💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
የወንጀል መዘዙ ከባድ ነው በተለይ እያወቁ ሲያጠፉ!

(وَلَوْ يُؤَاخِذُ اللَّهُ النَّاسَ بِمَا كَسَبُوا مَا تَرَكَ عَلَىٰ ظَهْرِهَا مِنْ دَابَّةٍ وَلَٰكِنْ يُؤَخِّرُهُمْ إِلَىٰ أَجَلٍ مُسَمًّى ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِعِبَادِهِ بَصِيرًا)

"አሏህ ሰዎችን በሰሩት በደልና ወንጀል ሁሉ እዚሁ ዱኒያ ላይ የሚቀጣቸው ቢሆን ኖሮ ምድር ላይ ማንንም ሳያስቀር ወንጀል የሰሩትንም ያልሰሩትንም እንስሳትንም ጭምር- ባጠፋቸው ነበር ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ ያቆያቸዋል አጀላቸውም ሲደርስ እርሱ የባሮቹን ምንነት ጠንቅቆ በሚያውቀው መሰረት የስራቸውን ይሰጣቸዋል" አል ፋጢር 45

=
t.me/https_Asselefya1
እዚህ ዱኒያ ላይ እስከ አለን ድረስ አላህ የሰጠንን እድሜ በመልካም ስራ ልናሳልፍ ከመጥፎ ነገር ልንርቅ ይገባናል። ከመልካም ስራዎች አንዱ ስነ_ምግባርን ማሳመር ነዉ።

=
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
【ኪታቡል ጀናኢዝ】   ━┅━┅━┅━ ❍ ክፍል  ② ☞የሟችን ፊት መግለጥ፣ ጀናዛውን መሳም እንድሁም ለሶስት ቀናት ያክል ማልቀስ ይፈቀዳል። ሟች ቤተሰቦች ደግሞ ትእግስትን የመላበስና የአላህን ቅድመ ዉሳኔ ወደው የመቀበል ግዴታ አለባቸው። ☞ የወዳጅንና የቤተሰብን ሞት በሚረዱበት ወቅት እኛ የአላህ ነን። እኛም ወደ እሱው ተመላሾች ነን ( إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ)…
【ኪታቡል ጀናኢዝ】

❍ ክፍል   ③

☞ሟች ሲሞት ከፊል ሙስሊሞች ፈጥነው ጀናዛውን የማጠብ ግዴታ አለባቸው።  እጥበቱም ሶስት ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ መሆኑ፣ በነጠላ ቁጥር መሆኑ፣ ከዉሃው ጋር የቁርቁራ ወይም እሱን የሚተካ ማጽጃ ሳሙና ወይም ኬሚካል መጠቀሙ፣ በመጨረሻው እጥበት ላይ ሽቶን መጠቀም ይወደዳል። በተለይም ካፉር የሚሰኘውን ሽቶ መቀላቀሉ ተመራጭ ነው።

☞ይህ ከመሆኑ ጋር ኢህራም ላይ ሆኖ የሞተ ሰው ከየትኛውም አይነት ሽቶ ነክ ነገራት ሊርቅ ይገባዋል። የተጎነጎነ (የተሰራ) የሴት ጸጉር መፈታትና መስተካከል ከዚያም በሶስት መሾመር መሰራት ይኖርበታል። የተሰራው ጸጉሯም ወደ ማጅራቷ ይለቀቃል።  በእጥበቱ ወቅት በቀኝ በቀኝ በኩል ያሉ አካላትን ማስቀደምና የዉዱእ ቦታዎችን ቀድሞ ማጠብ ይወደዳል።  ጀናዛው በጓንት ወይም መሰል እጅን መሸፈኛ በመጠቀም ይታጠባል።

☞ሰውነቱ እየታዬ ሳይሆን በመከለያ ሸፈን ተደርጎ፣ ልብሶቹ ሙሉ በሙሉ ተወልቀው፣ እጅን ብቻ ከመከለያው ውስጥ በማስገባት ነው የሚታጠበው።  ወንዶችን የማጠብ ሀላፊነት የወንዶች ሲሆን ሴቶችን የሚያጥቡት ደግሞ ሴቶች ናቸው። ባለትዳሮች ብቻ ሲቀሩ። እነርሱ ግን አንዳቸው ሌላቸውን ማጠብ ይችላሉ።

☞እጠብቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ጀናዛውን መከፈን ግዴታ ነው። ከፈኑ ረጅምና መላ አካሉን የሚሸፍን ሰፊ ልብስ መሆን ይኖርበታል።  ከፈኑ ሙሉ አካላቱን ለመሸፈን በቂ ካልሆነ ከጭንቅላቱ በመጀመር ከፈኑ መሸፈን እስከቻለበት አካል ድረስ መከፈንና ቀሪውን አካሉን በሰንበሌጥ ወይም በሳር ወይም በቅጠል መሸፈን ግድ ይላል።

☞ጀናዛዎቹ ከበዙና ከፈን ካነሰ በርከት ያሉ ጀናዛዎችን በአንድ ከፈን በመጠቅለል በአንድ ቀብር ውስጥ መቅበር ይቻላል። ከቂብላ አቅጣጫ የሚያርፈው የበዛ ቁርአንን የሸምደደው ወይም የተገነዘበው ነው። በጦር ሜዳ ላይ እየተዋጋ የሞተ ሰማእት የተገደለበትን ልብሱን ማውለቅ አይቻልም። ይልቁኑ በተገደለበት ልብሱ ይቀበራል።  በኢህራም ላይ እያለ የሞተ ሰው በሁለቱ የኢህራም ልብሶቹ ነው የሚቀበረው።

☞ከከፈን ልብሶች ሁሉ ነጭ ቀለም ያለው የበለጠ ይወደዳል።  የከፈን ልብስ ሶስት መሆኑ ሱና ነው።  ከፈኑን ሶስት ጊዜ በእጣን ማጠን ይወደዳል። ሆኖም ግን ይህ ተግባር ኢህራም ላይ ሆኖ የሞተን ሰው አይመለከትም። በዉድ ዋጋ የሚገዙ ልብሶችን ለከፈን መጠቀም ይከለከላል።  የሴቶች ከፈን እና የአከፋፈን ሁኔታ ከወንዶቹ ጋር ተመሳሳይ ነው።

☞ከፈኑ የታሰረበትን ገመድ ወይም ክር ጀናዛው በቀብሩ ውስጥ ካረፈ በኋላ መፍታቱ በቀደምት አበዎች ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ጀናዛን መሸከምና ተከትሎ መሄድ (መሸኘት) ግዴታ ነው።

☞ይህም ሟች ሙስሊም በህይወት ካሉት ሙስሊሞች የሚያገኘው ጽኑ ሀቁ ነው። ጀናዛን መሸኘት ሁለት ደረጃ አለው። አንድኛው ከቤት ጀምሮ እስከሚሰገድበት ድረስ መሸኘት ሲሆን ሁለኛው ደግሞ ተቀብሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መሸኘት ነው። ጀናዛን የመሸኘት ድንጋጌ የሚመለከተው ወንዶችን ብቻ ነው። ምክንያቱም ሴቶች ጀናዛ መከተልን ተከልክለዋል።

❝ ኢንሻ አላህ ይቀጥላል∼∼∼✍️

=
t.me/https_Asselefya1
ሌሎች ጉዳይ ላይ ይሁን ብለን ችለን እየኖርን ለምን ትዳር ሲሆን ሁሉ ካልተሟላ እንላለን ? አለ ኡስታዝ እዉነቱ ነዉ ! አሁን ስደት ላይ ሁሉ ሞልቶልን አይደለም ብዙ የጎደሉ የሚያስከፎን አሉ እሰዉ ቤት ግን ይሁን ብለን እንኖራለን ! ታድያ ለራሳችን ቤት ችለን መኖር እንደት አቃተን ? ተዉጅ ሴቶችዬ ሆይ አስቡበት በዉሀ ፈሰሰ ቤታችሁ አታፍርሱ ችላችሁ ኑሩ በሂደት ሁሉም ይሟላል ሁሉም ይስተካከላል ።
ጠንካራ ሁኑ💪

#መቻል
=
አንዷ ሰዉነቷ እንዳይታይ የተቻላት ያክል ሙሉ ተሸፋፍና ለመዉጣት ትጥራለች ሌላኛዉ ደግሞ ሰዉነቷ ለማሳየት የተቆራረጠ ስስ የሆነ የተወጣጠረ ልብስ ለብሳ ለመዉጣት ትጥራለች ?

#ልዩነት

=
የራስሽ ኢባዳዎች ከፈፀምሺ በኋላ ተሻጋሪ በሆነ ኸይር ስራ ላይ ትጊ ጣሪ !

ማስተማር ከቻልሽ ከበታችሽ ያሉ አስተምሪ ካልቻልሽ አስተማሪዎች አግዥ መንገዶች አመቻቺ ! መፃፍ ከቻልሺ ፃፊ ካልቻልሽ የተፃፈዉ አሰራጪ ! ሞተሽም ስምሺ የማይረሳበት ትልቅ ሚና ጥለሽ ለማለፍ በርቺ ! ከኡስታዜ ምርጥ ምክር! ላካፍላችሁ ብዬ እሺ ለእናንተም ይሆናል !

✍️أم عثيمين
=
t.me/https_Asselefya1
Audio
ألا نحن في دار قلـيل بقائــها.. 💦

=
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አመሻሽ ላይ እንድህ ያሉ ቦታዎች ብቅ ማለት ጥሩ ነበር ....!

=
ወደ አንተ ለመድረስ áˆŤáˆąáŠ• መስዋት የከፈለልህን ሰዉ ልብ አትስበር !!

=
t.me/https_Asselefya1
ሰዎች ስላንተ በሚያወሩት ነገር የማትረበሽ ከሆነ አንዱ የስኬት  እርምጃ አልፈሀል ማለት ነዉ።

=
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
【ኪታቡል ጀናኢዝ】 ❍ ክፍል   ③ ☞ሟች ሲሞት ከፊል ሙስሊሞች ፈጥነው ጀናዛውን የማጠብ ግዴታ አለባቸው።  እጥበቱም ሶስት ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ መሆኑ፣ በነጠላ ቁጥር መሆኑ፣ ከዉሃው ጋር የቁርቁራ ወይም እሱን የሚተካ ማጽጃ ሳሙና ወይም ኬሚካል መጠቀሙ፣ በመጨረሻው እጥበት ላይ ሽቶን መጠቀም ይወደዳል። በተለይም ካፉር የሚሰኘውን ሽቶ መቀላቀሉ ተመራጭ ነው። ☞ይህ ከመሆኑ ጋር ኢህራም ላይ ሆኖ የሞተ…
【ኪታቡል ጀናኢዝ】
━┅━┅━┅━┅

❍ ክፍል   ④

☞ጩኸትና እሳት ጀናዛን መከተል የላባቸውም። ክልክል ነው። ጀናዛውን በሚሸኙበት ጊዜ ጉዞውን ማፍጠን ግዴታ ነው።  በእግሩ የሚሸኝ ሰው ከጀናዛው ቀድሞ፣ ተከትሎም እንድሁም ከጀናዛው ከቀኝና ከግራም ሆኖ መሸኘት ይችላል።

☞መጓጓዣዎችን በመጠቀም አስክሬንን የሚሸኝ ሰው ግን ከጀናዛው በኋላ ሆኖ መከተል ነው ያለበት። በላጩ አሸኛኘት ጀናዛን በእግር መሸኘት ነው። ጀናዛን በጋሪ፣ በአስከሬን መኪና ወይም በሌሎች መጓጓዣዎችን መሸኘት እንድሁም ሸኝዎች በመኪና ውስጥ ሆነው መሸኘታቸው ይህ በፍጹም አልተደነገገም።

☞ ጀናዛ በሚያልፍበት ጊዜ ከተቀመጡበት መነሳት ተሽሯል። ጀናዛው መቃብሩ ቦታ በሚደርስ ጊዜ በቦታው ላይ የተገኙ ሸኝዎች ጀናዛው መሬት ላይ እስከሚቀመጥ ድረስ መቆማቸውም ተሽሯል። (ጀናዛው በሚቀበርበት ወቅትም በዙሪያው ያሉ ሸኝዎች መቀመጥ ይችላሉ።)

☞ የጀናዛን መነጋገር በተመለከተ በትክክለኛ መረጃዎች ስለተረጋገጠ አምኖ መቀበል ግዴታ ነው። ጀናዛን የሸኘ ሁሉ ዉዱእ ማድረጉ ይወደድለታል።

☞በተቀበረ ጀናዛ ላይ መስገድ ይቻላል። ከፊሎች ሰግደውበት በተቀበረ ጀናዛም ላይ በቀብሩ ቦታ በመሄድ መስገድ ይቻላል። ሶላተል ጀናዛ ሳይሰግድበት በሌላ ሀገር ለሞተ ሰው ከፊል ሙስሊሞች የሩቅ ሶላተል ጀናዛ ይሰግዱበታል። ለከሀዲዎችና ለሙናፊቆች ሶላት መስገድ እንድሁም አላህ ይቅር እንድላቸውና እንድያዝንላቸው ዱዓእ ማድረግ ክልክል ነው።

☞ ቋሚ ለሆኑት ግዴታ ሶላቶች በጀመዓ መስገድ ግዴታ እንደሆነው ሁሉ ለጀናዛ ሶላትም በጀመዓ መስገድ ግዴታ ነው። በጀናዛ ሶላት ላይ ጀመዓው በበዛ ቁጥር ለሟቹ የበለጠ መልካም ነው። ሰጋጆቹ ከኢማሙ በኋላ ሶስት እና ከዚህም በላይ መስመር ሆነው መቆማቸው ሱና ነው። ከኢማሙ ጋር የሚሰግደው አንድ ሰው ብቻ ከሆነ ለግዴታ ሶላት ከኢማሙ ቀኝ በኩል በትይዩው መቆም ሱና ቢሆንም ለጀናዛ ሶላት ግን ከኢማሙ ጎን መቆም የለበትም።

☞ይልቁኑም ከኋላው ነው መቆም ያለበት። ሶላተል ጀናዛ ላይ ኢማም ለመሆን ከሟች የቅርብ ቤተሰብ ይልቅ የሙስሊም መሪ እና ባለስልጣን ቀዳሚ ይደረጋል። ባለስልጣኑ ወይም ወኪሉ ካልተገኘ ደግሞ ለኢማምነት ተገቢ የሚሆነው ቁርአንንየበለጠ የሸመደደው ነው። ባጭሩ ለግዴታ ሶላቶች የተደነገገውን ቅደመ ተከተል በጠበቀ መልኩ ነው ኢማም የሚመደበው።

☞በርካታ የወንድና የሴት ጀናዛዎች በአንድ ላይ ከተገኙ ለሁሉም አንድ ሶላተል ጀናዛ ይሰገድባቸዋል። ከጀናዛዎቹ ውስጥ ህጻናትም ቢኖሩ እንኳ የወንዶቹ ጀናዛ ከኢማሙ ፊት ይሆናል። የሴቶቹ ጀናዛ ደግሞ ከቂብላ የሚቀርብ (ከወንዶቹ ጀናዛ ቀጥሎ) ይሆናል።  ለእያንዳንዱ ጀናዛ ራሱን የቻለ የብቻው ሶላት መስግዱ ሱና ነው። ምክንያቱም መሰረታዊ የሆነው መነሻ መርህ ይህ ስለሆነ ነው።

☞ የጀናዛ ስግደትን በመስጅድ ውስጥ መፈጸም ይቻላል። ሆኖም ግን ሱናውና በላጩ ከመስጅድ ውጭ ባለና ለጀናዛ ስግደት ተብሎ በተዘጋጀ ቦታ መደረጉ ነው። በመቃብሮች መካከል ሆኖ መስገዱ ግን ሀራም ነው።

❝ኢንሻ አላህ ይቀጥላል ∼∼∼ ✍️

=
t.me/https_Asselefya1