💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➽ትክክለኛና የተረጋገጠ ዓቂዳ (እምነት) ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ➠ትክክለኛ አቂዳ ማለት ረሡል صلى الله عليه وسلم የተላኩበትና ወደርሱ ጥሪ ያደረጉበት ነው፡፡ ➻የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በሚከተለው መልኩ ግልጽ አድርገውታል፡- ●"أن الأمة ستفترق من بعده على ثلاث وسبعين فرقة كلها في النار إلا واحدة" قالوا: من هي…
➽"ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ"
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

➻ክፍል ሁለት

➲ሐቅ የማይከፋፈል አንድና አንድ ብቻ ነው!
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➠አዎ ፣ ፊረቆች ወይም አንጃዎች በርካታ ናቸው ፤ እምነቶችና መዝሀቦች እልፍ አእላፍ ናቸው ፤ ንግግሮች ብዙ ናቸው ይሁን እንጅ ፣ ይህ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم
ዲን ነው
፡፡

➻አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

● وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

➠“ይህም ቀጥተኛ ሲሆን መንገዴ ነው፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ። ከቀጥተኛው መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡ እንሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ
፡፡” አል አንዓም፡ 153

➻የአላህ መንገድ ፡ ረሡልን صلى الله عليه وسلم የላከበት ፤ የተከበሩ ሶሃቦች ፣ ምርጥ ክፍለ ዘመን ላይ የነበሩት - ታብዒይና ታብዒዩ ታብዕይ - እንዲሁም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ የእነርሱን
ዱካ የተከተሉ የዚህ ኡመት ማህበረሰቦች የተጓዙበት መንገድ ነው፡፡ ይህ የአላህ
መንገድ ነው ፤ ይህን የአላህ መንገድ የተቃረኑ ሁሉ የጥመት መንገዶች ናቸው
፡፡

➳ነብዩ صلى الله عليه وسلم ቀጥ ያለ መስመር አሰመሩ ፤ ጠማማ የሆኑ መስመሮችን ደግሞ በጎን እና በጎን አሰመሩ ፡፡ ከዚያም ቀጥ ስላለው መስመር የሚከተለውን ተናገሩ፡ “ይህ
የአላህ መንገድ ነው” ፤ በጎን እና በጎን ስላሉት የተለያዩ መንገዶች ደግሞ “እነዚህ መንገዶች ናቸው፡፡ በእያንዳንዱ መንገድ ላይ ወደርሱ ጥሪ የሚያደርጉ ሰይጣናት አሉ” በማለት ተናገሩ
፡፡

አህመድ፡ ቲርሚዚይ፡ አድ ዳሪሚይ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ተኽሪጁ መሸካቲ አል መሷቢህ፡

➳ይህ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ንግግር ለሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ የተሰጠ ግልጽ ማብራሪያ ነው፡፡

● وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا

“ይህም ቀጥተኛ ሲሆን መንገዴ ነው” አል አንዓም፡153

➠ስለዚህ የሰላማዊ ዓቂዳ ባለቤቶች ፤ ከጥመት ፣ ከእሳትና ከልብ ወለድ ነጻ የሆኑ ጀማዓዎች ናቸው፡፡ እነርሱ ናቸው አህለሱና ወልጀማዓዎች፡፡ እኛንም እናንተንም ከእነርሱ ጋር አብሮ ያድርገን ፣ይሰብስበን! እርሱን እስከምንገናኝ ድረስ በእነርሱ ጎዳና የምንጓዝ ያድርገን!!

➠ኢንሻአላህ
ይቀጥላል


🖊ام فاروق
=
https://t.me/https_Asselefya1
{ وَمَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ إِذْ قَالُوا مَا أَنزَلَ…
القارئ عبدالله الموسى |تلاوة خاشعة
Audio
◾️ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የአልዋጂባት ሸርህ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔹በዲን ላይ ፅናት
🔹አውቆ አጥፊ መሆን
🔹ግለሰብን ማክፈር በተመለከተ

🔻【ክፍል 5⃣4⃣】
〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
‏قال العلَّامة أحمد النَّجمي رحمه الله :

"أصحاب محمد ﷺ هم أساس ⁧المنهج السلفي⁩ الذي يسير عليه أهل السنة والجماعة".

[إرشاد الساري صفحة ٣٨]
Audio
◾️አዝካር ወል አዳብ
➖➖➖➖➖➖
🔻الأذكار والآداب

↪️ ክፍል 3⃣7⃣ ↩️
〰〰〰〰〰〰

🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
🔷 #ወቅታዊ_ምክር

ነብዩ እንዲህ ይላሉ ፦

"ሙስሊም ለሙስሊም እንደ አንድ ሰውነት ናቸው ከሰውነት አንዱ ሲታመም ሌሎቹም በመታመም ይጋሩታል " ።

~~~~~~~~~~~~~~~~~

በስቃይ በችግር ላይ ያላችሁ የአኼራ ወንድሞቼ እህቶቼ ሆይ አብሽሩ የአሏህ ነስር ቅርብ ነው ።

🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

https://t.me/abuUseyminabdurehman
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➽"ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ" ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ ➻ክፍል ሁለት ➲ሐቅ የማይከፋፈል አንድና አንድ ብቻ ነው! 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➠አዎ ፣ ፊረቆች ወይም አንጃዎች በርካታ ናቸው ፤ እምነቶችና መዝሀቦች እልፍ አእላፍ ናቸው ፤ ንግግሮች ብዙ ናቸው ይሁን እንጅ ፣ ይህ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ዲን ነው፡፡ ➻አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ…
➽"ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ"
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➻ክፍል ሶስት

➲የአላህን ውዴታ ፈልገው የሚታገሱና
ለአላህና ለረሡል صلى الله عليه وسلم ታዛዥ የሆኑ ሰዎች ደረጃ

➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯

➳አህለሱናዎች በአንዳንድ ዘመን ቁጥራቸው ሊያንስ ፣ በአንዳንድ ዘመን ደግሞ ቁጥራቸው ሊበዛ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ቁጥራቸው ጥቂት ይሆናል፡፡ ይሁን እንጅ በሐቅ ላይ በመሆናቸው በውስጣቸው በረካና መልካም ነገር አለ፡፡

➠በሐቅ ላይ ከሆኑ የጠላት መብዛት ፣ የእነርሱ ቁጥር ማነስ አያሰጋቸውም፡፡


አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

● وَمَن يُطِعِ اللَّهَ وَالرَّسُولَ فَأُولَٰئِكَ مَعَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ النَّبِيِّينَ وَالصِّدِّيقِينَ وَالشُّهَدَاءِ وَالصَّالِحِينَ ۚ وَحَسُنَ أُولَٰئِكَ رَفِيقًا


➲“አላህንና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ
ከለገሰላቸው ከነቢያት ፣ ከጻድቃንም ፣ ከሰማእታትም ፣ ከመልካሞቹ ጋር ይሆናሉ፡፡ የእነዚያም ጓደኛነት አማረ
፡፡” አን ኒሳእ ፡69

➠ጓደኞቹ እነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ጸጋውን የዋለላቸው ናቸው፡፡ ጓደኞቹ የአላህን ውዴታ በመፈለግ ትዕግስትን የተላበሱ ነብያቶች ፣ ሲዲቆች ሹሐዳዎች እና ሷሊሆች ሆነው እንዴት ጠላትን ይፈራል? ነገር ግን ፣ እነርሱ በተጓዙበት መንገድ በጽናት ለመጓዝ ፣ ተቃራኒ አካላት
የሚያደርሱትን ብርቱ ችግር በትዕግስት ለመሸከም እውቀትና ግንዛቤ እንዲሁም
የእነዚህን ሰዎች ጎዳና መከታተልና ማጥናት ከባሪያው ይፈልጋል፡፡


➤በአላህ መንገድ ፣ ሐቅ በሆነው ዲን እና በሱናው ላይ ታጋሽ የሆነ ሰው ከሰዎች ብዙ መከራ ፣ ወቀሳ ፣ ዘለፋ ይደርስበታል፡፡ ፈተናው አንዳንድ ጊዜ ማሰቃየት ወይም ከአገር ማባረር ወይም መግደል ደረጃ ሊደርስ ይችላል
፡፡

➻ነገር ግን እርሱ በሐቅ ላይ እስከሆነ ድረስ የተንኮለኞች ሴራ አይጎዳውም፡፡ በዱንያ ላይ እያለ በርካታ መከራዎች ቢደርሱበትም ፍጻሜው ግን ለእርሱ ነው ፤ ፍጻሜው ለጥንቅቆች ነው፡፡


ኢንሻአላህ
ይቀጥላል

=
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የአልዋጂባት ሸርህ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔹የሩቅ ሚስጥር ጉዳይ
🔹ወደ ነፍሱ አምልኮት መጣራት
🔹የሰው ልጅ የእውቀት ገደብ

🔻【ክፍል 5⃣5⃣】
〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ወቅታዊው የሀገራችን ሁኔታ በተመለከተ የተሰጠ ምክር‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

✅ የሶብር አንገብጋቢነትና ውጤቱ

➡️ ሶብር ፅና ታገስ ድሉ ካንተ ጋር ነው።

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
Audio
📚አዲስ የተጀመረ ኪታብ ደርስ!
〰〰〰〰〰〰〰〰
🔻
#ከሽፉ_ሹቡሀት ‼️
~~~~~~~~~
✍ الشيخ الإسلام محمد ابن عبدالوهاب رحمه الله

🔅 شرح : العلامۃ الفقيه محمد ابن صالح العثيمين رحمه الله

✅ ክፍል => 5⃣

🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
◾️ሱፍያን ቢን ኡየይና አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

✅ ሙእሚን ለሆነ ሰው ምግብና መጠጥ በሚፈልገው ልክ ሶብር (ትእግስት) ያስፈልገዋል።

📕الصبر لابن أبي الدنيا
ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ ራሂመሁሏህ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

ትግስት ካደረገ አላህ ከእርሱ ጋር እንደሆነ ፣ የአላህ ውዴታና ፍቅርን
እንደሚያገኝ መገንዘብ፡፡ አላህ ከእርሱ ጋር የሆነ ሰዎች ከእርሱ ላይ ሊከላከሉት
የማይችሉትን ጉዳትና የስቃይ አይነት ከእርሱ ላይ ይከላከልለታል
፡፡

➻አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

●وَاصْبِرُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

“ታገሱም ፤ አላህ ከትዕግስተኞች ጋር ነውና፡፡” አል አንፋል፡46

◆وَاللَّهُ يُحِبُّ الصَّابِرِينَ

“አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡” አል ዒምራን፡146

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲የአህለ'ሱና ወል'ጀማዓ ዓቂዳ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➻ ክፍል አራት

➧በአላህ የማመን ትርጉም

●የአህለሱና ወልጀማዓ ዓቂዳ ፡ በአላህ ፣ በመላኢካዎች ፣ በመጽሐፎች ፣ በመልእክተኞች እና በመጨረሻው ቀን ማመን ፤ መልካምም ይሁን መጥፎ በአላህ ውሳኔ የሚከናወን መሆኑን ማመን ናቸው፡፡

➢እነዚህን መሰረቶች ከሰባ ሁለቱ ቡድን መካከል የተቃረኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ከትክክለኛው ጎዳና ሊንሻፈፉ ችለዋል፡፡
የሐቅ ባለቤቶች ፈተና ቢጋፈጣቸው ፣ ከሰዎች ጫና ቢደርስባቸው ምንጊዜም በሐቅ ላይ ጽኑ ፣ ለእውነታው ቅያርን የማይፈልጉ ናቸው
፡፡

➳በአላህ የማመን ትርጉም፡ በጌትነቱ ፣ በአምላክነቱ እና በመልካም ስሞቹና መገለጫዎቹ ብቸኛ የሆነ ጌታ መሆኑን በቁርጠኝነት ማመን ማለት ነው
፡፡

➻ይህ ማለት በውስጡ ሶስቱን የተውሂድ አይነቶች አቅፏል ማለት ነው፡፡

➳ተውሒድ አር'ሩቡብያ
➳ተውሒድ አል'ኡሉሑያ
➳ተውሒድ አስማእ ወስ'ሲፋት


➠ተውሒድ አርሩቡብያ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ይህ የተውሒድ አይነት ተፈጥሮን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ከፍጡር አንድም ይህን የሚቃወም የለም፡፡ የክህደት ቅንጭላት የሆነው ኢብሊስ እንኳ አልካደም፡፡

◆قَالَ رَبِّ بِمَا أَغْوَيْتَنِي
“ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ..” አል ሒጅር 39

◆قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ

“(እርሱም) አለ “በአሸናፊነትህ ይሁንብኝ ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ፡፡” ሷድ፡ 82

➳እርሱ በአላህ ጌትነት አረጋገጠ ፣ በአላህ ልቅና ማለ፡፡ ሌሎችም ከሀዲዎች ይህን የተውሒድ ክፍል አረጋግጠዋል። አቡጀህል ፣ አቡ ለሀብ እና ሌሎችም የክህደት መሪዎች አረጋግጠዋል፡፡

ክህደትና ጥመት ላይ ሆነው የአላህን
ብቸኛ ፈጣሪነትና ጌትነት ያረጋግጡ ነበር፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

◆ وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَهُمْ لَيَقُولُنَّ اللَّهُ ۖ
“ማን እንደፈጠራቸውም ብትጠይቃቸው “በእርግጥ አላህ ነው”ይላሉ፡፡”
አዝ ዙኽሩፉ:- 87
◆ قُلْ مَن بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ {سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ فَأَنَّىٰ تُسْحَرُونَ

“የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የሆነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን
ነው? የምታውቁ እንደሆናችሁ መልሱልኝ ” በላቸው፡፡ “በእርግጥ አላህ ነው” ይሉሃል
፡፡” አል ሙእሚኑን፡88_89

◆قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ أَمَّن يَمْلِكُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَمَن يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ الْمَيِّتَ مِنَ الْحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ الْأَمْرَ ۚ فَسَيَقُولُونَ اللَّهُ ۚ فَقُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ

➛"ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው? ከሙትም ህያውን የሚያወጣ ከህያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?” በላቸው፡፡
“በእርግጥም አላህ ነው” ይሉሃል፡፡ “ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን?” በላቸው
፡፡” ዩኑስ፡31

➠ኢንሻአላህ
ይቀጥላል

🖊ام فاروق
=
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የአልዋጂባት ሸርህ ደርስ

➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔹ወልዮችን ማምለክና መገዛት
🔹ወልዮችን መውደድና ማክበር

🔻【ክፍል 5⃣6⃣】
〰〰〰〰〰〰

➡️ የመጨረሻ ክፍል ⬅️

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w