💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
➲ቻት ዘመነኛው የሸይጧን ወጥመድ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

ሸይጧን በቻት አመካኝነት ብዙ ጠንካራ የሚባሉ ወንድም እና እህቶችን አንበርክኳል

➛በቻት ምክኒያት አሏህን እንዲያምፁ አድርጓል በቻት ምክኒያት ብዙ ሒሊናቸውን ጭምርት የሚያቆሽሽ ቀፋፊ ተግባር እንዲፈፅሙ አድርጓል
!!

➽በኒቃቧ ተሽፍና ከሰፈሯ ጋጠወጦች የተጠበቀችውን እህት ሸይጧን ቻት በሚባለው መርዛማ ወጥመዱ ጥልፎ ከማታውቃቸው ሌሎች ጋጠወጡች ጋር እንድትንዘላዘል ሰበብ ሁኗታል!!

መልካሙ የሚጠበቅለትን ለሌሎች መካሪና አርአያ ነው ተብሎ የሚታሰበውን ጀግና ወንድም ሸይጧን በቻት ምክኒያት ማጥመድ ችሏል!!

ወንድሜ ካልተፈቀደች ሴት ጋር ቻት ማውራት አይፈቀድም! ሴሜትህን የማይመቸውን ሀራም ብቻ እየመረጥክ አትራቅ ሀራም ሀራም ነው። ማንኛውንም ጌታህን የሚያስቆጣ ነገር ራቅ
!

➽አንዳንዶች ካልተፈቀደች ሴት ጋር በቻት ማውራት አይፈቀድም ሲባሉ ኧር እሷን እኮ እንደ እህቴ ነው የማያት!
ኧርሱንኮ እንደ ወንድሜ ነው የማየው በማለት ይመልሳሉ

ግን እሄ አባባል ብዙዎች ያልባነኑበት ሌሎቹ ደግሞ ገብቷቸው ነፍስያቸውን ማሸነፍ ተስኗቸው የተንበረከኩበት ሌላኛው የሸይጧን ወጥመድ ነው።

➢ለማንኛውም የአሏህን ውደታ ነፍስያችንን ከመኽለፍ ጊዜያውይ ስሜታችንን ረግጠን ከመያዝ ጀርባ ስለሆነ የምናገኘው ከማንኛውም ያልተፈቀደ ቻት እራሳችንን በማቀብ ወደአሏህ እንመለስ?

➽ወንድሜ አንችም እህቴ በሀራም የሚገኝ ደስታ አይቆይም ያልፋል ይረሳል ግንሳ ወንጀሉ አላህ ዘንድ አይረሳም በሗላም በእዝነቱ ካላዘነልን ሒሳቡና ቅጣቱ አይቀርም!

➥ጊዜህን ገንዘብህን አባክነህ ከዚህም በላይ ሸይጧንን ታዘህ ጌታህን አስቆጥተህ ያወራሀት ሴት ሌላ ካንተ የተሻለ አፈቀላጤ ቅቤ አንጓች አዛኝ መሳይ ስታገኝ ትታህ ወደሱ ዘወር ትላለች ከትንሽ ቆይታም በኋላ ትረሳሀለች


➲አንችም እንደዚያው ክብርሽን ጥለሽ ጌታሽን አስቆጥተሽ ጊዜና ገንዘብሽን አባክነሽ ጊዜያዊ ስሜትሽን ማሸነፍ ተስኖሽ የምታወሪው ወንድ ሌላ ሲያገኝ ጥሎሽ ዘወር ነው የሚለው በመጨረሻም አይደለም ቻትሽን ይቅርና ከነመፈጠርሽ ነው የሚረሳሽ


አሏህ ከሌሎች ተደብቀን የምንፅፈውን ማንኛውንም ፅሁፍ እንደሚያውቅ እንወቅ

« أَلَمْ يَعْلَم بِأَنَّ اللَّهَ يَرَىٰ»
"አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?"

ቀደምቶች እንድህ በማለት ይመክራሉ
"በግልፅ የአሏህ ወልይ(ወዳጅ) በድብቅ የሸይጧን ወዳጅ አትሁን"

አዎ እያወራሁ ያለሁት ይሻላሉ ስለሚባሉ ወንድም እና እህቶች ነው
።

➤ሸይጧን በሌላ በር እነርሱን ማጥመድ ሲሳነው በቻት ቀላል የማይባሉትን እንዳጠመደ የሚታወቅ ስለሆነ እሄን የሸይጧን ቀዳዳ በመዝጋት ወደጌታችን እንመለስ የድብቅ ወንጀል መጨረሻው አደጋ ስለሆነ በጊዜ ወደአሏህ እንመለስ ላለፈው ጥፋታችን ምህረትን እንጠይቀው ለማለት ነው
።

​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
✍ ወንድማችሁ/ ኢብኑ ሙሐመድዘይን

➽ቢረዝምም አንብቡት ይጠቅማችኃላ አላህ ካዘነልን በስተቀር ብዙዎቻችን በዚህ ነገር ስለተጠመድን አላህ የሂድያ ሰበብ ቢያደርግልን
!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የአልዋጂባት ሸርህ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

◾️የሽርክ አደገኝነትና ክፋት
🩸ስራን ውድቅ ያደርጋል
🩸ጀሀነም ያስዘወትራል
🩸ጀነትን እርም ያደርጋል
🩸ካልቶበተ አላህ አይምረውም

【ክፍል 3⃣7⃣】
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲የመውሊድ በዓል በዲን ውስጥ የተጨመረ (ቢደአቱል ሀሰና) መልካም ቢድዓ ነው ይላሉ…
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

ነገር ግን…

➻የላቀው አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡- 
«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ።»
📕[አልማኢዳህ: 3]

➧በዲን ውስጥ (በዲአቱል ሀሰና) መልካም ቢድዓ አለ ብለው ይናገራሉ

➽ነቢዩ  ግን ይህን ይላሉ፡- 
«ሁሉም የቢድዓ ተግባር ጥመት ነው።»
📕[ሶሂህ ሱነን ኢብኑ ማጃህ (42
)]

➧በዲን ውስጥ በዲአቱል ሀሰና መልካም ቢድዓ አለ ብለው ይናገራሉ

➲ታላቁ ሰሗባ ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዓንሁማ እንዲህ ይላል
፡- 

«ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው! ሰዎች መልካም ነው ብለው ቢያስቡትም።»
📕[ኡስውሉ አልኢቲቃድ (11/50)]



➧በዲን ውስጥ በዲአቱል ሀሰና መልካም ቢድዓ አለ ብለው ይናገራሉ

➲ታላቁ ሰሗባ አብደላ ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ አንሁ እንዲህ ይላሉ፡- 

«ተከተሉ አትፍጠሩ በርግጥም በመደንገግ ጉዳይ ላይ ተብቃቅታችሗል።»
📕[ዙሁድ ሊአህመድ (896
)]


➧በዲን ውስጥ በዲአቱል ሀሰና መልካም ቢድዓ አለ ብለው ይናገራሉ

➲ረሱል  ግን እንዲህ ይላሉ፡- 

«በቂያማ ቀን ሀውዳቸውን ለመጠጣት የተሰለፉ ሰዎችን ቢድዓ በመፍጠራቸው የተነሳ ከኔ በኋላ በዲን ውስጥ አዲስ ነገር ያመጣ ከኔ ራቅ ከኔ ራቅ በማለት ጀርባ ይሰጡሃል።»
📕
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

➻በዲን ውስጥ በዲአቱል ሀሰና መልካም ቢድዓ አለ ብለው ይናገራሉ

➲ታላቁ ኢማም አቡ ሐኒፋ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-  «አደራህን በሰለፎች የዲን ፋናና መንገድ ላይ። እንዲሁም ከሁሉም የቢድዓ ተግባርና የፈጠራ መንገድ አደራህን ተጠንቀቅ።»
📕[ዘም አልተዕዊል ሊኢብኑ ቁዳማህ (13)]

➧በዲን ውስጥ በዲአቱል ሀሰና መልካም ቢድዓ አለ ብለው ይናገራሉ

➲ታላቁ አሊም ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- 

«በኢስላም ውስጥ መልካም ናት ብሎ የሚያስባትን ቢድዓ የፈጠረ ሰው ሙሐመድ ተልእኳቸው ላይ ሸፍጥ ሰርተዋል ብሎ እየሞገተ ነው።»
📕[አልኢቲሳም ሊሻጢቢዪ (1/64
)]


⛔️የመውሊድ በዓልን ከማክበር ተጠንቀቁ በሰለፎች ፋናና መንገድ ላይ አደራችሁን አላህ ለመልካሙ ሁሉ ይግጠማችሁና!!

ኮፒ የተደረገ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➻ውድ እህቴ!

ጉዞሽን ቀጥይ በተውሒድ በሡና
አደራ እዳወጭ ከሐሀቁ ጎዳና

በዚሕ ዘመንማ አሁን ባለንበት
ሡና ተደብቆ ቢደዓ ነግሦበት

ባጢሉ ተሥፋፎቶ ሐቁ ባነሠበት
የባጢል እረኞች በተሰራፉበት


ተውሂድ እና ሡናን አጥብቀሽ ያዥ ና ቢደዓን ራቂ
በሠለፎች መንገድ በሡና ታቅበሽ በነሱ ተብቃቂ።


https://t.me/Asselefya1
Kitabu Tewhid #42
Ibnu Munewor
↪️ ተከታታይ የኪታቡ ተውሒድ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ ክፍል 4⃣2⃣↩️
〰〰〰〰〰〰

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔻حفظه الله تعالى
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የአልዋጂባት ሸርህ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖

✅ ኡለማዎች በመእስያ መታዘዝ
✅ የሽርክ አስከፊነትና ድብቅነት

🔻【ክፍል 3⃣8⃣】
〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
✅ የመውሊድ በአል ቀን፦
▪️ስጦታ መሰጣጣት
▪️እንኳን አደረሰን መባባል
▪️ለመውሊድ የታረደ ስጋ መመገብ
▪️በመውሊድ ዝግጅት ላይ መገኘት
▪️ለመውሊድ ተብሎ የተዘጋጀ ምግብ በተመለከተ

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
"ቁርኣንንና ሱናን ከታጠቅክ በጭራሽ አትሸነፍም ፡፡

➻ ነገር ግን እውቀት ከሌለህ!
መጀመሪያ ከሰማኸው ማምታቻ ጋር!
አብረህ ትነጉዳለህ !"

🖋《ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን》
【አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል አላህም በምትሠሩት ሁሉ ወስጠ ዐዋቂ ነው።】

📖(አልሙጃዲላህ፡11)
➲የላኢላሀ ኢለሏህ ዋጋና ትሩፋቶቿ!!
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➻ክፍል 2

➽ላኢላ ሀኢለሏህ ከዚክር ሁሉ በላጩ፣ከንግግርሁሉ በላይ ነች። ነብዩ ሰለሏህ አለይሒ ወሰለም እንድህ ይላሉ፦ {ከዱዓ ሁሉ በላጩ የዐረፍ ቀን ዱዓ ነዉ። እኔም ከኔ በፊት የነበሩ ነብያትም ከተናገርነዉ ሁሉ በላጩ ላኢላሀ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሑል ሀምዱ ወሁወ ዕላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር የሚለዉ ነዉ።

[አስሶሒሐ፡ 1503}

➽ ላኢላ ሀኢለሏህ ለወንጀል መርገፍ ሰበብ ነች። መልዕክተኛዉ ሰለሏህ አለይሒ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦{እርግጠኛ በሆነ ልቦና ከአሏህ በስተቀር የሐቅ አምላክ እንደሌለና እኔም የአሏህ መልዕክተኛ እንደሆንኩ የምትመሰክር ነፍስ አትሞትም፣ አሏህ ለሷ የማረላት ብትሆንጂ
።}

[ አስሶሒሐ ፡2278]

➽ ላኢላ ሀኢለሏህ የመልካም ስራ ሚዛን ትደፍለች። ነብዩ ሰለሏህ አለይሒ ወሰለም እንድህ ይላሉ ፦{በቂያማ ቀን የሆነ ሰዉ ከህዝብ መሀል ይጠራል።ከዚያም ዘጠና ዘጠኝ(የወንጀል) መዝገቦች ይበተኑለታል። ከዚያም የላቀዉና ከፍ ያለዉ አሏህ ከነዚህ የምትክደዉ አለህ? ሲለዉ የለም ጌታየ ይላል።ጠባቂ ፀሀፊዎቼ(መላዕክቱ በድለዉሀልን? ሲለዉ አልበደሉኝም ጌታየ ይላል
።

ከዚያም(መዳኛ) ምክንያት አለህ? መልካም ስራ አለህ? ሲለዉ ሰዉየዉ ይፈራና የለኝም ይላል። ይህኔ አሏህ'እንዴታ እኛ ዘንድ መልካም ስራ አለህ። እነሆ ዛሬ በደል የለብህም ይለዋል። አንዲት ከአሏህ በስተቀር የሐቅ አምላክ የለም፣ ሙሐመድ ደግሞ ባሪያዉና መልዕክተኛዉ ናቸዉ' የሚል ያለበት ካርድ ትመጣለች።

➥ጌታዬ ሆይ ከነዚህ መዝገቦች ጋር ይች ትኬት ምን አላት?ይላል ። በርግጠኝነት አትበደልም። ይለዋል አሏህ። ከዚያም መዝገቦቹ ይቀላሉ፣ካርዷ ደግሞ ትከብዳለች
።

(ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 8095)

➽ ላኢላ ሀኢለሏህ ጀነት ለመግባት ወሳኝ ሰበብ ነች። ነብዩ ሰለሏህ አለይሒ ወሰለም እንድህ ይላሉ፦[ከአሏህ በስተቀር የሀቅ አምላክ እንደሌለና እኔም የአሏህ መልዕክተኛ እንደሆንኩ እመሠክራለሁ ። አንድ ባሪያ እነዚህ ምስክርነቶች ምንም የማይጠራጠር ሆኖ ከአሏህ ጋር አይገናኝም፣ጀነት የሚገባ ቢሆንጂ።]{መስሊም፡147
}

¶ክፍል _3 ይቀጥላል ኢንሻ አሏህ

➢ተዉሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ ከሚለዉ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ
ከገፀ103___104 የተወሰዴ!!

🖊𝑢𝑚𝑢 𝑢𝑠𝑒𝑦𝑚𝑖𝑛

https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የአልዋጂባት ሸርህ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖

✅ የሽርክ አይነቶች
✅ የትልቁ ሽርክ ክፍሎች

🔻【ክፍል 3⃣9⃣】
〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
30 ኢና ኩና ፊ ጃሂሊያ ሊሸይኽ ሷሊሕ አል—ፈውዛን
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖

↪️ኢና ኩና ፊ ጃሒሊያ

↪️ አዘጋጅ ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን

◾️ክፍል 3⃣0⃣
〰〰〰〰〰

🎙 በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
3⃣✍ ከሚከተሉት ውስጥ ነብዩ ይህ ኡማ ለ73 ይከፈላል ካሏቸው ከጥመት ቡድኖች ውስጥ የሚመደበው የቱ ነው⁉️
Anonymous Quiz
9%
ኢህዋነል ሙስሊሚን
3%
አህባሺ
4%
ሶፍያ
2%
ጀመአተል ተብሊግ
2%
ዳኢሺ sis (ተክፊሪይ)
80%
ሁሉም