💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
∙ አንዳንድ ጊዜ ....

መጨረሻ ነዉ  ብለን እናስባለን  ነገር ግን በድንገት «አላህ ሁሉንም ነገር»ያስተካክላል።

=
t.me/https_Asselefya1
እያስተዋላቹህ!!


ልታገባው ነበር ነገር ግን "ከታማኝ ምንጭ" ባገኘችው መረጃ ሰውዬው በገንዘቡም በጤናውም ሆነ በፀባዩ ለትዳር አይሆንም ። ከዚያም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሰውየው ማግባቱን ሰማች ።

ማግባቱ አይገርምም ነገሩ ግን ወዲህ ነው ። ሰውየው ያገባው "ታማኝ ምንጯን" ነው
 የሶብር አይነቶች
Ibnu Munewor
የሶብር አይነቶች!

- የአላህን ትእዛዝ በመፈፀም ላይ መታገስ
- የአላህ ክልከላዎች በመራቅ ላይ መታገስ
-አሳማሚ በሆኑ የአላህ ዉሳኔዎች ላይ መታገስ

╭┈──── ••⇣⇣
╰┈➢ t.me/https_Asselefya1
የነገረኛ ሰው ጥፋት
ኢብኑ ሙነወር
በትዳርም ሆነ በጓደኝነት መካከል እየገባችሁ የምታራርቁ ምቀኛ፣ሸረኛ፣ተንኮለኛ ሰወች ተገሰፁበት ከክፉ ስራችሁ ተቆጠቡ ምንም አታተርፉበትም።

t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
❝አንበሳ እና ነብሩ❞
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
👉ለሸይኽ አወል እና ለዑስታዝ ኸድር ከሚሴ ሀፊዞሁሙሏህ

«አንበሳ እና ነብሩ»
----------------------
ፈጥነው እንደ ሌሎች ክፉ አይናገሩም ፡
የኔን ብቻ የሚል ሙሪድ አያፈሩም፡
ዕውቀት ፍለጋ እንጅ ከቶ ፊትና አይመሩም፡
በማንም ላይ ቢሆን በደልን አይሰሩም፡
የፊትና አራጋቢ ውርጋጥ አይቀጥሩም፡

እኔን ተከተሉኝ ብለው አይደነፉም፡
ከዕውቀት ገበታ ጧትም ማታ አይጠፉም፡
መጓዝ የፈለገን አያወላከፉም፡
እኔን ምሰል ብለው ማንንም አይለክፉም፡

የሰለፍያ ልጅ ውድ የተውሒድ ፈርጦች
የወሎ ላይ ተክል የከሚሴ ምርጦች፡
ፈጥኖ የገባቸው የሰውነት ክብሩ፡
ጀግኖቻችን ናቸው አንበሳና ነብሩ፡

...በኑረዲን አል-ዓረብ

t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
"ወንድሜ"

«ላታገባት ባዶ ተስፋ አትስጣት
«ላታገባት አለሁሽ አትበላት
«ላታገባት አትዋሻት
«ላታገባት እንደ ምርጫ አትጠቀማት

እህት አለህ አይደል በእህትህ ላይ እንደርስ የማትፈልገውን አንተ በሰው እህት ላይ አታድርስ።

«ላታገባት አትዋሻት  የቃላት ድርደራ በመሀላ ብዛት አታሳምናት አላህን ፍራ ውሸት አኗኗርን ቀርቶ አሟሟትን ያበላሻል እባክህ ወንድሜ በሴት ልጅ እድሜ አትጫዎት ነገ ሴት ልጅ ትወልዳለህ በቃ እውነቱን ንገራት አማራጭ አታድርጋት እባክህ አላህን አፍራ !! ነገ አላህ ፊት እራቁት መቅረብ አለና አስተውል በቃ አትዋሽ !

منقول
=
t.me/https_Asselefya1
«በትግስት___ጠብቃት!

የ
ህልም ንግስትህን እንዲህ ስትናፍቃት
የተፃፈዉ ደርሶ እስከ ምታገኛት

አደብ በልና በሰብር ጠብቃት
ዉስጥህን አዘጋጅ ዉድዬ እስክትመጣ
መሸከም እንድትችል የትዳርን ጣጣ

እስከዛዉ ግን ታገስ
የትም አትልከስከስ

የሰዉ ልብ አታውልቅ
አላማህን እወቅ

የዲን እህትህን ጊዜም አትሻማ
ላትሆንህ ላትሆናት መንፈሷን አታድማ

ያችንም ያችንም ላይሆን ቃል አትግባ !
ላንተም ደግ አይደለም የእህቶችህ እንባ!

ሰላምክን ታጣለህ ትዳር ስትገነባ!
የተለያየ ሴት ፀባይ መልክ ማየቱ

ቤትህን ይንደዋል ከነ መሰረቱ
ስለዚህ ወንድሜ የሰዉ ጊዜ አትግደል!
የተበዳይ ዱዐ እንዳይሰድህ ገደል!

አላህ ያለው ደርሶ እስከ ምታገኛት!
ኢማንህን ሰንቀህ በትግስት ጠብቃት!
አላህ ያለው ደርሰ እስከ ምታገኛት!


منقول
╭┈──── ••⇣⇣
╰┈➢
t.me/https_Asselefya1
አሁን ያለበት ገፀታ ሀገራችን ማለቴ ታች አንባ ☘

=
√ መጠለል እየቻሉ ግን ከናንተ ጋር ዝናብ ላይ የቆዩትን «ሰዎች» ምረጡ።

=
t.me/https_Asselefya1
النِّساءُ السَّلَفِيَّات أَغلَى مِنَ الذَّهَبِ الأَحمَر
Voice message
ወንዶቻችንን አታበላሹ ሰርተዉ እንዳይበሉ ወንድነት አታሳንሷቸዉ እረፉ በቃ! ጎበዝ ከሆንሽ ለቤትሽ ደጉሚ ግን ሙሉ አንች የሱ ቦታ አትያዥ አሃ¡¿ ለሁሉም ቦታ አለዉ ቦታሺ ላይ ተቀመጭ!
ባልን ወደ ሌላ ሴት አንድከጅል የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች አሉ ከነሱ መካከል፦
ለባል አለመዋዋብ፣ ባልን አለማክበር፣
ሁለየ በሆነ ባልሆነው ሲገባ ሲወጣ መጨቃጨቅ
ስራ ውሎ ሲመጣ ፊትን አኮሳትሮ
ሳይዋዋቡ መጠበቅ
የሚበላቸውን ምግቦች በፅዳት እና እድጣፍጡ አድርጎ አለመስራት
ሁለየ አሮጌ ልብስ ለብሶ ዝርፉጥፉጥ እዳሉ ተንጨብርሮ መጠበቅ
የራስ ንፅህናና የቤት ንፅህን አለመጠበቅ!!

እነዚህ ነገሮች ካሉብሺ ራስሺን ፈትሺ ባልሺ ጥሎሽ ወደሌላ ሳይሄድ!?
=
👉በግ.....ተኩላ.....እረኛ....!!

«ወዳጅህን ፍራ»

በጉ ሙሉ እድሜውን ይፈራል ተኩላ፡
ይሸሻል በስጋት በሱ እንዳይበላ፡
ይህ ነው የበግ ፀባይ የድሜ ልኩ ስጋት፡
ተኩላ ነው ነፍሱን ጭንቅ እሚያደርጋት፡

እረኛውንማ ጧት ማታ እያገኘው፡
አምኖት ስለነበር በክፉ አልተመኘው!?
በፍፁም በጭራሽ አልጠረጠረውም፡
ጠላቱ ነበረ ግን አላወቀውም፡
እረኛን መጠርጠር ለበግ አይገባውም፡

ጥንት የተሳለለት ተኩላ ነው ጠላቱ፡
እሱን ነው ያስረዱት እናቱም አባቱ፡
ግን ባያቅ ነው እንጂ ጠላት ነው እረኛ፡
የበግ ስጋ ወዳጅ በጣም ተንኮለኛ፡

ጠላት አበጀለት ተኩላ የሚባል፡
እረኛ አብሮ እሚኖር ወዳጅ ሆነ ደባል፡
ግን በመጨረሻ በእረኛ ይበላል፡
ባመኑት መከዳት አሁን ምን ይባላል⁉️

ወዳጂን መሸከክ አንጀት ባያስነፋም፡
የእምነትን ዋጋ ደረጃ ቢያጠፋም፡
ባለንበት ዘመን መጠርጠር አይከፋም፡

......እና ምን መሰለህ...⁉️

አንተም የበጉ እጣ እንዳይደርስህ ተራ፡
ባመንከው ተከድተህ ስህተት እንዳሰራ፡
ጠላትህን ሳይሆን ወዳጅህን ፍራ፡

በኑረዲን አል-ዓረብ


http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi