ፤ አላህ…
➲ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ"
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

➧ክፍል ስምንት

➠ቁርኣን የአላህን ስሞች እና መገለጫዎች ከማውሳት ያገለለ አይደለም
!
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫


➠አላህ ለእርሱ ከጣዖቶች አምሳያ ወይም ቢጤ ከማድረግ ከልክሎናል፡፡
ምክንያቱም አላህ አንድም እርሱን የሚመስል የለውም፡፡ ለእርሱም ተጋሪ ፣ ለእርሱ አቻ የለውም፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ጌታ ነው፡፡

➧አላህን በስሞቹ እና በመገለጫዎቹ እርሱን ብቻ በመጥራት እንገዛዋለን፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

●وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَا ۖ وَذَرُوا الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي أَسْمَائِهِ ۚ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

➻“ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ (ስትጸልዩ) በእርሷም ጥሩት፡፡ እነዚያንም
ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፡፡ ይሰሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይምመነዳሉ
፡፡” አል አዕራፍ፡ 180

አላህ ሱበሀነሁ ወተአላ የሚከተሉትን ነገሮች ግልጽ አድርጎልናል
፡-

➳ለነፍሱ ስሞችን አጽድቋል፤ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

●وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ

“ለአላህ መልካም የሆኑ ስሞች አሉት፡፡” አል አዕራፍ፡ 180

➳ሁሉም ስሞቹ በጣም ያማሩና መልካም መሆናቸውን ግልጽ አድርጓል፡፡

➳በእነርሱም እንድንማጸነው አዟል
➳ስሞቹን ከማጣመም ከልክሎናል


➠“ኢልሀድ” ማለት ማንሻፈፍ ወይም ማጣመም ማለት ነው፡፡ የአላህን ስሞች
ኢልሀድ ማድረግ ማለት ልክ ጀህምያዎች ፣ ሙዕተዚላዎች እና በነርሱ አካሄድ ላይ የተጓዙ ጠማማ ቡድኖች እንደሰሩት ያለትርጉሙ ወይም ከአላህ ፍላጎት ውጭ የተዛባ ትርጉም መስጠት ማለት ነው፡፡


➲አህለሱና ወልጀማዓህ በዚህም ይሁን በአጠቃላይ የዲናቸው ጉዳይ ቀጥ ባለ
መስመር ላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ዙሪያ የተከሰተው የጥመት አይነት በርካታና ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረታቸው ከሌላው ከፍ ያለ ነው
፡፡ በእርግጥ በዓቂዳ ላይ ያለው ስህተት ከእርሱ በታች እንዳለው ስህተት አይደለም፡፡ምክንያቱም በዓቂዳ ላይ ስህተት የፈጸመ ሰው ክህደትና ከእውነት የራቀ ብርቱ ጥመት ይፈራለታል፡፡

➸በእርግጥ በዲን ዙሪያ የሚፈጸም ስህተት በአጠቃላይ የሚፈቀድ ባይሆንም ከዓቂዳ ውጭ የተሳሳተ ስህተቱ የቀለለ ነው፡፡ የአንዱ ስህተት ከሌላው ስህተት የሚለያይ ቢሆንም በስህተት ላይ መዘውተር ፤ የተሳሳተን ሰው በጭፍን መከተል ክልክል ነው
፡፡

➧በዓቂዳ ላይ የሚፈጸም ስህተት በጣም የበረታ ነው ፤ በዓቂዳ ላይ መንሻፈፍ ከባድ የሆነ መንሻፈፍ ነው፡፡ ምክንያቱም የዓቂዳ ስህተት መጠገኛ የለውም፡፡ ከእርሱ ውጭ ያለው ስህተት ግን በአላህ መሽአ (ፍላጎት) ስር ነው፡፡

➧አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
●إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا

➻“አላህ በእርሱ የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ
፡፡” አን ኒሳእ፡ 116

●إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ

“አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም ሀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡” አን ኒሳእ፡48

➫ኢንሻአላህ
ይቀጥላል


=
https://t.me/https_Asselefya1