💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የሰዉ ልጅ የሚፈልገዉ አንድ ነገር መዘግየቱ ይሄ ለሱ ኸይር ነዉ።

መረጃዉም የላቀዉ አላህ ቃል ነዉ፦

وَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰ أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

" አንዳች ነገርን እርሱ ለናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም ነገር እርሱ ለናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም (የሚሻላችሁን) ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም፡፡

=
t.me/https_Asselefya1
∙ እያንዳንዱ ቀን አዲስ ጅምር ነው! ትላንትና የነበረው ትላንትና ቀረ ዛሬ አዲስ ቀን ነውና በአዲስ መንፈስ ጀምሩት።

#صباح الخير
=
ወዳጆቼ...

• አላህ ለግፈኞች ያዘገያል እንጂ አይረሳም፤
• ከዕድሜህ ዓመታትን የነጠቀህን አላህ የሚነጥቀው ይልክበታል፣
• አምነኸው ያጠቃህን ዝም ብለህ ጠብቀው ጀሊሉ ቀጠሮ ይዞለታል፤
• በሌለህ ነገር ያዋረደህን አላህ ኃያሉ ጌታ የሚያዋርደው ይሰድበታል፣
• በርካሽ ዋጋ የሸጠህን አላህ በቤሳቤስቲን የማይገዛዉን ያዝበታል፤ ይረክስና ዋጋው ይወድቃል፣
• ከጎኔ ይቁም ብለህ የተማመንክበት ቢሰርቅህ ይከብራል ብለህ አትጠብቅ፣

ሰው ሁሉ ባጠጣው ነገር ይጠጣል፤
ነገርኩህ እኮ…

~ በግፍ በፈታሃት ሴት ምክንያት አዲሱ የትዳር ዘመንህ እንደሚበላሽ እወቅ፣
~ በእውነተኛ ፍቅሩ ያላገጥሽበትን ወንድ መልሰሽ የምትለምኚበት ቀን ይመጣል፤
~ ምንም የማይሳነው ጀሊሉ አዋርደህ ባባረርከው ሰው ፊት መልሶ ያቆምሃል፤ 
~ ፊት የነሳኸዉን ድሃ አንድ ቀን በተራህ እርዳኝ ብለህ ትለምነዋለህ፤  
~ የገጠመህ አንገብጋቢ ጉዳይ በናቅከው ሰው እጅ ላይ እንደሚጥልህ ፍራ፡፡

ያስለቀሰህ ማልቀሱ፤ የካደህ መክካዱ ግድ ነው!

ቀልብ የተጎዳች እንደሆነ ሐቋን የሚመልስላት አምላክ፤ነፍስ ያዘነች እንደሆነ በደሏን የሚበቀልላት ጌታ አላት።

እናም ...ሳትበድሉ ዋሉ እደሩ።ጌታችሁ ረሺ አይደለምና ከበደል ተጠንቀቁ፡፡
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan
ገና ያላገባችሁት ወንድ በፍቅር ክንፍ ትሉና ከዛ ቲሸርት ኩባያ ስአት ላይ ስሙን እና ሌላ ተጨማሪ የፍቅር ቃሎች ፀፋችሁ ከዛ አሰርታችሁ ልክ ስትጣሉ ከዛ ከጠለባችሁ ቦታ አልወስድም የምትሉ አሃ!? እንደት ነዉ ነገሩ የእናንተ ሰዉ ፀሁፍ ቲሸርት እና ብርጭቆ ማ ሊጠጣበት ማ ሊለብስ ነዉ ዉሰዱ እና ስፈልጉ ልበሱት ካልሆነእንደፈለጋችሁ ኦላይ እየጠለባችሁ ነጋዴዎች አታስቸግሩ እሺ!!

ሲቀጥል ትክክለኛ ፍቅር ከኒካ በኋላ የሚመጣ ዉድ ነገር ነዉ እሺ። ደግሞም ፍቅር ብርጭቆ እና ቲሸርት ላይ በማሰራት አይገለፀም በልብ ላይ ነዉ የሚኖር የሚገለፀዉ በተግባር አብሮ ችሎ በመኖር በማክበር በመደማመጥ በመተሳሰብ በመታዘዝ .....ይመስለኛል ለኔ !

=
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ልብህ ዉስጥ ሀዘንን አታስገባ! በህፃን ጣፋጭ አንደበት ተግሳፀ !

=
አንዳንዴ የምንፈልገውን ለማግኘት ስንሮጥ ያለንን እናጣለን፤ ግን ሁሌም ህይወት በማግኘትና በማጣት ውስጥ ትኖራለች።

ሰዎች የሚፈልጉትን ለማግኘት ሲሉ የሚያስፈልገንን ሊያሳጡን ይችላሉ። አላህ ግን እንደሚያስፈልገን ስለሚያውቅ ይክሰናል። እናም እኛ እንደነሱ ክፉ መሆን የለብንም ይልቁኑ በነገር ሁሉ አላህን አመስጋኝ እንጂ።

ሁሌም ቢሆን ፍቅር ከሁሉም ነገር ይበልጣል።
ሰዎች ሲበድሉን በፍቅር እንካሳቸው። በደልን በበደል ከመለስን ግን የኛ በደል ከነሱ ይብሳል።
የፍቅር መስፈርቱ ደግሞ ፍቅር ብቻ ነውና።
           
=
t.me/https_Asselefya1
          ✍ጓደኝነት✍

ሁለት ተማሪ ጓደኛሞች የጠበቀ ወዳጅነት አላቸው፡፡ ወደ ትምህርት ቤትም ዘውትር አብረው ነው የሚሄዱት፡፡ አንደኛው ታዲያ የጓደኛውን ቦርሳ ተደብቆ በመፈተሽ ቼኮሌቱን የመስረቅ መጥፎ አመል ነበረበት፡፡
፡
አንድ ቀን በዚህ አመሉ ክፉኛ የጥፋተኛነት ስሜት ተሰማው እና ያደረገውን ሁሉ ለጓደኛው ሊናዘዝ ፈለገ፡፡ ነገር ግን በቀጥታ በጓደኛው ፊት ለመናገር ድፍረት አጣ፡፡ ስለዚህም ደብዳቤ ጻፈለት፡፡

‹‹እስከ ዛሬ ድረስ ከቦርሳህ ውስጥ ቼኮሌቶቹን ስሰርቅህ የነበርኩት እኔ ነኝ፡፡ ለዚህም በድርጊቴ በጣም ነው የማዝነው፡፡››

ጓደኛውም ደብዳቤውን ሲያነብ ሳቀ፡፡ መልሶ ሌላ ደብዳቤ ላከለት፡፡

‹‹ብዙም አትጨነቅ፡፡ ቼኮሌቶቹን ከቦርሳዬ ውስጥ አንተ እንደምትወስድ አውቅ ነበር፡፡ ለዚያም ነው ቼኮሌቶቹን በተመሳሳይ ስፍራ ሁሌም የማስቀምጣቸው፡፡›› ይላል፡፡
____
ስንቶቻችን እንሆን ጓደኛችን እያስቀየመንም ቢሆን ለጓደኝነት ጥንካሬ ስንል አይተን እንዳላየን ሰምተን እንዳልሰማን የምናልፈው???

ስንቶቻችንስ ለመጣላት እንሮጥ ይሆን እስኪ እራሳችን እንይበት፡፡


┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

      Ů…Ů†Ů‚ŮˆŮ„
ውሻ ቢነክስህ መልስህ ውሻውን አትነክሰውም፡፡#በህይውትክም የሚያጋጥሙህን መጥፎ ሰዎች እንዲሁ እለፋቸው፡፡ ዝም በላቸውና አንተ ከነሱ የተሻልክ መሆንህን #አሳያቸው፡፡

=
t.me/https_Asselefya1
ፈገግ በሉ‼️

ሽዓው

ያ አልይ አለ....

ኮሜንት ላይ አልይ የሚባል ወንድም

ነዓም ሀቢቢ ጠራኸኝ!?


በጣም ነው ያሳቀኝ

t.me/nuredinal_arebi
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሚወድህ ፦ ከአንተ ጥሩ ነገርህ ይፈልጋል !
የሚጠላህ፦ የአንተ ስህተትህ ይፈልጋል ትንሿ ልክ እንደተራራ ያደርጋታል!

الحب

=
t.me/https_Asselefya1
አንች ካመንሽበት ማረጋገጫ አትጠብቂ አዎ ሁሉም ሰው አንች የታየሽን አይታየውም አንች የተሰማሽን አይሰማውም ስለዚህ ራስሽን ብቻ አሳምኝ ለራስሽ ብቻ እርግጠኛ ሁኝ ከዚያም መንገድሽን ቀጥይ !!

منقول
አንዳንዴ ዲንገት መጥተዉ በሂወታችን ደስታ ሳቅ የሚዘሩ ልቦች ምንኛ የታደሉ ናቸዉ። ሰዉ አታሳጣኝ አይደል የሚባል። ሰዉ ይስጣችሁ !

መልካም ለይል ይሁንላችሁ !

=
ዛሬን አላህ ያማረ ቀን ያድርግልን በሰላም ስላሳደረንም ምስጋና ይገባው አልሀምዱሊላህ

           መልካም  ቀን

=
“የሰጠሁትን ቦታ በራሱ ጊዜ ላበላሸና ራሴን ከመውቀስ ለገላገለኝ ሰው ሁሉ ምስጋና አቀርባለሁ።” [ደርዊሽ]

አንዳንድ ሰዎች የተሰጣቸው ክብር እስኪደፈሩበት ድረስ አያውቁትም። ጥሩ የሚሆነው ደግሞ  እኛ ሳናስቀይማቸው የክብራቸውን ስፍራ ራሳቸው ሲያበላሹት ነው። እናም ደርዊሽም ፀፀት የሌለበትን ምስጋና አቀረበላቸው። እኛም "በኛ በኩል ሳናስቀይማችሁ የክብር ቦታችሁን ስለረገጣችሁ እናመሰግናለን። ነፍሳችንን የሚበላ ወቀሳ የለብንም። ይመቻችሁ።" እንላለን።
t.me/abdu_rheman_aman