💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
አንዳዴ .....ፈገግ በሉ! አብሽሩ ዘና ፈታ እያልን እሺ !

=
05 ፈዳኢሉል ቁርአን
አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
አዲስ  ኪታብ  ቂርአት
⏡⏡⏡⏡⏡

📔ኪታብ፦ «ፈዳኢሉል ቁርአን »

ክፍል  05

የኪታብ  𝐏𝐷𝑭 t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/12650

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

    ↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/https_Asselefya1
ወንድ ከወደደሽ...!

~
ወንድ ከወደደሽ ፣እንኳን ችላ ሊልሽ፣
ስላች ቀን ከሌት ሁሌ ባወራልሽ፣
የት ገባሽ ወዴት ነሽ እያለ ባላለሽ፣

ሽማግሌ ልላክ በይ የግሌ ላርግሽ፣
ካንች ወዷ ቆንጆ የት ላገኝ ብለሽ ፣
እያለ ሰባብኮ ከቤት ባላስገባሽ፣
በድንቅ ዉብ ቃሎች እያሰማመረሽ፣
ለዘመድ አዝማዱ ወደድኩኝ እያለሽ፣
የለለ ማስመሰል ዉሸት ሲነዛብሽ፣


መታመን ልማድሽ ፣አዉቃለሁ የዋህ ነሽ፣
ዉስጥሽ እየደማ አይንሽ እንባን አዝሎ፣
ልብ ያደማሽን ሰዉ መሄድ ተከትሎ፣

ቆይ ግን አትማሪም፣ማዘን አይበቃሽም፣
ለማይፈልግሽ ወንድ ሁሌ ከምታለቅሽ፣
ላንች ያለዉ መጥቶ አንችን ስጠይቅሽ፣

ምስጋና እያቀረብሽ ለሃያሉ ጌታሽ፣
ሴትነት እሱ ነዉ ቁጥብ ሀያ ካለሽ፣
የተዉሂድ ጀግና ከደጅሽ ከመጣ፣
አሏህ ከፈራ ካላበዝ ጣጣ፣

ሱናና ተዉሂድን ከልቦ የጠጣ፣
ቤተሰብ አክባሬ ከበር ከመጣ፣
ይኸ ነዉ ለአንች የአሏህ ስጦታ፣
ጀግናን ተመኝተሽ ያገኘሽዉ ለታ፣

ታዳ ጣጣ አብዝተሽ ልብሽ ካመነታ ፣
አልፈልግም ብለሽ በር የዘጋሽ ለታ፣
እመኝኝ ልንገርሽ ስሚኝ አንድ እዉነታ፣

ወይ እሚሸዉድሽ
ወይ እሚያታልልሽ
ወይ እማያስብሽ

ወይም እማያቅሽ የወደድሽ ለታ፣
አንድ ቀን ይመጣል የለቅሶ ቧቧታ፣


እናማ ቁጥቧ ጀግና ሰለፍይት፣
የአሁኗ እህቴ የወደፊት እናት፣

ግዜ እዳያመልጥሽ በግዜ እወቂበት፣


✍️በአቡ ዑበይዳህ ሶላሁድን

⇓↷⇓↷⇓↷⇓↷⇓↷⇓↷⇓↷⇓↷⇓↷⇓↷⇓
t.me/selahudin_Islamic_knowlages
t.me/selahudin_Islamic_knowlages
‏قال ابن عثيمين رحمه الله

إن الناس اتخذوا رمضان موائد ‏البطون
لا موائد القلوب.


اللقاء الشهري(٤/٤١)


=
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
🛑👉ከቁጣ ጥፋት ለመራቅ ከመንስኤዎቹ መራቅ አይነተኛ መፍትሄ ነዉ ከተከሰተ ደግሞ ነብያዊ ብልሀቶች መጠቀም ያስፈልጋል ከትላት የቀጠለ፦ ~ ⓶⁍በቁጣ ጊዜ ዝም ማለት፦ ነብዩﷺ አንዳችሁ ሲቆጣ ዝሞ ይበል ብለዋል። (አስሶሒሐህ:1375) ይህም በቁጣ ኋላ የሚፀፅተዉ ወይም መጥፎ ዉጤት የሚያስከትሎ ቃል እንዳይወጣ ይረዳዋል። ⓷⁍ቆመን ከሆነ መቀመጥ ካልሆነም መጋደም፦ ነብዩﷺ እንድህ ይላሉ ፦አንድ ሰዉ ሲቆጣ…
🛑👉ከአሻሚ ነገሮችን መራቅ!
     

- عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ يَقُولُ - إِنَّ الْحَلَالَ بَيِّنٌ، والْحَرَامَ بَيِّنٌ، وبَيْنَهُمَا مُشْتَبِهَاتٌ لَا يَعْلَمُهُنَّ كَثِيرٌ مِنَ النَّاسِ، فَمَنِ اتَّقَى الشُّبُهَاتِ فَقَدِ اسْتَبْرَأَ لِدِينِهِ، وعِرْضِهِ، ومَنْ وقَعَ فِي الشُّبُهَاتِ وقَعَ فِي الْحَرَامِ، كَالرَّاعِي يَرْعَى حَوْلَ الْحِمَى، يُوشِكُ أَنْ يَقَعَ فِيهِ، أَلَا وإِنَّ لِكُلِّ مَلِكٍ حِمًى، أَلَا وإِنَّ حِمَى اللَّهِ مَحَارِمُهُ، أَلَا وإِنَّ فِي الْجَسَدِ مُضْغَةً إِذَا صَلَحَتْ صَلَحَ الْجَسَدُ كُلُّهُ، وإِذَا فَسَدَتْ فَسَدَ الْجَسَدُ كُلُّهُ، أَلَا وهِيَ الْقَلْبُ. مُتَّفَقٌ عَلَيْهِ.



«ከአንኑዕማን ኢብኒ በሽር ረዲየላሁ ዐንሁማ ተይዞ የአላህ መልእክተኛﷺ እንድህ ሲሉ ሰምቻለሁ ይላሉ፦ » ሐላል (የተፈቀደ ነገር) ግልፅ ነዉ። ሐራምም(የተከለከለ ነገር) ግልፅ ነዉ።  በመካከላቸዉ አሻሚ ነገሮች አሉ። በእርግጥም ከሰዎች ብዙ አያዉቋቸዉም። ከአሻሚ ነገሮች የተጠበቀ ሃይማኖቱንም ክብሩንም ጠበቀ። በአሻሚ ነገሮች ላይ የወደቀ ሐራም ላይ ወደቀ። ልክ በጥብቅ ዙሪያ(እንስሳቶቹን )እንደሚጠብቅ እረኛ። ከሱ ዉስጥ(ግጦሽ) ሊግጡበት ይቀርባሉ። ንቁ! ለእያንዳዱ  አካል ንጉስ ጥብቅ ክልል አለዉ። ንቁ! የአላህ ክልሉ ክልከላዎቹ ናቸዉ። ንቁበአካል ዉስጥ ቁራጭ ስጋ አለች።እሷ ስትሰምር አካል ሙሉ ይሰምራል። እሷ ስትበላሺ አካል በሙሉ ይበላሻል። ንቁ ! እሷም ልብ ነች። (ቡዃሪና ሙስሊም ዘግበዉታል። 52/1599)

«ሐዲሱ ያለዉ የላቀ ደረጃ፦»

ይህ ሀዲስ ከሸሪዐ መሠረቶች ዉስጥ አንዱ መሠረት ነዉ። አቡ ዳዉድ  አስሰጂስታኒ ረሂመሁሏህ "ኢስላም በአራት ሐዲሶች ላይ ይሽከረከራል ብለዉ ከጠቀሷቸዉ ሐዲሶች አንዱ ይሄ ሐዲስ ነዉ። (ሸርሑል አርበዒን፣ ኢብኑ ደቂቀል ዒድ :26)

በዚህ ሀዲስ መሠረት ነገሮች ለሶስት ይከፈላሉ። ግልፀ የሆነ ሐላል፣ግልፀ የሆነ  ሐራም እና አሻሚ ተብለዉ። ሐላሉን መፈፀም መብታችን ነዉ።ሐራሙን መራቅ ግደታችን ነዉ። አሻማዉን መጠንቀቅ ሰላማዊ ቀጠና ነዉ። በህይወታችን በብዛት ለሚያጋጥሙን ወስዋሶች ይህንን ሐዲስ ብንከተል ትልቅ እፎይታ እናገኛለን።

«ከሐዲሱ የሚወሰዱ ቁም ነገሮች፦»

ሐራምና ሀላል በአብዘሀኛዉ ግልፅ እንደሆነ
↝መፈቀድ አለመፈቀዳቸዉ ከማይለዩ አሻሚ ነገሮች ልንርቅ እንደሚገባን
!
አሻሚ ነገሮች የሚዳፈር ሰዉ ወንጀል እየቀለለ እንደሚመጣ !
↝በሌሎች በክፉ የሚያስጠረጥሩን ነገሮች ችላ ልንል እንደማይገባ!

በምሳሌ ማስተማር ጠቃሚ የሆነ ስልት እንደሆነ !
ከአሻሚ ነገሮች መራቅ ዲናችንን ከጉድለት፣ ክብራችንን ከመጉደፍ እንደሚጠብቅ !
ልብን ከሚበክሉ ጥፋቶች ክፉ አመሎች መጠንቀቅ ከምንም በላይ ቅድሚያ ሊሰጠዉ እንደሚገባ !
የዉጭ መበላሸት የዉስጥ ብልሽት ነፀብራቅ እንደሆነ እንማራለን።

=
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
ቁርአን ጁዝ ⑩
الشيخ علي الحذيفي
ቁርአን በረመዷን አብረንእናኽትም!
∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼

«الليلة  (⑩)  رمضان ١٤٤٥»

ጁዝ

🎙الشيخ علي الحذيفي حفظه الله

«ከሱረቱል አንፋል አንቀፀ 41 እስከ ሱረቱል ተዉባህ አንቀፀ 92»

=
t.me/https_Asselefya1/18622
ፆመኛ ሰው ሲጉመጠመጥ አምልጦት ውሃ ወደ ጉሮሮው ቢወርድ ፆሙ አይበላሽም። አላህ እንዲህ ይላል:–

(وَلَیۡسَ عَلَیۡكُمۡ جُنَاحࣱ فِیمَاۤ أَخۡطَأۡتُم بِهِۦ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتۡ قُلُوبُكُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمًا)


"በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ሃጢአት የለባችሁም፡፡ ይልቁንምን ልቦቻችሁ አውቀው በሰሩት ነው፡፡ አላህም መሃሪ አዛኝ ነው፡፡"[አልአሕዛብ: 5]
=
የቴሌግራም ቻናል፡
https://t.me/IbnuMunewor
ምላስን መቆጣጠር የምናዉቀዉ ሳይሆን የምንኖረዉ መሆን ያለበት !

=


አሸናፊ  መሆን ከፈለግሺ  ሁሌም ስለ አሸናፊነት  ተማሪ !!

=
በዲንሽ በመነሀጅሽ  የሚያጠናክርሺን አግቢ የዱኒያ ኮተት በመነሀጅሽ ዉስጥ አምቀሽ እንደ ሁኔታዉ  ታስኬጅዌለሽ።

=
t.me/https_Asselefya1
🛑👉ረመዷን የቁርአን ወር ነዉ !
~

🛑👈شــهررمضــان شــهرالقــرآن
.
‏أكثِر من قراءة القرآن في
شهررمضان شهر رمضان هو شهرالقرآن .. أُنزِلَ القرآن في رمضان، أكثِر فيه من قراءة القرآن بتأمُّل وتدَبُّر واستحضار بأنك تقرأ كلام الله عز وجل، كلامَ رَبِّ العالمين.

لقاء الباب المفتوح للعلّامة ابن عثيمين ٤ / ٢٢٣


=
t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
🛑👉ከአሻሚ ነገሮችን መራቅ!       - عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ يَقُولُ - إِنَّ الْحَلَالَ بَيِّنٌ، والْحَرَامَ بَيِّنٌ، وبَيْنَهُمَا مُشْتَبِهَاتٌ لَا يَعْلَمُهُنَّ كَثِيرٌ مِنَ النَّاسِ، فَمَنِ…
🛑👉መልካም ተናገር ካልሆነ ዝም በል!
~      ⁍⁌⁍⁌⁍⁌⁍⁌⁍⁌⁍⁌⁍⁌⁍⁌⁍⁌⁍⁌⁍

۞ عن أبي هريرة رضي الله عنه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: ((من كان يؤمن بالله واليوم الآخر، فليقل خيرًا أو ليصمت، ومن كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليكرم جاره، ومن كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليكرم ضيفه))؛ رواه البخاري ومسلم.
 

«ከአቡ ሁረይራ ረዲየላሁ አንሁ ተይዞ የአላህ መልእክተኛﷺ እንድህ ብለዋል፦ በአላህ እና በመጨረሻዉ ቀን የሚያምን የሆነ ሰዉ መልካም ይናገር፣ወይም ዝም ይበል። በአላህና በመጨረሻዉ ቀን የሚያምን የሆነ ሰዉ  ጎረቤቱን ያክብር። በአላህና በመጨረሻዉ ቀን የሚያምን የሆነ ሰዉ እንግዳዉን ያክብር። ቡዃሪና ሙስሊም ዘግበዉታል።(6018/47)

«ሐዲሱ ያለዉ የላቀ ደረጃ፦»

۞ታላቁ የማሊኪያ ኢማም ኢብኑ አቢ ዘይድ አልቀይረዋኒ ረሂመሁሏህ እንድህ ይላሉ፦ ሁሉም ስነ ምግባራት ከአራት ሐዲሶች የሚመነጩ ናቸዉ። እነሱም፦ በአላህ እና በመጨረሻዉ ቀን የሚያምን የሆነ ሰዉ መልካም ይናገር ወይ ዝም ይበል" የሚለዉ የነብዩ ﷺ ንግግር "አንድ ሰዉ የኢስላም ዉበት የሆነዉ የማያገባዉን መተዉ ነዉ መለታቸዉ ፣ አትቆጣ የሚለዉ አጭር ምክራቸዉ "አንዳችሁ ለወንድሙ የሚወደዉን ለራሱ እስካልወደደ ድረስ አላመነም የሚሉት ናቸዉ። (ፈትሑል ቀዉዩል መቲን:49)

«ከሐዲሱ የሚወሰዱ ቁም ነገሮች፦»

ሁሌም መልካም መናገር የሚበረታታ እንደሆነ !
ፍሬ ከሌለዉ ወሬ ዝምታ እንደሚመረጥ !
መልካም መናገር፣ጎረቤትንና እንግዳን ማክበር ከኢማን እንደሆነ !
ኢስላም በሰዎች መካከል መከባበር  ያለበት ጤናማ ማህበራዊ ህይወት እንድኖር የሚያደርግ ዉድ ሃይማኖት እንደሆነ ከሐዲሱ እንማራለን።

🛑👉ማሳሰቢያ፦  አንድ ጎረቤት ሙስሊም እና ዘመድ ከሆነ ከጉርብትና ሐቅ በተጨማሪ የኢስላምና የዝምድና ሐቅ አለዉ። ሙስሊም ግን ባዳ የሆነ ጎረቤት ደግሞ የጉርብትና እና የኢስላም ሐቅ አለዉ። ሙስሊም ያልሆነ ዘመድ ጎረቤት የጎረቤትና የዝምድና ሐቅ አለዉ ። ሙስሊም ያልሆነ ባዳ ጎረቤት ደግሞ የጉርብትና ሐቅ አለዉ።

ከጎረቤትም በሩ ቅርብ በመሆኑ ወደ ቤት የሚገባዉን እየተመለከተ ልቡ የሚንጠለጠል የሆነዉ ይበልጥ መልካም ሊዋልለት ይገባል። የጎረቤትን ሐቅ ከባድነት የሚያመለክቱ ማስረጃዎች ዉስጥ አንዱ ነብዩﷺ እንድህ ማለታቸዉ ነዉ፦ ጂብሪል  በጎረቤት ላይ  አደራ ከማለትም አልተወገደም ፣ያስወርሰዋል ብየ እስከምጠረጥር ድረስ !! (ቡኻሪ :6015 ሙስሊም:2624)

ታድያ እንደዚህ ሐቁ ከባድ የሆነን ጎረቤት ማስቸገር፣ለጎረቤት  ስጋት መሆን  ኢማንን ጥያቄ ዉስጥ የሚከት ከባድ ጥፋት ነዉ። ነብዩﷺ አንድ ወቅት  "ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! አሉ።ማነዉ እሱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ ? ሲሏቸዉ  "ጎረቤቱ ተንኮሉን  የማያምነዉ (የሚሰጋዉ)ሰዉ ነዉ አሉ። (ቡኻሪ፡6016)

የእንግዳ ሐቅ ደግሞ  ከአቅም በላይ ለሆነ ወጭ ሳይዳረጉ ቤት ያፈራዉን በማቅረብ፣በፈገግታ መቀበል፣ መልካምን በመናገር እንግዳዉ ዘና እንድል እንዳይጨናነቅ ማድረግ ነዉ።

=
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1