💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች
~

ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-

* ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]

* ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]

* ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]

* ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።

* ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]

2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።

3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-

* አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
* አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
* የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
* እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!
የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
መውሊድ ፊቂህ ላይ
አብዱልጀባር ሙሀመድ ኑር
ኡስታዝ  አብዱልጀባር  ሙሀመድ  ኑር

የትኛዉም የፊቂህ ኪታብ ላይ
የማይታወቀዉ መዉሊድ

t.me/NABAWITUBE
ወሃብዮች ሰለዋት የሚከለክሉ
NABAWI TUBE
ኡስታዝ  ሳዳት  ከማል

መዉሊድ ላይ በሰለዋት አጨፍሩ ስትላቸዉ ሶደቃ ሰለዋት የሚከለክሉ መጡ ይላሉ

        t.me/NABAWITUBE
▫️የሰኞ ፆም እና መዉሊድ▫️

⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇
t.me/IbnuMunewor/6122
t.me/IbnuMunewor/6122
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🖊አላህ ያከበረዉን ያከበደዉን ልናከብር ልናከብድ ይገባናል አላህ ያከበረዉና ያከበደዉ አኼራን ነዉ። አላህ ያቀለለዉን ነገር ቀለል አድርገን ልንመለከት ይገባናል አላህ ዱኒያን ቀለል አድርጓታል።

=
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስኪ አሁን ይሄ ምን ይባላል? ለምንስ ነው እንዲህ የሚደረገው? ህግ አስከባሪ ህግ ማክበር የለበትም ወይ? ሁለ ነገራችን ግራ የሚያጋባ አገር?
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እስኪ አሁን ይሄ ምን ይባላል? ለምንስ ነው እንዲህ የሚደረገው? ህግ አስከባሪ ህግ ማክበር የለበትም ወይ? ሁለ ነገራችን ግራ የሚያጋባ አገር? = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
~አወ ልብ ይሰብራል…! ግን የኛ ጌታ ፍትሃዊ ጌታ አይደለም ብላችሁ ታስባላችሁ እንዴ?!በፍፁም የማይታሰብ ነው፡፡

• የበደለ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የእጁን ሳያገኝ መቃብር አይወርድም፡፡ ሰዎችን በድለን ያሳለፍንባቸው ቀናት ጠፍተው አይቀሩም፤ ታሪክ ሆነው አይቀበሩም፣ቢቆዩም ዞረው ተመልሰው ይመጣሉ፤ወላሂ አትጠራጠሩ፡፡

በሩቅ ያደረስነው ጉዳት በቅርብ ባሉት ይመለስልናል፣«ሁሉም ሰው ባጠጣው ነገር ይጠጣል!» ይላሉ ዐረቦች፡፡ እናማ…መርዝ ያጠጣ መርዝ መጠጣቱ አይቀርም፤ ማር ያጠጣም በመጨረሻም ማርን ይጎነጫል፡፡ጀሊሉ ለሁሉም እንደየድርጊቱ ይክሳል፣እንደየሥራው ይመልሳል።

ያለነባት ሐገር የፍትህ ሀገር ባትሆንም ነገር ግን አላህ ፍትሃዊ ዳኛ ነው፤የሰዎችን መልካም ነገር አይክድም፤ በደላቸዉንም አይረሳም፡፡ዱንያ አትቆምም ዞራ ትመጣለች፣አንድ ቀንም ተራህ በደረሰ ጊዜ መጥታ በርህ ላይ ትቆማለች፤ያጠፋኸዉን ታስከፍልሃለች፤
በሌላው ላይ የሠራኸዉን ባንተም ላይ ትሠራለች፡፡የበደልክባቸው ቀናት ባለዕዳህ ናቸው፤ ቢዘገይም ብድራቸዉን ሊመልሱ ይመጣሉ፤ ቀናት ቀን አላቸው፡፡ከአንዱ ቀንሰው ለአንዱ ይሠጣሉ፣በዳይን አሳፍረው ለተበዳይ ይክሳሉ፤ ክስተቶች አልፈው አይቀሩም፤ የሚደገሙበት ቀን ይመጣል፣ሰዎችም ቦታ ይቀያየራሉ፣ ሁሉም በጠጣበት ነገር ይጠጣል፣ግና የሚጠጣበት ጊዜ ሩቅ አሊያም ቅርብ ሊሆን ይችላል፤በሰው የሳቀ ይሳቅበታል፣የናቀም መንናቁ አይቀርም፣ የደበደበም ይደበደባል።

አላህ ለግፈኞች ያዘገያል እንጂ አይረሳም፤ከዕድሜህ ዓመታትን የነጠቀህን አላህ የሚነጥቀው ይልክበታል፣ አምነኸው ያጠቃህን ዝም ብለህ ጠብቀው ጀሊሉ ቀጠሮ ይዞለታል፤ በሌለህ ነገር ያዋረደህን አላህ ኃያሉ ጌታ የሚያዋርደው ይሰድበታል፣
በርካሽ ዋጋ የሸጠህን አላህ በቤሳቤስቲን የማይገዛዉን ያዝበታል፤ ይረክስና ዋጋው ይወድቃል፣ከጎኔ ይቁም ብለህ የተማመንክበት ቢሰርቅህ ይከብራል ብለህ አትጠብቅ፣


ቀልብ የተጎዳች እንደሆነ ሐቋን የሚመልስላት አምላክ፤ነፍስ ያዘነች እንደሆነ በደሏን የሚበቀልላት ጌታ አላት።
እናም…አብሽሩ ልባችሁ አይሰበር! ጌታችሁ ረሺ አይደለምና።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⏰️والموت

⏰️ሞት መጭ ነዉ መች እንደሚመጣ ግን የሰዉ ልጅ አያዉቅም !

=
t.me/https_Asselefya1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኢኽዋኖች እና መዉሊድ
አቡ አብዲላህ «ኢብኑ ኸይሩ»
🖊ኢኽዋኖች ስለመውሊድ ሲወራ ለምን ይከፋቸዋል ?

➡️የኢኽዋኖች መሪ ሀሰነል በና ስለመውሊድ ምን አለ?

🎙በአቡ አብዲላህ «ኢብኑ ኸይሩ»

=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13610
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዉጤታማ ለመሆን ከታች ያሉትን አቁሙ !

«ከመጠን በላይ መጨነቅ !
«ሐሜትን !
«ስንፍናን !
«በጣም ስሜታዊ መሆንን!
«ተገቢ ያልሆነ አመጋገብ!
«የማህበራዊ ሚድያ ሱስ!
«ፍርሃታችሁን
!

🎉መልካም አዳር ..!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
القارئ ماهر المعيقلي | ولئن أذقنا الإنسان
💭🌸خدمة تلاوات🎧
📔تلاوة صباحية

﴿وَلَئِنْ أَذَقْنَا ٱلْإِنسَـٰنَ مِنَّا رَحْمَةً ثُمَّ نَزَعْنَـٰهَا مِنْهُ إِنَّهُۥ لَيَـُٔوسٌ كَفُورٌ ٩۝﴾

🎙القارئ : ماهر المعيقلي

=
t.me/https_Asselefya1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
• يقول الإمام ابن الجوزي :

وإن وجدت مِن نفسِك غفلةً، فَاحْمِلها
إلى المقابر وذكّرها قُرب الرحيل.

📓 صيد الخاطر - صـ 513