💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ምናለ መሰላችሁ ኡስታዝ ሴቶች ሞኝ አትሁኑ ብልጥ ሁኑ ባላችሁ በፍቅር ያዙት በእልክ ከመጣችሁ ቤታችሁ ፈረሰ በእልክ ወንድ አታሸንፊዉም በፍቅር ግን ታንበረክኪዋለሽ አለ !!

በሉ እልካችሁ ወዳ ጣሉ ሴቶች !!

=
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
በስደት አለም የቆየዉን ያክል ሰዉ ቆይቶ በሰላም በሙሉ ጤና ወደ ሀገር መመለስ ትልቅ ነገር ነዉ ከዶዬ የኔ የዋህ እንኳን ደስ አለሺ በጉጉት ስትጠብቄት የነበረችዉ ቀን ዛሬ ደረሰች አልሀምዱሊላህ አላህ በሰላም ከምትወጃቸዉ ቤተሰቦቼሽ ያገናኚሺ! በስደት ቆይታ ካገኘሁሽ ስአት ጀምሮ እስከ አሁኗ ስአት ድረስ ደስ የሚል ጊዜ ነበሩ ያሳለፍናቸዉ የኔ ምርጥ እህት ሀገርም እንገናኛለን ኢንሻ አላህ አላህ በሄድሽበት…
ያ ሰላም ቤህሩት ያሉ እህቶች ወደ ሀገር መሄድ እሽቅድምድሙ እንደቀጠለ ነዉ። ዛሬም «እህታችን ኸይርያ አደም» ወደ እናት ሀገሯ ትመለሳለች የኛ ዉድ እህት አላህ በሰላም ለሀገርሺ ያብቃሺ  አላህ በሀገርሺ የተሻለ ሪዝቅ ይወፍቅሺ እንወድሻለን 🥀🥀


የሱና እህታችን ኸይርያ አደም
ሀገር  ብንለያይ ቢያራርቀንቦታ
ባለንበት ሁነን አለን በትዝታ
በድን በትስስር ጠንክረን እንበርታ!!

በሱና አሸብርቀሽ በሂጃብ ተዉበሽ
አብሽሪ የኛ እህት ኑሪ ቀጥ ብለሽ
ፅኚ በድንሽ ላይ  ፊትናም ቢበዛብሽ
አደራ የኛ እህት መጠንከር አለብሽ

የሱና ጥላት ፊቱን ቢያዞርብሽ
እንዳትጨነቂ ምንም እንዳይመስልሽ
በርችልን የኛ እህት መፅናት ነዉ ያለብሽ!!


በድንሽ ጠንክረሽ አውቀሽ አሳውቂ
የመጣው ቢመጣ እዳትጨነቂ፣
ሰወችም ይሉሻል አክራሪ አሸባሪ
አላህ ከኛ ጋር ነው ምንም እዳትፈሪ

አኼራን ረስተሽ ለዱንያ እዳታድሪ
በድንሽ ለመጣ አትደራደሪ፣
እናማ አህቴዋ አደራየ ይህ ነው
የተፈጠርንለት አላማ ተውሂድ ነው


ጉዟችን አድካሚ ቢሆንም መራራ
አላህ በእውቀቱ ነው ከእኛ ጋራ፣
ምንም አትስሚያቸው  ያወራ ቢያወራ

አንድ ላይ አይሆንም ስኳርና አቧራ
ይሄንንም ስልሽ አይደል ካንች አውቄ
ሁሉ እደሚገባሽ አውቃለው ጠንቅቄ፣


🌷መልካም ጉዞ ይሁንልሺ🌷

=
https://t.me/https_Asselefya1
04 ፈዳኢሉል ቁርአን
አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
❝አዲስ  ኪታብ  ቂርአት❞
⏡⏡⏡⏡⏡

📔ኪታብ፦ «ፈዳኢሉል ቁርአን »

☞ ክፍል  04

⭞የኪታብ  𝐏𝐷𝑭 t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/12650

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

    ↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/https_Asselefya1
ቁርአን ጁዝ ⓼
الشيخ علي الحذيفي
ቁርአን በረመዷን አብረንእናኽትም!
∟∟∟∟∟∟∟∟∟∟∟∟∟

«الليلة  (⓼)  رمضان ٥٤٤ټ

☞ጁዝ ⓼

🎙الشيخ علي الحذيفي حفظه الله

=
t.me/https_Asselefya1/18575
ቀዳሚው የጾም ፋይዳ የፈጣሪን ትእዛዝ መተግበር ሲሆን አያሌ ዱንያዊ ፋይዳዎችም አሉት።
=
የቴሌግራም:-
https://t.me/IbnuMunewor
የኛ ነገር ... ከሐላል እየፆምን በሐራም እናፈጥራለን!
~
ፆማችንን ከሐራም ነገሮች እንጠብቅ። ግብይታችን በየትኛውም መልኩ ከሰው ሐቅ ጋር እንዳይነካካ እንጠንቀቅ። አይናችንን ካልተፈቀደ አካል እንስበር። ስልኮቻችንን ወደ ሐራም እንዳያደርሱን እንቆጣጠር። በረመዷን ከሰው ጋር ያለንን ቅልቅል እንቀንስ። በተለይ ደግሞ የምላሳችንን ነገር እናስብበት። ፆማችን አጉል መርራብ እና መጥጠማት እንዳይሆን እንጠንቀቅ።
ታላቁ ታቢዒይ የሐያ ብኑ አቢ ከሢር ረሒመሁላህ ፆመኛ ሆኖ ሃሜትና ነገር ማሳበቅ ላይ ስለሚሰማራ አካል እንዲህ ይላሉ፦
"ሰው ንፁህ ከሆነ ሐላል (ምግብና መጠጥ) እየፆመ ቆሻሻ በሆነ ሐራም - በወንድሙ ስጋ - (በሃሜትና ነገር ማሳበቅ) ያፈጥራል።"
ምንጭ ፦ [አልሒልያህ፣ አቡ ኑዐይም፡ 3/69]

#ከደጋጎቹ_ቀዬ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
በረመዷን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች
~
① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣
② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሱሑርን አስቀድሞ በመመገብ ፈጅር ሳይሰግዱ መተኛት፣
③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም/ ሙሰልሰላት ማሳለፍ፣
④ ረመዷንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣
⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣
⑥ ተራዊሕ ላይ በየአራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣
⑦ የተራዊሕ ኢማሞች ከሶላቱ ይልቅ ለቁኑት ዱዓእ የበለጠ ትኩረትና ጊዜ መስጠት፣
⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣…ብዙ ነው)
⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ" እያሉ በእስፒከር መጮህ፣
(10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣
(11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣
(12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣
(13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያስፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣
(14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣
(15) ሴቶች ሽቶ ተቀብቶ ለተራዊሕ መውጣት፣
(16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች አላስፈላጊ መዝረክረክ፣
(17) ሃሜት፣
(18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣
(19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ እና መሰል አጉል ነገሮች ማሳለፍ፣
(20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣
(21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግድ ይላል። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ነው)፣
(22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርኣን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።)
(23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣
(24) አንዳንድ አካባቢዎች የዒሻእ ሶላትን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣
(25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣
(26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ሰዎችን ማስገደድ፣ ወዘተ

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
የአሕባሽ ብልሹ አካሄድ
ኢብኑ/ሙነወር
የአሕባሽ ብልሹ አካሄድ

ኢብኑ ሙነወር

የካቲት 30/2016 በወራቤ ከተማ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መስጂድ የተሰጠ ትምህርት

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
በመፀሀፍት ማመን
Sadat
🛑👉በመፀሀፍት ማመን

ከተራዊህ በፊት የተደረገ ዳእዋ

=
t.me/SadatKemalAbuMeryem
•

وَإِن تُطِعْ أَكْثَرَ مَن فِي الْأَرْضِ يُضِلُّوكَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ .

#تدبر_آية

=
በረመዷን ምግብ የምትሰራልህን አመስግን።ዱዓ አድርግላት አመስግናትም።የሚያስደስትህ ምግብ እንኳን ባህይሆን የእርሷን ሞራል የሚጎዳ ቃል ተናግረህ እንዳታጨናንቃት።አንተን ለማስደሰት ብላ በፆም አንጀቷ ከፍ ዝቅ ብላ መስራቷ ብቻ ለርሷ በቂዋ ነው።አንተም ምስጋና ቢስ ውለታ በይ አትሁን።


አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
.

وَاكْتُبْ لَنَا فِي هَٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ إِنَّا هُدْنَا إِلَيْكَ ۚ.

#تدبر_آية

.
t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
اللهم يا مُقلب القلوب ثبت قُلُبنا على دينك



العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله.
=
t.me/https_Asselefya1