💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
◾️ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የአልዋጂባት ሸርህ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔹የሩቅ ሚስጥር ጉዳይ
🔹ወደ ነፍሱ አምልኮት መጣራት
🔹የሰው ልጅ የእውቀት ገደብ

🔻【ክፍል 5⃣5⃣】
〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ወቅታዊው የሀገራችን ሁኔታ በተመለከተ የተሰጠ ምክር‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

✅ የሶብር አንገብጋቢነትና ውጤቱ

➡️ ሶብር ፅና ታገስ ድሉ ካንተ ጋር ነው።

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
Audio
📚አዲስ የተጀመረ ኪታብ ደርስ!
〰〰〰〰〰〰〰〰
🔻
#ከሽፉ_ሹቡሀት ‼️
~~~~~~~~~
✍ الشيخ الإسلام محمد ابن عبدالوهاب رحمه الله

🔅 شرح : العلامۃ الفقيه محمد ابن صالح العثيمين رحمه الله

✅ ክፍል => 5⃣

🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
◾️ሱፍያን ቢን ኡየይና አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

✅ ሙእሚን ለሆነ ሰው ምግብና መጠጥ በሚፈልገው ልክ ሶብር (ትእግስት) ያስፈልገዋል።

📕الصبر لابن أبي الدنيا
ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ ራሂመሁሏህ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

ትግስት ካደረገ አላህ ከእርሱ ጋር እንደሆነ ፣ የአላህ ውዴታና ፍቅርን
እንደሚያገኝ መገንዘብ፡፡ አላህ ከእርሱ ጋር የሆነ ሰዎች ከእርሱ ላይ ሊከላከሉት
የማይችሉትን ጉዳትና የስቃይ አይነት ከእርሱ ላይ ይከላከልለታል
፡፡

➻አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

●وَاصْبِرُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

“ታገሱም ፤ አላህ ከትዕግስተኞች ጋር ነውና፡፡” አል አንፋል፡46

◆وَاللَّهُ يُحِبُّ الصَّابِرِينَ

“አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡” አል ዒምራን፡146

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲የአህለ'ሱና ወል'ጀማዓ ዓቂዳ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➻ ክፍል አራት

➧በአላህ የማመን ትርጉም

●የአህለሱና ወልጀማዓ ዓቂዳ ፡ በአላህ ፣ በመላኢካዎች ፣ በመጽሐፎች ፣ በመልእክተኞች እና በመጨረሻው ቀን ማመን ፤ መልካምም ይሁን መጥፎ በአላህ ውሳኔ የሚከናወን መሆኑን ማመን ናቸው፡፡

➢እነዚህን መሰረቶች ከሰባ ሁለቱ ቡድን መካከል የተቃረኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ከትክክለኛው ጎዳና ሊንሻፈፉ ችለዋል፡፡
የሐቅ ባለቤቶች ፈተና ቢጋፈጣቸው ፣ ከሰዎች ጫና ቢደርስባቸው ምንጊዜም በሐቅ ላይ ጽኑ ፣ ለእውነታው ቅያርን የማይፈልጉ ናቸው
፡፡

➳በአላህ የማመን ትርጉም፡ በጌትነቱ ፣ በአምላክነቱ እና በመልካም ስሞቹና መገለጫዎቹ ብቸኛ የሆነ ጌታ መሆኑን በቁርጠኝነት ማመን ማለት ነው
፡፡

➻ይህ ማለት በውስጡ ሶስቱን የተውሂድ አይነቶች አቅፏል ማለት ነው፡፡

➳ተውሒድ አር'ሩቡብያ
➳ተውሒድ አል'ኡሉሑያ
➳ተውሒድ አስማእ ወስ'ሲፋት


➠ተውሒድ አርሩቡብያ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ይህ የተውሒድ አይነት ተፈጥሮን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ከፍጡር አንድም ይህን የሚቃወም የለም፡፡ የክህደት ቅንጭላት የሆነው ኢብሊስ እንኳ አልካደም፡፡

◆قَالَ رَبِّ بِمَا أَغْوَيْتَنِي
“ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ..” አል ሒጅር 39

◆قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ

“(እርሱም) አለ “በአሸናፊነትህ ይሁንብኝ ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ፡፡” ሷድ፡ 82

➳እርሱ በአላህ ጌትነት አረጋገጠ ፣ በአላህ ልቅና ማለ፡፡ ሌሎችም ከሀዲዎች ይህን የተውሒድ ክፍል አረጋግጠዋል። አቡጀህል ፣ አቡ ለሀብ እና ሌሎችም የክህደት መሪዎች አረጋግጠዋል፡፡

ክህደትና ጥመት ላይ ሆነው የአላህን
ብቸኛ ፈጣሪነትና ጌትነት ያረጋግጡ ነበር፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

◆ وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَهُمْ لَيَقُولُنَّ اللَّهُ ۖ
“ማን እንደፈጠራቸውም ብትጠይቃቸው “በእርግጥ አላህ ነው”ይላሉ፡፡”
አዝ ዙኽሩፉ:- 87
◆ قُلْ مَن بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ {سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ فَأَنَّىٰ تُسْحَرُونَ

“የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የሆነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን
ነው? የምታውቁ እንደሆናችሁ መልሱልኝ ” በላቸው፡፡ “በእርግጥ አላህ ነው” ይሉሃል
፡፡” አል ሙእሚኑን፡88_89

◆قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ أَمَّن يَمْلِكُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَمَن يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ الْمَيِّتَ مِنَ الْحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ الْأَمْرَ ۚ فَسَيَقُولُونَ اللَّهُ ۚ فَقُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ

➛"ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው? ከሙትም ህያውን የሚያወጣ ከህያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?” በላቸው፡፡
“በእርግጥም አላህ ነው” ይሉሃል፡፡ “ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን?” በላቸው
፡፡” ዩኑስ፡31

➠ኢንሻአላህ
ይቀጥላል

🖊ام فاروق
=
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የአልዋጂባት ሸርህ ደርስ

➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔹ወልዮችን ማምለክና መገዛት
🔹ወልዮችን መውደድና ማክበር

🔻【ክፍል 5⃣6⃣】
〰〰〰〰〰〰

➡️ የመጨረሻ ክፍል ⬅️

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
وَجَزَاهُم بِمَا صَبَرُوا جَنَّةً وَحَرِيرًا

በመታገሣቸውም ገነትንና የሐር ልብስን መነዳቸው
፡፡


مُّتَّكِئِينَ فِيهَا عَلَى الْأَرَائِكِ ۖ لَا يَرَوْنَ فِيهَا شَمْسًا وَلَا زَمْهَرِيرًا

"በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች በውስጧ ፀሐይንም ጨረቃንም የማያዩ ሲኾኑ"

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ወቅታዊው የሀገራችን ሁኔታ በተመለከተ የተሰጠ ምክር

✅ በቀደር ማመንና ጥቅሞቹ

➡️ ሁሉ ነገር እየሆነ ያለው በአላህ ውሳኔና ፍቃድ ነው።

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የአህለ'ሱና ወል'ጀማዓ ዓቂዳ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➻ ክፍል አራት ➧በአላህ የማመን ትርጉም ●የአህለሱና ወልጀማዓ ዓቂዳ ፡ በአላህ ፣ በመላኢካዎች ፣ በመጽሐፎች ፣ በመልእክተኞች እና በመጨረሻው ቀን ማመን ፤ መልካምም ይሁን መጥፎ በአላህ ውሳኔ የሚከናወን መሆኑን ማመን ናቸው፡፡ ➢እነዚህን መሰረቶች ከሰባ ሁለቱ ቡድን መካከል የተቃረኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ከትክክለኛው ጎዳና ሊንሻፈፉ…
➲ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➳ክፍል አምስት

➤ተውሂድ ሩቡቢያ
➫➫➫➫➫➫➫➫

➠ሙሺሪኮች ከላይ በተገለጸው ሁሉ አረጋጋጭ ናቸው፡፡ በብርቱ ጊዜ ዱዓን ፍጹም ለአላህ ብቻ ያደርጋሉ፡፡ምክንያቱም ጣዖቶቻቸው ከጥፋት ምንም የማዳን ችሎታ እንደሌላቸው ፤ አላህ እንጅ ከብርቱ ችግር የሚያድን አንድም አካል እንደሌለ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡

➛አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል

◆وَإِذَا مَسَّكُمُ الضُّرُّ فِي الْبَحْرِ ضَلَّ مَن تَدْعُونَ إِلَّا إِيَّاهُ ۖ فَلَمَّا نَجَّاكُمْ إِلَى الْبَرِّ أَعْرَضْتُمْ ۚ وَكَانَ الْإِنسَانُ كَفُورًا

“በባህሩም ውስጥ ጉዳት ባገኛችሁ ጊዜ የምትጠሩዋቸው አማልክት ሁሉ ከእርሱ ከአላህ በቀር ይጠፋሉ፡፡ ወደ የብስም በማድረስ ባዳናችሁ ጊዜ እምነትን ትተዋላችሁ፡፡ ሰውም በጣም ከሀዲ ነው፡፡
” አል ኢስራእ፡ 67

➠ይህን የተውሂድ አይነት አጥብቆ ቢይዝም ከኢስላም መግባትም ይሁን ከእሳት ነጻ መሆን አይችልም፡፡ ከሀዲዎች በተውሂድ ሩቡብያ ቢያረጋግጡም ወደኢስላም ፍጹም ሊገቡ አልቻሉም፡፡ ምክንያቱም በተውሂድ አርሩቡብያ እያረጋገጡ አላህ ሙሸሪክ እና ከሀዲ ብሎ ነው የሰየማቸው፡፡

➳ይህ ብቻ አይደለም እሳትን በዘውታሪነትም ነው የወሰነባቸው
፡፡
በፍልስፍናው አካሄድ በዓቂዳ ዙሪያ መጽሐፍ የሚጽፉ አንዳንድ ሰዎች ተሳስተው እናያቸዋለን፡፡ ተውሒድ ማለት ከእነርሱ ዘንድ አላህ ፈጣሪ ፣ መጋቢ መሆኑን ማረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ለእነዚህ ሰዎች የምንሰጣቸው መልስ ይህ ከሀዲዎችና ሙሽሪኮች - ኢብሊስን ጨምሮ - ያረጋገጡት የተውሂድ ክፍል እንጅ አላህ ነብያቶችን የላከበት ዓቂዳ ወይም እምነት አይደለም፡፡

➧ሩሡሎች የአላህን ፈጣሪነት ፣ መጋቢነት ፣ ህይዎት ሰጪነት ፣ ገዳይ መሆኑን ለማረጋገጥ አይደለም የተላኩት ምክንያቱም ይህን የተውሒድ ክፍል ማረጋገጥ ከአላህ ቅጣት የሚያድን በቂ የሆነ የተውሂድ ክፍል ባለመሆኑ፡፡

➲ተውሂድ አል'ኡሉሁያ
➻➻➻➻➻➻➻➻

➸ይህ የተውሂድ ክፍል “ተውሂድ አልዒባዳ” ፣ “ተውሂድ አልኢራዳህ ወልቀስድ” በመባል ይጠራል፡፡ ይህ አይነቱ የተውሂድ ክፍል የሩሡሎች ጉዞ መዳረሻ ፣ የህዝባቸው የክርክር ቦታ ነው፡፡ መልእክተኞች ሁሉ ወደህዝባቸው ሲላኩ “ህዝቦቼ ሆይ! አላህ ፈጣሪያችሁ ነው” የሚል ጥሪ ሳይሆን “ህዝቦቸ ሆይ! አላህን ተገዙ ከአላህ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ የላችሁም” የሚል ጥሪ ነበር የሚያደርጉት፡፡

➠ከህዝቡ የሚፈልጉት በፈጣሪነቱ፣ በመጋቢነቱ ፣ በጌታነቱ ፣ በአስተናባሪነቱ ብቸኛ መሆኑን ያረጋገጡለትን አምላክ በብቸኛነት እንዲያመልኩ ነው
፡፡በመፍጠር ፣ በማስተናበር ብቸኛ እንዳደረጉት ሁሉ በአምልኮትም ብቸኛ እንዲያደርጉት ከህዝባቸው ይፈልጋሉ፡፡ ህዝባቸው ባረጋገጠው ላይ ማስረጃን ያቀርባሉ፡፡

➠ኢንሻአላህ
ይቀጥላል


https://t.me/https_Asselefya1
የዉስጥ ዉበት ምንነት ከዉጫዊዉ መልካም ገጽታ ጋር አይነጻጸርም።

ዩሱፍ عليه الصلاة والسلام እንደዚያ ዉብ ቢሆንም ዉጫዊ ዉበቱ ከእስር አልታደገውም።

የውስጥ ዉበቱ ግን ከእስር ቤት እንድወጣ አስችሎታል
።

የሰው ልጆችም በጊዜያዊነት በዉጭ ዉበት ፈጥነው ሊማረኩ ቢችሉም
ለዉስጣዊ መልካምነት ግን ከፍ ያለን ደረጃ ይሰጣሉ።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Kitabu Tewhid #48
Ibnu Munewor
↪️ ተከታታይ የኪታቡ ተውሒድ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ርዕስ باب ما جاء في التنجيم


↪️ ክፍል 4⃣8⃣↩️
〰〰〰〰〰〰

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔻حفظه الله تعالى
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
288 - شرح حديث ما تركت بعدي فتنة هي أضر على الرجال: من النساء -…
شرح حديث ما تركت بعدي فتنة هي أضر على الرجال: من النساء -


الشيخ : عبدالرزاق البدر حفظه الله
……… ስድስቱ የተውበት መስፈርቶች ………
===========================
በህይወታችን ብዙ ጊዜ ወንጀሎችን እንፈፅማለን። አላህ ያደለው በወንጀሉ አላህ ፊት እንዳይጠየቅ ተውበት ማድረግን ያስባል። ግን ስንቱ ነው ተውበቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ እንዲሆን የሚጨነቀው? እራሳችንን በሚገባ ጠይቀን እናውቃለን?! ለመሆኑ መስፈርቶቹን ምን ያህሎቻችን በሚገባ እንለያቸዋለን? ለማያውቁ ጥቆማ፣ ለሚያውቁ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ እጠቅሳለሁ። የተውበት መስፈርቶች ስድስት ናቸው። እነሱም:–
① ኢኽላስ: – አላህን ብቻ በማሰብ ሊፈፀም ነው። አንድ ሰው ወንጀልን የሚቶወው ዱንያዊ ጥቅሞችን አስቦ ከሆነ የመጀመሪያውን የተውበት መስፈርት ዘንግቷል።
② ወንጀሉን ማቆም:– አንድ ሰው የሚፈፅመውን ወንጀል ባላቋረጠበት ሁኔታ "ቶብቻለሁ" ቢል ቀልድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ተውበት ያሰበ ሰው ጥፋቱን በቀጠሮ ሳይሆን ቀጥታ ሊያቆም ይገባል።
③ ወደ ጥፋቱ ዳግም ላይመለሱ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ። አንድ ሰው ከወር ቡሀላ እንደሚመለስ እያሰበ ረመዳን ሊገባ ሲል አንድን ወንጀል ቢተው መስፈርት ስላላሟላ ተውበት አድርጓል ማለት አይቻልም።
④ በወንጀሉ መፀፀት። ሰውየው ሲፈፅመው በቆየው ወንጀል ላይ ደንታ ቢስ ከሆነ ተውበቱ የሐቂቃ አይደለም። ፀፀቱ "ሰው ምን ይለኛል" ወይም "ክብሬ ጎደፈ" በሚል ሳይሆን የጌታውን ህግ በመጣሱ ሊሆን ይገባል። ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ዝሙት ፈፅመው ጌታቸው ዘንድ ካለው ሂሳብ ይልቅ ዱንያ ላይ ያለው የሰው ወሬ ሲያስጨንቃቸው ይፀፀታሉ። እንዲህ አይነት ፀፀት የተውበትን መስፈርት አያሟላም። ይልቅ ከዛሬው የበዛ ህዝብ ፊት ነገ በአኺራ መዋረድ ከመምጣቱ በፊት ትክክለኛውን ፀፀት እዚሁ ልናስገኝ ይገባል።
⑤ ተውበቱ ወቅቱን የጠበቀ መሆን። ይህም ሞት አፋፍ ላይ ከመድረሱ በፊት እና ፀሀይ በመጥለቂያዋ ከመውጣቷ በፊት መሆኑ ነው።
⑥ ወንጀሉ የሰው ሐቅ መግፋት ከሆነ ሐቁን ሊመልስ ወይም ይቅርታውን ሊያገኝ ይገባል። ወይም ኢስቲግፋርና ኸይር ስራ ሊያበዛ ይገባል።

https://t.me/IbnuMunewor
አርበዒን 35ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
↪️ደርስ

↪️አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር
↪️ሐዲሥ ቁጥር 3️⃣5⃣

↪️ የኪታቡን በ pdf ለማገኘት⤵️ https://t.me/IbnuMunewor/1672
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-