💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
➲በኒቃብ የተሸፍፈኑ ዉብ ሴቶች አምሳያ በደመና የተሸፈነች ፀሀይ ነች። ደመናው ጸሀይነቷን እንደማይነጥቃት ሁሉ ኒቃባቸው ትክክለኛውን ዉበታቸውን አያሳጣቸውም!!

🔖ያኦኽቲል ጋሊህ በኒቃብሺ ሺፍን በይ💎!

➣ t.me/Basmat_Salafiya1
القارئ أسامه الغانم | الذين عاهدت منهم
💭🌸خدمة تلاوات🎧​
🌾⛅•|تلاوة صباحية|•⛅🌾

﴿ٱلَّذِينَ عَـٰهَدتَّ مِنْهُمْ ثُمَّ يَنقُضُونَ عَهْدَهُمْ فِى كُلِّ مَرَّةٍۢ وَهُمْ لَا يَتَّقُونَ ۝٥٦﴾

=
ዋሽቶ ማስታረቅ እና ዋሽቶ ማጣላት
~
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

ليسَ الكَذَّابُ الذي يُصْلِحُ بيْنَ النَّاسِ، فَيَنْمِي خَيْرًا، أوْ يقولُ خَيْرًا
​"በሰዎች መካከል ለማስታረቅ ሲል መልካምን ነገር የሚያስተላልፍ ወይም መልካምን ነገር የሚናገር ሰው ውሸታም አይደለም።"

[አልቡኻሪይ፡ 2692] [ሙስሊም፡ 2605]

መልእክቱ ምን ማለት ነው?
=
የተጣሉት ሰዎች መሀላቸው ቅሬታ ባለበት ሁኔታ ላይ፣ አስታራቂው አካል አንዳቸው ለሌላው ጥሩ እሳቤ እንዳላቸው የሚጠቁሙ ቃላትን ዋሽቶ በመናገር ማስታረቅ ሊሆን ይችላል፣ ለምሳሌ። በሌላ ቦታ ከባድ ጥፋት የሆነው ውሸት እርቅ ለማውረድ ያህል ብቻ ተፈቀደ ማለት ነው።

ዋሽቶ የሚያጣላስ ከሆነ? ሁለት ከባባድ ወንጀሎች አለበት።
አንደኛው መዋሸቱ ነው። ሌላኛው ማጣላቱ ነው። ባልን ከሚስቱ ዋሽታ የምታጣላ ስንት እህት፣ ስንት እናት አለች?! አንድን ወንድ ከእህቱ፣ ከእናቱ ዋሸታ የምታራርቅ ስንት ሚስት አለች?! ጓደኛን ከጓደኛ በውሸት የሚያራርቅ ስንት ሰው አለ?! አላህ ማስተዋልን ያድለን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
↙️ بابُ خِصَال المَرأَةِ الصَّالِحَةِ
ዉድ ሞክሼዎቼ ሆይ በጣም እየሳሳሁላት ከእናንተ አይበልጥም ብዬ ሰጠኋችሁ ዉሰዱ🤝 ሞክሸዎቼ ብዙ አላህ ያብዛችሁ 🌹💎🌸
سيظل الحجاب فرضًا ولو خلعته كُل النّساء.

« ሁሉም ሴቶች ሒጃብን አውልቀው ቢጥሉም እንኳን የሒጃብ ግዴታነት ሁሌም የፀና ነው። »

#ትክክለኛው ሒጃብ

منقول
=
t.me/https_Asselefya1
"አንድ አይን ያለው በአይን አይቀልድም" ይባላል፤ አንተም አንድ ህይወት ነው ያለህ፤ አላህ በሰጠህ ዕድሜ ያመንክበትን ማድረግ አለብህ! "እኔኮ አልችልም! ይሄ ይጎድለኛል! እድል የለኝም!" እያልክ እስከመቼ ትቀጥላለህ? አንድ ሰው አስተሳሰቡን ሲቀይር ሁሉ ነገሩ ይቀየራል!

=
t.me/https_Asselefya1
إبراهيم مدهش المنصري
{ مَنْ خَشِيَ الرَّحْمَنَ بِالْغَيْبِ وَجَاءَ بِقَلْبٍ مُنِيبٍ }


=
ህይወት መርፌ ብትሆን፤ ሪዝቅህ በቀዳዳው ወደ አንተ የሚመጣ ክር ይሆናል። ብቻ አንተ áŠĽáˆ­áŒáŒ áŠ› ሁን፣ተረጋጋ!! አላህ ላንተ የፃፈው ያንተ ይሆናል፤ ለሌላ ሰው የፃፈውን ደግሞ መቼም አታገኘውም!!

አብሽሩ!!
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
ቃላት መድኃኒት ናቸው!

ሰሞኑን በደረቴ አንድ ጎን ላይ እንደ ስንጥር የምትወጋኝ  ህመም ስሜት ነበረች። እኔ ነገሩን ቀለል አድርጌ ብመለከተውም፣ሚስቴ ኡሙ ሱፍያን ግን «በፍፁም! ሀኪም ቤት መሄድ አለብን!Âť ብላ ቸክ አለች። እኔም ተስማምቼ ሰፈራችን ወደሚገኝ አንድ ክሊኒክ አመራን።

ክሊኒኩ ውስጥ ለሀኪሙ የሚሰማኝን ስሜት ማስረዳት ጀመርኩ። ገና ንግግሬን ሳልቋጭ፣ ቃላቶቼን ከአፌ ቀበል ብሎ፣ ምንም አይነት አካላዊ ምርመራ ሳያደርግልኝ እንዲህ አለኝ፦ «ይመስለኛል በደረትህ አካባቢ ያሉት ቀጫጭን አጥንቶች (Rib fractures) ተሰብረዋል። ጉዳዩ ከባድ ከሆነ ቀዶ ጥገናም ሊያስፈልግህ ይችላል!» አለኝ።

ይህን ሲናገር ከጎኔ ተቀምጣ በጭንቀት የምታዳምጠው ሚስቴ በጣም ደነገጠች።  ሀኪሙ ደረቴ ላይ የራጅ (X-Ray) ምርመራ እንዳደርግ ደብዳቤ ፅፎልን ወደ ሌላ ቦታ ሄድን። የራጅ ውጤቱ ሲመጣ አልሀምዱሊላህ! አልን፤ ደረቴ ፍፁም ንፁህ እና ጤነኛ ነበር።

ከምርመራው ውጤት ንፅህና በላይ፣ በልቤ ውስጥ የከበደኝ ግን የሀኪሙ የቃላት አጠቃቀም ነበር። አንድ የህክምና ባለሙያ በግምት ላይ ተመስርቶ፣ የታማሚን ስነ ልቦና ከግምት ሳያስገባ እንዴት እንደዚህ አይነት ልብ የሚያሰብር ንግግር ይናገራል? «አስኪ ለማንኛውም ውጤቱን እንየው» የሚል ተስፋ የተሸከመ ቃል ለምን ተሳነው? ለምን ያለ አንዳች ምርመራ ስለ ቀዶ ጥገና ማውራት አስፈለገው? መናገርስ ካለበት ከጎኑ ያለው ሰው ይደነግጣልና ሌላ ሰው ይውጣ ብሎ መናገርስ የለበትምን!?

የዚህ ጽሑፍ መልዕክት !
በየትኛውም የሙያ መስክ ላይ ሆናችሁ ሰዎችን የምታገለግሉ ወገኖቼ ሆይ! አደራችሁን በቃላቶቻችሁ የሰዎችን ልብ ጠግኑ። በንግግራችሁ ተስፋን ዝሩ። ኢማም አር-ራዚ እንዳሉት ፦
«ሀኪም የሆነ ሰው፣ የታማሚው ሁኔታ ከባድ መሆኑን ቢያውቅ እንኳ ለሚያክመው ሰው ተስፋ መስጠት ይኖርበታል።» ይላሉ። ምክኒያቱም ሰውነት ለጥሩ ቃላት ሳይታሰብ አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጥበት ጊዜ አለና።

አንዳንድ ሀገራት የመድኃኒት ማዘዣ ወረቀታቸው (ፕሪስክሪፕሽን) ግርጌ ላይ «አብሽር! በቅርብ ጊዜ ውስጥ  ይድናሉ»፣ «አይዞን ፈጣሪ ከእርስዎ ጋር ነው!Âť የሚሉ እና መሰል አጫጭር የፅናት እና የተስፋ መልዕክቶችን ይፅፋሉ። ይህን የሚያደርጉት በአካል ከመዳን በፊት የስነ-ልቦና መዳን ወሳኝ መሆኑን ስለሚያውቁ ነው።

እናማ ቃላት መድኃኒት ናቸውና ሰዎችን ፈውሱባቸው!
✈️ t.me/AbuSufiyan_Albenan
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM