💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.49K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያረብ የቀሩትንም ልብ ስጣቸዉ  ወይ ከምድር አንሳቸዉ ! ሰላም ከአንተ ነዉ ሀገራችን ሰላሙ መልስልን  ቤተሰቦቻችን ጥሩ እንቅልፍ ካጡ ስንት ጊዜቸዉ  ወንድሞቻችን እህቶቻችን  ከትምህርት ገበታ እርቀዉ ከቀሩ ስንትጊዜቸዉ  ስንት ንፁሀን አለቁ ስንት ሀብት ንብረት ወደመ ...!

ኢላሂ በቃ በለን ...!

=
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከምድር እልም ያድርግህ በአንተ ስንት ህዝብ አለቀ
አላህ ዉርደት እስከመጨረሻ ያከናንባችሁ የንፁሀን እንባ ጎርፍ ሁኖ ይዉሰድህ ኢንሻ አላህ !! ተቃጠልኮ ጎበዝ !? መሳቂያ ሁላ ¡

||
Audio
| By X9 Converter
🛑👉ፋኖ ትዉልድ ገዳይ ነዉ።

በደንብ አድምጡት በእነሱ ለተሸወዱ ሼር አድርጉላቸዉ !!

በተለይ ሙስሊም ሁናችሁ እነሱ የምትደግፉ ልብ ግዙ ንቁ እባካችሁ ይብቃ መታለሉ !

=
Audio
| By X9 Converter
እርማችሁ አዉጡ ደጋፊዎች¡

ስንት አባቶቻችን አስረዉ ገርፈዋል እሕቶቻችን እናቶቻችን ደፍረዋል ወንድሞቻችን እያገቱ ስንት ብር ዘርፈዋል የበግ እና የፍየል ጠቦች ጨርሰዋል አይ ፋኖ!!

=
ሌላ ትምህርት ቤት አዘግተዉ ትዉልድ እንዳይማር ! እነሱ ግን ትምህርት ቤቱ ትጥቅ መለማመጃ አድርገዉታል! ታድያ ይሄ ነዉ ነዉ ነፃ አዉጭ ይሄ ነዉ ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ ይሄ ነዉ ወይ?! ቆም ብለን እናስብ ለነሱ የምታጨበጭቡ ይብቃችሁ ተመለሱ ወደ እራሳችሁ !!


=
ኢብራሂም– አንድ ሰው፣ ሁለት ስም!
~
አንተ ከሰዎች ዘንድ ማነህ? ደግ ወይስ ክፉ? ትሁት ወይስ በጥራራ? ፊተ በሻሻ ወይስ ጨፍጋጋ? ምራቅ የዋጠ በሳል ወይስ በቀዳዳ ሱሪ የሚጀነን ከንቱ ፍንዳታ? አንተ ማነህ? ሰዎች ስላንተ ምን ይላሉ? ምን እንደሚሉ ታውቃለህ? በክፉ መነሳት ያሳስብሀል? ወይስ የሰው ጉዳይ የማይጨንቅህ በራስህ ዛቢያ ላይ የምትሽከረከር ፍጡር ነህ?
አንቺስ ከሰው ዘንድ ማነሽ? ማን መባል ያምርሻል? ምን ስም እንዳይወጣልሽ ይጨንቅሻል? ባገር በመንደሩ ምን ስም አለሽ? ጨዋ? ዘል.ዛላ? ምላሳም? ቁጥብ? አጉል ነቃሁ ባይ? ግብረ ገብ? ቀብራራ? ኮስታራ?

ይህ ከሰው ዘንድ ነው። ከአላህ ዘንድስ እኛ ማነን? ምንስ ቦታ አለን? እስኪ ራሳችንን እንመልከት? አላህ ካዘዘብን ቦታ አለን? አላህ ከከለከለን ቦታ ርቀናል? ከሆነ ምንኛ መታደል ነው?! ከሆነ ከሰው ዘንድ ያለን ስም አያስጨንቀንም።
ከሰዎች ዘንድ እፍኝ የማይሞሉ፣ አይን የማይገቡ፣ ቢናገሩ ቃላቸው የማይሰማ፣ ቢጠይቁ ፊት የማይስሰጣቸው፣ በሰዎች መለኪያ እዚህ ግባ የማይባሉ ከአላህ ዘንድ ግን የላቀ የራቀ ደረጃ ያላቸው ስንትና ስንት የአላህ ሰዎች አሉ?! አላህ ዘንድ "ሰው" ከሆኑ በኋላ ሰዎች እንደ ሰው ባይቆጥሯቸው ምን ያጣሉ?! ኢብራሂምን አታይም? ከነዚያ ከበርቴዎች ዘንድ ማን ነበሩ? አንድ ተራ ወጣት!

(قَالُوا سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُ إِبْرَاهِيمُ)
"ኢብራሂም የሚባል #ወጣት (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል ተባባሉ።" [አልአንቢያእ: 60]

ከአላህ ዘንድስ ማን ነበሩ?

(إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ)
"ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ የሆነ #ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡፡" [አንነሕል: 120]

ከሰዎች ዘንድ እንደ ዋዛ "አንድ ወጣት" ተብለው የተቃለሉት ኢብራሂም ከአላህ ዘንድ "ህዝብ" ተብለው ነበር የተሞካሹት!! አንዱ ኢብራሂም ሁለት ስም ሲኖራቸው ተመልከት። አንዱ እንደ ምድር፣ አንዱ እንደ ሰማይ። አንዱ ከምድር፣ ሌላው ከሰማይ። ልዩነቱን አየኸው?! አላህ እንዲህ ከሰቀላቸው በኋላ ፍጡር ሊያወርዷቸው ቢጣጣር ምን ያመጣል?! በተውሒድ የነገሰን ማን ያወርደዋል?!
¡
ድሮ ነው። ወሎ፣ ወረባቦ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ ዑካሻ የተሰኙ በተውሒድ ጠንካራ የሆኑ፣ ህዝቡን የወረረውን ሺርካ ሺርክ የሚነቅፉና የሚፀየፉ ሸይኽ ነበሩ። "ከዘልማዳችን ወጥጣ" ብለው በጊዜው የነበሩ መሻይኾች ተሰብስበው "ፌንጥ" አሏቸው።  ("ፌንጥ" አሁንም ድረስ ያለ አደገኛ ማህበራዊ ማእቀብ ነው። "ፌንጥ" የተባለ ሰው ከየትኛውም ማህበራዊ ህይወት ይገለላል። ሰላምታ እንኳን ይነፈጋል። ከሕዝብ መሐል እየኖረ በጫካ ውስጥ ከመኖር በላይ እየተሳቀቀ ባይተዋርነትን ይገፋል።)

ዑካሻ በጠንካራው የተውሒድ አቋማቸው የተነሳ አድማ ተመታባቸው። ከአቋማቸው ሊያሽመደምዷቸው በማለም ሸይኾቹ ተሰብስበው "ፌንጥ ብለንሀል" አሏቸው። የዑካሻ መልስ ግን ያልተጠበቀ ነበር። "እኔም ፌንጥ ብያችሁዋለሁ! ምን ታመጣላችሁ?!"
¡
አዎ ሁለ ነገሩን ለአላህ የሰጠ ሰው፣ የሰው ሴራ ለአላህ ብሎ ከያዘው አቋሙ አያጥፈውም። የሰው ጭብጨባ በሙቀት አያቀልጠውም። አላህን የያዘ ምን አጥቷል! ከአላህ ጋር የሆነ ምን ያስፈራዋል!
¡
ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! ከምንም በፊት ከአላህ ዘንድ ሰው እንሁን። በምኞት ሳይሆን በተግባር ሰው ለመሆንም እንጣር።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 13/2011)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
¶ውለታን አትርሳ !

በህይወትህ ትልቅ ዋጋ የከፈሉልህ ሰዎች እነማን ናቸው? ላንተ አሁን ላለህበት ቦታ ለመሆንህ እዚህ ለመድረስህ ከአላህ ቀጥሎ ትልቁን ሚና የተጫወተልህ ማነው? ያንን ሰው ከልብህ ዋጋ ስጠው ውለታውን መክፈል ባይቻልም እንኳን በምትችለው መጠን ያለህን ፍቅር እና ክብር ለግሰው !

ክብር የሚገባቸውን አንርሳ !

||
t.me/abuUseyminabdurehman
ከትዳር በፊት ፍቅር የለም ብዬ የኸዲጃን ፍቅር ገደል አልከተውም… ምክንያቱ ምንም ይሁን አፍቅራ እንዳገባቻቸው አልጠራጠርም… በሪራ በሚሏት ሰሓቢት ፍቅር ተለክፎ በመዲና መንገዶች ላይ ከኋላዋ እየተከተለ…  የእንባ ቋንጣውን በመዲና አድማስ  ሲወረውር የነበረውን ሰሓባው ሙጊስ … አፍቃሪ አልነበርክም ልለው አልችልም… ቀድመው ቢለያዩና ከዚያ በኋላ ባያገባትም “ሙጊስ ለበሪራ ባለው ፍቅር፣ በሪራ ደግሞ ለሙግስ ባላት ጥላቻ አልተገረምክም ወይ” የተባለለት አፍቃሪ ነው… ያውም በረሱል አንደበት።

አንድ ነገር ግን አምናለሁ… ፍቅር በስሙ የሚደረጉ ኃጥያቶችን እንደማያውቃቸውና  የአፍቃሪ መድሀኒቱም ትዳር እንደሆነ…  ማንነትህን ፣ እምነትህንና ጉዞህን የሚያመክንብህ ከሆነ በሽታ እንደሆነ… አምናለሁ። ነብይህ “ለተዋደዱ ሰዎች ከኒካህ ውጪ (አማራጭ) አላየሁም” ሲሉም… ከትዳር በፊት መዋደድ እንዳለና ኒካህ ካልታከለበት ግን የኪሳራ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ነው… አፍቅርሃል? በበር በኩል ና በቃ … በፍቅር ስም ሙድ አትያዝ!!
t.me/abdu_rheman_aman
"የሀገራችን በርበሬ'' የማጠን ባህላችን መመለስ አለበት ጋይስ ! አይመስላችሁም ¡ ?

=
🏷ታብዕዩ አልሃሰን አልበስሪይ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይሉ ነበር ፦
«የሰዎች መብዛት ያላታለለው ሰውን አሏህ ይዘንለት!
የአዳም ልጅ ሆይ!ብቻህን ትሞታለህ፣ ቀብርንም ብቻህን ትገባለህ፣ብቻህንም ትቀሰቀሳለህ፣ (ጌታህ ጋርም) ብቻህን (ስራህን) ትተሳሰባለህ»

ምንጭ፦[ኢማም አህመድ በ "አዝዙህድ" ቁ 1557]

||
t.me/https_Asselefya1
የፍቅር ህግ ...
~

"መዋሸት የለም ፣ ማጭበርበር የለም፣ መለያየት የለም፣ እንጣላለን፣ እንታረቃለን ፣ እስከመጨረሻ ድረስ አብረን እንቆያለን። "

||
t.me/https_Asselefya1
ወንድ ልጅ ሚስቱን ለመንከባከብ ምንም አይነት ድግሪ አያስፈልገው የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር ለስላሳ ልብና ጥሩ ስነ ምግባር ብቻ ነው.!

||
t.me/https_Asselefya1
አንዱ ሁለተኛ ሚስት ያገባል።

የመጀመሪያው ሚስቱ እሱን እጅግ ከመንከባከቧ የተነሳ ሀብሀብ ስትሰጠው ፍሬዎቹን በሙሉ  ለይታ አውጥታ ነው።

ሁለተኛዋ ደግሞ ዝምብላ ከተፍ ከተፍ አድርጋ ትሰጠዋለች። ከዚያ እሱም  ፍሬውን እየተፋ እየበላ… «ቱፍ ቱፍ… ሐስቢየሏህ…  ያቺማ ይህን ፍሬ እንኳ ከልክላኝ ነበር እኮ»

=
t.me/https_Asselefya1
እንደተጋባቹ ሰሞን ለትዳር አጋራቹ ታደርጉት የነበረ አሁን የተዋቹት ምንድነው??


እንደተጋባን ካልሲህን ካልተኮስኩልህ እለው ነበር አሁን ግን ግራና ቀኝ አርጎ ነው ሚሄደው አለች።

ፈገግ ብላችሁ ዋሉልኝ ¡

|||
አንድ ሚስት ባሏን ከጓደኞቹ ጋር እንዳይዝናና ቤት ተቀመጥ ብላ ትከለክለዋለች ...ባል ይሄኔ " አንዲት ሴት አስራ ባስቀመጠቻት ድመት ጀሃነም ገብታለች ...አንቺ አንበሳ አስረሽ አስቀምጠሽ ምን ሊደርስብሽ  እንደሚችል አስቢ እስኪ..."  ብሎ ተናገራት ...ህእ!

ፈገግ በሉ ፋሚሊዎች 🖐

=
🏷 ውበቷ ሲረግፍ አረጀሽ ብሎ አልተዋትም
ጤንነቱን ሲያጣም በሽተኛ ብላ አለተወችውም።


هكذا كان الحب في زمن أجدادنا


«ፍቅር በአያቶቻችን ጊዜ እንዲህ ነበር»


=
t.me/https_Asselefya1
🏷 በልብ ያለን ነገር ሁሉ መናገር ይከብዳል...ለዛም ነው አላህ ጩኸትን፣ እንባን áŠĽáŠ•á‰…áˆááŠ•áŠ“ ቀዝቃዛ ፈገግታን የፈጠረልን!

=
🏷 አንተን ከማግኘቴ በፊት ምድር ላይ ይህ ሁሉ ደስታ አለ ብዬ አላስብም ነበር‥.!

ለሀላልሽ ላኪለት 🖐

#ፍቅር

t.me/https_Asselefya1