💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲ቆንጆ ናት ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧አድስ ተከታታይ ፅሁፍ             ➳አቲካ  ክፍል ⓵ ➛አባቷ ዘይድ ከሪሳላ በፊት የሞተ ነገር ግን የአላህ መልክተኛ  (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)  ያማረ ልብሱ #ጀነት ውስጥ ሲጎትት  እዳዩት የተናገሩለት #ወንድሟ ሰኢድ  የሰይድና ኡመር (ረደሏሁ አንሁ) እህትን ፋጡማን ያገባ ነው #በቁንጂናዋ መካ ውስጥ የሚወዳደራት…
ቆንጆ ናት ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

      ➧አቲካ ክፍል ሁለት

💎ሰይዲና አቡበከር ሲዲቅ ረዲየላሁ አንሁ ፍታት የሚለውን ቃል ልክ ካፋቸው እንደወጡት ልጃቸው አብደላህ የሰማውን ማመን አቃተው በህልሜ ነው ወይስ በውኔ? ለአንድ አፍታ ብዙ ነገር በአዕምሮው ተመላለሰ ፍታት? ማንን ነው የምፈታት? አብሪያት እየዋልኩ አብሪያት እያደርኩ እንኳን ናፍቆቷን አልቻልኩም። ፍቺ የሚባል የብረት አጥር ሲለያየን ምን ልሆን ነው?

ምን አጠፋሁ እርሷስ ምንድን ነው ወንጀሏ? ያአላህ ድረስልን በማለት እያሰበ ሳለ በል እያየሁህ እየሰማሁህ ሂድና ፍታት የሚለው የአባቱ ትዕዛዝ ያዘለ ንግግር ካለበት ውዥንብር ውስጥ ይቀሰቅሰዋል።


አብደላህ ረዲየሏሁ አንሁ ነፍሱን ካወቀ ቀን ጀምሮ አባቱን አንድ ነገር እንቢ ብሎ አያውቅም አንድ ቀን አባቱ ላይ አምፆ አያውቅም,ለአባቱ ሁሌም ታዛዥ ነበር ፣ ዛሬ ግን ሊገባበት የማይፈልገው ሁለት መንገድ ከፊቱ ድቅን አለበት!አባቱን ማጣት አይፈልግም ፈፅሞ የማይታሰብ ነገር ነው። ነገር ግን የሱ ሂይወት ከሚወዳት ሚስቱ ተለይቶ መኖር መሰቃየት መሆኑን እየተረዳ የአባቱን ሀቅ አስበልጦ ወደ ሚስቱ እየተራመደ ሳይሆን እግሩ እየሳበው እራሱን እንደሳተ ሰው በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ መናገር እንደጀመረ ህፃን በተወሳሰበ አንድበት ለሚስቱ ፈትቸሻለሁ አላት።ሚስቱም የሰማችውን ማመን አቃታት

➪ከጥቂት ጊዜ በኃላ በፊት አብደላ ይነግራት የነበረው ባል ለሚስቱ ያለውን ፍቅር አክብሮት እና እዝነት የሚገልፅ ቃላቶች ነበር ግን አሁን ለምን ፈታኝ ፣ምን አጠፋሁ ባሌን ምን በደልኩት ምንስ ቀየረው እያለች ልትቆጣጠረውና ልታቆመው የማትችለው እንዳሻው የሚወርድ እንባ ፊቷን አጥለቀለቀውአብደሏህና ሚስቱከተፋቱ በኅላ ስለተለያዩ የሁሉም ሁኔታ በጣም አሳዛኝና የሚያሳስብ ነበር። አሁንም ይህን ታሪኳን የዘገበው ሰውየ የአብደላህን ሁኔታ ሲገልፀው ''አብደላ ሚስቱን ከፈታ በኃላ ያሳለፋቸው ቀናቶች የሌሊት ጨለማን የሚመስል ጥቁር ቀናቶች ነበር'' በሏል።

አሁን አብደላ እያደረ ሲሄድ ሂወቱ ለምን ወዳልፈለገበት መንገድ እንዳመራ ሰበቡን መመራመር ይጀምራል። ችግሩ ምኑ ላይ እንደሆነም ወዲያው ይደረስበትና በህይወቱ የሚጠበቅበትን ሀቆች ለሁሉም ሊሰጥና ሊያዳርስ ለራሱ ቃል ገብቶ ይነሳል።  ባለቤቱም ከፍታ ከአብደላ ጋር የነበራትን ትዳር ያሳለፍትንጊዜያት መለስ ብላ ስታስበው ባሏን በኸይር ነገር በኢባዳውና በኑሮው ማበረታታት ሲገባት ከሁሉም ነገር እርሱን መሺጉል ማድረጓ ተሰማትአንድ ቀን ሌሊት ሰይዲና አቡ በከር ረዲየላሁ አንሁ የለይልን ሰላት በቤታቸው ጣሪያ ላይ ሆነው ሲሰግዱ ከታች የልጃቸውን የአብደላን ድምፅ ይሰማሉ

👉ልጃቸው አብደላን ምን ሲል ሰምተውት ይሆን? በቀጣይ ክፍል እናየዋለን።



◉ኢንሻ አላህ ይቀጥላል

➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
እኔ አላልኩም እሽ ስዘዋወር የተገኘ ነዉ!
📱ባሏን ቤቱን እንዲናፍቅ በምታደርግ ባሏን አክባሪ ሃብትና ንብረቱን ጠባቂ ሐቁን ተወጪ አስተዋይና ሁሌም የምታበረታታዉ ምርኩዙ በሆነች ሚስት ላይ የአላህ ሰላም እና እዝነት ይስፈንባት!

=
t.me/https_Asselefya1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
{ فَسُبۡحَـٰنَ ٱللَّهِ حِینَ تُمۡسُونَ وَحِینَ تُصۡبِحُونَ (17) وَلَهُ ٱلۡحَمۡدُ فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ وَعَشِیࣰّا وَحِینَ تُظۡهِرُونَ (18) یُخۡرِجُ ٱلۡحَیَّ مِنَ ٱلۡمَیِّتِ وَیُخۡرِجُ ٱلۡمَیِّتَ مِنَ ٱلۡحَیِّ وَیُحۡیِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَاۚ وَكَذَ ٰ⁠لِكَ تُخۡرَجُونَ (19) وَمِنۡ ءَایَـٰتِهِۦۤ أَنۡ خَلَقَكُم مِّن تُرَابࣲ ثُمَّ إِذَاۤ أَنتُم بَشَرࣱ تَنتَشِرُونَ (20) وَمِنۡ ءَایَـٰتِهِۦۤ أَنۡ خَلَقَ لَكُم مِّنۡ أَنفُسِكُمۡ أَزۡوَ ٰ⁠جࣰا لِّتَسۡكُنُوۤا۟ إِلَیۡهَا وَجَعَلَ بَیۡنَكُم مَّوَدَّةࣰ وَرَحۡمَةًۚ إِنَّ فِی ذَ ٰ⁠لِكَ لَـَٔایَـٰتࣲ لِّقَوۡمࣲ یَتَفَكَّرُونَ (21) }

=
~በቀልባቸው ንፅህና ብቻ ሰላማቸው የበዛ ሰዎች አሉ።ለሌሎች መልካምን በመመኘታቸው ብቻ ሪዝቃቸው የሰፋ ሰዎች አሉ። በንያቸው ማማር ብቻ የሠሩ ያህል ተጽፎላቸው ምንዳቸው የበዛ በርካቶች አሉ።

ቀልባችሁ ንፁህ ሲሆን ሰላማችሁ ይበዛል፣ለሌሎች መልካም ስትመኙ ሪዝቃችሁ ይሰፋል፣በመልካም ንያችሁ ብቻ በመጥፎ ንያ በሥራ ከደከሙት በላይ ምንዳችሁ የሚበዛበት ሁኔታ አለ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
«ድሀ....ነበር»

በጨለመ ጊዜ ብቻየን ሳስበው፡
ከአሁን ተነስቼ ትላንትን ሳነበው፡
በዚያ በዚህ ብዬ ራሴን ስከበው!?

....እንደዚህ እላለሁ....

ሀብት የሰው ልጅ ቢሆን መግዣ መለወጫ፡
ድሀ ገንዘብ ነበር የሀብታም ማጌጫ፡
ግን አልሀምዱ ሊላህ አላደረገንም፡
ከነ ችግራችን ሰወች ነን አሁንም፡

«በኑረዲን አል አረብ»

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
«የወደደሽ ካለ እንደዋዛ አትግፊ ሴት ልጅ የሚወዳትን ብታገባ ይሻላታል ቢያንስ አይበድላትም ይወዳታልና።»

𝑻𝒆↳ t.me/https_Asselefya1
«لَا تَقۡلَقۡ اللُه سَيُصۡلحُ كُلَّ شَيۡءٍ بِطَرِقَةٍ جَمِيلَة»

«አትጨነቅ አላህ ሁሉንም ነገር ባማረ ሁኔታ ያስተካክለዋል።»

𝐓𝐞↝ t.me/https_Asselefya1
Welcome to mekiya jilbab&nikab

እንኳን ወደ መኪያ ጅልባብ እና ኒቃብ በሰላም መጣችሁ

-መኪያ ጅልባብ ስፌት የተለያዩ ኢስላማዊ ልብሶችን በማቅረብ ላይ ይገኛል
ጅልባብ
ኒቃብ
አበያዎች
ሂማሮች
ሂጃብ የህጻናት የአዋቂ
ሽቲወች
የመስገጃ ሸርሸፎች

የህጻናትም የአዋቂም በፈለጉት የጨርቅ አይነት በፈለጉት ከለር በፈለጉት ድዛይን እንሰራለን
- የጅልባብ አሰራር
በዚፕ
በላስቲክ
በገመድ
በቀጭን ላስቲክ በሽብሽቡ
ሰርክል
-እርሰዎ ድዛን ካለወት በፈለጉት ሁኔታ እንሰራለን


ልብ ይበሉ መኪያ ጅልባብ ተወዳጅነቱ ሸሪአውን የጠበቀ መስተንግዶ በሴት ተለክተው በሴት ተሰተናግደው በስራችን ተደስተው የሚመለሱበት መሆኑነው፡፡
ይምጡ ይጎብኙን ቤተሰብ ይሁኑን

አድራሻ አ አ ቤተል ተቅዋ መስጅድ በተዘጋው በሴቶች በር ፊት ለፊት አድስ ኢንተርናሽናል ባንክ 1ኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል
ለበለጠመረጃ 09 29 51 45 35 ይደውሉ
ወይም በውስጥ ማውራት ከፈለ @mekiajilbab

https://t.me/mekiajlbab
ዱባይ የወንድ ስራ ከሰማችሁ ንገሩን! ሳዑድ ሪያድ መካ ጂዳ ለሴቶች ስራ ከሠማችሁ ንገሩን!

Bot↝ @Ass_selefyaa_bot
تلاوة تدبرية آيات التفكر في خلق الله ( من سورة ال عمران) القارئ…
سعد أزويت - Saad Ezzaouit
{ إِنَّ فِی خَلۡقِ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ وَٱخۡتِلَـٰفِ ٱلَّیۡلِ وَٱلنَّهَارِ لَـَٔایَـٰتࣲ لِّأُو۟لِی ٱلۡأَلۡبَـٰبِ }

«አስተንትኗት....»

t.me/abu_reyyis_arreyyis
Forwarded from ስለ ቀልባችን
አላህ ሆይ!
ብዙ ማሰብና መጨነቅን አርቅልን፣
የልብ እርካታና የዉስጥ ሰላምን ለግሰን።
በሉ።

ያለምክንያት አትታገሱም አይደል መቸስ።አላህ የታገሳችሁለትን ነገር ይለግሳችሁ፣በተስፋ የጠበቃችሁትን ይሸልማችሁ፣የዱንያ አኺራ ደስታን ይስጣችሁ ።
=t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
الواسطة بين الحق والخلق ⊰አል ዋሲጠህ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ⊱ መግቢያ የቀጠለ ⓵፦ −−−−−−−−−−−− ምስጋና ሁሉ ለአላህ ነዉ። እናመሰግነዋለን፣በእርሱም እንታገዛለን፦ ምህረቱንም(ከእርሱ ብቻ)እንጠይቃለን። ከነፍሶቻችን ተንኮልና ከመጥፎ ስራችን በአላህ እንጠበቃለን። አላህ ያቀናዉን ማንም አያጠመዉም። አላህ ያጠመመዉን ማንም አያቀናዉም። ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ…
الواسطة بين الحق والخلق



«የአል ዋሲጠህ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ»


መግቢያ ከባለፈ የቀጠለ
   −−−−−−−−−−−−−−−−−−

⭞የመጀመሪያዉ የሸሪዐህ መርህን ሳያዉቁም ይሁን አዉቀዉ  እሱም  በሙሐመድ ላይ ከወረደዉ ዉጭ  አላህን ያመለከ ሰዉ ከሐዲ መሆኑ ጥርጥር የለዉም።
አላህም እንድህ በማለቱ፦

{ فَلَا وَرَبِّكَ لَا یُؤۡمِنُونَ حَتَّىٰ یُحَكِّمُوكَ فِیمَا شَجَرَ بَیۡنَهُمۡ ثُمَّ لَا یَجِدُوا۟ فِیۤ أَنفُسِهِمۡ حَرَجࣰا مِّمَّا قَضَیۡتَ وَیُسَلِّمُوا۟ تَسۡلِیمࣰا }

«በጌታህም እምላለሁ  በመካከላቸዉ በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከዉ ነገር በነፍሶቻቸዉ ዉስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍፁም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ ሙእሚኖች አይሆኑም።» ( አን ኒሳእ:65)


ሰይጣን እንደዚህ ስራቸዉን አሳመረላቸዉ። እዉቀትን በመታገል ብርሃኑን በማጥፋት። ከፊሏ ከከፉ የበላይ በሆነች ጨለማ ዉስጥ አደረጋቸዉ። ከእርሷ አላህን  እንድያመልኩ ወደ ዝንባሌያቸዉና ጥርጣሪያቸዉ አዞራቸዉ።እርሱ አላህ ቁርአን ላይ እንደገለፃቸዉ፦

{ قُلۡ هَلۡ نُنَبِّئُكُم بِٱلۡأَخۡسَرِینَ أَعۡمَـٰلًا } { ٱلَّذِینَ ضَلَّ سَعۡیُهُمۡ فِی ٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَا وَهُمۡ یَحۡسَبُونَ أَنَّهُمۡ یُحۡسِنُونَ صُنۡعًا } { أُو۟لَـٰۤىِٕكَ ٱلَّذِینَ كَفَرُوا۟ بِـَٔایَـٰتِ رَبِّهِمۡ وَلِقَاۤىِٕهِۦ فَحَبِطَتۡ أَعۡمَـٰلُهُمۡ فَلَا نُقِیمُ لَهُمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ وَزۡنࣰا }
«በስራዎች በጣም ከሳሪዎቹ እንንገራችሁን ? በላቸዉ።እነዚያ እነሱ ስራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸዉ ሲሆኑ በቅርቢቱ ሕይወት ስራቸዉ የጠፋባቸዉ ነቸዉ እነዚያ እነርሱ በጌታቸዉ ማስረጃዎችና በመገናኘቱ የካዱት ናቸዉ። ስራዎቻቸዉ ተበላሹ። እነርሱም በትንሳኤ ቀን(ጠቃሚ) ሚዛንን አናቆምላቸዉም።»(አል ከህፍ:103_105)


ይህች ቡዲን ወደ ብዙ ጭፍሮችና መንገዶች ተከፋፍላለች። የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸዉኝ በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸዉንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ የሆነችዉን ቀጥተኛዉ  መንገድ የራቀች  በመሆኑዋ አንዷ አንዷን ትዋጋለች። መልእክተኛዉ በንግግራቸዉ እንደጠቀሱት እነዚህ ቡድኖች (ፊረቆች) ሁሉ የእሳት ናቸዉ፦ ህዝቦቸ ወደ ሰባ ሶስት ፊረቅ ይከፋፈላሉ።ሰባ ሁለቱ የእሳት ናቸወሐ። አንዷ የጀነት ናት። እሷም እኔና ባልደረቦቼ ባለንበት አምሳያ ላይ ያሉ ናቸዉ።

2ኛ√ .ይህችን ወሳኢጥ በማፀደቅ ድንበር ያለፈና ስህተት የሆነ አረዳድን የተረዳ የማትሸከመዉን ያሸከመ(ቡድን)ነዉ።ከመልእክተኛዉ እና ከሌሎች ነብያት ደጋግ ሰዎች ዛት ወሳኢጥ የያዙ ሰዎች ናቸዉ አላህ የባሮቹን መልካም ስራ አይቀበልም  እነዚህን አዳራሽ አድርገዉ  በእነርሱ በኩል እስካልመጡ ድረስ ብለዉ እስከማመን ደረጃ ደርሰዋል።

አላህ ከሚሉት ነገር  ሁሉ ትልቅ ሆነ መላቅን ላቀ። አላህ ይጠብቀንና በበራቸዉ ላይ ጠባቂዎችን አስቀምጠዉ ወሳኢጥ ያለዉ ያልሆነን መግባት የሚከለክሉት  አንባ ገነን የሆኑ በዳይ መንግስታት እንኳ ሊገለፁበት በማይፈልጉት ባህሪ አላህን ገለፁ።

የዚህ አይነት አመለካከት ከእነዚህ የአላህ ንግግር የት አለ ?፦

{ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِی عَنِّی فَإِنِّی قَرِیبٌۖ أُجِیبُ دَعۡوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِۖ فَلۡیَسۡتَجِیبُوا۟ لِی وَلۡیُؤۡمِنُوا۟ بِی لَعَلَّهُمۡ یَرۡشُدُونَ }

«ባሮቸም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንድህ በላቸዉ)፦ እኔ ቅርብነኝ። የለመነኝን  ፀሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ። ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፣ በእኔም ይመኑ፣እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና። » (አልበቀራህ:186)

📝ይቀጥላል ኢንሻ አላህ...

↝↓↜↓↝↓↜↓↝↓↜↓
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1
ደቦ እርሻ..

ትዝታ በገጠር...!

=
«በሉ አብሽሩ የማያልፍ ነገር የለም። ዛሬ ዉስጣችሁ የረበሻችሁን ነገር ንገሩት ነገም ሌላ ቀን ነዉ ያልፋል ብላችሁ።»

«መልካም ለይል ተመኘሁ 🩵
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እያንዳዱ ታሪክ መጨረሻ አለዉ ነገር ግን በህይወት ዉስጥ ሁሉም ፍፃሜ በአዲስ ጀምር።

=
t.me/https_Asselefya1
القارئ عبدالمحسن الضباح | قال هل يسمعونكم إذ تدعون
💭🌸خدمة تلاوات🎧
﴿قَالَ هَلْ يَسْمَعُونَكُمْ إِذْ تَدْعُونَ ٢٧۝ أَوْ يَنفَعُونَكُمْ أَوْ يَضُرُّونَ ٣٧۝﴾

🎙القارئ : عبدالمحسن الضباح

=
t.me/https_Asselefya1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM