💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
በዚህ ሙቀት እዚች ነበር መዋል እ? እንደት አያችኋት ግን ?

=
ያዙ ሙቀት ነዉ ቀዝቀዝ ያለ ያስፈልጋል !

✍️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲ቆንጆ ናት ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው ➫➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬   ◊አቲካ ቢንት ዘይድ ክፍል ስምንት ➾ያአላህ! ምን አይነት ወርቃማ ትውልድ ነው ያለፈው። ዱሮስ ከዚህ ትውልድ ምን ይጠበቃል። አስተማሪዎቻቸውና መሪዎቻቸው ነብዩ ሙሀመድ ኢብኑ አብደላህ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በጥሩ ስነምግባር ያሳደጓቸው ትውልዶች ናቸው። አብደላህ ኢብኑ ኡመር ይህን የምስራች ከአኢሻ ለአባቱ ኡመር ረድየሏሁ አንሁም አጅማኢን…
➲ቆንጆ ናት ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው
➫➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

  ◊አቲካ ቢንት ዘይድ ክፍል ዘጠኝ

➧በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ከቀን ወደ ቀን ትንሺ እያገገመች ሶስት የሀዘን ወራት ትጨርሳለች። ይህችን ውብ ሴት የትዳር ህይወት በቃት ይሆን?  የዓቲካ የትዳር ጥያቄ አሁንም አላበቃም።እርሷንና ሀዘኗን ለብቻቸው እንተዋት የሚል አልነበረም።ቢያገባት ወዲያውኑ ሸሂድ እንደሚሆን ልቡ እያወቀ ዓቲካን ለትዳር መጠየቅ ወደ ኃላ አይልም ነበር አሁን ደግሞ ማን ይሆን አቲካን ለትዳር የሚጠይቅ አቲካ ከሰይዲና ኡመር ረድየላሁ አንሁ በኃላ ማንም ሰው ለትዳር ይፈልገኛል ብላ አላሰበችም።ድንገት አንድ የማትጠብቀው ሰሃባ አቲካን ለትዳር እንደሚፈልጋት በአንድ ሰው መልዕክት ላከባት።

➪ስለዚህ ታላቅ ሳሃባ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሲናገሩ እንድህ ብለዋል፦ "ሁሉም ነብያቶች ሐዋሪይ ነበራቸው የእኔ ሐዋሪይ  እርሱ ነው" በማለት የተናገሩለት ውድ ሰሃብይ ነው። ሐዋሪይ ማለት ከነብይ የማይለይ፣ የሚካድም፣ አማካሪ፣መልዕክት የሚያስተላልፍ ፣ ለነብይ ቅርብ የሆነ ሰው ማለት ነው። ይህ አሁን ለትዳር የጠየቀው ሰሃቢ በረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሐዋሪይ በሚል ቅፅል ስም የተሰጠው ነው። እንድሁም የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አክስት የሶፍያም ልጅ ነው። በተጨማሪም ከአስሩ በጀነት ቃል ከተገባላቸው ከሰሃቦች አንዱ ሲሆን ከስድስቱ የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አማካሪዎች አንዱም ነው።

➾ይህ ሰሃባ ወደ እስልምና የገባው በስምንት አመቱ ህፃን ሆኖ አጎቱ በእሳት እያቃጠለው በሙሃመድ ክፈር እያለ ሲያሰቃየው የነበረ በአስራ ስምንት አመቱ ከመካ ወደ መድና የተሰደደ ብርቅየ ሰሃባ ነው። ይህ ታላቅ ሰሃብይ ወደ ሀበሻ በመሰደድ እኛ ከጠጣነው ውሃ የጠጣ እኛ ያደግንበትን አፈር የረገጠ ነው። በፍፁም ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምጦርነት ወጥተው ተለይቷቸው የማያውቅ ሰሃብይ ነበር። ማን ይሆን ይህ ታላቅ ሰሃቢ? ዓቲካስ ይህን የጋብቻ ጥያቄ ትቀበል ይሆን? ዙበይር ኢብኑ አዋም ረዲየላሁ አንሁ ይባላል። ነገር ግን አቲካ ረዲየላሁ አንሃ የመጣላትን የትዳር ጥያቄ ማመን አልቻለችም።

➩አሁን ግልፅ የሆነላት ነገር ቢኖር ያገባት ሁሉ ሸሂድ እንደሚሆን ነው። ገና ሳታገባው ለምታገባው ሰው ትሳሳለት ጀመር። አሁን አግብቶኝ ትንሺ ሳይቆይ ሻሃዳ ሊያገኝ እንዳይሆን ብቻ በማለት አሰበች። ዓቲካ የዙበይር ኢብኑ አዋምን ደረጃውን ታውቃለች። የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የአክስት ልጅ የነብይ ሐዋሪይ ታሪኩ ተወርቶ የማያልቅ ታላቅ ሰሃቢ መሆኑን ጠንቅቃ ታውቃለች። ኒካህ ከመደረጉ በፊት ዓቲካ አንድ ሸርጥ ታስቀምጣለች። ምንድን ነው ሸርጥሺ ዓቲካ ብለው ጠየቋት? የዓቲካ ሸርጧ አምስት ወቅት ሰላት መስጅድ ሂዳ መስገድ እንደምትፈልግና ዙበይርም ረዲየላሁ አንሁም አጅማኢን እንዳይከለክላት ነበር። ሰይድና ዙበይርም በዚህ ሸርጥ ተስማምተው ከዓቲካ ጋር ኒካህ አሰሩ።

➾ሰይዲና ዙቤይር በየቀኑ ለዓቲካ ያላቸው ውደታና ፍቅር እየጨመረ ይሄዳል። እንደት አይጨምርም?አኽላቋ የሚረታ ፣ ውበቷ የሚማርክ፣ ያገባችውን ባል በሙሉ አላህ የደነገገባትን ሀቆች አሳምራ ሰጥታ ማታ እጇን ወደ ሰማይ ዘርግታ ያረብ የባሌን ሀቅ አሟልቼ እንድሰጥ እርዳኝ ላጎደልኩትም ማረኝ የምትል ሴት ላይ እንደት ውደታ አይጨምርም። ከጊዜ ቡኃላም ሰይድና ዙበይር ረድየላህ አንሁ ላይ አድስ ባህሪይ ይታይባቸው ጀመር። ይህም ዓቲካ ላይ መቅናት መጀመራቸው ነው። ሰይዲና ዙበይር ረዲየሏሁ አንሁ በየቀኑ ቅናታቸው ጎላና ከአንድበታቸው ማውጣት ጀመሩ።

👉የቀኑበት የሆነው ነገር ምን ይሆን? በቀጣይ ክፍል እናየዋለን።
◉
◉
◉
◉
ኢንሻ አላህ ይቀጥላል

➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
خالد الغامدي
Sheikh Khaalid al Ghamdi
የማለዳ ጣፍጭ ቲላዋ ግብዣ

تلاوة خاشعة من سورة النساء
للشيخ خالد الغامدي

=
የቁርአን እና ሀዲስን ምክር እየመረጡ መስማት መቸም ምርጥ ሰዉ እንዳይሆኑ ያደርጋል ።

=
አስቸኳይ
~
በሑዘይፋ መስጂድ ዘወትር እሁድ የሚሰጠው የደርስ ፕሮግራም በዛሬው እለት አይኖርም። በመስጂዱ ውስጥ የሚካሄድ የሴቶች ፕሮግራም እንዳለ ስለተነገረን ነው። ሰዎች እንዳይንገላቱ ይህንን መልእክት በማሰራጨት ወይም ለምታውቋቸው በመደወል አድርሱልን።
جزاكم الله خيرا
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲ቆንጆ ናት ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው ➫➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬   ◊አቲካ ቢንት ዘይድ ክፍል ዘጠኝ ➧በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ከቀን ወደ ቀን ትንሺ እያገገመች ሶስት የሀዘን ወራት ትጨርሳለች። ይህችን ውብ ሴት የትዳር ህይወት በቃት ይሆን?  የዓቲካ የትዳር ጥያቄ አሁንም አላበቃም።እርሷንና ሀዘኗን ለብቻቸው እንተዋት የሚል አልነበረም።ቢያገባት ወዲያውኑ ሸሂድ እንደሚሆን ልቡ እያወቀ ዓቲካን ለትዳር…
➲ቆንጆ ናት ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው
➫➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

  ◊አቲካ ቢንት ዘይድ ክፍል አስር

➧ሰይዲና ዙቤይር ረዲየላሁ አንሁ በየቀኑ ቅናታቸው እየጎላና ከአንድበታቸው ማውጣት ጀመሩ።አንድ ቀን ዓቲካ መስጂድ ልትሄድ ስትወጣ ያአቲካ አሏት! ወላሂ ከቤት የምትወጪው እኔ መውጣትሺን እየጠላሁ ነው። አሏት እርሷም ከበር ተመልሳ በተረጋጋ መልኩ ከፈለክ አልሄድም አቆማለሁ በማለት ጠጋ ብላ ታባብላቸዋለች። ያሰላም...ያአላህ አኽላቃችንን አሳምርልን! ተመልከቱ እሳቸው ባለቤቷ ዙበይር የሚመልሱትን እንደት እከለክልሻለሁ ስታገቢኝ ሸርጥሺ ሆኖ ብለው ከቤት አውጥተው ወደ መስጅድ ይሸኟታል።

➾ዓቲካ በረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ያአክስት ልጅ ላይ እያሳደረች የነበረው ተፅኖ ወደር አልነበረውም። ሰይድና ዙበይርም ግን መቋቋም አልቻሉም። ለሁለተኛ ጊዜ ዓቲካን መስጅድ መሄዷን መጥላታቸውን ሲገልፁላት ዓቲካም ይህ ጥያቂያቸው በቅናት ላይ የተመሰረተና ሊቀይሩት ይችሉ ዘንድ በለዘብታ የዓዋም  ልጅ ሆይ (በዚያን ጊዜ የሚወዱትን ሰው ሲጠሩ በአባቱ ስም ነበር) ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጋር አቡበክርና ዑመር ጋር የሰገድኩበት ሙሰላየን ለቅናትህ ብየ እንድተው ፈለግክ ወይ ብላ ጠየቀቻቸው ሰይዲና ዙበይርም ላ ወላሂ አልከለክልሺም አሉ። ነገር ግን ያደረባቸው ቅናት ቀላል አልነበረም። በጣም ያሳዝናሉ። ለሰላት ከወጣች የምትመለስ አይመስላቸውም። ልባቸው አልረጋ አለ ማስገደድ ባህሪያቸው አልነበረም አትሂጂ ማለትም አይበቃላቸውም። ነገር ግን ይህ ቅናት ወደሚያስገርም ድርጊት ይመራቸዋል።

➪ኢኽዋኒ ወአኽዋቲ ከዚህ በታች በምነግራችሁ የሰይድና ዙበይር ድርጊት ተገርማችሁ ምንም አይነት ነጌቲቭ ኮመንት እንዳታደርጉ ሲጀመር በሀሳባችሁም ውስጥ እንዳታመጡ ምክንያቱም ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም  ሰሃባዎች ጋር አደብ ሊኖረን ይገባል። ነብያችንም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አስጠንቅቀዋል። ልብ ብለን እናንብበው (አላህን ፍሩ ሰሃባዎቸን በሚመለከት )እኔ ከሞትኩ በኃላ እስልምናን ለመዋጋት እነሱን አላማ አታድርጋቸው እነርሱን የወደደ እኔ እንደምወደው ሆኖ ነው የሚወዳቸው እነርሱን ያስከፋ ያስቆጣ እንደምከፋበት እንደምቆጣበት ሆኖ ነው የሚያስቆጣቸው። እነርሱን አዛ ያደረገ እኔን አዛ እንዳደረገ ነው እኔን አዛ ያደረገ አላህን አዛ እንዳደረገ ነው። አላህን አዛ ያደረገ አላህ ክፉኛ ሊወስደው ተቃርቧል አሉ። በሌላ ሀድስ ላይ ሰሃባዎቸን እንዳትሰድባቸው አስሃባዎቼን እንዳትሰዲባቸው ነፍሴ በጁ በሆነው እምላለሁ አንዳችሁ እሁድ ተራራን የሚያክል ወርቅ ብታወጡ አንዳቸውንም ደረጃ አትደርሱም ነበር ወላ ግማሹን አሉ ከዚህ አስፈሪ ማስጠንቀቂያ በኃላ እንግድህ ሰሃባዎችን በክፋ ማንሳት ወይም ሊያስብ የሚዳፈር ያለ አይመስለኝም። ወደ ዓቲካ ታሪክ እንመለስ፦

➩ሰይድና ዙበይር ረ.አንሁ አቲካ ላይ ከመቅናታቸው የተነሳ አንድ የሚያስገርም ነገር ይሰራሉ። አንድ ቀን የሱብሂ ሰላት ለመስገድ ወደ መስጅድ ስትሄድ ሰይድና ዙበይር ውዱዕ አድርገው ቀድመዋት ወጡና በኒ ሰዐድ የሚባለው ቦታ ላይ አድፍጠው ጠብቀዋት በዚያ ጨለማ ሰውነቷን መታ አድርገዋት በፍጥነት ተሰወሩ አቲካም ደንግጣ ዞር ብላ ስታይ ማንም የለም። ምን ሆነሃል አላህ እጅህን ይቁረጠው አለችና በጣም ተደናግጣ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መስጂድ መሄዷን ትታ ወደ ቤት ተመልሳ ትሄዳለች። ሰላቷንም እቤት ሰግዳ ሰዎች እንድህ አደብ አጡ በማለት በጣም አዝና ስለደረሰባት ነገር እያብሰለሰለች ሳለ ሰይድና ዙበይር እቤት ተመልሰው ምነው መስጂድ አላየሁሺም ይላታል። አላህ ይራሃምክ የአብደላ አባት ከአንተ በኃላ ሰዎች ተበላሹ። ዛሬ ለሴት ልጅ መስጂድ ሄዳ ከመስገድ ጓዳ ውስጥ መስገድ ይሻላታል በማለት ከዚያች ቀን ጀምሮ መስጅድ ሄዳ መስገድ አቆመች። ሰይዲና ዙበይር ድርጊታቸው ቢፀፅታቸውም ሊቋቋሙት ያልቻሉት ስሜት እዚህ አደረሳቸው።
◉
◉
◉
◉
ኢንሻ አላህ ይቀጥላል

➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➲አሏህ ሆይ የኛ ባልሆነና በማናገኘው ነገር ላይ ልባችንን አታንጠልጥልብን!!ኢላሂ በራሳችን በሆነ ነገር ላይ መብቃቃትን ወፍቀን።
قال ابو الدرداء رضي الله عنه:

«ليس الخير أن يَكْثُر مالك وولدك، ولكنَّ الخير أن يَعْظُم حِلْمُك، ويَكْثُر علمك، وأن تنادي النَّاس في عبادة الله، فإذا أحسنت حمدت الله، وإذا أسأت استغفرت الله»

📚«تاريخ دمشق47/158»

አቡደርዳእ ~አላህ ስራውን ይውደድለትና~ እንዲህ ይላል
፦

" መልካም ነገር ማለት ገንዘብህና ልጆችህ መብዛታቸው አይደለም
። ነገር ግን መልካም ነገር ማለት  ቻይነትህ { ታጋሽነትህ } ትልቅ መሆን ፣  እውቀትህ ሲበዛ፣ ድምጽህን ከፍ በማድረግ ሰዎችን ወደ አላህ አምልኮ መጣራት፣ መልካም ከሰራህ አላህን አመስግን፣ መጥፎ ከሰራህ ማርታን ጠይቅ።

ታሪኽ ዲመሽቕ [47/158]
➴➴➴➴➴➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
«አንዳዴ ሰዉ ሰርፕራይዝ ልታደርጉ ሄዳችሁ ራሳችሁ ብትደረጉ ምን ይሰማችኋል እ ? ለማንኛዉም ዛሬ እሁድ ከኩሽና ወጣ ብለን ነበር እና አልኳችሁ ሰዉ ሰርፕራይዝ ላደርግ ሄጄ ለራሴም ተደርጌ ተመለስኩላችሁ እህታችን ሶፊያ ኡሙ ሀፍሷ መብሩክ እህት አላህ ጠቃሚ እዉቀት ያድርግልሺ 🌹 መኪያ ጂልባብ ኒቃብ አዘጋጅ የኔ ፈጣን እህት ያዘዝንሽ እቃ በፍጥነት ሰፍተሽ ሌላም የምንፈልገዉ ያዘዝንሽን መርሀባ ብለሽ ስለላክሽልን ከልብ እናመሰግናለን ጀዛኪላሁ ኸይር አላህ ይጠብቅሽ 🌹

«መኪን እዘዟት እሺ የትም ሁኑ ትልካለች ለኛ 2ኛ ጊዜ ባልናት ወቅት ቶሎ የላከችልን !»


 áˆľáˆáŠ­áŚ 09 29 51 45 35
ቴሌግራም፦
@mekiajilbab
𝐓𝐞«
t.me/mekiajlbab

✍️أم عثيمين
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እናማ አልኳችሁ ይሄ በስራ እና በማዳም ጩሀት የደነዘዘ አእምሮ አንዳዴ ወጣ እያሉ ማዝናናት ጥሩ ነዉ ሸሪአዊ የጠበቀ አለባበስ በመልበስ እና ሸሪዓ የማይፃረር ቦታዎች በመዉጣት !

#እየወጣችሁ

=
«መረዳት ከእዉቀት የበለጠ ጥልቅ ነዉ። ብዙ ሰዎች ያቁሀል የሚረዱህ ግን ጥቂቶች ናቸዉ።»

=
t.me/https_Asselefya1
የእኛ ሀገር ጴንጤዎች¡

:- እኔምኮ ድሮ ሙስሊም ነበርኩ

:- እና አሁን ከፍረህ ነው?

:- አዎ

:- ለምን?

:- ሱረቱል ቡኻሪን ካነበብኩ ቡሀላ እስልምና ትክክል አለመሆኑን ተረዳሁ

منقول
=
አንዳዴ ...!

ጨክነን እንረሳ ብለን ብዙ ታግለን የማይረሱ ሁለዬ የሚረብሹ መጥፎ አጋጣሚዎች አሉ!


=
القارئ ماجد الزامل يا أيها المزمل قم الليل إلا قليلا
💭🌸خدمة تلاوات🎧​
﴿يَا أَيُّهَا الْمُزَّمِّلُ (1) قُمِ اللَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا (2) نِّصْفَهُ أَوِ انقُصْ مِنْهُ قَلِيلًا ۝﴾

🎙القارئ : ماجد الزامل
=
t.me/https_Asselefya1