💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
«وكم من إمرأة تأتي يوم القيامة مكتوب في صحيفتها ( زانںِـِـة )»

«ስንት ሴቶች  የቂያማ ቀን ስራ መዝገባቸዉ ላይ"ዝሙተኛ" ተብሎ የተፃፈ ይመጣላቸዋል። »

«وهي لم تزںِْ قط ، وذلك بسبب عطرها وتبرجها بين الرجــال!»

«ነገር ግን እሷ ዝሙት ስርታ አታዉቅም። ምክንያቱ ግን፦  ሽቶ ተቀባብታ መዉጣቷ ለአጅነብይ ወንዶች መገላለጧ ነዉ።

=
t.me/https_Asselefya1
«النِّساءُ السَّعيداتُ نَتائِج أفعال رجالٍ يفعلونَ ما يَقولون،»

«ደስተኛ ሴቶች የወንዶች ተግባር ውጤት ናቸው፣ምክንያቱም የሚሏቸውን ስለሚተገብሩ !»

«والله إنَّ آثارَ الرُّجولةِ تُرى في زَوجتِه: أهيَ عَزيزةٌ أم مُهانةٌ؟»

«በአላህ እምላለሁ የወንድ ባህሪ እውነተኛ ምልክት በሚስቱ ላይ ይታያል፤ እሷ የተከበረች ናት ወይስ የተዋረደች ናት?

=
t.me/https_Asselefya1
«مُصيبة والله تجده متزوج ولا يصلي! يا أخي إتق الله في نفسك مهما أخطأت #صلي، سيقبل الله توبتك وأوبتك، أبشر

በአላህ እምላለሁ ይሄ ትልቅ ሙሲባ ነዉ። ያገባን ሰዉ  የማይሰግድ ሆኖ ታገኘዋለህ።  ወንድሜምንም አይነት ስህተት ብትሠራም በነፍስህ ላይ አላህን  ፍራ። ስገድአላህ  ተዉበትህን(ወደ እርሱ መመለስህን) ይቀበልሀል!  አብሽር

=
t.me/https_Asselefya1
መልካም ጓደኛ
ወንድም አቡ ሱፍያን
ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተዘጋጀው Welcome ፕሮግራም  ላይ በጉራጌ ዞን ከተሰጠ ምክር የተወሰደ...

🎙ወንድም አቡ ሱፍያን
t.me/AbuSufiyan_Albenan
ስደት ላይ ስትኖሪ ጠንካራ መሆን ምርጫሽ ሳይሆን ግደታሽ ነዉ። So ጠንከር በይ አይዞሽ!

=
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት ወንድማችን የሁለት ልጆች አባት ነው። አብዛኞቻችሁ እንደምታውቁት ቀደም ሲል በቴሌግራም ግሩፕ ተከፍቶለት በተደረገለት ርብርብ ከአላህ በታች በእናንተ እርዳታ የኩላሊት እጥባት (Dialysis) እያደረገ ቆይቷል።

ለአንድ ዓመት ከሦስት ወር አዲስ አበባ (ሀያት አደባባይ በሚገኘው በያኔት ሆስፒታል)፣ ከዚያም ካለፈው ዓመት የአረፋ በዓል ጀምሮ እስካሁን ድረስ በደሴ ከተማ የኩላሊት እጥባት ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ሁለት ዓመት ሊሞላው ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ከጎኑ የቆማችሁ ኡስታዞች፣ ወንድሞችና እህቶች አላህ ጤናችሁን ይስጥልኝ፤ ጀዛኩም አላሁ ኸይራን።

አሁን ግን ሁኔታው አስፈሪ ሆኗል። ወንድሜ አይኔ እያየ እየቀለለ ነው። ቀድሞ በሳምንት ሁለት ቀን ይታጠብ የነበረው አሁን በሳምንት ሦስት ጊዜ እንዲታጠብ ታዟል። ለአንድ እጥባት 4,500 ብር፣ በሳምንት 13,500 ብር እያወጣን ነው፤ የመድሃኒት ወጪው ደግሞ የባሰ ነው።

አሁን ላይ አንድ ተስፋ አግኝተን ነበር። ታናሽ ወንድሙ ኩላሊቱን ሊሰጠው ፈቃደኛ ሆኖ በአዲስ አበባ ጳውሎስ ሆስፒታል ሙሉ ምርመራውን ጨርሰን ለንቅለ-ተከላ ቀዶ ጥገናው ዝግጁ ሆነናል። ቀጣይ ሳምንት ትሰራለህ ተብሏል። ነገር ግን ይህንን ለማድረግ የገንዘብ አቅማችን ፈጽሞ አልቻለም።

ሐኪሞቹ ሂደቱ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ሊፈጅ እንደሚችል ነግረውናል። (በቅርቡ የተሰሩ ሰዎች እስከ 900 ሺህ ብር እንደፈጀባቸው አይተናል)። እኛ እጅ ላይ ያለው ግን 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ ነው።
ወገኖቼ! ወደ እናንተ ከመመለስ ውጪ አማራጭ አጣን፤ ጨነቀን። እባካችሁ ፕሮሰሱ አልቆ በገንዘብ እጦት ምክንያት ወንድማችንን እንዳናጣው ተባበሩን። ትንሽ የምትሉት ነገር የለምና ህይወቱን እንታደገው።

የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች፡-
ንግድ ባንክ (CBE)
1000580802684
አባይ ባንክ
2061011073393010
ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ
1830758700001
ሂጅራ ባንክ
1009072710001
ዘምዘም ባንክ
0035717820101
አቢሲኒያ ባንክ
45534529

የሂሳብ ስም፡- መካሻው አብደላ ሙሀመድ (Mekashaw Abdela Muhammed)

አንድት የሱና እህታችሁ የጭንቅ መልዕክት!
Forwarded from DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ] (Muhammed Fedlu [Abu Nuh])
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات
አስደሳች ለሊት ወላህ ! አላህ ያስደሳቹ ! በተለያየ አለም ያላችሁ ውድ ሰለፊ እህት ወንድሞቻችን አላህ ከክፉ ነገራቶች ሁሉ ይጠብቃችሁ።🤲 መልካም ለሊት ! ጥር 2/2018 ከለሊቱ 6:31
ኢብኑ ሐዝም እንዲህ ይላሉ፡

"ለጓደኛህ ነፍሱን የሚጎዳውን ፣ በማወቁ የማይጠቀምበትን ነገር አትንገረው። ይሄ የወራ ^ ዶች ተግባር ነው።"
[ረሳኢሉ ኢብኒ ሐዝም፡ 106]

=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
በህይወት ዘመንህ ልታዳብራቸው ከሚገቡህ ብልሃቶች አንዱ፣ ሰዎች ስላንተ የሚናገሩትን ነገር አልፎ የመሄድ ብልሃት ነው። ብንወድም ባንወድም፣ ወደ እኛ ደረሰም አልደረሰም፣ ሰዎች ስለእኛ ጤና ቢስ ነገር ከመናገር  ወደ ኋላ አይሉም።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
መቸም እንደማንለያይ እርግጠኛ ከሆንባቸዉ ሰዎቸ  ጋር  አሁን እንደማይተዋወቁ ሰዎች እየተላለፍን ነዉ።

#አይገርምም
=
t.me/https_Asselefya1
𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ክብርሽ በመህርሽ ብዛት አይለካም ~ •በአሁኑ ዘመን ብዙ እህቶቻችንና ቤተሰቦቻቸው ዘንድ አንድ የተሳሳተ አመለካከት ስር ሲሰድ ይስተዋላል። ይኸውም የሴት ልጅ ክብር፣ ማንነትና ውድነት የሚለካው በሚጠየቅላት የመህር (የጥሎሽ) ብዛት እንደሆነ ማሰብ ነው። ብዙ የተከፈለላት የከበረች ናት፣ ትንሽ የተከፈለላት ደግሞ እንደ ርካሽ ትቆጠራለች የሚል ሚዛን የሌለው አስተሳሰብ። ግን እውነት ነገሩ እንደዛ ነውን?…
• እንድህ ያስማማናል! ግን እከሌ በኪታብ፣በቁርአን አግብታለች እና አንችም አይባልም! ተመካክሮ በመጠነኛ መህር መስማማቱ መልካም ነዉ። ግን በቂ ማስተዳደሪያ ነገር ሳይኖረዉ በኪታብ ወይ በቁርአን ላግባ ብሎ ልጅቷ መጨቆን አግባብ አይደለም። ከመህር ይልቅ ከጋብቻ በኋላ መተዳደሪያዉ ላይ ጠንክሩና ስሩ ወንዶችዬ! ዋናዉ እሱ ነዉና! ሴት ልጅ ማቅበጥ፣ ማዝናናት፣ መንከባከብ..ተማሩ! አብዘሀኛ ወንዶች ሴት እንዴት እንደምትያዝ አያቁም። ገንዘብ ትወዳለች ብቻ የሚሉ! ሴት ከገንዘብ ይልቅ ፍቅር የሚሰጣትን የሚንከባከባትን ነዉ የምትወደዉ እሺ።

=
قُدوَتي الصَحَابِيَاتْ🎀
ነዓም ይህ ያስማማናል!! ከሁሉም በላይ ወንድሞችም ሆናችሁ እህቶችም በደንብ ዝግጅትና በራሳችን ላይ መስራት ያለብን ከመህሩ በላይ በዲናችን ላይ ያለን ጥንካሬ እንዲሁም ትዳሩ ላይ ከገባን ቡሀላ የህይወታችን አጋር ለምንለው ምን የምንመኘውንና ከአሰብነው በላይ ያማረና የሰመረ ትዳር መኖር እንድንችል የሚያደርገንን የእውቀትንና የአስተሳሰባችን ብልሀት ላይ ብሎም የተግባር ሰው ለመሆን በራሳችን ላይ በደንብ እንስራ…
ነዓም ይህ ያስማማናል!! ከሁሉም በላይ ወንድሞችም ሆናችሁ እህቶችም በደንብ ዝግጅትና በራሳችን ላይ መስራት ያለብን ከመህሩ በላይ በዲናችን ላይ ያለን ጥንካሬ እንዲሁም ትዳሩ ላይ ከገባን ቡሀላ የህይወታችን አጋር ለምንለው ምን የምንመኘውንና ከአሰብነው በላይ ያማረና የሰመረ ትዳር መኖር እንድንችል የሚያደርገንን የእውቀትንና የአስተሳሰባችን ብልሀት ላይ ብሎም የተግባር ሰው ለመሆን በራሳችን ላይ በደንብ እንስራ ሲቀጥል ወንድሞች ከመህሩ በላይ ንግስትህን ከአስገባሀት ቡሀላ የምታስተዳድርበት አቅምና ልከኛም ቢሆን የኑሮ ደረጃ ይኑርህ በኪታብ ወይ በቁርአን ብሎም በመፋቂያም ቢሆን እንኳ የምታገባት የማስተዳደር የምትመግባትና የምትንከባከባት የኑሮ አቅም ከሌለህ ልከክልሽ እከኪሊኝ ነው የሚሆነው ትዳሩ ያሁሉ የታሰበውም ፍቅር ጠፍቶ መጨቃጨቅና ያም እንኳ ባይኖር ስደትን እንደመፍትሄ አርጋችሁ ሂደሽ የተወሰነ ሰርተሽ ትመጪያለሽ ህይወታችንን ለማቅናት ወዘተ.... እየተባለ ሁለት ልቦች እየተነፋፈቁ የርቀት ትዳርና የናፍቆት ስቃይ ውስጥ የሚገባው ከምንታዘበው ነው ዳሰስ ያረግነው እንጂ አቅሙ ሳይችል ኡስታዝ ስለሆነ or የሚዲያ ሰው ስለሆነ ብቻ በኪታብና ቁርአን እየተባለ ኒካህ ተሳስሮ ስንቱ ህይወቱ እየተመሰቃቀለ እንዳለ ለሁላችንም አይሠወርምና አሏህ ለኛም ለእናተም ከሱ ዘንድ ስጦታ የሆነን ያማረ የትዳር ህይወት ይወፍቀን ጨርሻለሁ🙌🙌🙌

=
t.me/Qudwatii1/2124
ሁሉም ሙእሚኖች የአላህ ወሊዮች ናቸው። እንደ ኢማናቸው ጥንካሬ እና እንደ ተቀዋቸው ልዩነት የወሊይነት ደረጃቸው ይለያያል።

=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor